Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የገንዘባችን ዋጋ ስንት ነው?

$
0
0

ኤድመን ተስፋዬ *
* (የግብርናና ኢኮኖሚስት እና የገጠር ልማት ባለሞያ)

ethiopia-100birr
የ ፅሁፌ ትኩረት የገንዘባችንን ዋጋ በመፈተሸ ከንድፈ ሀሳብ እና ከሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ መነሻነት መንግስት ለዋጋ ግሽበቱ የሚሰጠውን የኢኮኖሚ እድገት ምክንያትነት ከመሞገት በተጨማሪ ከዋጋ ግሽበቱ ጀርባ አጮልቆ ማየት ነው፡፡ መነሻችን ኑሮአችን ነው ኑሮአችን ስንል ደግሞ ገንዘባችን አንዱ ና ዋነኛው ከመሆኑ አኩአያ እንቆቅልሽ የሆነብንን የገንዘባችን ዋጋ ከመግዛት አቅሙ አንፃር ዋጋውን በመፈተሽ በዋጋ ግሽበት አማካኝነት ገንዘባችንን መሰረቅ አለመሰረቃችንን መፈተሽ የሚያስፈልግ ይመስለኛል፣ የምን መሰረቅ ካሉ ከዛሬ አንድ ወር በፊት ዘንቢል ይዘው ወደ ገበያ ወጡ እንበል በ መቶ ብር ዘንቢሎን በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ሞልተው ተመለሱ እንደገና ከ አንድ ወር ወይም ከ አራት ወር በሁአላ በተመሳሳይ መልኩ ከአንድ ወር በፊት የሸመቱትን እቃ ለመሸመት መቶ ብር ይዘው ሲወጡ መቶ ብሮ ሊገዛሎት የቻለው እቃ ከዘንቢሉ ግማሽ አላለፈም እንበል ምክንያቱ ደግሞ በገንዘቡ የመግዛት አቅም መቀነስ የተነሳ በኪሶ የያዙትን ገንዘብ በመሰረቆኦ ነው:: ይህም ማለት የአንድ ብር ኖት የዋጋ ግሽበቱ 30 ፐርሰንት በሆነበት ሁናቴ ያለው ዋጋ (1 /1.30) 0.76 ወይም ሰባ አምስት ሳንቲም በመሆኑ ሃያ አምስት ሳንቲም ከአንድ ብር ላይ እንደ መሰረቅ ማለት ነው ፡፡ ስለ ገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ ወይም ስለ ዋጋ ግሽበት ሲነሳ በአሁኑ ወቅት ምሳሌ የምትሆነው የሮበርት ሙጋቤ ሀገር ዙንባቤ ነች፣ የዙንባቤ ገንዘብ ከመውደቁ የተነሳ በዙንባቤ ከተሞች በፌስታል ሙሉ ገንዘብ ቢያዩ ከገንዘቡ ይልቅ ፌስታሉ ዋጋ እንዳለው ማወቅ አለቦት በሚል ደረጃ እስኪቀለድበት ድረስ ገንዘባቸው የማገበያየት አቅሙ ሞታል፡፡ በሀገራችንም በአብዛኛው ህብረተሰብ ምነው ገንዘባችን የሱማሌ (ሱማሌ ከወራሪው ዚያድባሬ መውደቅ ጀምሮ እሰከ አሁን ምን ያህል ገንዘቡአ የማገበያየት አቅሙ እንደሞተ ልብ ይሉአል) ብር ሆነ በሌላ በኩል የኛን መቶ ብር ከ ከጃማይካዊው ዩዝየን ቦልት ጋር በማመሳሰል ዩዝየን ቦልት መቶ ሜትሩን ከ አስር ሰከንድ እንደሚገባው ሁሉ የኛም የመቶ ብር ኖት ተዘርዝሮ ለማለቅ ከአስር ሰከንድ ያላነሰ ጊዜ ነው የሚወስድበት የሚል እና ሌሎች ተመሳሳይ ማህበረሰባዊ ትዝብቶች እና ብሶቶች የገንዘባችንን የመግዛት አቅም መድከምን እና የኑሮ ውድነትን ተንተርሶ ይነሳሉ፡፡ በአንድ ወቅት በፖርላማ የሀገራችንን የዋጋ ግሽበት አደገኛነት በመግለፅ የግሽበቱን ምክንያት ከመንግስት ቅጥ ያጣ የገንዘብ ወጪ ስርአት ጋር የተገኛኘ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እንዲሁም መንግስት የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ተጨማሪ የገንዘብ መጠን ወደ ኢኮኖሚው በማስገባቱ ግሽበቱን እንዳባባሰው በመግለፅ መንግስት ወጪውን እንዲቀንስ በአንድ የተከበሩ የፓርላማ አባል ለተነሳው ጥያቄ ነብሳቸውን ይማርና የቀድሞው የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሰጡት መልስ ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ የዋጋ ግሽበት ( inflation) መከሰቱ አዲስ ነገር አለመሆኑን በመግለፅ የዋጋ ግሽበቱ ከኢኮኖሚው እድገቱ ጋር በተመጣጠነ መልኩ የተከሰተ መሆኑን በማብራራት ለዋጋ ግሽበቱ ሲባል የሚቀነስን የመንግስት ወጪ ልማትን ከመቀነስ ጋር አያይዘው ጫማ ጠበበኝ በሚል እግር አይቆረጥም ሲሉ ኬይኔዥአዊ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የኬይኒዝ የኢኮኖሚክስ ንድፈ ሀሳብ እንደ ሚያወሳው መሀከለኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት የኢኮኖሚ እድገትን በማቀላጠፍ የኢኮኖሚ እድገት አቀጣጣይ መሳሪያ ሊሆን ይችላል ይህ ሊሳካ የሚችለው ግን እንደ ኬይኒዝ የኢኮኖሚክስ ንድፈ ሀሳብ መሰረት መሀከለኛ (moderate) የሆነው የዋጋ ግሽበቱ የመቆጠብ አቅማቸው አናሳ ከሆኑት የሰራተኛው እና የአርሶ አደሩ መደብ ሀብትን ወደ ካፒታሊስቱ በማሸጋገር የመዋእለ ነዋይ ፍሰትን በማስፋፈት እና በማቀላጠፍ ለኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ ሚና መጫወት ሲችል ነው ይህንን ለማሳካት ደግሞ የኢኮኖሚ ስርአቱ በፍላጎት እና በአቅርቦት መርህ መመራት ይኖርበታል ፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ ሙሉ የስራ እድል ወይም ሙሉ ሰራተኛ መኖርን እንደ ቅድመ ሀሳብ (Assuption) እንደመነሻ በመውሰድ የዋጋ ግሽበትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ዝምድና የሚተነትነውን የሞላ የስራ እድል (full employment model) የሚባለውን የኢኮኖሚክስ ሞዴል መነሻ ብናደርግ የስራ እድል ወይም ሰራተኛ ሙሉ በሆነበት የኢኮኖሚ ስርአት የኢኮኖሚ እድገት ከኢኮኖሚ እድገቱ ስፋት አኩአያ ላልተጠበቀ የዋጋ ግሽበት ምክንያት ሊሆን ይችላል ነገር ግን የድህነት ስፋቱ በገዘፈበት ሀገር ከ 10-12 % የኢኮኖሚ እድገት በተመዘገበበት ሁናቴ 35-40 % የዋጋ ግሽበት ተከስቶ ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር ማያያዝ የተጋነነ ሲሆን እንዲያውም በእንደዚህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት መጠን ይህ አይነቱ የዋጋ ግሽበት የኢኮኖሚውን ጤናማ አለመሆን አመላካች ነው፡፡

የዋጋ ግሽበት ምክንያቶች ስንል

በኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ ከልኬቱ ያለፈ የዋጋ ግሽበት ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅ( inflation) በሀገር ላይ ከኢኮኖሚያዊ መመሰቃቀል ባለፈ ለማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መመሰቃቀል ምክንያት ሊሆን ይችላል፣ የገንዘብ ኢኮኖሚስቶች የዋጋ ግሽበትን ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅን (inflation) በዜጎች ላይ የሚፈጸም ስርቆት በማለት ይገልፁታል፡፡ የዋጋ ግሽበት ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅን የሚያስከትሉ መንስኤዎች ፍላጎታዊ ( demand pull) እና ወጪያዊ ግፊቶች (cost push) ሲሆኑ በወጪያዊ ግፊቶች ምክንያት የሚባለው የሰራተኛ ዋጋ መናር፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፣ የግብርና ግብአቶች መወደድ ፣ በምንዛሬ መወደድ የተነሳ ከውጪ የሚገቡ ግብአቶች መወደድ፣ በሀይል ዕጥረት የተነሳ የምርታማነት ግብአቶችን መወደድን ተከትሎ አምራቹ አካል ኪሳራን በመፍራት በሚጨምረው የእቃዎች ዋጋ ምክንያት የሚከሰት የዋጋ ግሽበት ሲሆን ፍላጎታዊ ምክንያት የሚባለው ደግሞ ከገቢ መጨመር ጋር የተያያዘ የፍላጎት መጨመር እንዲሁም የአቅርቦት ማነስ ( ሸማቾች አንድአይነት እቃዎችን በተለይ የፍጆታ እቃዎችን የመግዛት ፍላጎት ከአቅርቦት ማነስ ጋር ተያይዞ የሚፈጥረው የዋጋ ንረት)፣ ከመንግስት የበጀት ጉድለት ጋር ተያይዞ የገንዘብ ኖት አቅርቦት መጨመር ጋር ተያይዞ የሚከሰት የዋጋ ግሽበት ነው፡፡ የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅ( inflation) እስከ 2 % ብቻ ከሆነ በኢኮኖሚው ላይ ይሄነው የሚባል ችግር ሊፈጥር ስለማይችል ጤናማ ለባል ይችላል ከ 2 % በላይ ከሆነ ግን እንደየደረጃው በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲኖረው በተለይ ሀይፐር ( hypher) የሚባለው ደረጃ ከተደረሰ የመገበያያውን ገንዘብ እስከ መለወጥ እንደሚያስደርስ አብዛኛዎቹ የገንዘብ ኢኮኖሚስቶች ይገልፃሉ፡፡

የአንድ ብር የገንዘብ ኖትን ለማተም ወጪው 0.25 ሳንቲም ከሆነ 0.75 (ሰባ አምስት ሳንቲም )ሳንቲሙን ትርፍ የሚያገኘው አንድ ብር አሳታሚው አካል እንደሆነ ለማወቅ የተጋነነ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ መሆን አስፈልግም፣ ይህ አይነቱ ንድፈ ሀሳባዊ ምሳሌ መንግስታት የበጀት ጉድለታቸውን ለመሸፈን ከኢኮኖሚው አቅም በላይ ተጨማሪ የገንዘብ ኖትን ብሄራዊ ባንክን በመጠቀም ማተም እንደ አማራጭ የሚወስዱበትን ምክንያት በትንሹ ለመረዳት ያስችለናል፡፡የሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ እንደሚነግረን ደካማ እና በሙሰኛ አመራሮች የተሞላ የመንግስት ስርአት ወጪውን እና የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን እና ለበጀቱ ምንጭነት መበደርን እና የብድርን ምንጭ ከልኬቱ ባለፈ (ከገቢው በላይ) መልኩ ያለ ቅድመ ሁኔታ መጠቀም ሲሆን በዚህም የተነሳ ከመንግስት ስርአቱ ገለልተኛ በመሆን የኢኮኖሚውን የገንዘብ ፍሰት መቆጣጠር እና ማስተካከል የሚገባውን ብሄራዊ ባንክ በፍፁም ገለልተኛ እንዲሆን አይፈቅዱም፡፡ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋአም በተደጋጋሚ ሁኔታ እንደሚገልፀው በሀገራችን ካለፉት ስምንት እና ዘጠኝ አመታት ወዲህ በኢኮኖሚው ውስጥ የገንዘብ አቅርቦት በተለየ ሁነታ መጨመሩን ሲሆን በባንኮች ያለው የተትረፈረፈ የገንዘብ ክምችት ደግሞ በካሽ ያለውን ብዛት ያለው የገንዘብ ኖት በኢኮኖሚው ውስጥ መኖሩን ማሳያ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እውቁ ኢኮኖሚስት ፍሪድማን አገላለፅ የዋጋ ግሽበት በከፈተኛ መጠን ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተከሰተ የገንዘብ አቅርቦቱም በኢኮኖሚ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ዶ/ር አሳየሀኝ ደስታ Economic Growth for Inflation: The Ethiopian Dilemma በተባለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው ሀገራችን በዋጋ ግሽበት አዙሪት ውስጥ ለመገኘቱአ በዋናነት የሚያነሱት ምክንያት የገንዘብ ኖት አቅርቦቱን መጨመር ሲሆን ለዚህም ማሳያነት እ.ኤ.አ በ 2002 19.4 % የነበረው የገንዘብ አቅርቦት በ 2006 ወደ 23.3 % መጨመሩን ሲሆን ይህ ሁናቴ ደግሞ ከ 2002- 6 በአማካይ የተመዘገበውን 6.8 % የኢኮኖሚ እድገት ጋር (የኢኮኖሚ እድገቱ በራሱ ግሽበታዊ በሆኑ ምክንያቶች የተሞላ መሆኑ እና በክፍለ ኢኮኖሚዎች ትስስር ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ እንዳለ ሆኖ) የገንዘብ ክምችቱን ለማስተካከል የገንዘብ አቅርቦቱን በ 18 % መጨመር ያስፈለገ ሲሆን ይህ ሁናቴ ደግሞ ባለው የዋጋ ግሽበት ላይ በአማካይ ለተጨማሪ የ 12 % የዋጋ ግሽበት ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ሁናቴ ውስጥ የመንግስት የበጀት ጉድለት ኔጋቲቭ መሆኑን በመጥቀስ ምንም እንኩአን የገንዘብ አቅርቦቱ መጨመር ለመዋእለ ነዋይ ፍሰቱ ምክንያት ቢሆንም እንኩአን የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የመንግስትን የበጀት ጉድለት ማእከል ካልተደገ ዋጋ ቢስ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

በሀገራችን የምግብ ፍጆታዎች የሆኑት የግብርና ምርቶች እጥረት ለምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ንረተ በምክንያትነት በሚበቀርብበት ወቅት መንግስት የሚሰጠው ምላሽ የምግብ ፍጆታ የሆኑት ምርቶች ዋጋ ሊንር የቻለው በኢኮኖሚ እድገቱ የተነሳ እና አምራቹ ገበሬ ለምርቱ ትክክለኛ ዋጋ በመፈለጉ እንደሆነ ነው ይህም ማለት የግብርና ስራው ህይወቱን ስለ አሻሻለለት ለእለት ፍጆታው ሲል ብቻ ምርቱን ያለ ዋጋው ስለማይሸጥ እንደ ማለት ነው ነገር ግን የአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ድርጅት (UNICEF) ሆነ የተባበሩት መንግስታት በሀገራችን በየአመቱ ለምግብ እጥረት የሚጋለጡት ሰዎች ህፃናትን ጨምሮ 26 ሚሊዮን እንደሚደርስ በሚገልፁበት ሁናቴ መጋቢያችን የሆነው አርሶ አደር በግብርናው እንቅስቃሴ የተነሳ ህይወቱ መለወጡን እና ሀብታም መሆኑ ሲገለፅ ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡

ያለአግባብ የኬሚካል ግብአቶችን ለ ግብርና በመጠቀም የተነሳ ሀገራችን ከአፍሪካ ከፈተኛ የፀረ ተባይ (pesticides) መድሀኒት ክምችት የሚገኝባት ቀዳሚ ሀገር መሆንዋን ኤድዋርድ የተባሉ አጥኚ Greening Ethiopia for self-sufficiency. በተባለው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ይገልፃሉ፣ በከፍተኛ ደረጃ የኬሚካል ማዳበሪያ መጠቀምን ተከትሎ የገጠሩ አምራች የሆነው የግብርና መሬት ለስነምህዳራዊ ችግር የተጋለጠ ሲሆን የችግር መጠኑም ከ መሬት ምርታማነት መውደቅ እስከ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያትነት የሚደርስ ሲሆን ይህም በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ሲሆን ይህም የሚያሳየን የግብርና ምርቶች ዋጋ መናር መንስኤን ውስን የሆነ የግብርና ምርታማነት ቴክኖሎጂ በገጠሩ አካባቢ በመኖሩ የተነሳ የሚለው የሚገልፀው ይመስለኛል ፡፡

ከዋጋ ግሽበት ጀርባ

ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ቀጣይነት ባለው መልኩ በሚከሰትበት ሁናቴ በኢኮኖሚው ስርአት ውስጥ የሚተገበር የወለድ ተመን ፖሊሲ የዋጋ ግሽበትን መጠን ማእከል በማድረግ የኢኮኖሚ ስርአቱን ሚዛናዊነት በጠበቀ መልኩ እና የዋጋ ግሽበቱን ከመቀነስ አኩአያ በተመቻመቸ መልኩ ተግባራዊ ካልሆነ በባንኮች ና በፋይናንስ ተቋአማት ውስጥ የሚሰጠውን የቁጠባ ና የብድር አገልግሎት በተበዳሪ ሰራቂነት እና በቆጣቢ (በአበዳሪ) ተሰራቂነት መሀል የወደቀ አገልግሎት ያደርገዋል በመሆኑም ትልቁ ጉዳይ ከዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው የቆጣቢ በ ተበዳሪ መሰረቅ ነው፡፡ የቅርቡን የብሎንበርግ 29.6 % በአማካይ የሚለውን የሀገራችንን ያለፉትን አምስት አመታት የዋጋ ግሽበት መነሻ ብናደርግ ከወለድ ተመኑ (አማካይ ከ 8-10%) ጋር ባነፃፀረ መልኩ የዋጋ ግሽበቱን ያማከለው የወለድ ተመን ኔጋቲቭ 20 % መሆኑን እንረዳለን ይህ ማለት ደግሞ አንድ ተበዳሪ ( ከባንክ ተበዳሪ የሆነ ግለሰብ) ከአበዳሪ (ብሩን በባንክ ውስጥ ቆጣቢ ከሆነ ግለሰብ) 100 ብር ቢበደር አበዳሪው ተጨማሪ 20 ብር ገንዘቡን እንዲጠቀም ለተበዳሪው መክፈል እንደማለት ነው ይህን ወደ ጠቅላላው የኢኮኖሚ ስርአት ስንመልሰው በዋጋ ግሽበት አማካኝነት ባንክ ውስጥ ቆጣቢ ከሆነው ግለሰብ ወደ ባንክ ተበዳሪው ግለሰብ የሚሸጋገርን ሀብት መነሻ በማድረግ በዋጋ ግሽበት አማካኝነት በጠቅላላው ኢኮኖሚ ውስጥ የሚፈጠርን የሀብት ሽግግር ለመገንዘብ አዳጋች አይሆንም በተጨማሪም በዋጋ ግሽበት ወቅት በቢሮክራሳዊ እና በጥቅመኝነት የተነሳ የተወሰኑ አካላትን እና ድርጅቶችን ብቻ ያማከለ ከፍተኛ መጠን ባለው የብር መጠን ደረጃ የብድር አገልግሎት መኖሩ ሰራቂን ማዘጋጀት እንዳለ ለመገንዘብ አዳጋች አይደለም፣ የትኛው ኢኮኖሚስት ነበር ለሰላምታ እንኩአን ለፖለቲከኞች እጆቼን ከዘረጋውላቸው እና ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁአላ ጣቶቼን እቆጥራቸዋለው ምክንያቱም ሊሰረቁ ይችላሉና በማለት የተናገረው፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>