ሚያዝያ 27 ቀን፣ 1934 ዓ.ም. በጣሊያኖች ፈርሶ የነበረውን የዳግማዊ ሚኒልክ ሃውልት እንደገና ሲቆም፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እንዲህ አሉ።
“ይህ ዛሬ የሚመለከተን ሃውልት በ1922 ዓ.ም. በጥቅምት 22 ቀን እኛ ስንመለከተው የነበረው ነው። ለታላቁ ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ እጅግ ከፍ ላለ ስራቸው መታሰቢያ እንዲሆን አቆምነው።ጊዜ የሚያስመሰግናቸውን ስራቸውን በዚህ ሃውልት ተመለከትንበት። የኢጣሊያ ፋሽስት የጦር ሰራዊት በግፍ አገራችንን ከወረረ በኋላ በኢትዮጵያ ባለፈው ስራቸው የታወቁትን ኢትዮጵያውያኖችን ሲያጠፉ የኢትዮጵያንም ገናናነት ታሪክ ለመደሰሰ ተጣጥሯል። በዚህም መሰረት ሃምሌ 4 ቀን፣ 1928 ዓ.ም. የአጼ ምኒልን ሃውልት ነቀለው። በዚያን ጊዜም ኢትዮጵያዊያኖች ከትልቅ እስከ ትንሹ የአይን እንባ ብቻ ሳይሆን ልቡ ያለዘነ አይገኝም። ነገር ግን ታሪክ አይደመሰም። የታላቅ ስራ መታሰቢያ ለጊዜው ከመታየት ቢሰወር ጠላት ሊማርከው አይችልም።”
የአድዋ ድል እና የአጼ ምኒልክ ሃውልት ትዝታችን!
ዳዊት ከበደ ወየሳ ከአትላንታ