Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የረዳት አብራሪ ኃይለመድህን ተግባር

$
0
0

ናትናኤል ካብትይመር (ኦስሎ ኖርዌይ)
Natnael Kabtimer
ስለ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን ብዙ ተብሏል ብዙ ተፅፏል ቢሆንም የጀግንነት ተግባሩ ስላኮራኝ እኔም የበኩሌን ልበል። ጥቂቶች በተለይም የወያኔ ህወሃት አባላትና አቀንቃኞች እንዴት ጀግና ይባላል ሲሉ እያስተዋልኩ ነው ፡ ነገር ግን እኔም ሆንኩ በርካታ ሰዎች ረዳት አብራሪውን ጀግና ያልንበት ዋነኛ ምክንያት “በጭቆና ስርዓት ውስጥ ላሉና ብሶታቸውን ማሰማት ላልቻሉ ድምፅ የሆነና ብሶታቸው እንዲሰማ ብሎ ራሱን መስዋዕት ያረገ ሁሉ ጀግና ስለሆነ ነው” እንላለን።
በአየር መንገድም ሆነ በተለያዩ ከፍተኛ አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት በሚያገለግሉ ከወያኔ ዘር ወይም አባል ባልሆኑ የተለያዩ ባለሞያዎች ላይ ገሃድ የወጣ የመብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሆነ እናውቃለን። በማናለብኝነትና በዕብሪት ላይ የተመሰረተ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በርካታ ለሃገር እድገት ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ ባለሞያዎችን በአግባቡ አላሰራና አላፈናፍን ማለቱን ማንም ኢትዮጲያዊ ያውቃል።
የኢትዮጲያ አየር መንገድም በተለያዩ ግዜያት የመንግስት ጣልቃ ገብነት እያማረረው እንደኖረ የቀድሞ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዋቄ በተለያዩ ግዜያት ለመጠቆም ሲሞክሩ አስተውያለው። የኢትዮጲያ አየር መንገድ እንደ አለማቀፍ ድርጅትነቱ ከሌሎች ሃገራት አምሳያ ድርጅቶች አንፃር ሲታይ የበለጠ የሰራትኞች ስራ መልቀቅ (Employee turnover) በእጅጉ የሚያጠቃው እንደሆነ በርካታ ኢትዮጲያዊያን ያውቃሉ። በርካታ ወጣትና አንጋፋ ባለሞያዎች በአየር መንገድ በተለያዩ ሞያዎች በአብራሪነት ፣ በበረራ አስተናጋጅነት ፣ በቴክኒሺያንነት ፣ በአስተዳደር ፣ በማርኬቲንግ እና በደንበኞች አገልግሎት ስራ የተሰማሩ ድርጅቱ ለስልጠናና መሰል ክህሎት ማጎልበቻ ከፍተኛ ወጪ ያወጣባቸው ሰራተኞች ባለው የህወሃት ሰዎች አጉል ጣልቃ ገብነት በፈጠረው መጠነ ሰፊ አስተዳደራዊ በደል ተማረው ስራቸውንና የሚወድዋትን ሃገራቸውን ጥለው ወደተለያዩ የሌላ ሃገራት አየር መንገዶች ሄደው እንደሚሰሩ የሰነበተ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በወያኔ አስተዳደራዊ መድሎና ብልሹነት በርካታ ለሃገር ጠቃሚ የህክምና ባለሞያዎች ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንዲሁም በርካታ የተለያዩ ክህሎቶች ባለቤት የሆኑ ባለሞያዎችን ሃገራችን ስታጣ መቆየቷ ሁላችንም ስናየው የኖርነው ሃቅ ነው። የእድገት ፣ የስልጠናና የደሞዝ ጭማሪን የመሳሰሉ የሰራተኞች የኑሮ ደረጃና ክህሎት ማሳደጊያ ለተወሰነ ዘርና ሰዎች ብቻ የማረግ ሌሎችን የበይ ተመልካች በማድረግ መግፋት መረን ወጥቶ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ከፍተሻ ሰራተኛ እስከ ዋና ስራ አስፈፃሚ ድረስ የወያኔ ህወሃት አባላትና አቀንቃኞች መቆጣጠራቸውን በሌሎች መንግስታዊ ተቋማትም እንዲሁ መሆኑን ማንም ኢትዮጲያዊ ያውቃል።
ረዳት አብራሪ ኃይለመድን በአጠቃላይ የወያኔ ህወሃት አካሄድ አጉል የሆነና ሃገርን የሚጎዳ መሆኑ እንዲሁም በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የተንሰራፋው አስተዳደራዊ መድሎ በሃገር አቀፍ ደረጃ ስር ሰዶ ሃገራችንን ባለሞያ አልባ እያረጋት እንደሆነ የተረዳ መሆኑና ለዚህም የጀግንነት ተግባር እንደፈፀመ እንዲሁም ለሌሎች በሃገራቸው ተምረው በሞያቸው ሃገራቸውን ለማሳደግ ፣ ህዝባቸውንም ለመጥቀምና ለማገልገል አላሰራ ላላቸው ጨቋኝ አገዛዝ ድምፅ መሆኑን ሁላችንም ገብቶን ጀግና ብለነዋል።
አሁንም ሁልግዜም አምባገነናዊነትን አጥብቀን እንቃወማለን !!
natnaelkab@gmail.com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>