ባንድ ወቅት የቀዲሞ የኢትዮጵያ አየር ወለዶች ግዳጅ ተሰቶዋቸው በተሰማሩበት ዉጊያ ከባድ ድካም ዉስጥ በመግባታቸው የመፍረክረክ ሁነታ ይታያል በዚህን ጊዜ የብርጌዱ አዛዥ ኮሎነል ግሩም አበበ የምን መፍረክረክ ነዉ፣ አየር ወለድ ግንባሩን እንጂ ጀርባዉን አይመታም፣ በሉ ተከተሉኝ ብሎ ሳንጃዉን ወድሮ የጅቦምቡን ቅርቃር ነቅሎ ወደፊት ተንደረደረ። ሰራዊቱም ተከተለዉ ለሰዓታት ከምሽግ ምሽግ አይዘለለ ስዋጋ እና ሲያዋጋ ጦሩም በጠላት ላይ አያየለ መጣ፤ ከተወሰኑ አርሚጃወች በሖላ ኮሎኔል ግሩም ከፍጥነቱ አየቀነሰ በጉልበቱ በርከክ አለ፣ ወዲያዉም በሙሉ ሰዉነቱ መሬት ላይ አረፍ አለ። ከወዲወድያ እየተሯሯጡ ይዋጉ የነበሩ ኮማንዶች እንደገና ኮሎኔሉ አጠገብ መሰባሰብ ሲጀምሩ፣ እኔ ደሕና ነኝ ዉጊያዉን ቀጥሉ ብሎ ጋደም አለ። የተወሰኑ ወታደሮች ደግፈዉ አንዲት ዛፍ አስደግፈዉት በእልህ ወደ ዉጊያዉ ሮጡ። የመሰላቸዉ ላለፉት አርባ ስምንት ሰዓታት ምግብ ስላልቀመሰ ደክሞት ይሆናል ብለዉ ነበር። ከሰአታት አስቸጋሪ ትንቅንቅ በሖዋላ ጠላትን ደምስሰዉ ፩፮ኛ ሰንጥቅ መከናይዝድን ከከበባዉ በማዳን የተሰጣቸዉን ቦታ ከተቆጣጠሩ በሆዋላ በድል ወደ ኮሎኔል ግሩም በመሮጥ ድሉን ለማብሰር ስመጡ፣ ኮሎኔል ግሩም አበበ የ፭ኛ አየር ወለድ ብርጌድ ኣዛዥ ቅድም አንደተራ ወታደር በየሚሽጉ አይዘለለ ስዋጋ ተመቶ ኖሮአል ግራ ጎኑ በደም ርሶ የጦርነቱን መጠረሻ ሳያይ፣ ልጆቼን፣ በተሰቤን፣ ሳይል ለአገሩ ሲል አንዲት ሂይወቱን በመስጠት ለዘላለሙ አንቀላፍቶ አገኙት ።(የጦር ሜዳ ዉሎን ያንብቡ)
ኢትዮጵያ ብዙ ግሩሞች ነበሩዋት። ከነሱ ኣልፎ ለሌላዉ የምተርፍ ብዙ እዉቀት ብዙ ነገር እያላቸዉ ብቸኛ ህይወታቸዉን ለአገራቸዉ ክብር የሰጡ፤ ለነብሳቸዉ ሳይሳሱ የማይቻል የመሰለ መስዋእትነት የከፈሉ፣ ከዉርደት ይልቅ በክብር መሞትን የመረጡ። ኢትዮጵያ በጣም ብዙ ግሩሞች ነበሩዋት ከምንዳ ከገንዘብ ከትራፊና ከፍሪፋሪ ይልቅ ስለኣገራቸዉ መራብን የመረጡ። ኢትዮጵያ ብዙ ግሩሞች ነበሩዋት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስገኝ አውቀታቸዉን ለሚስኪኑ ህዝባቸዉ ሲሉ ንቀዉ በድህነት ኖረዉ በድህነት የሞቱ። ኢትዮጵያ ዛሬም ብዙ ግሩሞች አሉዋት ገድላቸዉ አንድ ቀን የሚወራላቸዉ፣ እነ አስኪንድሮች፣ እነአንዱአለሞች፣ እነርዮቶች፣ እነበቀለወች፣ እነኦልባናወች፣ እነናትናኤሎች፣ እነዉብሸቶች፣እነ እነ እነ እነ እነ ብዙ ብዙዎች።
ኢትዮጵያ ለሎችም አሉዋት ሆድ አምላካቸዉ፣ ዉርደት ክብራቸዉ፣ ክሂደት ዝናቸዉ፣ ዉሸት እዉቀታቸዉ፣ ባርነት ስብዕናቸዉ፣ እነብርሃኑ ዳምጤወች (ኣባመላ የሚለዉ ስም ሰልማይመጥነዉ ነዉ)።
ዉርደት በጩኸት ብዛት ክብር ላይሆን ኢትዮጵያ ብዙ ከርሳሞች ሞልተዋታል የተደገሰ ቦታ የማይጠፉ በልተዉ የማይሄዱ አንደዉሻ ካልጮሁ ።ከጢቂት ወራቶች በፍት በሳኡዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያኖች ሲታረዱ ብዙሆች ጮኸዉ ነበር አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ከጢቂት ከርስ አደሮች ጋር ሆነዉ። ዛሬ ከርስ አደሮቹ ከርሳቸዉን ወደ ሚሞሉበት ሲመልሱ አሁንም ኢንጮሃለን ከዱን ብለን። የሳኡዲ ጥቃት ሲያበሳጨን ጮኸን ፣ሆድ አደሮች ሲከዱንም ጮኸን አንችልም፣ ነብሰገዳዮች አገራችንን ሲበታትኑ ጮኸን ለዉጥ አላመጣንም፣ ቅርሳችን መለያችን ለባዳዎች ሲሳይ ሲሆን ጮኸን ጠብ ያለልን ነገር የለም። በጩኸት ብዛት ለነሆድ አደሮች ክብር እንደማይመጣ ሁሉ ለተቀረነዉም የነሱ አይነት ጩኸት ነጻነት አይሰጠንም። ነጻ የሚያወጣን እንደነ ግሩም አበበ ደም መክፈል ስንችል ብቻ ነዉ።ነጻ የሚንወጣዉ በአመንንበት ነገር ላይ ጸንተን መቆም ስንችል ብቻ ነዉ። የታላቁን ኢትዮጵያዊ የዓባመላን ስም ቅጥሉ አንዳደረገዉ አሳማ ወደነፈሰበት ብንዘም ውርደትን አንደ አካላችን ከማየት ያለፈ ነገር አይኖረንም፣ እንደ ኮሎኔል ግሩም ስንጸና ቢያንስ ሞታችን እንኩዋን በኩራት ዘንተ አለም ይነገራል። ሳኡዲወች አዋረዱን ብለን ስንጮህ የነበርነዉ በስተት ነበር ምክኒያቱም አራሳችንን ያዋረድነዉ አራሳችን መሆናችንን ስላልተረዳን። ብዙሺ ግሩሞች ጠዉልገዉ ያቆዩአትን አገራችይንን ለእነ አባአተላ ፣ለነ አባባንዳ፣ ለነ አባሆድ አምላክ፣አሳልፈን ሰተን ስደትን አንደመፍትሔ ቆጠርን በተሰደድንበትም ቢሆን ከነሱ መለየትን ባለመድፈር እራሳችንን አዋርደን ተዋረድን ኢንጂ በምንም መንገድ ሰኡዲወች አላዋረዱንም።
በምንም መንገድ አረቦች አላዋረዱንም ስብእናችንን አሳሞች ሲረጋግጡት መከላከል የተዉን፣ ከመሰሪዎች ጋር የተቆራኘን ጢቂቶች የተሻለ አማራጭ እያላቸዉ በሞታቸዉ ያስረከቡንን ነጻነት ዋጋ ያቃለልን እራሳችን እንጂ። በምንም መንገድ እራሳችንን ያዋረደን እኛዉ ነን፣ የእምቢ ጽናታችንን ከዉስጣችን አዉልቀን የጣልን፣ ከሃሰተኞች ጋር ቤተክርስቲያን የምናጣብብ፣ከአረመኔዎች ጋር መስግድ የሞላን ለእዉነት ካልቆሙ ለሃሰት ከምጸልዩ ጋር የተባበርን።አባቶቻችን ደም ከፍለዉ ያቆዩትን ነጻነት በፍርፋሪ ከሸጡ የሉኝንታ ካልፈጠረባቸዉ ከሃዲዎች ጋር እስከቆምን ድረስ እኛም ነጻነታችንን ለዘላለሙ እናጣዉ እንድሁ አንጂ መልሰን አናገኘዉም። መለየት የሚባልን ድፍረት የግድ መልመድ ካልተቻለ ዛሬም ነገም ብዙ ለሆዳችዉ ያደሩ ስያስጮሁን መኖራችን የማይቀር ነዉ። ጣይቱ በበቀለችበት ምድር ሊጁዋን እንዝርት ከማስያዝ ፋንታ ለዚሙት የምታሰማራን፣ ስብዕና በጎደላቸዉ አረቦች መጫወቻ ሆና አስክሬኑዋ የመጣን የጎሮቤት ልጃገረድ ቀብራ የራሱዋን የ፩፭ ዓመት ልጅ ባወጣዉ ያዉጣሽ ብላ መልሳ ወደዛዉ የምትልክን እናት፣የኮሎኔል ግሩም አይነት በሞሉባት ኢትዮጵያ ፣ ዛሬ እኔ ሞቼ ልጆቹን ከዉርደት ማዳን አለብኝ ከማለት ፋንታ እርሱም ፈርቶ ለመብታቸዉ የሚቆሙትን ሊጆቹን ለስደት ልኮ ባህር በላቸዉን ዜና ከሚጠብቅ አባት፣ መቀበሪያዉን ኢንኳን ለማትሞላ መሬት ማንነቱን የሸጠን ሰደተኛ ማህበረሰቡ በቃቹ ካላለ ፣ ለሆድ ማደር አገርን ማዋረድ ፣ ሃፍረት መሆኑ ቀርቶ ጥበብ በሆነበት ዘመን በሆድ አደሮች ጩኸት መደንቆራችን መልሰንም መጮሃችን ይቀጥል ኢንድሁ አንጂ ክብርን አያመጣም።ዉርደታችን የሚያበቃዉ የህዝብና የአገር ጠላቶች የሆኑትን የወያኔ ቅጥረኞች በቃቹ ብለን ፍትለፍት ለመጋፈጥ ስንቆርጥ ብቻ ነዉ።
ዉርደታችን የምያበቃዉ ትላንት እነሱ ተቀጥረዉለት የነበረዉን ሻቢያን ኢንዳላገለገሉት ሁሉ ዛሬ ከእናንተ ጋር ተዋረደን ከምንኖር ሞት ያሉትን በምንም መስፈርት የሻብያ አሽከር ብላቹ ብትጮሁ አንሰማቹሁም የማለት ብቃት ስናገኝ ነዉ።
ዉርደታችን የምያበቃዉ ገንዘባችንን በማዉጣት ለነጻነት የምደረግን ትግል ለማገዝ ስንቆርጥ፣ አስፈላጊም ከሆነ ለዘላለም ተዋርዶ ከመኖር እንደ ግሩም በክብርም ብሆን ለመሞት መቁረጥ ስንችል ነዉ።
ዉርደታችን የሚያበቃዉ በየእስር ቤቱ እየማቀቁ ያሉትን ወገኖቻችንን ልቀቁ ካልሆነም እናንተ ሌቦችን ከስር ቤት ኢያስመለጣቹ ለስልጣን ኢንደበቃቹ እኛም የወገኖቻችንን በዸል ለመበቀል ቆርጠናል ስንል ነዉ።
ዉርደታችን የሚያበቃዉ ከ፴ ሺ ብር በላይ ደሞዝ ፣ስም ፣ ዝና፣ ክብር፣ አለምን መዞር በጁ እያለ የወገኑን ብሶት ለአለም በማሳየት ወሂኒ መጣልን እንደመረጠዉ ሀይለመድህን አበራ እምቢ ስንል ብቻ ነዉ።መቀራረብን በመሻት፣ መቻቻልን ለመፍጠር የሚደረግ ነገር ሁሉ ለቅጥረኞች ለሆድ አደሮች ካልገባቸዉ ከነሱ መለየት አማራጭም አቆዋራጭም መሆኑ ግድ ነዉ።
ያለን አማራጭ ሁለት ብቻ ነዉ፣
አንድም እንደ ኮሎኔል ግሩም አበበ ወደፊት ሄዶ ግንባርን ሰጥቶ በክብር ማለፍ ሁለትም ከነዉርደት ፵ የማትሞላዋን ዕድሜ መኖር። አንድም እንደ ሀይለመድህን አበራ ሃምሳ ዓመትም ቢሆን ወይኒ መጣል ሁለትም በገዛ አገሩ የመጨረሻ ደረጃ ዜግነት መቀበል። አንድም እንደባህር ዳር ህዝብ መቆጣት ሁለትም በባዶ እግሩ የሚሄድ ለሃጫም አየተባሉ መኖር። አንድም የዓዱዋን ጀግኖች ፈለግ መከተል ሁለትም የደደቢትን ሹምባሾች ካልሲ ማጠብ። አንድም ሰዉ ሆኖ መራብ ሁለትም እንደ አባመላ ተብየዉ ትፋትን ልሶ መጥገብ።
ያለዉን ምርጫ መለየት ካልተቻለ ዉርደትን ከክብር የቆጠሩ አሳሞች ስጮሁ በአሳሞቹ የበገኑም አትጩሁ ኢያሉ ስጮሁ ዉርደቱም ጩኸቱም ይቀጥላል ኢስከወዲያኛዉ።
አዩም አያኔ ዘ ኢትዮጵያ
pompidoayane@ymail.com