Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

[የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ጉዳይ] –ማን ለጠበቃ ፈረመ???

$
0
0

ሰላም ለሁላችሁ፤
debereselam Minnesota
ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙ ምዕመናን የተላለፈ መልዕክት፦

በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ቤተክርስቲያኑን ወክሎ ማንኛውንም ውለታ/ሰነድ መፈረም የሚችለው ሊቀመንበሩ ብቻ እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል። የእየአንዳንዱ የቦርድ አባል የሥራ ድርሻ በተዘረዘረበት አንቀጽ 6 ላይ ማን በቤተክርስቲያኑ ስም ሰነዶችን
መፈረም እንደሚችል ተደንግጎ እናገኛለን ። አንቀጽ 6 ክፍል 3 ሀ ተ.ቁ 7 እንዲህ ይላል፦

“ሊቀመንበሩ፦

7. ጠቅላላ ጉባኤው፤ የባለአደራዎች ቦርድና የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ የተስማሙባቸውን ሰነዶችና ስምምነቶች ቤተክርስቲያኒቱን በመከወከል ይፈርማል”

ቤተክርስቲያኑን ወክያለሁ የምትለው ይህች ጠበቃ ግን ገና ሊቀመንበሩ በቦርድ ሕገወጥ ስብሰባ ታግደዋል ሳይባል ነው የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ነኝ ያለችው። ይህም ለሕጋዊው ሊቀመንበር በማያገባት ገብታ የሕዝብ ተምራጭ የሆኑትን ሊቀመንበር ከቦርድ ተባረዋል ብላ በጻፈችው ደብዳቤ ተጠቅሷል። እነርሱ ሊቀመንበር ያሉት እኛ ግን በሊቀመንበርነት የማናውቀው ሰውም ይህን ሰነድ የመፈረም ስልጣን የለውም። እነርሱም መርጠነዋል ያሉት ከዛ በሗል ነው። እናም የማርች 9ኙ ቤተክርስቲያኑ ተከሰሰ አዋጅ አጣብቂኝ ውስጥ የመግባታቸው ውጤት ነው። ድሮም ወያኔ ወንዝ አያሻግርም።
የእምነት ሕፀጽ የሌለባትን ቤተክርስቲያን በጥብጠው፣ ሲካፈሉት የኖሩትን ቅዱስ አገልግሎት እንደ መርገም ቆጥረው ቀኖና ያጎደለ ቤተክርስቲያን ነው ሲሉ የማይሰቀጥጣቸው፣ ሕዝቡን በማሸበር የፖለቲካ ተልእኳቸው ተከታይ የሚሆን መስሏቸው የሌለውን ችግር ፈጥረው ሰላማችንን ሲያምሱ መክረማቸውን
ያየ መድኃኔዓለም ቤቱን ባጸዳበት ቀን እነዚህንም ሊያጸዳ እያጻፋ አናገራቸው። በጥፋት ላይ ጥፋት በክስረት ላይ ክስረት ብቻ ስለሆነ ትርፉ እባካችሁ የበደላችሁትን ጌታ አና ኅዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ። የባሰ ሳይመጣ። ጊዜው ለዚህ የተመቸ ነውና።

ይህ ሕዝብ ሳይፈቅድና ሳያምንበት በቤተክርሲታኑ አቋም ላይ አንዳች ለውጥ አይመጣም!!! አሁንም ወደፊትም በአባቶች መካከል ያለው መለያየት እስኪወገድ ድረስ ከቤተክርስቲያናችን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ሳይሆን ከስልጣን ሽኩቻ፣ በዘረኝነትና በሙስና ከተጨማለቀ አስተዳደር ገለልተኛ ነን !!! ወዳጆቼ የአስተሳሰብ ልዩነት እኮ እንዲህ በግትረኝነትና ለምን ፍርስርስ አይልም እያሉ የሚያራምዱት አይደለም። ሕዝብ ወሰነ። እናንተ ግን 40/50 ሰው ጎድሎ ነበርና በክፍተኛ ድምጽ የተወሰነውን ውሳኔ አንቀበልም ብላችሁ በማያዋጣ ጎዳና መጓዝ ጀመራችሁ። መጨረሻችሁም ይኽው ከፍተኛ ወጪ አስከተለ። አሁንም አስቡበት አያዋጣችሁም። ሽንፈትን መቀበል ከባድ ቢሆንም ሊመጣ ካለው ከባድ ሽንፈት ይሻላልና ክርስቲያን ከሆናችሁ ይብቃችሁ። ባስቸኳይ ኅዝቡ ባቀረበው አጀንዳ መሠረት ጠቅላላ ጉባኔ ጥሩ። ሕዝቡ ከፈለገ ትቀጥላላችሁ ካልፈለጋችሁ ደግሞ እንደመረጣችሁ ያወርዳችኋል።
እስኪ እንደ ክርስቲያን ይቅርና እንደሰው ለደቂቃ አስቡት? በዚህ ባመጣችሁት ጉዳይ ምክንያት ምን ተጠቀምን? ምን አተረፍን? ችግር ተፈታ? ተቃለለ? ወይንስ ተባባሰ? ገለልተኝነት ቀረ? የችግሩ ምንጭ ፖለቲካ ነው። ችግሩ የሚፈታውም ፖለቲካው የሆነ ለውጥ ሲያመጣ ነው ወይንም ሲለወጥ ነው። ማንም ቢዳክር የተለያዩት አባቶች ሳይስማሙ/ሳይታረቁ ይህ ችግር አይፈታም!!!

በደብራችን በደብረሰላምም ሆነ በተዋሕዶ እምነታችን ላይ ምንም ከወትሮው የተለየ የእምነት ችግር የለም!!! ችግሩ የአስተዳደርና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነው። የእምነት ችግር አለ ለሚል ሰው ግን እስካሁን በገለልተኛ ቢተክርስቲያናት የተካፈለውን መንፈሳዊ አገልግሎት ምን ሊያደርገው ነው? ንሰሐ ሊገባበት ነው? ከዚህ በኋላስ በገለልተኛ ቤተክርስቲያን ይገለገላል? በርግጥ ያየበት መነጽር ስሕተት እንደነበረ ካመነ ምንም አይደል። አለበለዚያግን ክርስትናው አጠያያቂ ነው። ለማንኛውም መድኃኔዓለም ልቦና ይስጣችሁ። እውነት የቤተክርስቲያን ነገር ካሳሰባችሁ ብዙ የሚሰራ ሥራ አልና እዛላይ ብንሰራ ይሻላል። እናም እባካችሁ ይብቃችሁ!!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>