Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የኛ ነገር፡ ክፍል 20፤ ሰይፋችንን አጥተነው፤ ሰልፋችንንም ልንቀማ ?? (ከተክለሚካኤል አበበ )

$
0
0

ከ ተክለሚካኤል አበበ

የሳኡዲ ግፍና የኛ ሰልፍ፤

እንደመግቢያ፤ የፋና ነገር

  1. ፋና፤ ኢትዮጵያዊ ካናዳዊት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፡፡ እሱዋ እንደምትለው ከሆነ ፖለቲካ አትወድም፡፡ በአባይ ቦንድ ሽያጭና በመሰል የመንግስት መርሀ ግብር ዝግጅቶች ላይ ግን ቀድማ የምትገኝ ጎበዝ ነች፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ተቃዋሚዎች መፈክር ይዘው በኢህአዴግ ላይ ሲሰለፉ ስትመለከት ግን ደምዋ ይፈላል፡፡ ሰሞኑን በዚህ በሳኡዲአረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ ስላሳዘናት፤ ሳውዲዎችን ልክ ልካቸውን ልትነግራቸው ቆርጣ ተነስታለች፡፡ ስለዚህም በመጪው አርብ መሰል ጉዋደኞችዋን ይዛ ሰልፍ ልትወጣ ተፍ ተፍ ትላለች፡፡ በፋና እምነት በሳኡዲ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የሰልፉ እንዱ ደንብ በምንም አይነት መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ስም በክፉ አይነሳም የሚለው ነው፡፡ ሰናይም ወንዱ ፋና ነው፡፡ እንደፋና ያምናል፡፡ ከፋና ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር፤ ኢትዮጵያውኑን በግዜ ባለመርዳቱ የኢትዮጵያን መንግስት የሚመለከተው ቢሆንም፤ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮች ማንገብ ይከፈፍለናል ባይ ነው፡፡ በተወሰነ በሰሞኑ ሰልፎች የገረመኝ፤ ያሳሰበኝ፤ ያቃጠለኝም ነገር ይሄ ነው፡፡
  1. የሳኡዲን ግፍ ተከትሎ፤ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ሰዎች ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ተከትሎ በየከተማው የሚገኘውን ተቃውሞ በመገናኛ ብዙሀን በመመልከት በኢትዮጵያዊን አንድነትና መደጋገፍ የረኩ፤ በተቃውሞው ግዝፈትም የተደሰቱ ይመስላል፡፡ እኔ ደግሞ በየስፍራው ከሚታዩት ተቃውሞዎች ጀርባ የተደበቀውን ፍርሀት፤ ጥርጣሬና ድንቁርና ስመለከት፤ እጅግ አዝኜ ልጽፍ ነው፡፡ ስለተደፈሩና ስለተገደሉ፤ ስለተዘረፉና ስለተገረፉ ኢትዮጵያውን በበቂ ስለተዘገበ ስለነሱ አልጽፍም፡፡ በነሱ ላይ በደረሰውና በኛ በውች በምንገኝ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵዊ ድርጅቶች በኩል ስለታየው ምላሽ እንጂ፡፡ ከኒው ዮርክ እስከ ሲያትል፤ ከኦታዋ፤ እስከ ከቶሮንቶ እስከ ቺካጎ … ያለውን የተቃውሞ ሰልፎችናና የተቃውሞዎቹን አፈጣጠር እንዲሁም አካሄድ በጥልቀት የተመለከትን እንደሆን፤ ከቁጣው ጀርባ የሚያሳስብና ርምጃ ሊወሰድበት የሚገባ ነገር አለ፡፡ አንዳንዶቹ ሰልፎች የኛ አልነበሩም፡፡ የነሱ እንጂ፡፡ ኮሚቴ ለማቁዋቁዋም ላይ ታች ስንል ተመለከተም፤ ከ23 አመታት በሁዋላም ይሄንን መሰል ግፍ ለመቃወም የሚያስተባብር ቁዋሚ ተቁዋም አለመኖሩም አሳዛኝ ነው፡፡

ቶሮንቶ፡

  1. በቶሮንቶ በዚህ በሳኡዲ ግፍ ጉዳይ ላይ፤ እስካሁን አራት ሰልፎች፤ አንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ተደርገዋል፡፡ የመጀመሪያው የተቃውሞ ሰልፍ የተጠራው የአካባቢውን የሙዚቃ ባለሙያዎች ተገን ባደረጉ፤ ሰልፍና ፖለቲካ መደባለቅ የለባቸውም በሚሉ ግለሰቦች ነበር፡፡ ተቃውሞው ሙሉ በሙሉ በሳኡዲ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛው ሰልፍ የተጠራው ደግሞ ሕወሀትን በሚቃወመው ወገን ነበር፡፡ ሁለቱም ሰልፎች የተጠሩት ባንድ ቀን ነው፡፡ በሰልፉ እለት፤ የሁለተኛው ሰልፍ ጠሪዎች ሰልፋቸውን አስቀድመው ጨርሰው ወደአንደኛው ሰልፍ ወርደው ሰልፉን በተቃውሞ መፈክሮች ባያጥለቀልቁት ኖሮ፤ መጀመሪያ የተጠራው ሰልፍ ኢትዮጵያዊያን ከአገራቸው ስለሚፈነቅላቸው ስርአትም የሚቃወም ሳይሆን፤ የሳኡዲን ግፍ ብቻ አውግዞ የሚለያይ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያት፤ ከላይ በአንቀጽ አንድ የጠቀስኩትና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶችም፡፡ ግፍ ግፍ ነው፡፡ በሳኡዲም ይፈጸም በጋንዲ፤ በመለስም ይፈጸም በዳዲ፤ ግፍ ግፍ ነው፡፡ ፖለቲካ አንወድም ወይንም ፖለቲካ እንፈራለን በሚሉ ወገኖች ዘንድ ግን ይሄ ግንዛቤ ያለ አይመስልም፡፡ ቢኖርም፤ እነዚህ ሰዎች፤ የራስ-መንግስት ግፍ ተቀባይነት አለው አይነት የሞራል አስተሳሰብ አላቸው፡፡ ፖለቲካና ሰብአዊ መብት የተለያዩ ናቸው አይነት ነገር፡፡
  1. የቶሮንቶውን በተመለከተ፤ በሰልፉ ላይ ትንታግ ሆና የዋለች እህት፤ ይሄንን ፖለቲካና ሰብአዊ መብት አትደባልቁ ስልት በተመለከተ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡፡ Just to let you know all, this is the new trend TPLF has started now, they organize protests before activists do … Please, also spread this word and warn innocent Ethiopians not to be used in every media outlet available. Jiraf erasu gerfo, erasu yichohal, sad. አዲሱ የህወሀት ስልት፤ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ አይነት ነገር፡፡ ወይም ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል፡፡ የዋህ ኢትዮጵያዊያን እንይሸወዱና መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ለመገናኛ ብዙሀን አሳስቡ፤ ስትል ተናግራለች፡፡

 

ኒውዮርክ፤ ሺካጎ፤ ኦታዋ

  1. አንድ የኒው ዮርክ ሰው እንደጻፈው፤ ሌላ የቺካጎ ሰውም እንደዘገበው፤ የኦታዋ ጋደኞቼ እንደነገሩኝ ከሆነ፤ በኦታዋ፤ በሺካጎና በኒው ዮርክም የሆነው ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ አቶ አለማየሁ በሁሉ ከኒው ዮርክ እንዲህ ብሎ ጽፎዋል፡ The demonstration was organized by pro-Woyanne, but overtaken and led by anti-Woyanne group which included loud verbal disagreement and some shoving, pushing between the 2 groups for few minutes:: ሰልፉ የተዘጋጀው በአፍቃሬ መንግስቶች ነበር፤ ነገር ግን ከጥቂት አተካሮ በሁዋላ አፍቃሬ ዴሞክራሲዎቹ ቀሙት እንደማለት ነው በግርድፉ፡፡ ሺካጎዎች ለጊዜው የተረቱ ይመስላል፡፡ የረዥም ግዜ የሺካጎ አካባቢ ተሙዋጋች አቶ አበራ ሲሳይ ስለሺካጎ ተሞክራቸው እንዲህ ብለው ጽፈዋል፡፡ We in Chicago tried to do the same but overtaken by a group named “hand to hand” .We proposed that we collectively denounce the woyane government along with the Saudi officals in our slogans and petition. The group rejected our proposed idea. They said they will not allow woyane to be denounced. በሺካጎም እንደኒውዮርኩ ወይም ቶሮንቶው ቡድን ከሳውዲ ጎን ለጎን የወያኔ ስርአትንም ማውገዝ አለብን ብለን ጠየቅን፡፡ ነገር ግን ወያኔ አይነካም በሚል እጅ በእጅ በተሰኘ ቡድን ተዋጥን እንደማለት ነው በጥሬው፡፡

 

ትንታኔ፤ ትችትና ጥቆማ፤

  1. በሳኡዲ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ አሰቃቂ ነው፡፡ በርግጥ መጠኑና ቅርጹ ለየት አለ እንጂ፤ የሴቶቻችን መደፈር፤ የኢትዮጵያዊያን በአረብ አገር መገደልና መንገላታት ያለና የነበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ቅርጽ እስካለችም ወደፊትም የሚኖር ይመስላል፡፡ ከግፉ ይልቅ ግን፤ ስለግፉ በኢትዮጵያውያን መካከል የታየው ግዙፍ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ ጎን ለጎንም፤ ይሄ ወቅት፤ መንግስት ዜጎቹን ለመሰብሰብና ለመጠበቅ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሲሰንፍ፤ በተቃዋሚው በኩል ለዜጎች እንደተለዋጭ መንግስት የሚያስብና የሚሙዋገት ፖለቲካዊ ተቁዋም አለመኖሩ የትግላችንን ሰንካላነትና የተቃወወሞዋችንን ጉዶሎነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶዋል፡፡ ከሀያ ሶስት አመት በሁዋላም፤ ይሄ ነው የምንለው እኛን የሚያሰባስብ አስተማማኝ ተቁዋም ባለመገንባታችን፤ እንደገና ኮሚቴ ወደማቁዋቁዋም ስንራወጥ መመልከት እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ትግላችን የአድ ሆክ ኮሚቴ ግንባታ ሆነ፡፡
  1. የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ፤ ከዚህ ከሳኡዲ ችግር ጋር በተያያዘ ያቁዋቁዋምነው አለማቀፍ ኮሚቴም፤ አስር ሀያ አመት ከምናደርግበት የትግል ስልት ብዙ ፈቀቅ ያለ አይመስልም፡፡ የኮሚቴው ሙሉ ዝርዝር ባይኖረኝም፤ የሶስቱ ሰዎች ስም እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ኮሚቴው ዘመኑን ያልዋጀ፤ የአንድ ብሄር ስብስብ ነው የሚመስለው፡፡ ስብስቡ አለማቀፍም አገርአቀፍም ደረጃውን እንዲጠብቅ አልተደረገም፡፡ ወዳጆቼ ታማኝና አበበን በቅርበት አውቃቸዋለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነት ስሜታቸው ከነሱ የተሣለም የተሻለም አለ ለማለት ይከብዳል፡፡ አቶ ብርሀኑ ዳምጤም እንደሰማሁት ከሆነ ሌሎች የግል ህጸጾች ቢኖሩትም፤ በኢትዮጵያዊነቱ ጥያቄ የሚነሳ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን፤ ቢያንስ ሴቶችና የእስልምና እምነት ተከታዮች መታከል፤ ካሉበትም ደግሞ ግንባር ላይ መቀመጥ ነበረባቸው፡፡  ከታላቁ የኦሮሞ ብሄረሰብም በግልጽ ሚታይ ሰው አለመወከሉ ስህተት ነው፡፡ እንዲህ ያለው እነሱን ያላካተተ ኮሚቴና አካሄድ መብዛቱ ነው ብዙ የኦሮሞ ተቆርቃሪዎችን ሌላ መፈክርና መለያ ይዘው እንዲወጡ የሚጋብዛቸው፡፡ በዚህ ሌሎችን ብሄሮች በማስተናገዱ ረገድ፤ ኢህአዴግ/ሕወሀት ከኛ ብልጥ ነው፡፡
  1. ብዙ በተለምዶ የአንድነት ሀይል ተብሎ በሚጠራው ስብስብ የሚገኙ ሰዎች ይሄንን ብሄርና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ትችቴ እንደሚጎመዝዛቸው አውቃለሁ፡፡ ጎበዝ፤ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ሆነ፤ ወደድንም ጠላንም ያላፉት 23 አመታት እንደሚያሳዩን፤ ብዜ ግዜ ብሄርን፤ አንዳንዴ ሀይማኖትን መሰረት ያደረገው የኢህአዴግ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም  ገዢ ሆኖ ቆይታል፡፡ ሰዎች በብሄር ነቅተዋል፡፡ ሰዎች በሀይማኖትም ነቅተዋል፡፡ ስለዚህ ብንቀበለውም ባንቀበለውም፤ በአደባባይ እንደዚያ ብለን ባናውጅም፤ ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ለማለስለስና ለማስቀልበስ የምናቃቁማቸው ተቁዋማትና ስብስቦችም ሁኑ ሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሲቪክ ማህበራቶቻችን፤ በተዘዋዋሪ ይሄንን የሀይማኖትና የብሄር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገቡ መሆን አለባቸው፡፡ እስከአሁን እንደታዘብኩት ከሆነ፤ በኛ በአንድነቱ በኩል ያለምንም ማሻሻያ የድሮውን ኢህአዴግ ከመግባቱ በፊት የነበረውን አሰላለፍ እየደጋገምን ከማንንጸባረቅ ውጪ፤ የኢህአዴግን ርእዮተዓለም የሚያንፉዋቅቅም ይሁን የሚተካ አስተሳብ ማምጣት አልቻልንም፡፡ በዚህ በሰሞኑ ክስተት ውስጥ፤ በትንሹ፤ ለሳኡዲ፤ ከታማኝ ልቁ ሀጂ ነጂብ፤ ከአበበ ይልቅ አባስ አይነ-ግቡ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ከፍተኛ አለማቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ስራም ስለሚፈልግ፤ ኮሚቴው በቀድሞ ጎምቱ ዲፕሎማቶች ቢጠናከር መልካም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያንን ለማስተባበርና ሳኡዲዎችን ለመጀንጀን የምናቁዋቁመውን ኮሚቴ መለየት ያለብን ይመስለኛል፡፡

ሰልፎቹን ግን ተቀምተናል፡፡

  1. ከዚያ በተረፈ፤ በዚህ በሳኡዲ ግፍ ማግስት በሚደረጉ ሰልፎች ላይ የተወሰኑትን ሰልፎች ተቀምተናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የካናዳ ዋና ከተማ፤ ኦታዋ ነች፡፡ የዛሬ ሶስት አመት ለድህረ ምረቃ ትምህርት ኦታዋ ስገባ፤ የአንጋፋው ፖለቲካ ድርጅት፤ ኢህአፓ አባላት፤ ይሄማ የኛ ግዛት ነው እያሉ እያንዳንዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በነሱ ፈቃድና ቡራኬ እንዲያልፍ ለማድረግ ይንጎማለሉ ነበር፡፡ ባይሳካላቸውም፡፡ እነሆ የሳኡዲውን ክስተት ተከትሎ በኦታዋ ሰልፍ ሲጠራ ግን፤ የቶሮንቶ ሰልፈኞች በአውቶብስ ተጉዘው ብርታት እስኪሰጡዋቸው ድረስ፤ እነዚያ እኛ ጋር ዘራፍ ይሉ የነበሩት የኢህአፓ ቀናተኞች፤ አንገታቸወንም ይሁን የያዙትን የተቃውሞ መፈክር እንኩዋን ቀና አድርገው ለመሄድ አልደፈሩም፡፡ ኢህአፓዎች ልጆቻቸውን እንኩዋን ሳይተኩ ማርጀታቸው እንዴት እነደማያሳስባቸው ይገርመኛል፡፡ ጎበዝ እያረጀን ነው፡፤ ተተኪ አባላት ሳንወልድ ልናልፍ ነው ብሎ ማን እንደሚነግራቸው እንጃ፡፡ በንጽጽር ግንቦት ሰባት ለወጣቱ የተሻለ መስህብ ቢኖረውም፤ ይሄንን አጋጣሚ እንዋን ተጠቅሞ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ከማውገዝ ባሻገር፤ መደረግ ስለሚገባቸውም ነገሮች ተጨባጭ ነገር መጠቆም አልቻለም፡፡ በውጭ አገር መሪ አጣን፡፡ በዚህ ረገድ በአገር ቤት ያሉት፤ ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች ይሻላሉ፡፡

እንደ ማጠቃለያ

  1. ጎበዝ ባንዲራውን ተቀምተናል፡፡ አገራችንን ተቀምተናል፡፡ ነጻነታችንን ተቀምተናል፡፡ ሰልፋችን ነበር የቀረን እሱንም ልንቀማ ነው፡፡ ለጊዜው ድነናል፡፡ በዘላቂነት ግን እንጃ፡፡ የኒው ዮርኩ አቶ አለማየሁ እንደጻፈው፤ እነሱ፤ ኢህአዲጎች  መተካካታቸው የምር ነው፡፡ I was hoping that the Woyanne and its supporter’s children grew up in melting pot cities such as, Addis and free of hatred. It appears they are here to make us shut our mouth and take their parent’s torch:: ወያኔና ደጋገፊዎቹ እንደአዲስ አበባ ባሉ ሰፊ ከተሞች በማደጋቸው ከጥላቻ ነጻ ናቸው ብዬ አስብ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፤ የወላጆቻቸውን ችቦ ተቀብለው፤ እዚህም አፋችንን ሊያዘጉን ይፈልጋሉ፡፡ የህወሀት ልጆች ዘመናዊ ትምህርት በአውሮፓና አሜሪካ ቢማሩም፤ ባህላዊውን ፖለቲካም በሚገባ እየሸመደዱት ነው፡፡ በርግጥም በተወሰነ መልኩ የመፈክሮቻችንን ቅኝቶች ለውጠዋቸዋል፡፡ በዚህ ሳምንት የቶሮንቶ የኢትዮጵያ ማህበር ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ፤ አመራሩ መፈክሮቹና ንግግሮቹ ፖለቲካዊ እንዳሆይኑ ለማድረግ ያደርግ የነበረውን ጥንቃቄ ለተመለከተ፤ በርግጥም ኢህአዴግ/ሕወሀት አካሄዳችንን ምን ያህል እንደሸበው ያሳያል፡፡
  1. በዚህ የሳኡዲ ክስተት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከዚህ ቀደም በተካንበት ነገር ስንኩዋን መቀደማችንን ነው፡፡ በአንዳንዶቹ እኔ በቅርበት በታዘብካቸው ሰልፎች ያየሁት ነገር ቢኖር፤ ሰልፎቹ የተዘጋጁት ወይንም የመጀመሪያውን ተነሳሽነት የወሰዱት፤ አንድም የመንግስት ደጋፊዎች ናቸው፤ ወይንም ከጀርባቸው የመንግስት ደጋፊዎች የተደበቁባቸው ፖለቲካን እንደእሳት የሚፈሩ ገለልተኛ የተሰኙ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ ክስተት ድክመታችን የተጋለጠበት፤ ገመናችን የታየበት፤ እኛ እያረጅን ልጆቻችንን ሳንተካ፤ ኢህአዴግ/ሕወሀቶች ግን ልጆቻቸውን ሲተኩ የተመለከትንበት ክስተት ነው፡፡ ኢህአዴግ የደንቆሮዎች ስብስብ መሆኑ እንጂ፤ ይሄ እንኩዋን እርቅ ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ ይሄ አንድነት አንድነት የሚባል ነገር ባይመቸንም፤ በተቃዋሚውም ዘንድ የኢህአዴግን ድንቁርና ትንሽ ስለምንጋራ እንጂ፤ ለአንድነት መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ ልዩነታችን ግን፤ ቢያንስ አነሱ አውራ-ፓርቲ አላቸው፡፡ እኛ ግን አውራም፤ አውራ ፓርቲም የለንም፡፡ ጎበዝ፤ 23ኛ ፓርቲ አያስፈልገንም፡፡ አንድ አሸናፊ እነጂ፡፡

 

ተክለሚካኤል አበበ ሳኅለማሪም፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ የህዳር ሚካኤል ሳምንት፡ 2006/2013

Pen


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>