Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

በቃን ሊባል የሚገባው ሥርዓት (ዮናስ አዲሱ ቱፋ)

$
0
0

ዮናስ አዲሱ ቱፋ / ከጀርመን

Bekaበየትኛውም ታሪካችን በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ኢትዮጵያውያን እንደተዋረድን መቼም ተዋርደን አናውቅም ።  ሊያውም በዚህ ዓለም በሰለጠነችበት ዘመን የአገሬ ህዝቦች ለስደት የተዳረግንበት፣ በልዩ ልዩ አገራት ለችግር የተዳረግንበት፣ ጥቂቶች አይን ባወጣ ብዝበዛ ውስጥ የተሳተፉበት፣ የህዝቦች የመሬት ባለቤትነት ተነጥቆ የአገሪቷ መሬትና የተፈጥሮ ኋብቶች በጥቂቶች በቁጥጥር ስር የሆነበት ዘመን ፣ የተወሰኑ ኋይሎች አገሪቷን በቁጥጥር ስር አስገብተው ህዝቡን በሚፈልጉት መንገድ የሚመሩበት ፣ ህዝቡና አገሪቷ በግዳጅ የምትመራበት ዘመን ሊያውም በሰለጠነ ዘመን፣ አገራችንና ህዝቦቿ በእፍረት ውስጥ የወደቅንበት ዘመን፣ የህዝባችን መከራ ከሃገራችን አልፎ በውጭው አገራት በመከራ ላይ ያለንበት ዘመን ፡፡

ይበልጥኑም የአገራችን ወጣቶችና ሴቶች በአገሪቷ ውስጥ የስራ እድል የሚሰጠው ለኢህአዲግ አባላትና ደጋፊውች ብቻ እንደሆነ   አውቀው የሰው አገርን እንደተሻለ የስራ እድል ስፍራ የመረጡ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየአረብ አገራት ለዓመታት ሊያውም በከፍተኛ ችግርና መከራ ውስጥ ሆነው፣ ያለባቸውን ጭቆናንና መከራ ተቋቁመው በኖሩና በአገር ቤት ለሚገኙ ዘመዶቻቸው በተለይም በድህነት ያሳደጓቸውን  አባትና እናቶቻቸውን ለመደጎም ቁምስቅላቸውን እየዩ በሚኖሩባት ሳውዲአረቢያ ይባስ ብሎ ወገንና አገር እንደሌላቸው ፤ ይልቁንም ሊከላከልላቸው የሚችል መንግስት እንደሌላቸው የተረዱት ሳውዲ አረቢያዎች፤ በሌሎች  አገራት ዜጎች ላይ ባልፈጸሙት መልኩ ኢትዮጵያውያኑን ዓለም ሁሉ እያየ ሲግድሏቸው፣ ሲገርፏቸው፣ ሲደፍሯቸው፣ እየገደሉ ስጋቸውን ሲቆራርሱና እንደውሻ በመንገድ ላይ ሲታዩ ማየት ምን ያህል ያደማል፣ ያቆስላል፣ ያማል፣ ያስለቅሳል።

የሳውዲ አረቢያው በዚህ መልኩ ታየ እንጂ በሌሎችም የአረቡ ዓለም በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና መከራ ምን ያህል አስቸጋሪና የከፋ መሆኑን በቀላሉ መገመት ይቻላል። በአረቡ አለም የታየው ስቃይ ምን አልባትም ኢትዮጵያውያን በአገራችንም ከምናየው መከራና ስቃይ በምንም መልኩ እንደማይተናነስ ከማንም  የተሰወረ አይደለም። በአረቡ አለም የተፈጸመው በባዕዳን የተፈጸመ ከመሆኑ ውጭ በመንገድ ላይ ተገደሉ አገር ቤትም ውስጥ ግድያ አለ፣ እስራትና ድብደባም በአገር ቤትም አለ፣ ችግርና ድህነት በአገር ቤት በዝቶ አይደለም እንዴ እህቶቻችን ለመሰደድ የተዳረጉት ፣ ሳዊዲአረቢያ ሁሉም  በህግ ወጥ መንገድ በሌላ አገር ዞረው ወጡ እንዴ? አይመስለኝም! ብዙዎች የህወሃት ባለማዋሎች  በደላላነት በተሰማሩበት የሰዎች  ማዟዟር አማካኝነት ይህ እንደተከናወነ እየታወቀ  እንዳላወቁ እየሆኑ ህወሃቶች በህዝቡ ላይ ሲያላግጡ ያሳዝናል። ለመሆኑ ከአገር ተደብቆ የወጣው ምን ያህሉ ነው? አብዛኛው ወጣት መሆኑና ይልቁንም በዚሁ በአገራችን ዘረኛ ቡድን አመራር ዘመን  የተወለዱና ያደጉ መሆናቸውን ማንም ምንም መረጃ ሳያገላብጥ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ያሉትን ፎትግራፎች አይቶ በቀላሉ መገመት ይችላል።

ዛሬ አገራችን ለራሳቸው ጥቅም በተደራጁ ሃይሎች እየተመራች መሆኑ፣ ለአገር ሳይሆን ለቡድናዊ ጥቅሞቻቸው ቆርጠው በተነሱ፣ ለአገሪቷ ህዝቦችና ለአገሪቷ ምንም የማይቆረቆሩ ተሰብስበው አገሪቷን የሚመሩ በመሆኑ ፤ ምንም የህዝብ ውክልና ሳይኖራቸው በግድና ህዝብን በማስገደድ ለሁሌም አገሪቷን ለመበዝበዝ በቆረጡ ኋይሎች እጅ ወድቃ ያለች አገር በመሆኗ ፤ የተፈጠሩ ችግሮች እንጂ በህዝብና በመንግስት መካከል ልዩነቶች ባይኖሩና ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው በጋራ ሰርተን መኖር አቅቶን አይደለም፣ ማደግም አቅቶን አይደለም፣ ተሳስበን ለሃገራችን መስራትም አቅቶንም አይደለም ፣ 22 ዓመታት አሁን ካለንበት ውድቀት ለመዳንበቂ ጊዜ ሳይሆን ቀርቶም አይደለም።

በኢትዮጵያውያን  ስም ከውጭ አገራት  በብድር፣ በእርዳታና በንግድ የተሰበሰቡ ገንዘቦችን በውጭ ባንኮች እያሸሹ የሚያስቀምጡት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን? በአገሪቷ ሃብት ላይ የብዝበዛ ስራን የሚፈጽም ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ለዚህስ የህዝብ ድህነት ላይ መውደቅና ለችግር መዳረግ ምክንያቱ ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ ሀብታሞቹና በአገሪቷ ውስጥ እንደፈለጉ በአገሪቷ ሃብት የሚባልጉት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ የአገሪቷ ህዝብ መከራ የሚያየው በማን ሆነና ነው ዛሬ ህወሃት/ኢህአዲግ አሳቢ ሆኖ ለመታየት የሚፈልገው ?

የችግሮቻችን ምክንያቶች የህዝባችን ስንፍና፣ አልሰራ ባይነት እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሳይሆኑ ህወሃት የፈጠረው የማህበራዊ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንጂ ህዝቡ በራሱ ላይ የፈጠረው ችግር እንዳልሆነ ማንንም ለማስረዳት መሞከር አያስፈልግም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የችግሩ ምክንያትንም ሆነ የአገሪቷንና የህዝቧን መከራ ምክንያቶች ህወሃቶች እንደሆኑ በግልጽ ያውቃል  ። ይህንንም አፍረት ለመቋቋም ህዝቡ የሚችለውን ለማድረግ የቆረጠበት ሰዓት ነው።

እንግዲህ ህወሃቶች የአገሪቷና የህዝቧ እፍረቶች ስፍራችሁን አዘጋጅታችኋል፣ የምትፈልጉትን በዝብዛችኋል፣ አይን ያወጧ ዝርፊያን ፈጽማችኋል፣ ዘረኝነትን አንግሳችሁ ህዝቡን በመለያየት ለጋራ አላማ እንዳይሰራ አድርጋችኋል፣ ለእናንተ የብዝበዛ ዘመናችሁን ለማርዘም ጠቅሟችኋል ለህዝቡና ለአገሪቷ ግን ትልቅ ፈተናና መከራ ሆናችኋላና ይበቃችኋል ።  እናንተ የማትሸከሙትን ሁሉ አሸክማችሁ አሰቃይታችሁታል፣ በእናንተና በልጆቻችሁ ወይም በቤተሰቦቻችሁ ላይ ሊደርስ የማትፈልጉትን ፈጽማችሁበታል። አሁን ለራሳችሁ ስትሉ የምታስቡበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛላችሁ።

ይህ ካልሆነ ግን ህዝቡ ብዙ ታግሷል፤ አሁን ግን የእፍረታችን ምክንያቶች የሆናችሁ ህወሃቶች ካልሆነ ግን ይህ የፈጸማችሁትን ግፍ ለፍርድ የሚያቀርብን ትግል እያፋጠናችሁ እንደሆነ ልመክራችሁ እፈልጋለሁ። አገራችን የናንተ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት። ወደዳችሁም  ጠላችሁም የአገሪቷ መጻኢ ፋንታን የመወሰን መብት የአገሪቷ ህዝብ እንጂ የጥቂት በዝባዥ ህወሃቶች እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።

የአገሬ ህዝቦች ዛሬ የችግራችንን ጥልቀት ከዚህ በኋላ በጽሁፍ በማስረዳት መሞከር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም  ማንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የህወሓት/ኢህአዴግ ችግር እቤቱ ያልገባ የለም፣ በህወሃት ያልተገደለ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ክብሩ ያልተነካ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ያልተሰደደ የለም፣ በህወሓት/ኢህአዴግ ቤት ንብረቱ ያልተነጠቀ የለም፣  በህወሓት/ኢህአዴግ ያላለቀሰ የለም ዛሬ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ልንስማማ ይገባናል። ይህም የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያትና የመከራችን ሁሉ፣ የአፍረታችንም ሁሉ ምክንያት በሆነው በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብ ላይ የተስፋችንን ችቦ ማውለብለብ ይገባል። ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ለትግል ሊቆርጥ ይገባል። በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብር ላይ የተስፋችንን ችቦ እናቀጣጥል! በዚህም የአገራችን ህዝቦች መከራ ያብቃ!   አት ባለሓት ሕሕሕ

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች !


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>