———- አምቦገነኖችን በሰላማዊ እምቢተኝነት መፋለም ሕይወትን የሳጣል ! በትግሉ ሜዳ እስካለን ድረስ የሚከፈለው መሰዋትነት እስከዚህ ድረስ ነው፡፡ ጓድ ሳሙኤል አወቀ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲመሰረት የበኩልን ድርሻ የተወጣ፣ፓርቲያችን ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የፓርቲውን ዓላማና ግብ ለማሳካት የተቻለሁን ሁሉ ያደረገ ወጣት የህግ ባለሙያ ነው፡፡ ሳሙኤል በፓርቲያችን ውስጥ ጠንካራ እና ደካማ ጎን በመለየት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከሚተች እና ከሚያበረታቱ መካከል አንዱ ነው፤በፓርቲያችን ውስጠ-ዴሞክራሲ እንዲዳብር ላደረጋቸው ጥረቶች እኔ ምስክርነቴን ለመስጠት እወዳለሁ፡፡
ሳሙኤል በፖለቲካ አስተሳሰቡ እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆኑ ብቻ ከዚህ ቀደም ይደርስበት የነበረው ጫና እንዲሁም እንግልት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ሃቅ ነው፡፡የሚፈፀምበት አሰቃቂ እንግልቶች በአገር ውስጥና በውጪ ለሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ሲገለፀ የቆየ የአደባባይ እውነት ነው ፡፡በተለይ ለመጨረሻ ጊዜ ድብዳባ ተፈፅሞበት በደረሰበት የአካል ጉዳት ሳይንበረከክ ከኢሳት ከ“ሰብአዊ መብቶች” ፕሮግራም አዘጋጅ Wendmagegne Gashu ወንድምአገኝ ጋሹ ጋር ያደረገው ቃለ መጠየቅ ሳሙኤል ጠበንጃ አልባ በሆነ ትግል አምባገነኑን የህውሓት/ኢህአዴግን ሥርዓት ለመጋፈጥ ምን ያህል ቁርጠኛ እንደነበር የሚያስታውሰን አጋጣሚ ነው፡፡በሚያደርጋቸው ሰላማዊ ትግል ሕይወቱን ሊያጣ እንደሚችልም ግን እስከመጨረሻ ድረስ እንደሚታገልም በዚኹ ፕሮግራም ላይ ገልፆኦ ነበር፡፡
ወንድማችን ሳሙኤል በቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ በሆኑ በአካለ-ሥጋ አሁን ከአጠገባችን የለም ! ሰው እንደመሆናችን መጠን ይሄን የመሰለ ቆራጥ ጓድ ከእጃችን ሲያመልጥ ሐዘንና ቁጭታችን እጅግ መራር ነው፡፡ ማንም ምንም የሆነ ሞት ይሞታል፣ ሳሚ ግን የጀግና ሞት ሞተ !ጅግና አይሞትም ሞቱ ጀግናን ይወልዳል እንጂ !!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላላም ትኑር !!!
The post የጀግና ሞት ጀግናን ይወልዳል! appeared first on Zehabesha Amharic.