Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የኢሳት የውይይት መድረክ ከየት ወዴት!!?

$
0
0

ethsat ይህ ርዕስ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በቀጣይነት ብዙ ልንወያይባቸው የሚገቡ ሃሳቦችን ይጠቁማል፤ እኛም ለወደፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ የምንል መሆኑን ከወዲሁ ማሳወቃችን አስፈላጊ ነው። ስለሆነም ለመንደርደሪያነት ይጠቅም ዘንድ ለዛሬ ሃሳባችንን ባጭሩ እንደሚከተለው ጠቆም አርገን ማለፍ ግድ በመሆኑ አነሆ እንላለን።

[የኢሳት-የውይይት-መድረክ-ከየት-ወዴት.pdf"]


እዬገደለ የመጣ ቅጥረኛና ፋሽስት ኃይል የሚኖረውም እየገደለ ነው። (እምብኝ በል-ጎፍንን )

$
0
0

እምብኝ በል-ጎፍንን                             

 እዬገደለ  የመጣ ቅጥረኛና ፋሽስት ኃይል የሚኖረውም እየገደለ ነው።

Yekofelewየሰው ልጅ ህይወት እጅግ በጣም ውድ ነው በድሮው ጊዜ የሰው ልጅ ሕይወት ይቅርና ሰው የሚመገባቸው እንሥሣትም ሊታረዱ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቡናው ሲፈላ እጣኑ ሲጨስ ጮፌው ሲነሰነስና ሊታረዱ ሲቀርቡ አራጁ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን  በአዕምሮው ላይ ሥነ-ልቦናዊ መረበሽ እንደሚፈጥርበት ይታመናል። የለየለት ደም አፍሳሽ ከሆነ ግን ይህ ላይከሰት ይችላል። ታራጆቹ እንሥሣትም በአራጃቸው ወይም በገዳያቸው እጅ ሲገቡና ሲታሰሩ ጭንቀትና መረበሽ ሊኖር እንደሚችል እገመታለሁ። ሕይወት አንዴ ካለፈች አትመለስምና ከባድ ጫና ያሳድራል ነገሮች ሁሉ ይጨልማሉ ይህ ግን የሚሆነው ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡ ላደረበትና አርቆ ለሚያስብ ብቻ ነው። ለአረመኔዎቹና አምባ-ገነኖች ይህ በፍጹም አይገባቸውም።

በሰው ልጅ ላይ የሚፈፀሙ የግድያ ሁኔታዎችን ስንመለከት ዘርፈ ብዙ ሆነው እናገኛቸዋለን።-በሕግ ዓምላክ በሚባልበትና የሕግ የበላይነት ባለበት አገር በሰው ልጅ ላይ ሞት የሚፈረደው ተከሳሹ ወንጀል መፈጸሙ ታምኖበት በፖሊስ ተይዞ በአቃቢ ሕግ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ቀርቦ የፈጸመው ወንጀል በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ የፍርድ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ወንጀሉ በሞት የሚያስቀጣ ከሆነ ዳኛው ወይም ዳኞች የሞት ፍርድ እንዲበየንበት ያደረገውን የወንጀል አፈጻጸም ድርጊትና ምክንያት በዝርዝር ከሕጉ ጋር እያገናዘቡ ካስረዱና ብዙ ተመልካችን እንዳያስደነገጥ ጥንቃቄ በማድረግ ወይም ዝግ በሆነ ችሎት በወንጀለኛው ላይ የሞት ፍርድ ይፈጸምበታል። ይህ እርምጃ የሚወሰደው የአካባቢውን ሕዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ፤ሰላም እንዲሰፍንና የተረጋጋ ለማድረግ ዳግም የዚያ አይነት ወንጀል እንዳይፈጸምና ሕብረተሰቡ በሥነ-ምግባር የታነጸና በሕግ የሚገዛ እንዲሆን ለማድረግ ፤ የወንጀል መፈጸም ተግባርን እንዳይስፋፋ ጤናማ ሕብረተሰብ ለመገንባት የሚወሰድ የመንግሥት እርምጃ ነው። የፖሊስ ፤ አቃቢ-ሕግና የዳኛ ተግባሮች በፍጹም የማይለያዩ ተያያዥነት ያላቸው ሲሆን የአንድን ማሕበረሰብ ደህንነት ፤ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ለማድረግ ደረጃ በደረጃ በየተቋማቸው ማድረግ የሚገባቸውን ፈጽመው መገኘትና አንዱ ሌላውን እያገዘ በጋራ የሚሰሩት የተቀናጀ የሥራ ውጤት ግቡን ይመታል።

ግለሰቦች ከሕግ በላይ በሆኑበትና በሕግ ዓምላክ በማይባልባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሚኖረው ግድያን ወስደን ስንመለከት ደግሞ ሁኔታዎች ቦታቸውን ለቀው በግልባጩ እናገኛቸዋለን። ከዚህ በታች ስማቸውን የጠቀስኳቸው አገር መሪዎች በዓለም ላይ እንዲታወቁ ያደረጋቸው ተግባር ምን እንደሆነ አንባቢዎቼ በግልጽ የሚረዱት እንደሚሆን አምናለሁ። «ዘለው ኦፍ ጃንግል» (the law of jangle )«የጫካ ሕግ» በሚል የተፃፈች ትንሽ መጽሐፍ አንድ ወቅት ላይ አንብቤ ነበር። ያች ትንሽ መጽሐፍ ያዘለችው መልዕክት ሕግ ለምን እንደሚወጣና ጠቀሜታው ምን ያህል እንደሆነ ያሳደረብኝ ግንዛቤ እስከ መቼውም አይረሳኝም።መጽሐፏ በጫካ ስለሚኖሩ የዱር አራዊት(እንሥሣት) ህግ አለመኖርና ጉልበታሙ ወይም ጉልበታሞች ተባብረው ጉልበት የሌለውን አስገድደው ገድለው ተመግበው እንደሚያድሩና እንደሚውሉ እንደሚኖሩ ግልጽ አድርጋ ታሳያለች። በሩዋንዳ ፤ካሞቦዲያ እንዲሁም እስከ አሁን ድረስ ትኩሳቱ ባልበረደው ሶሪያ የምንሰማውና የምንመለከተው በዘረዘርኳቸው አገሮች የተካሄደውና እየተከሂያደ ያለውን ስንመረምር በምን አይነት መርህ እየተጓዙ እንደሆነና ጨካኞችና አምባገነኖች የሚፈጽሙትና የፈጸሙት ተግባር  ከጫካው ሕግ ያልተለየና አረመኔያዊ ተግባር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።

አገርንና ዳር ድንበርን ለማስከበር ይሞታል፤ በሀሰት በፍርደ ገምድል ዳኛ ተፈርዶም ይሞታል፤ ሲሰርቁና ሰው ሊገድሉ ሲሞከርም ይሞታል ፤ በትንታም ይሞታል ፤ሌባ በረት ሲከፍት ፤ ከባለትዳር ሴት ሲልከሰከሱም ይሞታል፤ የሰው ቤት ሲበረብሩም ይሞታል፤ በሕመምና እድሜ ሲደርስም ይሞታል የሰው ልጅ ሕይወት ማለፊያዋ መንገድ ብዙ ነው። የእኔ መነሻ ግን ይህ አይደለም ሥልጣን ለመያዝና ከያዙ በኋላም ጨካኝና ነብሰ ገዳይ ሆነው ለመቀጠል የሚያስቡ አርመኔዎችን አስመልክቶ ትንሽ ለመግለጽ ያህል ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የዘውዳዊ አገዛዝ ዘመን የ1966ቱ የየካቲት የሕዝብ አልገዛም ባይነት ለማንበርከክ የተወሰዱትን እርማጃዎች ፤ቀደም ሲል በአርሲ ፤በጎጃምና በትግራይ የአርሶ አደሮችን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማፈን የተደረግውን እርማጃ ፤በደርግ የወታደራዊ አገዛዝ ዘመን ለመገንጠል በተነሱ ጎጠኞች(ጠባብ ብሔረተኞች) የተወሰደው ፤አዲስ ሥር ዓት እንገነባለን ብለው በሕብረ- ብሔር ድርጅት ተቃውሞ ያነሱትን ትግል ለመበተን የተደረገውን ጥቃት ፤ህወሃት ከኤርትራ ጋር በጫረው ጦርነት የያለቁት የሁለት ወገን ትውልዶችና፤ «ራስ ሳይጠና ጉተና እንዲሉ» ወደ ሶማሊያ ሄደው ያለቁት ኢትዮጵያውያን ፤ ወደ ሩዋንዳ ፤ኮንጎ፤ ኮርያ የሄዱት ኢትዮጵያውያን ፤ ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ በስውር የፈጀው ታጋይ የትግራይ ወጣት ፤ በቀን በአደባባይ መሠረት በሌለው ቂመኝነት የተገድሉት ኢትዮጵያውያን አሁንም በሰበብ አስባቡ እተጨፈጨፉ የሚገኙት ዜጎቻችን ሕይወት ቀጠሮ ተይዞለት በአዲስ ዓመት ይመለሳል የሚባል እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን ። በደርግ ጊዜ ደርግ ሕዝቡን ፈጀው እያሉ ነፍጥ አንስተው የተንቀሳቀሱት የዛሬዎቹ ገዥዎቻችን ለምን ሕዝባችን ይጨፈጭፋሉ?ወይስ ከጌታ ትእዛዝ ወርዶ ተፈቅዶላቸው ነው?ደርግ በሕዝብና በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ባለሥልጣናት ላይ ኢ-ፍትሃዊ እርማጃ ወሰደ ያ አስፈሪ ሞት በራሱ ላይ መጣ። ህወሃት ከዚያ አስፈሪ ሞት የሚያመልጥበት ምን ብልሃት አገኘና ነው እንዲህ በእብሪት ተወጥሮ ሕዝብን በጅምላ የመጨፍጨፍ ተግባሩን እንደ ሰደድ እሳት እያቀጣጠለ ያለው? ግራኝ መሐመድ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነበር በውጭ ድጋፍና እርዳታ  በክርስቲያን ሕዝባችን ላይ ጨካኝ ጭፍጭፋ እንዳደረገ ታሪክ ዘግቦት አልፏል ። ቶርኮች ፤ ግብጾች እንዲሁም በዓረቦች ድጋፍ በሱዳን መሐዲስቶች(ድርቡሽ) እየተባለ የሚታወቀው በተመሳሳይና በተደጋጋሚ በክርስትና እምነት(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ሃይማኖት) ላይ ዘምተው አልተሳካላቸውም።ኢትዮጵያዊ  የእስልምና እምነት ተከታዮችን እስላማዊ መንግሥት ሊያመጡብህ ነው ብሎ ሕዝብን ማስፈራራትና የማከፋፈል ዘመቻ ማካሄድ የት ሊያደርስ ነው? ለመሆኑ ህወሃት ምንስ እምነት ኖረውና ነው እስላማዊ መንግሥት  ክርስቲያናዊ  መንግሥት እያለ ሊሰብከን የከጀለው ? ይህ ከንቱ ውዳሴ ነው። ስለዚህ ሕዝቡ ጀሮውን ሊሰጥ አይገባውም ባይ ነኝ። መጀመሪያ የዜጎችን መብት ማክበር ይቅደም።የቻይና ባለሀብቶች ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ተወልደው በአደጉበት እትብታቸው በተቀበረበት በአጥቢያቸው በአገራቸው ምን እየሆኑ  እንደሆነ የሚያውቀው ህወሃት ዜጎቼ ተደፈሩ ብሎ ለምንስ እርምጃ አልወሰደም ? ከዚህ በላይ መርከስና መውረድ የበለጠ ምን ሊመጣ ይችላል?  አቶ በረከት እናቱ ሲቀበሩ መድፍ እንዲተኮስላቸው አስደርጓል እናቱ ቢሞቱ እህት እንኳ የለውም የሚያዝን ልብ? እግዚአብሔር ያሳያችሁ!! እውን እኒህ ጠይም ደማማ እናት እንዲህ ተፈንክተው ደማቸውን እያዘሩ እንዲሄዱ ማድረግ ይገባል ? ምን አይነት ሥልጣኔስ ሊባል ነው? አሁን እኒህ እናት ጠቅላይ ሚንስቴር ለመሆን መንግሥትን ለመፈንቀል እያሸበሩ ነው? እንዲህ የተቀጠቀጡት? ኢትዮጵያ አገራቸው አይደለችም ? ወይስ ኢትዮጵያዊ መሆን የግድ ካልተቀጠቀጡና ደማቸውን እያዘሩ ካላሳዩ (ካልታዩ) ኢትዮጵያዊ ዜግነት አይገባቸውም ?ኢትዮጵያ እኮ የሁላችን አገር ናት። እንዴት ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያዊ እናቱን ደም እያዘሩ እንዲሄዱ ያደረጋል? ምን አይነት ሰው በላ ሥርዓት ነው የተፈጠረብን? ለመሆኑ ይህ በህወሃት ዘመን ተወልዶ በህወሃት የታጠቀ የአጋዚ ነብሰ በላ ጠመንጃ አንጋች ኃይል  እናት እህት ሚስት ይኖረው ይሆን ? ሴቶችን እንደ ፊውዳሉ ሥርዓት ማናናቄ አይደለም እኒህ እናታችን ሴትና በእድሜ ጠና ያሉ ናቸው በምን ሂሳብ ነው የተደበደቡት በምን ምክንያት ነው ደማቸው እንዲፈስ የተፈረደባቸው? ይህ የህወሃት አጋዚ ሠራዊት አደብ የሚገዛውና ለሕግ የሚገዛው መቼ ነው ?እኛ ኢትዮጵያውያንስ መቼ ነው እንደበግ እየተጎተትን ከመታረድ የምንድነው? ድምፃችን ይሰማ በማለት ሁለት ዓመት አንዲት ጠጠር ሳይወረውሩ፤አንዲት ቅጠል ሳይበጥሱ የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው ጥያቄ ስለአቀረቡ ችግሩ ምኑ ላይ ነው? መልሱን መስጠት ወይስ እያፈሱ ማጎርና መደብደብ በጥይት መቁላት? ኧረ እናስተውል ጎበዝ እስከ መቼ ነው ቀን እንዲህ ሊገፋ የሚችለው ?አሸባሪውስ ማን ሆነና ነው? አሸባሪ የሚሉት ለእምነታቸው ነፃነት የሚታገሉትን ነው ወይስ ከነዚህ ለእምነት ነጻነት ከሚታገሉት ኢትዮጵያዊ እስላሞች ውስጥ ሰርጎ የገባ አለ በሚል ነው ? ሰርጎ የገባ ካለ ለይቶ ማውጣትና በሕግ እንዲቀጣ ማድረግ የማን ተግባር እንደሆነ ከጠፋቸው እውነትም ጠፍተዋል ማለት ነው ቢጠፉም ይሻላቸዋል።

እየገደለ የመጣ ፋሽስታዊ ኃይል የሚኖረውም እየገደለ ነው።  ያልኩበት አብይ ምክንያት ህወሃት በወርሃ የካቲት 1967 ዓመተምህረት እንደ ድርጅት ከመቆሙ በፊት የተለያዩ መጠሪያዎችን ይዞ ይንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን በመጨረሻ ህወሃት በሚለው ስም ጸንቶ ሲቀጥል ከቀን አንድ ቀን ጀምሮ በሰው ግድያ የተጀመረ የራሱን አባላት ሳይቀር እየበላ ያደገ ድርጅት ሲሆን 17 ዓመት ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት 22ዓመት መላ አገሪቱን ከወረረ በኋላ ጊዜውን ያሳለፈው ሰው በመግደል ነው። ሰው መግደልና በደም መጠማት ደግሞ በሕክምና ሊድን የማይችል በሽታ መድኃኒቱ በመሰል እርምጃ(አክሽን )ሊወገድ የሚችል ከቫይረስ የከፋ በሽታ ነው። ህወሃቶች የፈለገው ብዛት ያለው ሰው ይሙት አንድ ሰው ይሙት ቅንጣት ታህል አይሰማቸውም የሚሰማቸው የሰው በላው ሥርዓት አስከባሪ ወይም እንደ አበደ ውሻ የሚክለፈለፈው አንጋች ሲሞት ብቻ ነው። ሰው የገደለ እኮ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ራሱን ለመሸሸግ መታገል አለበት።እንዴት ሰው ገድሎ ታማኝነቱን ማስመስከር እንደ ዝና ተቆጥሮ ይሳለቁብናል? ቤተመንግሥታችንስ እንዴት የነብሰ ገዳዮች መናኻሪያ ይሆናል?እየገደሉን መጥተው እንዴት እየገደሉን እንዲኖሩ እድሉን እንሰጣቸዋለን? ስማቸው ተቆጥሮ የማያልቅ ወንዝ የማያሻግሩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወይም ከአውሮፓና  አሜሪካ ሄዶ ኢትዮጵያውያንን ከህወሃት የአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ሊያወጣ የሚችል እንደሌለ እንቅጩን እንነጋገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወጣት ኢትዮጵያውያን የሚመራው ሰማያዊ ፓርቲና አሁን ከእንቅልፉ የባነነው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን እንደ አንድ ግኝት እንደ አንድ ርምጃ እንውሰድና ትግሉን አጋግሎ መቀጠል ያለበት ሲሆን ከዚያ ባሻገር ያለው ግን መድሕሃኒቱ ያለው ከየሁላችን እጅ ነው ። እምብኝ አልገዛም ማለት ፤ ፍርሃትን ማስወገድ ፤ ራስን ነፃ ለማውጣት መታገል ፤መደራጀት ፤ አንድነት መፍጠር የህወሃትን ሰርጎ ገቦችና ሰላዮችን ማዋከብና ማጋለጥ ፤የሚሠሩት ጸረ-ሕዝብ ተግባር ህወሃት በአማራ እናትና እህቶቻችን ላይ የሚያመክንና የአማራውን ሕዝብ ቁጥር ዝቅ እያደረጉ ከሁሉም አካባቢ እያፈናቀሉ እየገደሉ ዘሩን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ድርጊት በቀጣይነት ማጋለጥ በርን ከፍቶ አለማስገባት…ወዘተ እንጅ እንደ ብሉይ ኪዳን ቀኙን ሲመታህ ግራውንም ስጠው ወይም በየተራ እንደ ዓመት በዓል በግ እየተጎተቱ መታረድና በየከርሸሌው እየገቡ በፈላና በቀዝቃዛ ውሃ መቀቀል በሌባ ጎማ ተዘቅዝቆ መገረፍ፤ በኤሌክትሪክ ሽቦ መጠበስ ፤በሴትና በወንድ ብልት ወስጥ አሰቃቂ ተግባር በመፈጸም የገደሉትን ሰው ዘቅዝቆ ማንጠልጠልን በመኪና መጎተት በደርግ ጊዜ ከነበረው በሚበልጥ ሁኔታ መዋረድ እንዴት እንዲቀጥል እድሉን እንሰጣቸዋለን? እኛም ቤት እሳት አለ መባል አለበት። ነፍጥ ወይም ጠመንጃ አንግቶ የሚንቀሳቀስ ኃይል ካለም የህወሃትን የመከላከያ ሠራዊት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማዋከብና ቢያንስ ወደ ሕዝብ ያዞረውን መሣሪያ እንዲያነሳ ማድረግ፤ በህወሃት ፖሊስ ፤ ደህንነትና የመከላከያ ሠራዊት፤በካድሬው ላይ የመበተን ወይም በውስጡ ያለው ቅራኔ እንዲባባስ የፕሮፓጋንዳ ሥራ አዘውትሮ መሰራት አለበት ወደዚህ ለመግባት የሚያስችሉ ብዙ ክፍተቶች አሉ በፖሊስና በመከላከያ በደህንነት ውስጥ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር የተያዘው ከአንድ ጎሳ በመጡ ስለሆነ ሌላውን ለማነሳሳት ለም ሆኖ ያለ ነጥብ ነው። በግንባሩ በውስጡ የተፈጠረውን የእኔ እቀደም እኔ ሽኩቻም እንዲባባስ መገፋፋት ይገባል በተጨባጭ ያየነው የግንባሩ አባላት ባኮረፉ ቁጥር እንዳያፈነግጡ ተሰርቶ የማያውቅና ራሱ ባወጣው ሕግ ላይ እንኳን ያልሰፈረ 3 ጠቅላይ ሚንስቴር ወዘተ…የፖለቲካ ሥልጣን ከችሎታና ከአቅም ብቃት የተመዘነ ሳይሆን ላለመቀያየም የሚደረገው ጥረት ውስጡ ምን ያህል የነኮረና የበሰበሰ እንደሆነ ስለሚያሳይ ይህን መጠቀም ያሻል። በግብር የሚሰበሰበው ገንዘብ ገቢ እንዳይሆን ማድረግ ፤ ከውጭ የሚገኘውን እርዳታ እንዳይሰጥ ማድረግ  በማንኛውም አይነት መንገድ የሚገኘው ገቢ ለአገር እድገትና ልማት ሳይሆን የሚውለው የህዳጣኖችን ከርስ መሙያና ፍላጎት ማስተናገጃ እንጅ ለሕዝብ ብሶትና ችግር ስለማይውል ይህን በጡንቻው የሚያምን ኃይል ለማሽመድመድ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንዲወርድ ማድረግ ማዳከም ገበሬው ፤ነጋዴው ፤ ሌላው ግብር ከፋይ አልከፍልም እንዲል ማድረግ ያስፈልጋል። ተተኪ ትውልድ እንዳይኖር የተስማሙ ጭፍኖችን በማሳከም በሕብረት ለአንዲት ኢትዮጵያና ለአንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም አይነት ዘርፎች መስዕዋትነት መክፈል ይገባናል። ኢትዮጵያ ተተኪ ትውልድ እንዳይኖራት የማድረጉ ዓላማ የማን እንደሆነ አስፈፃሚው ማን እንደሆነ እንተዋወቃለን። ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆንን የጠሉና ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ላለመጋፈጥ ታሪክን ሸምጥጠው የካዱ ሁሉ ፈጥነው ችግራቸውን ቢያስተካክሉ ይበጃቸዋል። አዎ ኢትዮጵያ አሁን ከራስዋ በበቀሉ የአገር ውስጥ ጣሊያኖችና ከውጭ እንግሊዝና ጣሊያን አጥልተውብን በሄዱት የመከፋፈልና የእርስ በርስ አለመተማመን ምክንያት ችግር ገጥሟታል ።ነገር ግን በቅርቡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ትሆናለች። ያኔ ታዲያ እነዚህ የእናት ጡት ነካሾችና የበሉበትን መሶብ የደፉ የአገር ውስጥ ጣሊያኖች ጀንበር ትጠልቅባቸዋለች፤አንገታቸውን እንዲደፉ የግድ ይሆንባቸዋል።ለሆዱ ያደረው የሚበዛ ቢሆንም እውነቱ የት ላይ እንዳለ መርምረው ያወቁ ወይም የሚያውቁ በዚህ ሥርዓት ውስጥ ስለሚገኙ ምርቱን ከገለባው የመለየት እንቅስቃሴም ሊሰራ ይገባል።የራስን ደጋፊ ኃይል በየተቋሙ መፍጠር ካልተቻለ መሣሪያ አምላኪ የሆነው ቡድን የውስጡን ቅራኔ ጋብ በማድረግ ነገሮችን በመለጠጥ የተለከፈበትን ወረርሽኝ ወደ ሌላው እያላከከ እድሜ ለመግዛት ስለሚችል የዚህ ዓይነቱን እድል አለመስጠትና በሩን መዝጋት አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን በጣም ጠቃሚ ነው። ሥርዓቱ መበስበሱን ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልግም የአማራው ነገደ ብሔር ዘሩ እንዳይራባና ቁጥሩ እንዲቀንስ የተደረገው ፀረ-ሕዝብ ተግባር ቀላል አይደለም ነገር ግን ምሥጢሩን ደብቆ ለመያዝ አለመቻል ዋና ምልክት ነው። አሁንም ይህን ትኩረት ሰጥቶ ቢቀሰቀስበትና ለዓለም ሕብረተሰብ እንዲደርስ ቢደረግ አንዳንድ ጤናማ የሆኑ አገሮች ድጋፋቸውንና ግንኙነታቸውን ስለሚያቋርጡ ሥርዓቱ ብጥስጥሱ የሚወጣበት ጊዜ እየፈጠነ እንዲሄድ ያደርጋል። የታሰሩ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ድርጅት አባላት እነአንዱ ዓለም አራጌ (የሕሊና እስረኞች) የታሰሩበትን መርምሮና ግልጽ አድርጎ ማቅረብ አንዱ የማጋለጥ ሥራ ተሰራ ማለት ነው። ክቡር አምባሳደር እምሩ ዘለቀ እንደጻፉት ሳይቦዝኑና ሳይሰላቹ በተቻለው መንገድ ሁሉ ሥርዓቱን ማዋከብ ያስፈልጋል።

(Adolf Hitler German-Rodolfo Graziani Italy– Joseph Stalin Soviet Union -Omar Hassan al-basher Sudan–Mengistu Haile Mariam- and Meles Zenawi in Ethiopia)

                ራዶልፍ ሂትለር በጀርመን አገር የሚኖሩ ይሁዳዎችን ጨረሰ ፤ አዶልፎ ግራዚያኒ አውሮፓን አቋርጦ ባሕር ተሻግሮ በአፍሪካ ምድር የቅኝ ተገዥ አገሮችን ለማስፋፋትና ሀብታቸውን ለመዝረፍ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ ሕዝባችን ጨረሰ ፤ጆሴፍ ስታሊን የብላድ ሚር ኢሊችን ሥልጣን ከተረከበ በኋላ እንደ ሬድ ተረርና የስታሊን ዱላ በሚል የራሱን ሕዝብ ጨፈጨፈ ፤ የሱዳኑ ኦማር ሀሰን አልበሽር ከዐረብ ጋር ያልተዳቀሉትን የደቡብ ሱዳንን ሕዝብ ፈጀ ፤ ዝሃና ግራውን መለየት የተሳነው መንግሥቱ ኃይለማሪያም በቀይ ሽብር ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር እያለ ተኪ የማይገኝለትን ወጣት ምሁር ሠራተኛ ፤ አርሶ አደር ፤ የከተማ ነዋሪ ፤ ነጋዴ  አዛውንት ጨረሰ የኤርትራን ተቃዋሚዎች በኃይል ለማንበርከክ ሞክሮ የመገንጠል እድል እንዲታደሉ አደረገ ። ሌላው የአገር ጉድና አረም የምዕራባውያንና የዐረቦች አሽከር አያት ቅድመ አያቶቹ የጣሊያን አባሽ አጎንባሽ ሹምባሽና ለባሽ የነበሩት ልጅ  በነ-ስብሃት ነጋና አባይ ፀሐየ አጆሃ! እየተባለ የሻእቢያን የመገንጠል ዓላማ ነዳጅ ሆኖ አገለገለ ኢትዮጵያን ወደብ የሌላት አገር አደረገ ፤ አብዛኛውን ከውጭ አገር የሚያዋስነውን የአገሪቱን ለም መሬት ለባዕዳን በረከት ሰጠ ፤ ሊበርድ የማይችል የጎሳና የሃይማኖት ግጭትና ጦስ አቀጣጥሎ በአበበ ገላው (አንድ ጋዜጠኛ ወቀሳ) ምክንያት በ30 ሰከንድ ውስጥ በድንጋጤ ርዶ ያለቀኑ የተቆረጠ ቅጠል መስሎ እኛን ረመጥ ውስጥ ከቶ ከማይጠየቅበት ዓለም ተጓዘ ያ ሚፈራውን ሞት ሞተ። መለስ ዜናዊና ድርጅቱ ህወሃት ነፍጥ ያነሱት የትግራይ ሕዝብ በሁሉም አይነት መንገድ ተበደለ ብለው እንደሆነ አድርገን የምንረዳ ልንኖር እንችላለን። የዛሬውን አላውቅም እንጅ ህወሃት የትግራይ ወላጆችን ጨርሷል።የተረፉትን ጧሪ አልባ አስቀርቷል፤ተኪ የማይገኝለት ወጣት ትውልድ በልቶ ያደገ ድርጅት ነው።በርግጥ በሥርዓቱ ዙሪያ ያሉት ሚሊየነር ሆነዋልከሚገባው ብላይ ከበርዋል ። የትግራይ ሕዝብ ግን በሳውዝ አፍሪካ እንግሊዞች ካራመዱት የአፓርታይድ አገዛዝ ሊመሳሰል የሚችል ሲኦል ውስጥ ገብቶ ነው የሚገኘው።በቅርቡ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የሚሊዮኖችን ድምጽ ለማሰባሰብ በጀመረው ዘመቻ መቀሌ ላይ በክልሉ ገዥዎች የተደረገውን ሰምተናል።ትግራይ ውስጥ ወይን ከሚለው የህወሃት ጋዜጣና ከህወሃት ራዲዮ አልፎ ዜና ማድመጥና ማንበብ ወይም በሌላ አነጋገር ሌሎችን ጋዜጦችና መጽሔቶች አይገቡም የመገናኛ ብዙሃንን መስማት የሚያስቀጣ እንደሆነ ይታወቃል።የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ይህን እሥራት ሰብሮ መውጣትና መብቱን ማስከበር ይገባዋል።

በመጨረሻም በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት አስተዳደር ክፍል አዘጋጅነት በ18/08/2013 ዋሽንግተን አርሊንግተን የሚካሄደው የታዋቂ ግለሰቦች ፤ የፖለቲካ አክቲቪስቶች ፤ የሃይማኖት መሪዎችና የተቃዋሚ ድርጅቶች ፤ የስቪክ ማህበራትና ሌላውንም ያካተተው ስብሰባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ የምሥራች ይዞ ብቅ እንደሚል ተስፋ አደርጋለሁ። ለሁሉም ግን የማሳስበው ቢኖር ሰጥቶ መቀበል ፤ መናበብ ፤ መደማመጥ ፤ መከባበርና ፍቅርን መተሳሰብን የሚያጎናጽፍ እንዲሆን መልካም አርአያ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!

ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

$
0
0

“እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” ኦባንግ
በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


peace roconእሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ።

“አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም” የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ። በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው መንግሥትም ችግሩን ከመፍታትና አገሪቱን ከስጋት ከማላቀቅ “ጥሪ አይቀበልም” በሚል የሃይል ርምጃ መምረጡ ነገሮችን ይበልጥ እንዳወሳሰበ ይናገራሉ።

በየአቅጣጫው ያሉ ወገኖች ቆም ብለው ሊደበቁት ከማይችሉት ከህሊናቸው ጋር ሊነጋገሩ እንደሚገባ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ግብጾች ግብጾችን ገደሉ፣ ገና ቀውሱ ይቀጥላል። ይህ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ቀውስ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ወደ እርቅ እናምራ። ለእውነተኛ እርቅ ጊዜው አሁን ነው” በማለት አንገብጋቢ ያሉትን ጥሪ ያስተላልፋሉ።

“ላለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያ ላይ ከየአቅጣጫው የተረጨው መርዛማ ፖለቲካና፣ ሰብአዊነት የጎደለው አስተዳደራዊ መዋቅር የፈጠረው ውጥረት ወደ መፈረካከስ እየነዳን ነው” በማለት የስጋቱን መጠን የሚጠቁሙት አቶ ኦባንግ ፣ በግብጽ የተፈጠረው ቀውስ በሃይል ሊቆም የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ምዕራባዊያንም ሆኑ አሜሪካ የሃዘን መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ስራ አለመስራታቸው ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ትምህርት ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል።

በሩዋንዳ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሰዎች አልቀዋል። በኮሶቮ ህዝብ ተጨፍጭፏል። ዳርፉር ንጹሃን የጥይት ራት ሆነዋል። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሃያላን መንግስታትና “ድርጅቶቻቸው” በእነዚህ አገራት ውስጥ ነበሩ። እያወቁት ነው የሆነው። ግን ጉዳዩ የጥቅም ችግር ስለማይፈጥርባቸው አገራቱ በደም ጎርፍ ሲታጠቡ በዝምታ ተመልክተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦባንግ፣ “ሶሪያ ስትፈርስ፣ ከ100 ሺህ ሰው በላይ ሲያልቅና አሁንም እያለቀ ባለበት ሁኔታ እልቂቱን ማስቆም እየቻሉ ዝምታን መርጠዋል” በማለት አቶ ኦባንግ ከነዚህ አገሮች፣ በተለይም “አሁን ግብጽ ላይ በተፈጠረው ችግር ካልደነገጥንና ለሚቀርበው የእርቅ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የማንዘጋጅ ከሆነ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ጥያቄው የስልጣን ሳይሆን አገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሞት አደጋ የመግፈፍ አንደሆነ፣ ይህ አሁን ያንዣበበው የቀውስ ደመና ባስቸኳይ ካልተገፈፈ መከራው የሁሉም ወገን እንደሚሆን ጥርጥር እንደማያሻው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ “ንጹህ ልብናና ንጹህ ህሊና ያላችሁ ውጡ፣ ለእውነተኛ እርቅ እንስራ፣ አገሪቱንም እናድን፣ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና እኛው አገራችንን በማስቀደም እንታደጋት” ሲሉ ከወትሮው በተለየ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው በዓመጽ መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው ፕሬዚዳንት ሙርሲን የሚደግፉ የሙስሊም egyptወንድማማች ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ የሃይል ርምጃ ከመወሰዱ በፊት በግብጽ ይህ ችግር ሊደርስ እንደሚችል የወተወቱ ነበሩ። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከስልጣን የተወገዱበት አግባብ ቀውስ ሊያስነሳ እንደሚችል ቢነገርም ሰሚ ባለማግኘቱ ቀውሱ ግብጻዊያንን እርስ በርስ አጋደለ። ግብጾች ግብጾችን ጨፈጨፉ። እስከ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ቀውስ እንዴት ሊቆም እንደሚችል ፍንጭ የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የሰዓት እላፊ፣ ግድያና እስር ዓመጹን ሊገታው አልቻለም። ይልቁኑም መሳሪያ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ግብጽን በጥይት እያመሷት ነው። እየገደሉም ነው።

በኢትዮጵያም በተለያዩ ወቅት የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በጸረ ሽብር ህግ፣ በእስር፣ በድብደባ፣ በግድያ፣ በማስፈራሪያና በጡንቻ የማስተናገዱ አዝማሚያ ከእለት እለት መጠናከሩ የሚከፋቸውን ሰዎችና ቡድኖች እያበራከተ ነው። የተፈናቀሉ ወገኖች ተበራክተዋል። በተፈናቀሉና መሬታቸው እየተቸበቸበ ያሉ ወገኖች ምሬት የከፋ ደረጃ ደርሷል። ሚዛናዊ ያልሆነው የአስተዳደር መዋቅርና የኢኮኖሚ ልዩነት የፈጠረው ቅሬታ በቃላት የሚገለጽ አልሆነም። እንደ አቶ ኦባንግ ሁሉ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ በማመን እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩትና ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ታዋቂ ምሁር ለጎልጉል እንደተናገሩት “በአሁኑ ወቅት ጥላቻው ከርሮ ህዝብ በገሃድ ስምና ብሔር እየለየ ፊት ለፊት መናገር ጀምሯል፤ የኑሮው ውድነት፣ የመብት ረገጣው፣ ዕንግልቱ፣ … የጥላቻውን መጠን አደባባይ ላይ እንዲታይ እያደረገው መጥቷል። አገራችን ያለችበት መንገድ አደጋ አለው። እርቅ የግድ ነው” ብለዋል፡፡

እኚህ ምሁር “ኢህአዴግ ውስጥ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑና አሁን በየአቅጣጫው ያለው ችግር የሚያሳስባቸው ወገኖች ስላሉ እነዚህን ወገኖች በመቅረብ ለእውነተኛ እርቅ ለመስራት ጊዜው አሁን፣ ለዚያውም ሳይረፍድ በቶሎ ሊሆን ይገባል። ይህንን ካላደረግን ሁላችንም እናዝናለን። ይቆጨናል። በቀላሉ ልናልፈው ወደ ማንችልው ጣጣ ውስጥ ሳንገባ እንረባረብ” በማለት ተናግረዋል። አስተያየት ሰጪው በቅርቡ ራሳቸውን ገልጸው አስተያየት እንደሚሰጡ፣ ለጊዜው የተጀመሩ ስራዎችን በነጻነት ለመስራት ሲሉ ራሳቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡበትን ምክንያት ተናግረዋል።

“አገር እንደ ሰው አካል ነው። አንድ ቦታ ሲታመም ስሜቱ የሙሉው አካሉ እንጂ የተጎዳው አንድ ክፍል ብቻ አይደለም” በማለት የማጠቃለያ አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሲቋቋም ዓላማው ሁሉም ነጻ የማውጣት ታላቅ ዓላማ አንግቦ በመሆኑ በዚህ ረገድ በቅርቡ የእርቅ ተግባሩን ሊከውን የሚያስችለውን እቅዱንና የድርጊት መርሃ ግብሩን ይፋ እንደሚያደርግ፣ ለዚሁም ተግባራዊነት ኮንፍራንስ እንደሚያዘጋጅ አመልክተዋል።

በነጻ አውጪ ስም መደራጀትና መታገል ሙሉውን አካል /አገር/ ሊያድን እንደማይችል ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ከንባታ፣ ሲዳማ፣ ከፊቾ … እያልን በተበጣጠሰ አመለካከት ከማነከስ የአገራችንን ህልውና በአንድ ትልቅ አጀንዳ ውስጥ በማካተት ለመስራት ድርጅታችን ለሚያቀርበው ጥሪ ህዝብና ጥሪ የሚደረግላቸው ወገኖች ሁሉ ቀና ምላሽ ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሙስሊም፣ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ ወዘተ በማለት ከብሄርና ጎሳው ልዩነት በተጨማሪ መለያየት መፈጠሩ የአገሪቱን እጣ ፈንታ አሳዛኝና አደጋ እንኳ ቢፈጠር ለተግሳጽ የሚፈራ ሰው እንዳይኖር ማድረጉ አሳሳቢ የሆነባቸው በርካታ ዜጎች አሉ። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት ግን ሁሉም ቦታ የፖለቲካ ኮተት የሌለባቸው፣ ንጹህ ልብና ያላቸውና ህሊናቸውን የሚያከብሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች ብቸኛ አማራጭ በሆነው እርቅ ላይ አበክረው መስራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል። እሳቸው የሚመሩት አኢጋንም ለእንደዚህ አይነቶቹ ንጹሃን በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም “አሁን ችግር በተባባሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ‘እርቅ’ እንደ መፍትሄ የሚቀርበው፣ ዓለም አሁን ከመቻቻል ሌላ አማራጭ ስለሌላት ስለሆነ እኛም እርቅ ላይ ያለአንዳች ማቅማማት መስራት ይገባናል፤ ይህ ዕርቅ ግን በደፈናው ምህረት የሚያሰጥ ሳይሆን በፍትህ ላይ የተመሠረተ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “ድርጅታችን እርቅ ላይ ያለው ሃሳብ ከሌሎች በተለየ የተቋቋምንበት፣ የሰፋና የተፈጠርንበት መሰረት በመሆኑ ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ እስካሁን የሰራናቸውን ስራዎች ውጤት ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፤ ይህም እንደወቅቱ ሁኔታ ተለዋዋጭ ሳይሆን የጋራ ንቅናቄው ገና ከጅምሩ የወጠነውና እስካሁን ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ጉዳይ ነው። ኢህአዴግም ሰላም ስለሚያስፈልገው፣ ባለስልጣኖቹም መኖር ስለሚፈልጉ፣ ደጋፊዎቹም ዋስትና ስለሚያሻቸው የተቃዋሚ ወገኖችም አገራቸውን ስለሚያስቀድሙ፣ ሁሉም ወገኖች ቀና ምላሽ ይሰጣሉ ብለን እናምናለን” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።


ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

“አቶ እያሱ አለማየሁና አቶ ፍሰሐ በለጠ ኢሕአፓን አይወክሉም”–ከኢሕአፓ የእርምት እንቅስቃሴ

$
0
0

በዚህ ሐገራችን በምትገኝበት እጅግ አሳሳቢና ውስብስብ የታሪክ አጋጣሚ የኢሕአፓ አባላት ጥንካሬና ብቃት ወሳኝ ሆኖ ሳለ፣ አሁን ድርጅታችን በሁለቱ የአመራር አባላት እና ታማኞቻቸው ታፍኖ እየነጎደ ያለበት መስመር እጅግ የተሳሳተ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል። ከእለት እለት ራሳቸውን በእውቀት በማዳበር ፈንታ ግዜያቸውን በአልባሌ አሉባልታ የሚያሳልፉ፣ ስድብን እንደትግል የሚቆጥሩ፣ በጸያፍ ስነ ምግባር ትግሉን የሚያውኩ ግለሰቦችን እያሰባሰበ፣ ነባር እና በጸረ ወያኔው ትግል በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን አባላት የሚበትን ድርጅት እራሱን ለትግል ሳይሆን ለውድቀት ያዘጋጀ መሆኑም ግልጽ ነው።

ሙሉውን ጽሑፍ በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአቶ መለስ የሙት ዓመት ልዩ ዝግጅት (ESAT efeta 21 August 2013)

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ –ከዶ /ር ብርሃኑ ነጋ

$
0
0

Dr. Birhanu Nega

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

1. መግቢያ:

ካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግል፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሊሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንድን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት? የሚለውን ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሀይማኖቱ ተከታዮች አልፎ ያጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የሀገሩ) ትልቅ የመወያያ አርዕስት እየሆነ ነው:: ይህ ጉዳይ ግን ጥቅል ከሆነ ያመለካከትና የንድፈ ሀሳብ ጥያቄ በተጨማሪ ጥልቅና አስቸኳይ የሆነ የተግባር ፖለቲካ ጥያቄም ነው ይዞ የመጣው::

ሙሉውን ጽሑፍ በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

 

የሰማያዊ ፓርቲ ያላቻ ጋብቻ (ከይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0

semayawi party
የሰማያዊ ፓርቲ ያላቻ ጋብቻ
መንግስት ተግባሩን ሣይወጣ ቀርቶ መንደርተኛና ቧልተኛ ሲሆን እንዴት ያሳፍራል ! ይህን ለመፃፍ ያነሣሣኝ አዲስ ዘመን ጋዜጣ “ የሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ተግባራት ” በሚል በገፅ 3 አጀንዳ ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪን በተጨማሪ ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እና በሬዲዮ ፋና በዜና እና በልዩ ዘገባ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች፤በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱ ጥቃቅን አነስተኛ ስብሰባዎችና ሰልፎች የሚሰሙ መፈክሮች የመንግስትን ፍርሃቱን እና ውንጀላ በሚገባ የሚያሳዩ በመሆናቸው ነው፡፡
መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄ አቅራቢዎች የሚያስርበት እና የሚያሰቃይበት አዋጅ ማውጣት ይቀለዋል፤ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም መነሻውን 4 ኪሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረሻውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ተደርጓል፡፡ በዕለቱም ለመንግስት የቀረበለት ጥያቄ የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲስተካከሉ፣የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣በዓይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲቆም በዚህም ምክንያት የታሰሩት እንዲፈቱ፣የኑሮ ውድነቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚል ጥያቄዎች ናቸው፤እጅግ በሰለጠነ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄው ለመንግስት የቀረበ ሲሆን መንግስትም ለዚህ ምላሽ የሦስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡
ይሁን እንጂ መንግስት ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስም ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሎበታል፤መንግስት ስም ለማጥፋት ብሎ ያነሳቸው አንኳር ሀሳቦች መሰረታዊ የሰው ልጅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስት ይህን ለመረዳት ተጨማሪ 22 ዓመታት ቢያስፈልገውም ህዝብ ግን ያጣውን ነፃነት ለማግኘት ትግሉን ይቀጥላል፤ ለህዝብ የመብት ጥያቄ የሆኑት መንግስት ለመወንጀል የሚያነሳቸው ሃሳቦች በጥቂቱ እንመልከት፡፡
1ኛ. “በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዛሬ ደግሞ በአዲስ ኮፍያ የሚንቀሳቀሱ” የተባለው ቁጥር አንድ ውንጀላ ነው፤ ምላሹ ደግሞ ፡- ይህ ሀሳብ ከእውነት የራቀ አይደለም ከዛሬ 8 ዓመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ይቅሩና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ለነፃነት እና ለመብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተደረገበት ወቅት ነው፤ በወቅቱ ለሚፈለገው ነፃነት ደም ተከፍሎበታል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባዶ እጁን አደባባይ ወጥቶ “ድምፃችን ይከበር” በማለቱ አገርን ሊወር እንደመጣ ጠላት በመከላከያ ሠራዊት ለዛውም በሰለጠኑ ነፍሰ ገዳይ ታሪክ ሁሌም የሚዘክራቸው ኢትዮጵያውያን በግፍ ገሏል፤ በዚህም ምክንያትና በሌሎች የሚፈለገው ነፃነት ታጥቷል፡፡ እናም ያኔ ያጣነውን ነፃነትና መብት መንግስት በአዲስ ኮፍያ ቢለውም እጅግ በሠለጠነና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በአዲስ እስትራቴጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈቀደው መልክ ተደራጅቶ ይህን አምባገነን ስርዓት ታግሎ ለማሸነፍ የሚያደርገው ጥረት ወንጀል የሚሆነው ምኑ ላይ ነው?
2ኛ. “በውጭ ከሚገኙ ፅንፈኛ አክራሪ ኃይል ጋር በመቀናጀት በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት” ይህ ሁለተኛው ውንጀላ ነው፤ ሌባ አባት ልጁን አያምንም የሚባለው ተረት ለዚህ ውንጀላ ተስማሚ ይመስለኛል ምክንያቱም ያሁን መንግስት የበፊት አማፅያን (ወያኔዎች) ከሱዳን፣ ከሶሪያና ከግብጽ ከመሳሰሉት አገራት የጦር መሣሪያና ስልጠና እንዲሁም መሸሸጊያ በማግኘት አዲስ አበባ ቤተ መንግስት መግባታቸውን የሚታወቅ ነው፤ እነሱ በክደት የፈጸሙት ሁሉ ሌላው ያደርገዋል የሚል ከንቱ አሳብ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የተመሠረተው በኢትዮጵያውያን ነው ትግሉም ሆነ ዉጤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ሌላው ደግሞ በአረቡ አለም የታየው አብዮት ኢትዮጵያውያን ከ8 ዓመት በፊት በአስደናቂ ሁኔታ የተገበርነው ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ከ8 ዓመት በፊት ያጣነው አብዮት መንግስት አልሰማና አልለወጥ ካለ የአረቡን አብዮት በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታና ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በመስቀል አደባባይ ወጥተን ብናደርገው ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?
3ኛ. “ከውጭ አሸባሪ ግንቦት ሰባት ቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ኢሳት’ ጋር በመቀናጀት” ይሄ ደግሞ ሦስተኛ ውንጀላ ነው በመሠረቱ በአገር ቤት ያለው የዳኝነቱ ስርዓት እውነተኛ ፍትህ የሚሠጥ ቢሆን ኖሮ “መልካም ስምና ዝናን በማጉደፍ በተጨማሪም መረጃን የማግኘት መብት በመንፈግ” የወንጀል ክስ መመስረት ይቻል ነበር ግን ምን ዋጋ አለው?፡፡ ይህን ለማለት የፈለኩት አንደኛ ኢሳት መረጃን ለተጠሙ በዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን አይንና አንደበት የሆነ ሚዲያ እንጂ የግለሰብ ወይም በተወሰኑ ቡድኖች የሚንቀሳቀስ ሚዲያ አይደለም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሚዲያው የእገሌ ድርጅት ነው መባሉ የስም ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ መረጃን ማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ነው፤ ይሁን እንጂ በአገራችን እኛ የመረጥነው ሳይሆን መንግስት የመረጠልን ሚዲያ ነው የምንመለከተው፣ የምንሰማውና የምናነበው ለዚህም ማሳያ በአገር ውስጥ ትክክለኛ መረጃ የሚያስተላልፉ ጋዜጠኞች መጨረሻቸው ስደት ወይም እስራት ነው፤ ከሀገር ውጭ ያሉ ሚዲያዎች ደግሞ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ይታፈናሉ በዚህ ምክንያት መረጃ የማግኘት መብታችን በኃይል ተከልክለናል፡፡
4ኛ. “የጥቂት ሙስሊም አክራሪዎች አጀንዳ በመደገፍ አደባባይ ይዞ መውጣት” አራተኛ ውንጀላ መሆኑ ነው፤ ጥቂት፣ አነስተኛ፣ ጥቃቅን የመንግስት አፍ መፍቻ ከሆኑ ሰነባብተዋል፤
“ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረከክነው
ዛሬን እንሞታለን ነገ ታሪክ ምስክር ነው”
የሚለው የእናንተ የትግል መዝሙር አስታወሰኝ እባካችሁ ትላንትና ለጥቂቶች የነበራችሁ ከፍተኛ ግምት ዛሬ የት ገደል ገባ? የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል የጥቂቶች አይደለም የአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ለአገር የቆመ ፓርቲ ለመብትና ለነፃነት በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ እያለ መብትና ነፃነታቸውን ለማስመለስ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ “ድምፃችን ይሰማ” ለሚሉ እውነት ነው ድምፃቸው ይሰማ ብሎ ሰማያዊ ፓርቲ ድምፁን ቢያሰማ የሚያስወነጅለው ምክንያቱ ምንድን ነው?
5ኛ. “ሰማያዊ ፓርቲ ሠልፍ ላይ መካከለኛ እድሜ ላይ ያሉና አዛውንቶች ጭራሹንም በሰልፉ ላይ የሉም በአብዛኛው ለአክራሪዎች ወግኖ የቆመ ኃይል ነው” ይሄ በአምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ከውንጀላ ይልቅ በኢህአዴግ ቋንቋ የሠልፉን ገፅታ ጥላሸት ለመቀባት ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ሁሉንም የህብረተሠብ ክፍል ያካተተ እንደነበር የአለም ሚዲያ የዘገበው ነው፤በጣም የሚገርመው በ1997 ዓ.ም አደባባይ የወጣውን ወጣት “ አደገኛ ቦዘኔ ” በማለት ሠልፈኛውን እና የሠልፉን ዓላማ የተለየ ለማድረግ መንግስት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ አሁን ደግሞ ከ8 ዓ.ም በኋላ በተካሔደው የተቃውሞ ሰልፍ ወጣቱ ብቻ ነው የተገኘው በማለት ለወጣቱ ያለውን ንቀት መንግስት በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ እኔ የምለው! ወጣቱ ስለሀገሩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ አያገባውም እንዴ? በተጨማሪም ተገፋን፣ ተበደልን ከሚሉ ሰዎች ጋር ወግኖ መቆም ጥፋቱ ምን ላይ ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ታስቦና ታቅዶ የሚፈፀም በደልና መገፋት በኔ አልደረሰም ተብሎ እንዴት ይታለፋል፤ ዛሬ ከተገፉትና ከተበደሉ ወገኖች ጋር ወግኖ ያልቆመ ነገ ለሱ ማን ሊቆምለት ነው?
በአጠቃላይ ከላይ የተገለፁት ሀሳቦች በመንግስትና ካድሬዎች እና ሚዲያዎች የሚነዙ አሉባልታ ወሬዎች መሆናቸውን ለማሳያት ለመንደርደሪያነት የቀረበ ፅሁፍ ነው፡፡ መንግስት ከሰሞኑ የተያያዘው ነገር ቢኖር ከስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍ ባለ ሁኔታ የሃይል እርምጃ መውሰድ ነው፤ለዚህም ማሳያ በተለያዩ ከተሞች በእስልምና እምነት ተከተዮች ላይ ግድያ እና ድብደባ እንደሁም እስራት እየተካሄደ ነው፤ ቀጣዩ ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መሆናቸው የዘፈን ደርዳርታ እስክስታ ነው እንደሚባለው ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጀምሮ እስከታችኛው የስልጣን እርከን የተቃዋሚ ፓርቲ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲን መንግስት የነገር አባት ( ሽማግሌ) በመሆን በቅርብ ከማያገኛቸው ነገር ግን እንዲህ አይነቱን ውንጀላ ለመፈረጅ ከሚመቻቸው ከግንቦት ሰባት እና ከሙስሊም አክራሪዎች ጋር ፓርቲውን እየዳሩት ይገኛል ፤ጋባቻው ግን ያላቻ ጋባቻ ነው፡፡
በመሆኑም መንግስት በተሠጠው ጊዜ አላፊነቱን በመወጣት እኛ ተበዳዮቹ ብቻ ሳንሆን እናተም በዳዮቹን በጋር በነፃነትና በእኩልነት የምንኖርበት አገር በማቅናት ሁሉ በህግ ፊት እኩል ሆኖ የሚዳኝበትን ጊዜ እናቅርበው፤ አለበለዚያ የምትፈሩት ህዝባዊ አብዮት መምጫው ቀን እሩቅ አይደለም፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊ

 

ዋ! እዮብ መኮንን! –‹‹እግዚአብሔርን ባገኘው የምጠይቀው የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠኝ ነው››

$
0
0

eypbበአቤል ዓለማየሁ

ጊዜው ከአምስት ዓመት በፊት ነው፤ በሚሊኒየሙ፣ ሚያዚያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፡፡ ሠራበት በነበረው ጐግል ጋዜጣ ‹‹ጥበብ›› አምድ ላይ እንግዳ ላደርገው ረፋድ ላይ ወደ እዮብ መኮንን የእጅ ስልክ መታሁ፡፡ መልካም ፈቃዱን ገለጾ… አንጃ ግራንጃ ሳያበዛ ‹‹ከተመቸህ ዛሬ መገናኘት እንችላለን›› አለኝ፡፡ ትንሽ መዘጋጀት እንዳለብኝ ነግሬው ዛሬ ከሆነ ምሽት ላይ መገናኘት እንደምንችል ነገርኩት፡፡ ጥያቄዎች ሳሰባስብ እና ሳሰላስል ዋልኩ፡፡ የቀጠሮ ቦታ ስላልቆረጥን ከመገናኘታችን በፊት ልደውልለት ተስማማን፡፡ ደወልኩለት!

‹‹ፒያሳ አካባቢ ነኝ፡፡ እዚህ መምጣት ትችላለህ?›› (እዮብ)
‹‹መልካም ግን ትንሽ እንዳልቆይብህ መገናኛ አካባቢ ነኝ፡፡ መሀል ላይ መገናኘት ከቻልን መልካም ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ልምጣ››
‹‹እሺ! የት እንገናኝ? መኪና ይዘሀል?››
‹‹መኪና? ይሄ አራት ጎማ ያለው ነገር?››
‹‹ይስቃል››
‹‹አለኝ ግን butter fly ነው፡፡ (የልብስ ስፌት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) ከቤት ውጪ አልነዳውም››
እየሳቀ ‹‹እሺ! የት ልምጣልህ››
‹‹ዑራዔል አካባቢ አማካይ ስፍራ ነው፡፡ ፕላዛ ሆቴል እንገናኝ?›› እውነት ለመናገር እኔ የነበርኩት ፕላዛ አካባቢ ይገኝ የነበረው ቢሯችን ውስጥ ነበር፡፡ የጀመርኩትን ሥራ ሳጠናቅቅ፣ ኮምፒውተር ስዘጋጋ፣ እንዳልቆይበት ብዬ ግርጌዬ ላይ እንዲመጣ ጨከንኩበት፡፡ የሚገርመው እኔ ቢሮ ስድበሰበስ እሱ ቀድሞ ፕላዛ ደረሰ፡፡ ሮጥ ብዬ ስደርስ ሆቴሉ ግቢ ውስጥ ጥቁር ቪታራ መኪናውን እየዘጋጋ ነበር፡፡ ሆቴሉ ምግብ አዳራሽ ውስጥ ገበታ ሳይቆርሱ መስተናገድ ባይፈቀድም ቃለ ምልልስ ለመስራት ሳስፈቅድ ይሁንታ አገኘሁ፡፡ የሆቴሉ ባልደረቦች ድሬድ ጸጉሩን የተሸለተውን እዮብን እያዩ ‹‹እሱ ነው/አይደለም›› እየተባባሉ ነበር፡፡
አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮምኛና ሱማሊኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ እንደሚናገር የነገረኝ እዮብ ቃለ ምልልሱን ከመጀመሬ በፊት ማስጠንቀቂያ አስቀመጠ፡፡
‹‹በድምጽ መቀዳት ስለማልፈልግ፣ ወረቀት እና እስክሪብቶ አውጣ››
‹‹ለምን››
‹‹ከዚህ በፊት ያላልኩትን ብለው መጽሔት ላይ ስላወጡ ይሄን ስህተት መድገም አልፈልግም፡፡ ስለዚህ እየጠየቅከኝ መልሱን ጻፍ!››
‹‹እኔ እንዲህ እንደማላደርግ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ቃል ልገባልህ እችላለሁ››
‹‹ኖ! አይሆንም››
ላሳምነው ሞከርኩ፡፡ ሊዋጥለት አልቻለም፡፡ በዚያው ሰሞን አንድ መጽሔት ያልዘፈነውን ራጋ ‹‹የራጋ ስልት ያለው እንትን የተሰኘ ዘፈኑ›› እያለ አልበሙን ጥንብ ርኩሱን አውጥት ስለነበር ፕሬሱ ላይ ያለው እምነት የበለጠ እንዲሸረሸር አድርጎታል፡፡ የመጨረሻ አማራጭ ልሰጠው ጉሮሮዬን ጠረግኩ፡፡
‹‹እውነት ለመናገር መልስህን በቃል እየጻፍኩ አልዘልቀውም፡፡ በዚህ ላይ እኔ እስክፅፍ ስትጠብቅ ሃሳብህ ይቆራረጣል፡፡ ለዛ ቢስ ቃለ ምልልስ ይሆናል፡፡ ማድረግ ያለብኝ [ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም] እስከዛሬም ለማንም አድርገነውም ባናውቅም ድምጽህን ወደ ወረቀት ከገለበጥኩ በኋላ (After transcription) አምጥቼ ላሳይህ እችላለሁ፡፡ አለበለዚያ ግን በቃል…››
አመነታ፡፡ እንደምንም አሳመንኩትና ‹‹ሽጉጤን›› ተረክ አደረግኳት [ለእንደ እኔ አይነት ጋዜጠኛ ተብዬ ሽጉጡ ድምጽ ማስቀሪያው ነች፡፡] አወራን፡፡ በቀጣዩ ቀን ምሽት ላይ ይሰራበት የነበረው ፋራናይት ክለብ (ልምምድ ላይ የነበረ ይመስለኛል) ወስጄ አሳየሁት፡፡ አነበበውና ምንም ሳያንገራግር በደስታ ሸኘኝ፡፡ ከዚያም የሚያዚያ 10/2000 ዓ.ም ጐግል ጋዜጣ ላይ ጨዋታውን ዳርኩት፡፡ ካወራናቸው ውስጥ ጥቂቱን እንካችሁ፡፡

የተለያዩ አይነት የሬጌ ስልቶች አሉ፡፡ አንተ የምትጫወተው የትኛውን አይነት ነው ትክክለኛ (Pure የሆነውን) ሬጌ ትጫወተዋለህ
ሬጌ የተለያየ አይነት ስታይል አለው፡፡ ሩትስ፣ ስካ፣ ዋን ድሮፕና ሌሎችም አሉ፡፡ የምቱ ሁኔታ ነው ሩት፣ ስካ… ሊያስብለው የሚችለው፡፡ እኔ ሁሉንም የሬጌ ቶን እጫወታለሁ፡፡ ስለ እኔ መናገር ቢከብደኝም ሙዚቃ የሚያውቁ ሰዎች በአብዛኛው በትክክል እንደምጫወተው ይናገራሉ፡፡

‹‹ይዞ የመጣው ለአገራችን አዲስ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያሰልፈው የሚችል አዘፋፈን ነው፡፡ ሬጌ የሚፈልገው ነገር አለው፡፡›› ተብሎ ስለ አንተ የተጻፈ ጽሁፍ አንብቤያለሁ፡፡ በዚህ ትስማማለህ?
ጸሐፊው ያመነበትን ጽፏል፡፡ እኔ ከምናገር አድማጭ ቢፈርድ ጥሩ ነው፡፡

በሙዚቃ ስራህ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረብህ ሰው አለ?
አሊ ቢራ እና ቦብ ማርሌይ በጣም የምወዳቸው ድምጻዊያን ናቸው፡፡ የእነሱ ተፅዕኖ አለብኝ፡፡ የሁለቱንም ዘፋኞች ዘፈን ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማም፣ እዘፍንም ነበር፡፡

ሬጌ ሙዚቃ መጫወት ያለበት ሰው ምን ማሟላት አለበት?
መጀመሪያ ሙዚቃውን ማፍቀር አለበት፡፡ ከዚያም በደንብ መስማትና ደጋግሞ ልምምድ መሥራት ይኖርበታል፡፡

በአልበምህ ላይ የሰራሀቸው ዜማዎች ተመሳሳይነት አላቸው ይባላል፡፡
በፍጹም አይመሳሰሉም፡፡ ለአንድ የውጪ አገር ዜጋ የትግሪኛ ዜማ ብታሰማው ሁሉም አንድ ዓይነት ነው የሚመስለው፡፡ የእኔም እንደዚያው ነው፡፡ አሰማማችን ነው እንጂ ዜማዎቹ አይመሳሰሉም፡፡

አልበምህ ያሰብከውን ያህል ተደምጧል?

ገና ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ ሰውም በበቂ ሁኔታ የሰማው አይመስለኝም፡፡ የተወሰነ ሰው ግን ሰምቶታል፡፡

ለምሳሌ የሚካያ በኃይሉ አልበም ከወጣ ጀምሮ (1999 ዓ.ም.) የወደዱት ቢሆንም ይበልጥ የተሰማው እየቆየ ሲሄድ ነው፡፡ ያንተም አልበም እንደዚያ…
እመኛለሁ ግን እንደዚያ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ አምላክ ነው የሚያውቀው፡፡

‹‹እዮብ በአብዛኛው የሚጫወተው የሬጌ ዘፈኖችን ስለሆነ ጸጉሩ መለያው ነበር፡፡ ሲቆረጠው ዘውዱን የተገፈፈ ንጉስ መስሏል ያሉኝ አሉ፡፡

ለእነሱ የሚታያቸው እንዳልከው ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን በመቆረጤ ደስተኛ ነኝ፡፡

መቼና ከማን ጋር ስትሆን ደስ ይልሀል?

ለብቻዬ፣ ከጓደኞቼ ጋር ስሆንና መጽሐፍ ቅዱስ ሳነብ ደስ ይለኛል፡፡ ሁሌም አዲስ ስለሆነ ባነበብኩት ቁጥር ይገርመኛል፡፡ ያነበብከውን መተግበር ስትጀምር ይበልጥ አዲስ ይሆንብሀል፡፡ ሌላ መጽሐፍ ማንበብ ትቼያለሁ፡፡

eyob mekonen 2ትልቁ ራዕይህ ምንድን ነው?
አላውቀውም፡፡ ዛሬን ብቻ መኖሬን ነው የማውቀው፡፡ በፕሮግራም ነገ እንዲህ አደርጋለሁ አልልም፡፡ አስተማሪና መካሪ ዘፋኝ ብሆን ደስ ይለኛል፡፡ ስለ ነገ የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፡፡

አሁን የምትኖረው ሕይወት እና ያለህበት ደረጃ የምትፈልገውን ዓይነት ነው?

ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ትልቅ ነገር ነው፡፡ ደስተኛ ነኝ፡፡ ሕይወት ደግሞ የምትጣፍጠው አማራጭ ስታጣ ነው፡፡ በሕይወቴ ከዚህ በላይ ብሆንም ካለሁበትም ዝቅ ብልም ምንም አይመስለኝም፡፡ አማራጩ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

በቆይታችንየእግዚአብሄርንስምደጋግመህአንስተሀል፡፡ብታገኘውበቀዳሚነትየምታነሳለትጥያቄምንድንነው?
የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠኝ ነዋ!

በደረሰበት ደንገተኛ ህመም ቅዱስ ገብርዔል ሆስፒታል ሲታከም የነበረው ከዚያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ናይሮቢ አቅንቶ ሳይነቃ በሳምንቱ መጨረሻ ሕይወቱ ያለፈው ተወዳጁ ድምጻዊ እዮብ መኮንን ጋ ያኔ በተገናኘንበት ወቅት አልበሙ እንዲህ ይገናል ብሎ አላሰበም፡፡ ‹‹ታያለህ እንደ ሚካያ አልበም ነው የሚሆነው›› ብዬ ‹‹ስጠነቁል›› አልመሰለውም ነበር፡፡ ሥራው ከገነነ በኋላ ‹‹አላልኩህም ነበር!›› ብዬ ከመፎከር አልቦዘንኩም፡፡ አንድ ቀን አጋጣሚ ቦሌ አካባቢ አግኝቼው አንድ ካፌ ትንሽ ተቀምጠን አወራን፡፡ አወራን ከማለት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሰብከኝ ነበር ማለት ይቀላል፡፡ ልቡ ተሰብሮ፣ ግንኙነቱ ከአምላኩ ጋር ብቻ ይመስል ነበር፡፡ ዛሬ በ9 ሰዓት በሥላሴ በተፈጸመው የቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ ጥቅምት 12/1967 ዓ.ም. መወለዱ የተነገረው እዮብን ሁኔም በማይሰለቹ ዜማዎቹ እናስታውሰዋለን፡፡ በርካታ ሰውም በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ሀዘኑን ገልጿል፡፡ እንደተመኘውም በላይኛው ቤት ‹‹የዘላለም ሕይወት እንዲሰጠው›› እመኛለሁ፡፡ ዋ! እዮብ! ከልቤ አዝኛለሁ! ነፍሱን ይማረው!


መለስና ደሃ ዘመዶቹ

$
0
0

ክፍሉ ግርማ

ሰሞኑን የቀድሞውን የዲክታትር መለስ ዜናዊ የሞተበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት በየድረገጹ የተለያዩ የተቃውሞም የድጋፍም ጽሁፎች እየወጡ ነው ከሁሉ ግን አውራምባ ታይምስ በተሰኘው ድረገጽ ላይ አንድ ስለ መለስ ወንድምና እህት የሚገልጽ ፊልም አየሁ ነገሩ ሁሉ በጣም ገረመኝ ብዙ አስተያየቶችንም አነበብኩ ለእኔ ግን የማይውጥ ነው!! በጣም ስለድሃ ይሚያስብ ታላቅ መሪ…. ዘመዶችን እንኳን ለሃገሩ ሲል የረሳ መሪ…..ወ.ዘ.ተ እነዚህን የመሳሰሉ ውደሳዎችን የሚወዱት ኮሚኒስቶች ብቻ ናቸው

አንድ ሃይማኖት ያለው ወይም በትክክል የሚያስብ ሰው እንዴት ዘመዶችን ይረሳል በክርስትናም ሆነ በሙስሊሙ እምነት እናትና አባትን ከዚያም ወንድምና እህትን ማክበር መረዳዳትም እንዳለብን ያስተምራል.. አሁን እስቲ ይታያችሁ የመለስ እህት ጠላ መሸጥ ማለት መለስ ታላቅ መሪ ማለት ነው ? እዚህ አሜሪካን ሃገር በቀን 16 ሰዓት ከባድ ስራ እየሰሩ ወይም በአረብ አገር እህቶቻችን 24 ሰዓት በሰው ሰራተኛነት እይተቃጠሉ ወንድምና እህቶቻቸውን የሚስተምሩ ከቻሉም በብዙ ሺ የሚቆጠር ብር እየከፈሉ ከሃገር ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርጉት ቤተሰባቸውን ለመቀየር አይደለምን? በሃገራችንም አንዱ ከቤተሰብ የተሻለ ቦታ ካለ ሌላውን መርዳትም የተለመደ ባህላችን ነው ወደ ቁም ነገሩ ለመለስና በእኔ እምነት መለስ እነዚህን ደሃ ወንድምና እህቱን አይውዳቸውም ወይም ያፍርባቸዋል ያልተማሩና ደሃ ስለሆኑም ይሆናል ወይም ሌላ ሚስጢር አለ እንጂ ለነዚህ ሚስኪን ሰዎች መለስ ትንሽ ቦታ አጥቶ አይደለም ለመሆኑ እነዚህ ወንድምና እህት ቤተመንግስት ለቅሶ ለመቀመጥ ተፈቅዶላቸው ይሆን በቀብር ስነ ስረአቱ ላይስ….ወ/ሮ አዜብስ ኤፈርት ካሰራቸው ብዙ ፋብሪካዎች በአንዱ ተቀጥረው ትንሽ ከጠላ ሻጪነት ብትገላግላቸው ጥሩ ነበር ኤፈርት የትግራይ ህዝብ ሀብት አይደለም እንዴ? ለመለስ እህት ያልሆነ ለማን ሊሆን ነው?

ከክፉ ውንድም ይጠብቅዎ

ፍልሙን ለማይት

አምስተኛው ባርነት –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ቤቶችበጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ።
ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየው አምስተኛው የባርነት መንገድ 40 በ60 ከሚባለው የቤት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ የባርነት መንገድ ለመጓዝ የወሰነው ደግሞ ዲያስፖራው ( በውጭ የሚኖረው) ኢትዮጵያዊ ነው። መንግስት ለዲያስፖራው 40/በ60ን ሲያዘጋጅ ሁለት አላማዎችን ታሳቢ አድርጎ ነው- ዲያስፖራው ጥሮ ግሮ ያገኘውን ሀብት ሰብስቦ ደቋናውን ለመሙላት እና ዲያስፖራው ስለነጻነቱ እንዳይጠይቅ ወይም መንግስትን እንዳይቃወም አፍ ለማዘጋት።

40 /በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ እናት እና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ፣ በአጠቃላይ የአገሩ ሰዎች ቢገደሉ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢሰደዱ፣ ቢራቡ ፣ ቢጠሙ፣ ” ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የመጠየቅ እና የመቃወም ነጻነት አይኖረውም፤ ነጻነቱን በ40/በ60 ተገፎአል። ለሌላው መብት ሊሟገት ቀርቶ፣ በጥፊ ቢመታም እንኳን፣ “ጥፊው እንዴት ይጣፍጣል፣ እባክህ ግራ ጉንጨንም ድገምልኝ” ከማለት ውጭ፣ “ለምን ትመታኛለህ?’ ብሎ የአባትና እናቱን ወኔ ቀስቅሶ ብድሩን የመመለሻ ልብ አይኖረውም። እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ እና ሌሎችም፣ ከስጋቸው ድሎት ነጻነታቸውን ያስቀደሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ባርነት በቃን በማለታቸው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት ተነጥቀዋል።
40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ ስለወገኑ ለመጮህ ከእንግዲህ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እጅግም አይታይም፣ ለይሉንታ ቢታይ እንኳ ፊቱን በወረቀት ሸፍኖ ከሁዋላ ከመሰለፍ የዘለለ ሚና አይኖረውም። በነጻነት አገር እየኖሩ ገንዘብ ከፍሎ፣ በፍላጎት ባርነትን መምርጥ ማለት ይህ አይደለምን? የሚገዛ የለም እንጅ እነዚህ ሰዎች እኮ መንግስት ቢሸጣቸው እንኳ ምንም የሚናገሩ አይደሉም። ገንዘብ ተከፍሎ ባሪያ አድርጉን ብሎ የሚጠየቅበት አሰራር በታሪክ ታይቶ ይታወቃልን?

በአገር ቤት ያለው ህዝብ ለ 20/በ80 ቢመዘገብ አይገርመኝም፤ በባርነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ አንድ ቀን ራሱን ነጻ እስኪያወጣ፣ ለጊዜው ተመችቶት ይኑር። ባሪያም እኮ ልብሱን ይቀይራል፣ የምኝታውን ሳር ተባይ ሲወርበት በሌላ ሳር ይተካዋል፤ ባበርነት ስር ያለው የአገር ቤት ሰው በነፍሱም በስጋውም ሊበደል አይገባውም፤ ቢያንስ እስከ ጊዜው በስጋው ይደሰት። ዲያስፖራው ግን የኢትዮጵያን ምድር ከለቀቀባት ጊዜ ጀምሮ ከባርነት ነጻ ወጥቷልና በነጻነት መኖር የሚችለበት እድል አለው፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ነጻነት ለመታገል ሁኔታው ተመቻችቶለታል፤ ይህን ነጻነቱን ግን እራሱ ገንዘብ ከፍሎ ሊሸጠው ይደራደራል። ፍርፋሪ እየተጣለለት ወደ ቄራ የሚወሰድ እሪያ መጨረሻው ሞት እንደሆነው ሁሉ፣ 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራም መጨረሻው ባርነት ነው። አምስተኛው ባርነት!

የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት) ፦ አዳክሞ ማደህየት –ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ሐምሌ 2005

አንድ በጣም የተገረመ ደቡብ አፍሪካዊ ይህንን ሁሉ መንገድና ሕንጻ በአንድ ጊዜ ለማሠራት ገንዘቡን ከየት ነው የምታገኙት? ብሎ ጠየቀኝና ከወርቅ-ቡና አልሁት፤ ሳቅ አለና እኔኮ ከልቤ ነው የምጠይቅህ አለኝ፤ እንግዲያው ዘክዝኬ ልንገርህ አልሁት፤ ለወትሮው ብዙ የምክር ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም ለመንግሥትህ እንዳትናገርና የዚሁ ዓይነት ሥራ በደቡብ አፍሪካ እንዳይጀመር ቃል ግባልኝ አልሁትና ቀጠልሁ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመንግሥት ባንኮች ደጃፍ ላይ የነበረውን መጨናነቅ አይተሃል ወይ? ብዬ ጠይቄው ማየቱን ካረጋገጥሁ በኋላ ጉዳዩን እንደሚከተለው አስረዳሁት፡፡

Pro Mesfinአገዛዙ መሬቱንም ሆነ ቤቶችን የራሱ ካደረገና ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኋላ በየመንገዱ ዳር እንጀራ፣ ዳቦ፣ ቆሎ፣ ጠላና ትናንሽ ነገር እየሸጡ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶች፣ በየቤቱ እየሠሩ በነዚህ ቤቶች ተዳብለው ኪራይ እየከፈሉ የሚኖሩ ሴቶች በብዛት ነበሩ፤ በነዚህ ደሀዎች ላይ ቀበሌዎች በየጊዜው እየዘመቱ ቤቱ እንደሚፈርስባቸው እያስፈራሩ ደሀዎችን ያሸብራሉ፤ በዚህ ዓይነት ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ለጥቂት ወራት ካቆዩአቸው በኋላ ክረምትን ጠብቀው በግድ ያስለቅቁአቸዋል፤ በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባ ውስጥ የተፈናቃይ ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ የሚኖረው ሰው ቁጥር እየበዛ ለጤንነት ክፉ ጠንቅ እየሆነ ነው፤ ይህ ችግርና ስቃይ ትልቅ የሀብት ምንጭ ሆኖአል፤ ደሀ የሚበላው አንጂ የሚከፍለው አያጣም፤ ነጭ ደሀ ነጭ ማር ይከፍላል፤ እነዚህ ባህላዊ አነጋገሮች ተጠንተው በተግባር ላይ እየዋሉ ነው።

እንዴት? ማለት ጥሩ ነው፤ እነዚህ (ቤቶቻቸው ከማለት ይልቅ) መጠለያዎቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ከረሀቡ ሌላ በብርድና በጸሐይ በመጉላላታቸው የመጠለያ ችግራቸው በጣም ከባድ ስለሆነ በቀላሉ የሚበዘበዙ ናቸው፤ ችግሩን መፍቻ የሚመስል የደሀውን ነፍስ በጉጉት ሰንገው የሚይዙበት ኮንዶሚንየም የሚባል ማቁለጭለጫም አለ፤ ደሀ ሁሉ ኮንዶ አግኝቶ የሚያልፍለት ይመስለዋል፤ ስለዚህ ሁሉም ይፈልጋል፤ ስለዚህ የኮንዶ ፈላጊው ሰልፍ በጣም ረጅም ነው፤ ስለዚህ በመስገብገብ እየተተኮሰ ዋጋው በጣም ከፍ ያለ ነው።

ማፍረስ ከመገንባት የቀለለ ቢሆንም በአዲስ አበባ የሚካሄደው አብዛኛው የመገንባት ሥራም ከማፍረሱ ሥራ የተሻለ መሆኑ በጣም ያጠራጥራል፤ እንዲያውም የማፍረሱንም ሆነ የመገንባቱን ሥራ የሚመሩት የውጭ አገር (ምናልባትም የቻይና) ሰዎች ናቸው ለማለት ያስደፍራል፤ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ነፍስ ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የተጋድሎ ጀግንነት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የአገር ፍቅር ውስጥ መሬት እንዳለ የውጩ አገር ሰው በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል? አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ባለው ቤት ውስጥ ምን ምን ይሠራል? አንዴት ይሠራል? በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ አገሩ ሰው ምንም ያህል አያውቅም፤

ስቱድዮ በወር አንድ መቶ ዘጠና አምስት ብር፣ ባለአንድ መኝታ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር፣ ባለሁለት መኝታ አምስት መቶ ብር እንደሚከፈል ተወስኖአል፤ ይህ ኪራይ ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደለመድነው ዓይነት ያለ ኪራይ አይደለም፤ ልዩ ነው፤ አንዱ ልዩ የሚያደርገውም መጠለያዎቹን ሁሉ ያፈረሱትና ችግሩን የፈጠሩት ራሳቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸው ነው፤ ዋናው ልዩ የሚያደርገው ግን ለኮንዶዎቹ ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ሕንጻዎቹ ተሠርተውና አልቀው ተከራዮቹ ከገቡ በኋላ አይደለም፤ የሕንጻዎቹ ሥራ የሚጠናቀቀው ቢያነስ ከአምስት ዓመት በኋላ ሲሆን ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ዛሬ ነው! ደሀዎች ለማይኖሩበት ቤት ኪራይ ይከፍላሉ! ማንም አላስገደዳቸውም፤ ያስገደዳቸው ደካማነታቸውና መናጢ ደሀነታቸው ነው፤ መስገብገባቸው ነው።

ከቀረበው መረጃ ተነሥተን እስቲ ትንሽ ስሌት እንሥራ፤ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ስምንት መቶ ሺህ ያህል ሰዎች ለኮንዶ ተመዝግበዋል እንበል፤ በስቱድዮ፣ በአንድ መኝታ፣ በሁለት መኝታ፣ በሦስት መኝታ በእያንዳንዳቸው የቤት ደረጃዎች ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ቢመዘገቡ     ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት በዝቅተኛ የደሀነት ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሢሶ የሚሆኑት ደግሞ የደሀነት መሀከለኛ ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሌሎቹ ማለትም አንድ አምስተኛ የሚሆኑት በተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ደሀዎች ቢሆኑ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በያመቱ የሚሰበሰበው ገንዘብ እንደሚከተለው ይሆናል፤

 

ደሀነት ሲበዘበዝ

ኮንዶ የተመዘገቡ   የወር ኪራይ በደሀነት ደረጃ የዓመት ኪራይ
ስቱድዮ

200 000

 200 000 x 195=  39 000 000

  468 000 000
1 መኝታ

200 000

200 000 x 274=  54 800 000

  657 600 000
2 መኝታ

200 000

200 000 x 500= 100 000 000

1 200 000 000
3 መኝታ

200 000

200 000 x 750= 150 000 000

1 800 000 000
ድምር 1 000 000                279 700 000 4 125 000 000

 

እንግዲህ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከመጠለያ ማጣት ጭንቀት ለማምለጥና ያደረባቸውን የኮንዶ ጉጉት ለማሳካት ከአራት ቢልዮን ብር በላይ እየተራቡ ይገብራሉ፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ገና ኮንዶው ውስጥ ሳይገቡ ላባቸውን ያንጠፈጠፉበትን 20 625 000 000 ብር ይከፍላሉ ግፍ ሌላ ትርጉም የለውም።

ማፍረስም በጣም ትርፋማ ሥራ ሆነ።

በፈረሰው ላይ የሚገነባውስ? ስለኮንዶው ሕንጻ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሣት በግድ ያስፈልጋል፤ አንደኛ የኮንዶው ሥራ መቼ ተጀምሮ መቼ ያልቃል? ያልቃል ሲባልስ ለመኖሪያ ብቁ የሆነ፣ በሮችና መስኮቶች ተገጥመውለት፣ ወለሉና ጣራው፣ የመታጠቢያ ቤቱ ሁሉ ተሟልቶ ነው ወይስ ባለቤት የሚሆኑት ሰዎች የሚጠብቃቸው ሥራ አለው? ሁለተኛ የኮንዶው ሕንጻ ስንት ክረምትና ስንት በጋ የሚችል ይሆናል? ሦስተኛ ኮንዶው ሰዎችን ወደከፍተኛው ፎቅ የሚያደርሳቸው ‹ሊፍት› አለ ወይስ ሰዎች በእግራቸው በደረጃ ሊወጡ ነው? ይህ ከሆነ ለሽማግሌዎችና አሮጊቶች ምን ዝግጅት ተደርጎላቸዋል? ሽማግሌዎችንና አሮጊቶችን ወደምድር ቤቱ አካባቢ ለመደልደል ታስቦአል ወይ? አራተኛ የውሀ አቅርቦቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ውሀ በሚጠፋበት ጊዜ ነዋሪዎቹ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት የመጸዳጃ ቦታ ካልተዘጋጀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አካባቢው ለጤና ጠንቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፤ ‹‹የአበሻ ኑሮ›› የሚባል ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ቡናና ጌሾ መውቀጡ፣ ብቅልና በርበሬ ማስጣቱ፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ አንጀራ መጋገሩ፣ ማኅበሩ፣ ለቅሶው — እነዚህና ሌሎችም ማኅበራዊ ግዴታዎች ኮንዶው ሲሠራ ታስበው ነበር ወይ?

ደሀው ራሱን በማፈራረስ፣ ይበልጡኑ በሚደኸይበት ሥራ እንዲጠመድ፣ በፍርስራሽ እንዲነግድ በምናምን ተይዞአል! የሥላሴዎች እርግማን!

የልማታዊ ጋዜጠኞች አንዝህላልነት እና የአብርሃ ደስታ እማኝነት “የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች “

$
0
0

arab ethiopiaከነብዩ ሲራክ

ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዲ አረቢያ ግፍ ተፈጸሞባቸው ወደ ባገር ቤት የሚሸኙ እህቶች የመኖራቸው መረጃ ደረሰኝ ። በተለይም በቅርብ እከታተላቸው የነበሩ አህቶች እንግልት በመጠቆም በዚው በፊስ ቡክ የማለዳ ወግ ዳሰሳየ ላይ አንድ መልዕክት አስላልፊ ነበር! መልዕክቱም ለልማታዊ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች ሲሆን የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ ” የምንናገረውን ማመን መቀበል አቅቷችሁ እንደ ጠላት ከምታዩን ረቡዕ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ሂዱና ከፍተኛ ግፍ ተፈጸደሞባቸው ከሳውዲ ተጠርፈው ወደ ባገር የሚገቡትን የኮንትራት ሰራተኞችን ተመልክቱ !”የሚል ነበር።
ንቁ እዝነ ልቦንና ያልታደሉት ልማታዊ ጋዜጠኞች በቦታው ሄደው ከቤሩት የተመለሱትን ሻንጣ የደረደሩ እህቶች በቴሌቪዥኑ መስኮት ብልጭ አድርገው ከማጥፋታቸው ባለፈ ከሳውዲ ያለጫማና የረባ ልብስ ተደብድበውና ተደፍረው የተመለሱትን ግፉአን ሊያሳዩን እንኳ አልፈቀዱም! ጋዜጠኞቻችን አልተሳሳቱም!!! የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ያን ሰሞን “ስደት ይቅር ” ምንቴስ ሰፊ ሽፋን በየሚዲያው እየሰጡ ፣ የደበቁትን መከራችን እያሳዩ እያሉ ህዝበ አዳም ፣ ሃገሬውን ሲያስለቅሱን የከረሙት ወደ ነፍሳቸው ተመልሰዋል ብየ በማሰቤ ስህተቱ የእኔ ግምት ነው!!! ጉዳታችን እዩት ቀሪው እንዲማርበት ፣ ሃላፊዎቻችን ይዩትና ወደ ዘነጉት የዜጎች ጉዳይ ያተኩሩ ዘንድ የተገፊ ግፉአኑን ጉዳይ ተከታትየ መጠቆሜ በአደባባይ ቃል የገቡትን ይፈጽማሉ ብየ በማሰቤ የተሳሳትኩት እኔ ነኝ!!! ስህተቴ አንድና አንድ ነው!!! የአረብ ሃገሩን የስደት መከራ የሚፈልጉት ለፕሮፖጋንዳ እንጅ ቀሪውን ማስተማርን እንደልሆነ አለማሰቤ ነው ስህተቴ ! በእንዝህላል ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን አዝኘም ብቻ ሳይሆን አፍሬ ዝም ማለቴ ግን እውነት ነው! ዛሬ ማለዳ ግን መልካም መረጃም የሚየ ስፈነጥዝ ባይሆንም መረጃው በመሰራጨቱ የተደሰትኩበትን መጣጥፍ ተመለከትኩ ።
ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ከአረብ ሃገር ወደ ሃገር የገቡትን እህቶች አብርሃ ደስታ አግኝቷ እንዳነጋገራቸው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ካስተላለፈው መልዕክት ለመረዳት በመቻሌ ደስ አለኝ ! በገዥው የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደር ላይ በተለይም ስለ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመቀሌ ሆኖ በሚያሰራጫቸው የሰሉ ሚዛናዊ ሂሶች ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው አብርሃ ድስታ ግፉአን እህቶቸችን ቦሌ አየር ማረፊያ አግኝቷቸው ያየውን የሰማውን እጥር ምጥን ባለው የለመድነው መረጃ አቀባበል እንካችሁ ብሎናል ። የአብርሃ እማኝነት አስደስቶኝ እኔም ለዛሬ ወግ ዳሰሳ አበቃሁት ! ወዳጃችን አብርሃ ደስታ ሆይ ! የአረብ ሃገሩ የብዙሃን የኮንትራት ሰራተኞች አስከፊ ህይዎት ያጫዎቱህ ወደ ሃገር ለመግባት የታደሉት መሆናቸውን አስረግጨ እነግርሃለሁ ! ያየሃቸው የታደሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው ! የመንግስት ተወካይ አለን ለማለት አልደፍርም ! እውነቱ ይህ ነው ! አንተም እንኳን ከግፉአኑ ሰምተህ አሰማህን ! ይህ የማናችንም ሃላፊነት መሆን ሲገባው እያደረግነው አይደለም! የእህቶቻችን ህይዎት በአረብ ሃገር ምስክርነቱ ይህ ነው ! እንዲህ ይኖራል ! የእኔን በዚህ ላብቃና እጥር ምጥን ወዳለችው የአብርሃ ደስታን እማኝነት ከዚህ በታች እንድትመለከቱ ስጋብዝ ለአብርሃ ምስጋና በማቅረብ ጭምር ነው! እነጰ አበቃሁ ! ቸረወ ያሰማን !
ነቢዩ ሲራከ
Abrham Desta By Abraha Desta የኢትዮዽያውያን ህይወት በዓረብ ሀገሮች ——————————————— ሮብ ነሓሴ 15, 2005 ዓም ጠዋት ቦሌ ኤርፖርት ነበርኩ። ኢንተርናሽናል ተርሚናሉ ከዓረብ ሀገራት በተመለሱ እንስት ኢትዮዽያውያን ተጥለቅልቋል። የተከፉና የተረበሹ ይመስላሉ። ከሰዓት በኋላ ወደ መቐለ ለመመለስ ወደ ሀገር ውስጥ ተርሚናል ገባሁ። ከነዚህ ጠዋት ረጅም ሰልፍ ይዘው ያየኋቸው ተመላሾች የተወሰኑ አገኘሁ። ስለ ህይወታቸው፣ ስለሚደርስባቸው እንግልት ወዘተ አጫወቱኝ። በዓረብ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እንደሰው አይቆጠሩም፤ ብዙ አካላዊና ስነ አእምራዊ ችግር ይደርሳቸዋል። ብዙዎቹ አብደዋል፣ ራሳቸው አጥፍተዋል። ኢትዮዽያውያን በመሆናቸው ራሳቸው ይረግማሉ፤ በመፈጠራቸው ያዝናሉ። የኢትዮዽያ ኤምባሲ ግን ምንድነው የሚሰራው? የዜጎች ደህንነት መጠበቅ’ኮ የመንግስት ሐላፊነት ነው። የኢትዮዽያውያን ስደትና ግፍ ሀገራችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊመራት ይችላል።

የመለስ ዜናዊ “የሁለት አሐዝ ዕድገት” እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ***

$
0
0

ከበፍቃዱ ዘ ኃይሉ

“ለ7 ዓመታት በተከታታይ 11·6 በመቶ አድጓል” የተባለው የመለስ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፥ የዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍም ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚገኘው መረጃ ላይ ቢመሠረቱም “የለም፤ ከ6 እስከ 8 በመቶ ነው ያደገው፣ ቢሆንም ቀሽት ነው” ይላሉ።

“ኢኮኖሚው ሲመነደግ” የሕዝቦች ኑሮ ደረጃስ እንዴት ነው?

ኢትዮጵያ በየአረብ አገራቱ የቤት ሠራተኛ አቅራቢነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰችው በመለስ ዘመን ነው። (ለምሳሌ አሁን ኢትዮጵያውያንን አልቀበልም ያለችውን ሳውዲ አረቢያ የቤት ሠራተኛ ፍላጎት 10 በመቶ ኢትዮጵያ ትሸፍን ነበር።) በየአረብ አገራቱ የኢትዮጵያውያን ስም ከሌብነት እና ሴተኛ አዳሪነትጋ የተያያዘ ነው።

ethiopia-famine
ከኢትዮጵያ ውጪ መውጣት ለሁሉም ዜጋ ቢፈቀድ ዐሥር ሚሊዮን ሰው እንኳን ይቀራል ብዬ መገመት ይከብደኛል። ከተሜውም ገጠሬውም ወደቻለው ቦታ ይፈልሳል። የተማረውም፣ ያልተማረውም ኢኮኖሚያዊ ስደትን የመምረጡ እውነት የኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን እውነተኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል።

የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተለይ የመንገድ ሥራዎች ሲነቃቁ የግሉ ዘርፍ (ከኢሕአዴግ “የኢንዶውመንት” ቢዝነሶች በቀር) ተዳክሟል። ያሉትም የግል ቢዝነሶች ቢሆኑ በፖለቲካ ጥቅም የሚለመልሙ በመሆናቸው በከተሞች መሐል የሚበቅሉ ብልጭልጭ ሕንፃዎች የሙስና ሲሳይ ናቸው። ከሕንፃዎቹ ጀርባ ያሉት ያው የድሮዎቹ ቆሼ ሰፈሮች ናቸው። እንደ HDI ያሉ የUN የሰብኣዊ ልማት መለኪያዎችም የሚያሳዩን ኢትዮጵያውያን ዛሬም በድህነት እየማቀቁ መሆኑን ነው።

“ስኳር የተወደደው ድሃው ስኳር መብላት ጀምሮ ነው” ያሉት መለስ ስኳሩን የሚልሱት እነማን እንደሆኑ እንኳ ሳይረዱ ያለፉ ይመስለኛል።

አቶ መለስ ምንጩንና መጠኑን ማንም ያልገመተው፣ የባለብዙ ሀብት ባለቤት፣ የትዳር አጋራቸውን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሀብታሞች ያሉበት የጥቅመኞች ክበብ እየዳጎሰ ብዙኃኑ የሚቀጭጩበትን የቢዝነስ ስርዓት በመፍጠር በቁጥር ጫወታ አድጋችኋል ይሉናል። ድሃ ተኮር ፖሊሲ ቀርጫለሁ፣ ለልማቱ ብዬ ነው ዴሞክራሲን የበደልኩት ብለው ያተረፉልን ነገር ቢኖር አገርክን ጥለህ ብረር፣ ብረር የሚያሰኘው ምስኪን፣ ድሀ ትውልድ ብቻ ነው።

“በህግ አዋቂ ፣ በመብት አስጠባቂ ”ሹም መብት ሲጣስ እንዴት ያማል ?

$
0
0

 ነቢዩ ሲራክ

ከሳውዲ አረቢያ

Nebiyu Sirak

ነቢዩ ሲራክ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ ሃላፊዎችን የያዘ ቡድን በአንባሳደር ውብሸት ተመርቶ ሳውዲ መግባቱን ሰምቸ ነበር ። ከፍተኛ ሃላፊዎችን የያዘው ቡድን ሪያድና ጅዳ የኮንትራት ሰራተኞችን ይዞታ ለማየት እንደመጣ መስማቴ ደግሞ ጉዳዩን እግር በእግር እንድከታተለው ምክንያት ነበር። የጅዳው ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ከመድረሱ በፊት የኮባንያ ስራየን በጊዜ ሸካክፊ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ … ! በቆንሰሉ መጠለያ ድርሸ ወደ ግቢው በር ስገባ እንግዶቹ ከቆንሰሉ በር ወደ መጠለያው ወደሚገኝበት በር ሲንቀሳቀሱ ደረስኩ። ቀድሜ መጥቸ ስለነበር ቀድሜ የግቢውን በር ተሻገርኩ ። ዘልቄ ልገባ ስል የጅዳው ቆንስል ተሶርፈውም ቢሆን እንደመሳቅ እያሉ ጨበጡኝ ። ጨበጥኳች ። ትከሻየን እየደባበሱ ወደ ውስጥ መግባት እንደማይፈቀድልኝ አስታወቁኝ ። ” ለምን ተከልከልኩ? ” ስል ጠየቅኳቸው ” እሱን ሌላ ጊዜ እንነጋገራለን አሉኝና እንግዶችን እየመሩ ወደ ተፈናቃዮች የሚደርጉትን ጉብኝት ለመከወን በጥድፈት ረምድ ረመድ ብለው ጥለውኝ ሄዱ … እንቅስቃሴውን በርቀት እየተከታተልኩ እያለ የኮሚኒቲው ግቢ የጥበቃ በትህትና ጠጋ ብሎ ሰላምታ ካቀረበልኝ በኋላ እንዲህ አለኝ ”

አቶ ነቢዩ ይቅርታ! ” ሰላምታ አቅርቤለት ምን ልታዘዝ አልኩት” አይ ምንም አይደለም ከይቅርታ ጋር ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከግቢው እንዳስዎጣት ትዕዛዝ ስለሰጡኝ ልነግርህ ነው! ” አለኝ!የወንድሜ ትህትና ልቤን ቢሰብረውም አቶ ዘነበ ማነጋገር እንደምፈግ በትህትና ጠየቅኩት ፣ በርቀት ሆነው በአይናቸው የሚቆጣጠሩኝን አቶ ዘነበን ጠራልኝና መጡ! ለምን እንደመከለከል አጥብቄ ሞገትኳቸው ፣ የሚመልሱት ባይኖርም በመረጃ ቅበላው ዙሪያ የምስራው ስራ አስነዋሪ እንደሆነ በደምሳሳው በመናገር ” ግድ የለም ግባ !” ሲሉ በገዛ ቤቴ የከለከሉኝ ሹም አቶ ዘነበ ፈቃድ ሰጡኝ!”ህግን ጠንቅቄ አውቃለሁ!” በሚሉት የጅዳ ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ የተላለፉት፣ የገሰሱትን መብቴን መልሰው ቢያከብሩትም የምሰራው የፖለቲካ ስራ እንጅ ለዜጎች በመቆርቆር እንዳልሆነ ጉብኝቱ አብቅቶ ከእንግዶቹ መካከል የመብቴን መገፋት ትክክል እንዳልሆነ ሳስረዳቸው ደጋግመው በሰጡኝ ምላሽ ገለጹልኝ !እንግዶችን ከበው እያነቡ በደላቸውን የገለጹትን ተፈናቃዮች እና መላሽ ይሰጡ የነበሩትን ሃላፊዎች ተመልክቻለሁ።

በአውላላው ሜዳ ላይ ጸጉራቸውን አንጨፍርረው የሚንቀዋለሉት ያበዱ እህቶችን ባስሙ ባያዩም ጩኽት ምሬታቸውን ያስተጋቡት ወደ መቶ የሚጠጉትን ተፈናቃዮች አቤቱታ ሰምቻለሁ!እመለስበትማለሁ !የእኒህን እህቶች በደል መናገር ፖለቲከኛ ካስባለ የምሰራው የፖለቲካ ስራ አለመሆኑን ለማሳየት የግፉአኑን በደል የሚያሳዩ ለማየት የሚሰቀጥጡ መረጃዎች ለማቅረብ ልገደድ ነው!! ይህን የማደርገው ከለመድኩት መቀመጫን ለመከላከል ከሚደረገው ተራ ውንጀላ ራሴን ከውንጀላ ለማጽዳት ሳይሆን እውነቱን ልነግራቸሁና ማን በህዝብ እና በሃገር ላይ ግፍና በደል እንደሚፈጽም ፍርድ ትሰጡ ዘንድ ለማሳየት ያህል ብቻ ነው!

ለሁሉም ከስሜት ወጥቸ በምቀጥልበት የማለዳ ወግ እናዎራለን!

ቸር ያሰማን ! ነቢዩ ሲራክ

የግብፅና ኢትዮጵያ መጪው ዘመን ምን ሊመስል ይችል ይሆን?

$
0
0
ከደምስ በለጠ
Blue Nileግብፅ (ምስርእንደሃገር ከምትታውቅበት ማለትም ከፈሮኦኖች ዘመን ጀምሮ ፤ የታሪኳም ሆነ የህልውናዋ መሰረት አባይ ነው። አባይ ባይኖር የግብፅ የቆየና ጥንታዊ ታሪኳ የለም ፤ የፈርኦኖች ታሪክ የለም፤ አባይ ባይኖር የክሊዮፓትራ ታሪክ የለም ። ባጠቃላይ አባይ ባይኖር ግብፅም ታሪኳም፤ ጥንታዊ ስልጣኔዋም፤ የአለማችንን እውቅ የታሪክ ምርምር መፃህፍት ገፆች ባላጣበቡ ነበር ። ታላቁ የግሪክ የታሪክ ሰው ሄሮዶቱስ ግብፅ የአባይ ስጦታ ነች ያለውም ለዚህ ነበር ። ታላቁ አሌክሳንድር ከግሪክ ተነስቶ መካከለኛው እስያ የሚባለውን ምድር ወርሮ ወረራውን በጊዜው ታላቅ አገርና አስፈሪ ጦር የነበረውን ፐርሽያን በዛሬው አጠራር ኢራንን ድል አድርጎ ወደ ህንድ ድንበር ከተጠጋ በሁዋላ በድንገት አረፈ ።
ከታላቁ አሌክሳንደር ሞት በኋላ ጀነራሎቹ የአሌክሳንደርን ግዛት ለአራት ከፍለው እጣ ተጣጥለው ፤ ግብፅ ፕቶሎሚ ለተባለው የጦር ጀነራል ደረሰችው ። የሮማውያንን ታሪክ የለወጠችው ክሊዎፓትራ ይሕ ግሪካዊው ጀነራል የመሰረተው ፕቶሎሚያዊ ስረወመንግስት የመጨረሻዋ ወይም 11ኛዋ ልጅና ገዢ ነበረች ፤ በሷ ዘመን ደግሞ ሌላ ሃያል አገዛዝ ከሮም ተነስቶ ግብጽን ይወርራል ። በፍቅሯ ከወደቀው ከመጀመሪያው የሮማ ቄሳራዊ ዲክታተር ጁሊየስ ቄሳርም ልጆች ትወልዳለች አንዱን ልጇንም ለሮማ ገዢነት እሷም ሆነች አባቱ ጁሊየስ ቄሳር ያዘጋጁት ነበር ። ጁሊየስ ቄሳር በሮም ከተገደለ በኋላ ፤ የሮማ ጀነራሎች የሮማን ግዛት ለሶስት ከፍለው ግብፅ ለማርክ አንቶኒ ደረሰችው ። ማርክ አንቶኒ በክሊዎፓትራ ፍቅር ወድቆላት እዚያው ከግብፅ መንቀሳቀስ ያቅተዋል ። እሷና አዲሱ ሮማዊ ወዳጇ ፤ በአውግስጦስ ቄሳር ጦር ድል ሲሆኑ ፤ ክሊዎፓትራ ብዙ ገንዘብ አስይዛ ከቄሳር የወለደችውን ልጇን የላከችው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸሽ ነበር ። ክሊዎፓትራ እንዳሰበችው ልጇ ኢትዮጵያ ሳይደርስ በጠላቶቹ ተይዞ በ17 አመት እድሜው ታንቆ ተገደለ።
ግብፅ በታሪክ የምትታወቅባቸው ሁለት ስሞች አሏት ። በመፅህፍ ቅዱስ “ምስሪያም” ይላታል ፤ በኛ “ምስር” ( “ስ” አይጠብቅምሌላው ደግሞ ከግሪክ የተወረሰው “ኤጊፕቶስ” የሚለው መጠሪያ ስም ራሱ ከአባይ ጋር የተያያዞ የወጣላት ስም ነው ፤ ጥቁር አፈር ማለት ነው። የግብፅ ምድር በተፈጥሮው አሸዋና የምድሩም ቀለም ሽሯማ ነው ። አባይ ወንዝ ግብፅ ደርሶ ግራና ቀኝ ሞልቶ ሲፈስና ዳርቻዎቹ ከኢትዮጵያ በመጣው ደለል ሲሞሉ መሬቱ ይጠቁራል ። በዚህ ምክንያት ነው “ኤጊፕቶስ” የሚለውን ግሪካዊ መጠሪያ ያገኘችው ግብጽ ። ይህ ጥቁር መሬቷ በየአመቱ በደለል ተሞልቶ ለዘር ስለሚዘጋጅ ፤ ለጥንታዊት ግብፅ ፤ የፈርኦኖቹ መለኮታዊነትም ምስጢር መገለጫም
ነበር። ስለዚህም አባይ ለግብፅ የህልውናዋም ፤ የአንፀባራቂ ታሪኳም ፤ ያለፈውም ሆነ መፃኢ ህልውናዋ መሰረት ነው።
የግብፅ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ታሪኳ ፤ ከፈሮኖች የ4500 አመታት ግዛት በኋላ በግሪኮች ወደመቶ አመታት ፤ ቀጥሎም በሮማውያን ለ3መቶ አመታት ፤ ከዚያም በቢዛንቲያ ለ3መቶ አመታት ፤ በመቀጠልም ለ1100 አመታት አረቦችና ማምሉኮች በፍርርቅ ፤ ቀጥሎም የትውልደ-አልባኒያዊው የሞሀምድ አሊ ስርወ-መንግስት በቀጥታ ወደ ሰማኒያ አመታት ከገዟት በኋላ ፤ ቀሪዎቹ የመሃመድ አሊ ልጆች የእንግሊዝን ቅኝ ገዢነት ተቀብለው እስከ 1922ድረስ ቀጥሎም የእንግሊዝ ከባድ እጅ ቢኖርበትም የመሃመድ አሊ ልጆች እስከ 1952 ድረስ በንጉስነት ገዝተዋታል ። በዚህ አይነት ግብፅ ከፈሮኖች በኋላ ፤ ወደ 2500 አመታት ገደማ ግብፃዊ ባልሆኑ ባዕዳን ተገዝታለች ። ከዚህ የባእዳን ግዛት በኋላ ግብፅ የመጀመሪያውን ግብፃዊ መሪ ፤ በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት አገኘች ።”የሪፐብሊክ ዘመን” የሚል መጠሪያ ስም በመስጠት ወታደሮች ፤ 1ኛ ጀማል አብደል ናስር ፤ 2ኛ አንዋር ሳዳትና 3ኛው ሆስኒ ሙባረክ ለ60 አመታት እስከ 2012 ድረስ በይስሙላ ምርጫ ገዝተዋታል ። ከሶስቱ ወታደራዊ መሪዎች ዘመን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የሆስኒ ሞባረክ አገዛዝ ነው የፈጀው። ይህን ከላይ ለማስገንዘብ የወደድኩበት ዋናው ምክንያት ለዘመናት በበእዳንና በአምባገነኖች ሲገዛ የኖረው የግብፅ ህዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጀመሪያውን መሪ መርጦ ነበር ።
በግልፅና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት መሃመድ ሞርሲ ለአንድ አመት ሃገሪቱን ካስተዳደሩ በኋላ በወታደራዊ መፈቅለ-መንግስት ከስልጣናቸው ተውግደዋል ። በምንም መለኪያ ይሁን ፤ ባለፈው አመት ለግብፅ ፈንጥቆ የነበረው ዲሞክራሲያዊ ብርሃን ዛሬ ጨልሟል ። ወታደሮች በፈለጉት ሰዓትና ጊዜ ምክንያት ፈጥረው የግብፅ ህገ-መንግስት ከሚያዘው ውጪ የግልበጣ እርምጃ ወስደዋል ። ይህ እርምጃ ግብፅን ቀጣይ ወደሆነ የመንግስታዊ አስተዳደር ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አዙሪት ውስጥ ለወደፊትም የሚከታት ይሆናል ።
በአለማችን ዘመናዊ የመንስታት ግልበጣ ታሪክ እንደሚታየው መጀመሪያ አንድ ጀነራል ወይም የጦር መኮንን መንግስት ይገለብጥና የሃገሪቱን መሪ ያስራል ፤ ህገ-መንግስቱን ይሽራል ፤ ፓርላማውንም ይበትናል ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ያውጃል ፤ ህዝብ የሚቃወም ከሆነ በደም ህገሪቱን ያጥለቀልቃታል ። ግብፅም ከዚህ አላመለጠችም ። ጀነራል አብዱል ፋታህ አልሲሲ በውሻ ገመድ አስሮ እንደፈለገ ከኋላ ሆኖ የሚሽከረክረው ሲቪል መሰል ጊዜያዊ መንግስት አቋቁሟል ። ይህ መንግስትም እስካሁን የተገደሉት ግብፃውያን ቁጥር ከስምንት መቶ አይበልጥም እያለ ነው ፤ መረጃዎች የሚያሳዩት ግን ከዚያ በላይ ነው ። ገለልተኛ አቋም አለው ይባል የነበረው የግብፅ
ሴኩላር ህብረተሰብና እስላማዊ ፓርቲዎች መካከል ተፈጥሮ ነበር የሚባለው የፖለቲካና የአይዲዎሎጂ ግብግብ ዛሬ መልኩን ቀይሮ ፤ የሙባረክ ዘመን ሰዎች ወደስልጣን የተመለሱበት ትያትር ሆኗል ። የሴኩላሩ ህብረተሰብ ቁንጮ ይባል የነበረውም ሞሃመድ አል ባራዳይ ፤ በህዝቡ ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ምክንያት የጊዜያዊው መንግስት ምክትል ፕሬዝደንትነቱን በፈቃዱ ለቅቆ ከግብፅ ውጥቶ ስዊዘርላንድ ገብቷል ። በዚህ አይነት ሴኩላሩ ህብረተሰብ በሙባረክ ሰዎችና በጀነራል አልሲሲ ተሸውዷል ። ሃገሪቱን ለ32 አመታት በፈላጭ ቆራጭነት ያስተዳደረው ሙባረክም ከወንጀሎቹ ሁሉ ነፃ ሆኖ ከእስር ተፈትቷል ። የሚገርመው ሙባረክ ሃገሪቱን ባስተዳደረባቸው 32አመታት ጥሎት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከስልጣን እስኪወርድ ድረስ ተነስቶ አያውቅም ነበር ። አሁንም ጀነራል አልሲሲ ሞርሲን ከገለበጠ በኋላ መጀመሪያ ያደረገው ይህንኑ አዋጅ መመለስ ነበር።
የእስላማዊ ወንድማማችነት ፓርቲ በሞሃመድ ሞርሲ አማካይነት ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ ተከታታይ የፖለቲካ ስህተቶች ሰርቷል ። ከ70 አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው እስላማዊ ወንድማማችነት ፓርቲ ፤ ብዙ የግብፅ ምሁራንን ከተለያዩ የሙያ መስኮች ያካተተ ድርጅት ቢሆንም ፤ የመንግስት አስተዳደራዊ መዘውር ላይ ባለፈው አንድ አመት ተሞክሮው ደካማነቱ ተጋልጣል ። ያም ሆኖ ግን ተቃዋሚዎቹ እንደሰለጠነው አለም የምርጫውን ጊዜ ጠብቀው በምርጫ ቢጥሉት ኖሮ ፤ ለራሳቸውም መፃኢ እድል ይበጃቸው ነበር ። አሁን ያለው የግብፅ ሁኔታ እንደሚያሳየው ግብፃውያን ተከፋፍለዋል ። የጨሰው አቧራ ሲረጋና ጭጋጉ ሲገፈፍ የግብፅን ህዝብ እንደገና ለአንድነቱ መስራቱ አይቀሬ ነው የሃገር ጉዳይ ነውና ።
መጪው የግብፅ መንግስት ወታደራዊም ሆነ ወይም በወታደሮቹ ከኋላው የሚገፋ ጋሪ ፤ በአምባገነኖች እንደተለመደው ፤ የህዝቡን ትኩረት አቅጣጫ ማስለወጫ አንድ ዘዴ መፍጠር ይኖርበታል ። ይህ ዘዴ ደግሞ የቆየ ታሪካዊ መሰረት ያለውና የአገሪቱ ቁስል መሆን ይኖርበታል ። ለማንም የፖለቲካ ታዛቢ በግልፅ እንደሚታየው የመጀመሪያውን ትኩረት የሚስበው ፤ ግብፅ ከእስራኤል ጋር ያላትን የቆየ አረባዊ ችግርን በመቆስቆስ የህዝቡን እኩረት አቅጣጫ ማስለውጥ ይሞከር ይሆናል ፤ ሆኖም ግን በወታደራዊ አቅሟም ሆነ ባሏት ጡንቸኛ ወዳጆችና ምክንያት እስራኤልን ለዚህ አላማ ለማዋል መሞከር የሚያስከፍለው ዋጋ ከፈተኛ ሊሆን ስለሚችል የማይሞከር ይሆናል ።
ሁለተኛውና ቀጣዩ የአቅጣጫ ማስለወጫ የቆየና ታሪካዊ የግብፅ ቁስል አባይና ኢትዮጵያ ይሆናሉ ። ከላይ እንደገለፅኩት አምባገነኖች የሚጠቀሙበት ዘዴ ነውና ፤ በኢትዮጵያም የአካባቢው አገሮች ህዝባዊ አመፅ ጣራ በነካበት ጊዜ ሟቹ አምባገነን የኢትዮጵያን ህዝብ ትኩረት የሳበውና ሊመጣ ይችል የነበረውን የህዝባዊ አመፅ ሰልፍ ወደአባይ ግድብ ግንባታ የድጋፍ ሰልፍ የቀየረው በዚሁ
አይነት ዘዴ ነበር ። አሁን ደግሞ በተራቸው የግብፅ አምባገነኖች ይህን ዘዴ የማይጠቀሙበት ምክንያት አይኖርም ። ለዚህም አራት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል ።
1አባይ ለግብፅ ህይወቷም ህልውናዋም ነው ። ህዝቧንም በቀላሉ ወደአንድ የሰልፍ መስመር ሊያመጣ የሚችል ጉዳይም ነው ። ሌላው ቀርቶ ብዙ መከራ እየተቀበሉ ያሉት የግብፅ ክርስቲያኖች ዛሬ ወታደራዊውን መፈንቅለ መንግስት ደግፈው ይገኛሉ ፤ እንዲያውም ባለፈው አርብ የኦርቶዶክሱ ፅ/ቤት ሙሉ ድጋፉን የገለፀበትን መግለጫ አውጥቷል ። እነሱም ቢሆኑ ግብፃዊ ናቸውና ወደሰልፉ መቀላቀላቸው አይቀርም ። በአባይ ጉዳይ ላይ ሊይዙት የሚችሉት አቋም ከሙስሊሙ ግብጻዊ አይለይም ። ለማሳያ ያህል ክርስቲያን የሆነውና የቀድሞው የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር (በኋላ ላይ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሁፊ ሆኖ ያገለገለውቡትሩስ ቡትሩስ ጋሊ ፤ “የአካባቢያችን ቀጣዩ ጦርነት የሚደረገው በፖለትካ ሳይሆን በአባይ ምክንያት ነው ፤ ወደዚያ ደረጃ ከተደረሰ ደግሞ ጄቶቻችንን ልከን ግድቡን በአንድ ቀን እናፈነዳውና ወዲያው እንመለሳለን ፤ ጉዳዩ ይህን ያህል ቀላል ነው ፤ ሲል የተናገረው የሚረሳ አይደለም ።
2የግብፅ ወታደራዊ ሃይል ከኢትዮጵያ ጋር ሲወዳደር ጠንካራ ነው በተለይ የአየር ሃይሉ። የግብፅ አየር ሃይል በአሁኑ ጊዜ 240 ተዋጊ አውሮፕላኖች አሉት ፤ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ አሜሪካን ሰር F16 የተለያዩ ሞዴሎች ሲሆኑ በቅርቡም እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን ተዋጊዎች ከአሜሪካ አግኝቷል ። የምእራቡ አለምም የሚቆመው ለጥቅሙ ነውና ከኢትዮጵያ ይልቅ ግብፅ ላይ የበለጠ ጥቅም ስላለው ከግብፅ ጋር መቆሙ አይቀሬ ነው ።
3የኢትዮጵያ ጎረቤቶችም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት አስተማማኝ አይደለም ። በዚሁ የፈረንጆች አመት ኤፕሪል ላይ ፤ ኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯን እና የኢሲያስ አፈውርቂን የፖለቲካ አማካሪ የማነ ገብረ-አብን ካይሮ ድረስ በመላክ ፤ የግብጽን የቅኝ-ገዢነት ዘመን የአባይ ውሃ ስምምነት እንደምትደግፍ ፤ ከስልጣን ለተወገዱት ሞሃመድ ሞርሲ አሳውቃ ነበር ። ሰሜን ሱዳንም በተለዋዋጩ የፖለቲካ ባህሪዋና አረባዊ ተባባሪነቷ የተነሳ በተለይ ደግሞ ካላት የአባይ ጥቅም ጋር ተደማምሮ ፤ የገልፍ አረብ አገሮችም ተጨማሪ ግፊት ካደረጉባት ባልተጠበቀ ጊዜ ግልብጥ የምትል ሃገር ናት ። በተለይ ደግሞ የሳውዲው ልዑል በአረቦች የውሃ ሚኒስቲሮች ስብሰባ ላይ የሰነዘረውን አይነት ፤ ማለትም ጥቃቱ ሁሉ በመላው አረቦች ላይ እየተሰነዘረ ነው የሚለውን ሃሳብ ፤ ከተለያዩ አረብ ሃገራት ከተደረገባት አሁን የለበሰችውን ቆዳ ቀለም በቀላሉ የማትቀይርበት ምክንያት የለም ።
4ግድቡ እየተሰራ ያለበትም ስፍራ በቀላሉ ለአደጋ የተጋለጠ ያደርገዋል ፤ በተለይ ለአየር ሃይል ድብደባ ። ከኢትዮጵያ ድንበር በ40 .ሜ ወይም በ25 ማይል ርቀት ላይ ነው ግድቡ የሚገኘው ። በቀላሉ የሰሜን ሱዳንን አየር ክልል አቋርጦ ወደግራ እጥፍ ያለ F 16 ተዋጊ አውሮፕላን በደቂቃዎች ውስጥ የአየር ድብደባውን አከናውኖ ሊሄድ ይችላል ። ኢትዮጵያስ የአየር መከላከያ አቅሟ ምን ያህል ነውአጸፋውን ለመመለስ የሚያስችል ብቃትስ አላት ወይ ከስልጣን የተወገዱት ሞሃመድ ሞርሲ እንኳን ከመገልበጣቸው 10 ሳምንታት በፊት “ የአባይን ውሃ እያንዳንዷን ጠብታ በደማችን እንከላከላለን” ሲሉ ተናግረው ነበር :: እስከ አለፈው አመት ድረስ የግብፅ የውሃና የመስኖ ሚኒስትር የነበረው ሞሃመድ ናስር ኤል አላም “ ሚሊዎኖች እንራባለን ፤ የውሃ እጥረት በየቦታው ይከሰታል ፤አደጋውም ከፍተኛ ይሆናል” ብሎ ነበር ። አሁን ደግሞ ወደ ስልጣን እየተመለሱ ያሉት የቀድሞዎቹ የሙባረክ ዘመን ሰዎች ናቸው ። የሁለቱ ተቃራኒ የፖለቲካ ቡድኖች ሰዎች አባባል የሚያመለክተን አባይ ላይ የሚያስማማ ነጥብ ያላቸው መሆኑን ነው ።
እናም ይህን በተመለከት እትዮጵያዊው ህብረተሰብ ምን እየሰራ ይገኛል ግብፃውያኑን የማስተባበሩ ተግባር በመጪው የግብፅ መንግስት በኩል ሲጠናቀቅ በኛስ በኩል ምን መደረግ አለበት ጦርነት አይቀሬ የሚሆንበት ሁኔታዎችም ሊመጡ ይችላሉ ። እንደዜጎች እያንዳንዳችን ልናስብበት አይገባም ወይ ወይስ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን የቅርብ ጊዜ የፅሁፋቸውን አባባል ልዋስና “በግብፅና በኢትዮጵያ ውዝግብ የሚያሸንፈው አሜሪካ መሆኑን የሚጠራጠር ይኖር ይሆን?” ስለዚህ አሜሪካ ለሚያሸንፈው ጦርነት እኛ ለምን እንለፋለን ብለን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ?
በእኔ በኩል ፅሁፌን አበቃሁ ።
ተጨማሪ
ትንሽ ለዲያስፖራው ትግል ማሳሰቢያ !
ቀጥሎ የምገልፀው የቅርብ ጊዜ ትዝታየን ነው ። በተለይ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በቋፍ ያለው የዲያስፖራ ትግል መሰንጥቅ ይጀምራል ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የደረሰውን ማስታወሱ በቂ ማስረጃ ይሆነናል ። ዛሬ የውጪውን ትግል ክፉኛ የሚታገሉት እዚሁ ከኛው ጋር አብረውን የነበሩና በኤርትራ-ወያኔ ጦርነት ወቅት ወደ ባንዳነት የተቀየሩ የዲያስፖራው ሰዎች ናቸው ። ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል ። ዛሬ በየአቅጣጫው የዲያስፖራው ትግል ተቀናቃኝ ሚዲያዎች በዲያስፖራው ድጋፍ እግራቸውን የተከሉና በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኩል “አገራችን
ስትደፈርማ ቁጭ ብለን አናይም” በሚል ምክንያት እጃቸውን የሰጡ ናቸው ። የሰሜን አሜሪካ
አመታዊ የእስፖርት ፈደሬሽንን ለመገንጠል ያሰቡትና በተመሳሳይ ጊዜም ለሁለተኛ ጊዜ ውድድር በተደራቢ ያዘጋጁት ወገኖች ፤ እንዴ !! አገራችን ተወራለች እንዴት ነው ነገሩ ብለው ፤ ተዉ ሲባሉ ፡ እኛ ደሞ ከወያኔ ጋር ልንሰራ አብዳችኋል እንዴ እያሉን ገብተው ፡ ቀልጠው የቀሩ ወገኖች ናቸው ። እናም በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ሊነሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ተጠቅመው ለመግባት የሚንደረደሩ አይጠፉምና ጠንቀቅ ማለት ይገባል ። መግባቱን ሊገቡ ይችላሉ አትግቡም ብንላቸው አይቀሩም ፤ ሆኖም ግን እንደተላከ ውሻ ጩሀታቸውን መጥተው እንዳይለቁብን በማለት ነው ይህን ማሳሰቤ ለሁሉም መዘጋጀቱ ተገቢ ይመስለኛልና ፡፤


መንግስት የሙት ዓመትና ተዝካር ማለት ትቶ ትኩረቱን ለሐገራዊ መግባባት ቢሰጥ – ግርማ ሠይፉ ማሩ

ትንሽ ስለ ‘መለሲ-ዝም’: ከኢህአዴጎች የምስማማበት ነጥብ

$
0
0

Abraha Desta from Mekele, Tigrai

Abrham Destaሳስበው ሳስበው ስለ ‘መለሲዝም’ ሰበካ የተጀመረ ይመስለኛል። በመለስ ማመናቸው ችግር የለብኝም። ግን መለስ ፈጣሪያቸው መሆኑ እየነገሩን ነው። ብዙ ነገሮች በሱ ስም እየተሰየሙ ናቸው። እነሱ እንደሚነግሩን ከሆነ የኢህአዴግ ፖሊሲ የመለስ ነው፣ መለስ ወታደራዊ መሃንዲሳቸው ነበር፣ መለስ አንቀሳቃሽ ሞተራቸው ነበር፣ የኢህአዴግ ሓሳብና ተግባር የመነጨው ከመለስ ነበር፣ ባጠቃላይ መለስ ሁለመናቸው ነበር።

ለዚህም ነው የኢህአዴግ አባላት አውቀውም ሳያውቁም መለስ የተናገረውን እንደ ፓሮት የሚደግሙት። በራሳቸው ማየት ሳይችሉ መለስ በመራቸው ይጓዛሉ። ለዚህም ነው መለስ ያወጣውን ፖሊሲ መተግበር የማይችሉ። ፖሊሲው መተግበር ያልቻሉበት መንገድ ማየት ስለሚሳናቸው ፖሊሲው ጥሩ መሆኑ ተናዘው ችግሩ ያለው ግን አፈፃፀሙ ላይ መሆኑ ይለፍፋሉ።

ግን አንድ ትክክል ወይ ጥሩ የሆነ ፖሊሲ እንዴት ላይፈፀም ይችላል? ፖሊሲ’ኮ አፈፃፀም ነው። ፖሊሲ ከህልም የሚለይበት ዋነኛው መስፈርት ስለሚፈፀም ነው። ስለዚህ አንድ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ችግር ካጋጠመው ፖሊሲው ትክክል አይደለም ማለት ነው። ግን የመለስ ልጆች ‘ፖሊሲው ስህተት ነው’ ብለው የማጋለጥ ዓቅሙና ድፍረቱስ አላቸው? አይመስለኝም። ምክንያቱም ፖሊሲው የመለስ ነው። ፖሊሲው ስህተት እንደሆነ መናገር ማለት መለስ እንደሚሳሳት መመስከር ነው። መለስ ደግሞ ፈጣሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ከነ ስህተቱ ‘የመለስ ሌጋሲ ወይ ራእይ’ እያሉ የመለስን የተሳሳተ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማስቀጠል የሚባዝኑ።

ከኢህአዴግ አባላት የምስማማበት ነጥብ አለኝ፤ መለስ ሁለመናቸው ነው። እሱ የተናገረውን ያደርጋሉ፣ ይፈፅማሉ። ከነሱ ጋር የምስማማበት ነጥብ ይሄ ነው። ይሄንን ነጥብ ትርጓሜ እንስጠው።

የኢህአዴግ አባላት (እነሱ ራሳቸው እንደሚነግሩን) መለስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዕይታ ምንጫቸው ነው። አዎ! ነው። ይህ ማለት አባላቱ ምን መስራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው መለስ ይነግራቸው ነበር ማለት ነው። እነሱም ‘የታላቁ ባለራእይ መሪ’ ትእዛዞች ተቀብለው ይተገብሩ ነበር ማለት ነው።

የመለስና የአባላቱ ግንኙነት እንዲህ ከነበረ መለስ dictate ያደርጋቸው ነበር ማለት ነው። በእንግሊዝኛው አጠራር ሌሎችን dictate የሚያደርግ መሪ Dictator ይባላል። ስለዚህ ከተግባራዊ ትርጓሜው ተነስተን መለስን ስንገልፀው Dictator ነበር ማለት ነው። “Dictator’ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ‘አምባገነን’ (ብትግርኛ ‘ዉልቀ መላኺ’) የሚል ትርጓሜ ይይዛል። ስለዚህ ‘ሁሉም ወይም አብዛኞቹ የፓርቲው ስራዎች የመለስ ነበሩ’ በሚል ከተስማማን ‘መለስ አምባገነን ነበር’ በሚልም መስማማት ይኖርብናል።

እኔ ‘መለስ አምባገነን ነበር’ ሲል ‘የሁሉንም አድራጊ እሱ ነበር’ እያልኩኝ ነው። እናንተም በራሳቹሁ ሚድያና አንደበት ተመሳሳይ ነገር እየነገራችሁን ነው። ስለዚህ ሓሳባችን አንድ ነው። ተስማምተናል። በመለስ ስራና ስያሜ ላይ ልዩነት የለንም።

(ስለ መለስ ላለመፃፍ ዕቅድ የነበረኝ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ግን ስለሱ እያስታወሱ አስቸገሩኝ)

በወያኔ “ያደገችዋን” ኢትዮጵያ ዓለም እንዴ ያያታል?- ዶ/ር ዘላለም ተክሉ

$
0
0

ነሐሴ 25 2013

በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢሳት የቀረበውን “ የእሁድ ወግ” ፕሮግራም ሳዳምጥ ነበር:: በዚሁ ፕሮግራም ከቀረቡት ዋና ዋና መወያያ ርዕሶች ውስጥ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ አጎናጸፉት እየተባለ ስለሚደሰኮረው ዕድገት የተሰጡት አስተያየቶች ትኩረቴን ስበውኝ ነበር:: በተለይ ሰውዬው (ከሳቸው የተማርኩት አባባል ስለሆነ ይቅርታ) ህዝቡን ጥጋብ በጥጋብ አደረጉት፣ ብዙ ሃብታም ገበሬዎችን ፈጠሩ፣ሚሊዮኖችን ከድህነት አረንቋ አላቀቁ ስለሚባለው አቶ ሲሳይ አጌና የሰጠው ምላሽ በጥሩ ትንተና የተደገፈ መሆኑ ያስደሰተኝ ሲሆን በዚች ትንሽ መጣጥፍ የበለጠ ማጠናከሪያ በመስጠት ፕሮፓጋንዳውን ለመሞገትና ምስኪኑ ህዝባችንም እውነታውን ራሱ ፈትሾ እውነቱን እንዲያውቅ ፈለኩ::
MDG : Ethiopia : Meles Zenawiአቶ ሲሳይ ሙግቱን (argument) ሲያስረዳ፣ በእውነት የፕሮፓጋንዳ ማሽኖቹ በተደጋጋሚ እደሚነግሩን በእርሳቸው መጀን ኢኮኖሚያችን አድጎዋል ከተባለ ከ 80 በመቶ በላይ የሆነው ገበሬው ህዝባችን ኢኮኖሚው አድጓል ማለት ነው:: የገበሬዎች ገቢ ደግሞ አደገ ከተባለ ያ ሊሆን የቻለው ያመረቱቱትን ብዙ ምርት ወደገበያ አውጥተው ሸጠው ጥሩ ገቢ ሰብስበዋል ማለት ነው:: እነሱ ብዙ የእርሻ ምርት ወደ ሽያጭ አመጡ ማለት ደግሞ በየከተሞቹ በኢንዱትሪና አገልግሎት ዘርፎች እየሰራ የሚተዳደራው ህዝባችን ከበቂ በላይ የምግብ አቅርቦት አግኝቷል ማለት ነው:: ገበሬዎች ገቢያቸው አደገ ማለት ደግሞ ከከተማው ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች የሚመረቱትን ምርቶች የመግዛት ፍላጎታቸውና አቅማቸው ጨምሩዋል ማለት ነው:: የነዚህ ዘርፎች መነቃቃት ደግሞ ምርታቸውን የበለጠ እንዲያድግ ያበረታታዋል የከተሜውም ገቢ ይጨምራል ማለት ነው:: የምግብና የኢንዱስትሪ ውጤቶች ምርት አቅርቦት (supply) ከፍላጎት (demand) በላይ ከሆነ ዋጋ አይጨምርም:: ወይም ደግሞ የምርት ፍላጎት እና አቅርቦት ከገቢ መጨመር ጋር በትይዩ (parallel) ሊያድጉ ከቻሉ በዋጋ ላይ ምንም ለውጥ አያመጡም ማለት ነው:: በአሁኗ ኢትዮጵያ ያለው እውነታ በተቃራኒው ስለመሆኑ ግን ይህን ሁሉ ትንታኔ ሳያስፈልገው አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ እንኳን ሊያስራዳው የሚችለው ነው:: እየኖረበት ስላለው ድህነቱ ለመናገር የሮኬት ሳይንቲስት መሆን አያስፈልግምና::
የከተሜው ህዝብ የሚበላውን ዳቦና እንጀራ ከዛሬ 5 እና 6 ዓመት በፊት ከሚገዛበት ከ 4 እስከ 5 እጥፍ በላይ የሚሸምትበትና ከአለፈው ዓመት እንኳን በ 20 በመቶ ጭማሬ የሚሻማበት፣ የገጠሩ ህዝባችን የሚያስፈልገውን ጨው፣ስኳር፣ ዘይትና ለእርሻ የሚያስፈልጉት ማዳበሪያና ማራሻ መሳሪያዎች በተመሳሳይ ጭማሪ ዋጋ እየተንገታገተ የሚገዛበት ዋናው ምክንያት ገቢው “በአርቆ አሳቢውና ልማታዊው” መሪ አስተዋጽዖ በማደጉ ሳይሆን በተዝራከረከው፣ በጠባብ ብሄረተኛው፣ በሙናስና በተጨማለቀውና በአድሎአዊ አመራር ድክመት ምክንያት ከፍተኛ የምርት ፍላጎትና አቅርቦት ክፍተት (Supply and Demand Gap) በመፈጠሩ ነው:: ይህም ክፍተት የምርትና የሃብት እጥረትን (scarcity) ፈጥሯል:: ይህ እጥረትም ለዋጋ ንረቱ ዋነኛ አስተዋጽዎ አድርጓል:: ስለዚህ የምግብና የኢንዱስትሪ ምርት እጥረት በሰፈነበት አንጻር ዕድገት አለ ብሎ ማናፋት “እናንተ ዓይናችሁን ጨፍኑ እኔ እንደፈለገኝ ላፏልል” እንደማለት ይቆጠራል::
የዓለም ባንክና ዓለምአቀፍ የገንዘብ ድርጅት የአገራችን ኢኮኖሚ “እንዳደገ” ቢነግሩን ሊደንቀን አይገባም:: እነዚህ ድርጅቶች በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ወያኔ የሚሰጣቸውን መረጃ (data) ብቻ እየወሰዱ መልሰው እንደሚነግሩን መገንዘብ ይገባናል:: አንደኛው ሁለቱም የሚታዘዙት በአሜሪካ መንግስት ፍላጎት ነው:: አሜሪካ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የነዚህን ድርጅቶች በጀት የምትች ስለሆነች በድርጅቶቹ ህልውናና በሃላፊዎቹ ቅጥርና ዕድገት ላይ ወሳኝ ሚና አላት:: አሜሪካ ደግሞ አሸባሪነትን ለመዋጋት ወያኔን እንደ ፈለገች ስለምትጠቀምበት እሱን የሚነካባትን ሁሉ ድራሹን ማጥፋት ትችላላች:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔም ይህን ግንኙነትና መስተጋብር ስለሚያውቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲህ ወይም የምታቀርበው የዕድገት መረጃህ ትክክል አይደለም ብለው የሚከራከሩ የባንኮቹ ሃላፊዎች ካሉ ከጣፋጩ ሥራቸው እንዲሰናበቱ ሊያደርግ ይችላል:: ስለዚህ ባንኮቹ ጉዳዩን ቢያውቁት እንኳን የተሰጣቸውን መረጃ ይዘው ከማዳረስ ሌላ ምንም አማራጭ የላቸው::
ለነገሩ ይህ የሚነገረን የተቀቀለና የበሰለ የዕድገት መረጃ ለጂኦፖለቲካዊ ፍጆታ ከመዋል በስተቀር ዓለም አሁንም ጠንቅቆ የሚያውቀን እስካሁን በመከራ፣ በድህነት፣ በበሽታ እንደምንማቅቅ ነው:: ይህንንም ያልኩበት ከሰሞኑ ከሥራዬ ጋር በተያያዘ አንድ የ Health Economics መጽሃፍ ሳነብ አንድ አሳዛኝ መረጃ ስላየሁ ነው:: በመጽሃፉ የኢትዮጵያ ምሳሌ የቀረበው እጥረት (scarcity) የተባለውን የኢኮኖሚ ንድፈ ሃሳብ (theory) በተግባር (Application) ለማስረዳት ታስቦ ነበር:: በዚህ ንድፈሃሳብ መሰረት የሃብት እጥረት የትም ሃገር አለ፣ በደሃውም በሃብታሙ ውስጥም አለ ይልና ነገር ግን ከእጥራትም እውነተኛ እጥረት አለ (There is scarcity and there is real scarcity) ያም በኢትዮጵያና በባንግላዴሽ በከፋ ሁኔታ ይታያል ብሎ ከነዝርዝር መረጃው ያስረዳል::

ምንጭ: Folland, S., Goodman, A. G. and M. Stano (2013). The Economics of Health and Health Care. (7th edition). New Jersey: Pearson Education, Inc.
ይህ መረጃ በተጠቀሰው መጽሃፍ ላይ የቀረበው በአለም ዙሪያ ቢዝነስን ለሚማሩና ቢዝነስን ለሚሰሩ ሁሉ ያሁንዋን ኢትዮጵያ ከሌላ ሃገራት ጋር ሲነጻጸር እንዴት ማየት እንዳለባቸው ለማስረዳት ነው:: በሰንጠረዡ እንደታየው በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አሜሪካና ጀርመኒ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸው ከራሻና ብራዚል ከ3 እስከ 5 ጊዜ እጥፍ፣ከቻይናና አልባኒያ ከ 6 እስከ 8 ጊዜ እጥፍ፣ ከባንግላዴሽና ኢትዮጵያ ከ 83 እስከ 133 ጊዜ እጥፍ እንደሆነ፣ በዚህም ምክንያት ጤንነታቸውን ለመጠበቅ የሚያወጡት ወጪ ከፍተኛ እንደሆነ፣ስለዚህም በበሽታ የመጠቃት ዕድላቸውና የህጻናት ሞት መጠናቸው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ሲያሳይ:: ኢትዮጵያን ደግሞ በዝቅተኛና እጥረት (በተሞላበት በቀን ከ 1 ዶላር በታች ገቢ) እንኳን ለጤንነታቸው በቂ ሊመድቡ የዕለት ምግብ ፍላጎታቸውን እንኳን ሊያሟሉ ባላመቻላቸው በቲቢ (Tuberculosis) በከፍተኛ ደረጃ ለመጠቃትና ለየህጻናት ሞት መዳረጋቸውንና በዚህ የተነሳ ረጅም ዕድሜ የመኖራቸው ዕድል ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል:: እንግዲህ ያሁንዋን ኢትዮጵያ ዓለም የሚያያት እንደዚህ ነው:: የዓለም ባንክ ሆነ የአሜሪካ መንግስት መጥቶ ይህ የጠላት ወሬ ነው ወይም የአክራሪ ተቃዋሚዎች የተሳሳተ መረጃ ነው ሊል አይችልም፣ወይም አይሞክርም::
ወያኔ የፈለገውን ያክል ያምታታ ወይም ረጂ ሃገራትን ለማባበል የፈለገውን ዓይነት የማክሮ ኢኮኖሚ (Macroeconomic) ማስተካከያ እርምጃ ይውሰድ፣ ነገር ግን ምርት እንዲጨምር ማድረግ ካልቻለና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚፈጥር መዋቅራዊ ለውጥ ካላደረገ የሚደሰኩረውን ዕድገት በእውን ሊያሳይ በጭራሽ አይችልም:: ዳሩ የሥርዓቱ ይሄ ሁሉ ፕሮፓጋዳ ከምሩ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ዕድገትን ለማጎናጸፍ ሳይሆን በፖለቲካውና በሰባዊ መብት ረገድ የሚሰራውን ግፍ ለመሸፈንና ይህን የዝርፊያና አንድ ብሄርን ብቻ በማበልጸግ አቅጣጫ የተያያዘውን ጉዞ እንዳይሰናከል የሚከላከልበት ዋነኛ መሣሪያው ስለሆነ ነው:: ከነሱ እጅ እውነተኛ ዕድገት ይመጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ስንፍናና ፈሪነትም ጭምር ነው:: መፍትሄው ከቅርብ ወራት ወዲህ እየተጠናከረ የመጣውን የለውጥ እንቅስቃሴ አጣናክሮ በመቀጠል አገዛዙንና ሥርዓቱ መቀየር ብቻ ነው:: ይህ ብቻ ሲሆን ነው ዓለም አሁን የሚያውቃት መከረኛዋና ችግረኛዋ ኢትዮጵያ ልትለወጥ የምትችለው:: የፕሮፓጋዳ ዕድገት ግን ዘበት ብቻ ነው!!!

አገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!!

በትዞራለች …ትዞራለች …ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች !

$
0
0

dudi
በአዕምሮ ሁከት የተለከፈችው እህት በጅዳ!
አንድ ወዳጀ መሃመድያ ተብሎ በሚጠራው የጅዳ ከፍል ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህር ቤት አካባቢ ይህችን በፎቶው ላይ የምታዩዋትን እህት አግኝቶ ሊያነጋግራት ቢሞክርም ፈቃደኛ አልነበረችም። ከየት ነው የመጣሽ ? ስትባል” ከመቀለ ” ከማለት ባለፈ ስሟንና የሆነችውን አትናገርም ። ብዙ ሊያግባባት ሞክሮ ያልተሳካለት ይህ ወዳጀ ይህች እህት ያደፈና የተቀደደ ጥቁር “አባያ” ለብሳና መናኛ ነጠላ ጫማ የተጫማችው እህት የአዕምሮ ሁከት እንዳለባት የተረዳው ብዙ ለማነጋገር ሞክሮ በሰጠችው አንዳንድ ምላሽ እንደሆነ ገልጾልኛል! ልጁን ትምህርት ቤት ሊያስመዘግብ በሔደበት አጋጣሚ በጠራራው ሜዳ ስትንከራተት በማየቱና ምንም መርዳት ባለመቻሉ ያዘነው ወዳጀን መረጃ ይዠ የጅዳን ቆንስል ሃላፊዎች ስልክ በመደዎል ይህችን እህት በመጠለያው አምጥተው ሌላው ቢቀር ካሉት የአዕምሮ በሽተኞች ጋር ቀላቅለው ከመኪና እና ከመሳሰሉት አደጋዎች አንዳትጋለጥ ይሰበስቧት ዘንድ ለማሳወቅ ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም!
አንድ ሌላ ወዳጀ ከትናነት በስቲያ የዚህችን እህት አሁን ድረስ በአካባቢው መኖርና ዝም ብላ እንደምትዞር ነገረኝና ወዳለችበት አካባቢ ሔጀ በአካል ለማነጋገር ሞክሬ ነበር ። በጠራራው ጸሃይ የውሃ ፕላስቲክ ባንድ እጇ በሌላ እጇ ፊስታል አንጠልጥላ እየሳቀች እና እየተኮሳተረች ክው ክው እያለች የምትራመደው እህት አገኘኋት። ብዙ ከተከትልኳት በኋላ አረፍ ስትል ጠብቄ አማርኛ ትችያለሸ ? አልኳት “ግደፈኒ” አለችኝ ፊቷን ዘወር እያደረገች! ለማግባባትና ለማቅረብ ሞከርኩ ፣ ልታሰቀርበኝ አልቻለችም! ብዙ ተከተልኳት! … ትዞራለች …ትዞራለች …ሲደክማት ታርፈና አሁንም ትዞራለች ! በቃ ! እንዲህ ሆናለች …
ዛሬም እዚያው አካባቢ እየዞረች እንደምትገኝ ወደ ትምህርት ቤት ለጉዳዩ የሔደ ወንድም አግኝቷት በስልክ ገልጾልኛል። ስትንከራተት አይቶ ሊረዳት የፈለገው ይህ ወንድም እሱም ሆነ ያየውን የዚህች እህት አበሳ ያሳያቸው የትምህርት ቤቱ ሴት ኢትዮጵያውያን መምህራን ተከትለው ሊያነጋግሯትና ሊረዷት ቢፈልጉም ፈቃደኛ ባለመሆኗ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ እያዘን ካነሳው ፎቶ ጭምር ልኮልኛል! ዛሬም ይህን መረጃ ለማቀበል ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ ቆንስል ጀኔራል ዘነበ ከበደ እና ቆንስል ሙንትሃ ስልክ ደውየ የነበረ ቢሆንም ሊመልሱልኝ ግን አልቻሉም! ይህ በእንዲህ እንዳለ በተፈናቃይ ሰራተኞች ዙሪያ ጥናት ለማድረግ በአንባሳደር ውብሸት የተመራ ቡድን ዛሬም በጅዳ ከቆንስል ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ መሆኑን ታውቋል።
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

ማን ይናገር የነበረ….. የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ!

$
0
0
(በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)
           ዕድል አጋጣሚ፣ ለሰው ልጅ ስትመጣ፣
           መልካምና ክፉ፣ አላት ሁለት ጣጣ !!!
           (ከበደ ሚካኤል፣ “የዕውቀት ብልጭታ”፤)
Man Yinager Yenebere... (Yetahisasu Girgir Ena Mezezu)የታኅሣሥ 1953ቱን (ዓ.ም) “ሥዒረ-መንግሥት” ዋዜማ፣ መባቻና ማግስት ያካተተ መጽሐፍ ታትሟል፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ፣ አቶ ብርሃኑ አስረስ ሲሆኑ፣ አሳታሚው ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ፣ ማን ይናገር የነበረ…..፣ የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ የሚሰኝ ሲሆን፣በ2005 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ ታትሟል፡፡  ይኼንን የሚያህል ቁምነገረኛ መጽሐፍ በ144.00 (አንድ መቶ አርባ አራት) ብር ገዝቶ ቁምነገር መዝረፍ ያጓጓል፡፡ ገጽ በገጽ ሲገልጡት ከ እሰከም ስለሌለው ነፍስን በሃሴት ያጭራል፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ አንበውት የማያልቅ ሃተታ የያዘ ድንቅ ድርሳን (Masterpiece) ነው፡፡ ድርሳኑን ደጋግሞ ማንበብ እውነትን የበለጠ ማወቅ ነው፡፡ “ድንቅ የሆነ ድርሳን” ነው ያልኩት ለማጋነን አይደለም፡፡ በእርግጥም፣ ውብ ነው! እጹብ ድንቅ ነው!….
ይኼው ልንገመግመው የመረጥነው መጽሐፍ እጅግ ከፍ ያለ የዋጋ የሚሰጠው፤ የነገረ-መረጃ (Intelegenece)፣ የወታደራዊ፣ የፖለቲካ፣ የሕግ፣ የታሪክ፣ የንግድ፣ የማህበራዊ ሳይንስና የግብረ-ሠናይ ይዘት ያለው ሥራ ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ በሀገራችን የነገረ-መረጃ (የስለላ-ነክነት) ያላቸው መጽሐፍት ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡ ያሉትም ትቂት መጽሐፍት ቢሆኑ የትርጉም ሥራዎች ናቸው፡፡ ለዚያውም ደግሞ የአቶ ማሞ ውድነህ ጥረቶች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡
አንደኛ፣ የደኅንነት (የመረጃ) መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎቹ በተከታታይ ሕይወታቸው በምስጢራዊ አኳኋን በማለፉና የሚያውቁትን ምስጢራዊ መረጃ ሊዘግቡት ባለመቻላቸው ነው፡፡ በጃንሆይ ዘመን የነበሩት የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሃላፊዎች በሙሉ በሰው እጅ አልፈዋል፡፡ አቶ መኮንን ሀብተ ወልድ ዋናው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሌ/ኮለኔል ወርቅነህ ገበየሁም ቢሆን ተታኩሶ ነው የሞተው፡፡ ኮ/ል ዳንኤል ደግሞ በሻለቃ ዮሐንስ አራት ኪሎ ቤተ-መንግሥት ውስጥ (ከነሰናይ ልኬ ጋር አንድ ቀን  ነው) የተገደለው፡፡ የደርግ  ዘመን፣ ለረጅም ጊዜያት የደኅንነትና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ኮ/ል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴም ቢሆን፣ ከ21 ዓመታት እስር በኋላ ሊለቀቅ ቀናት ሲቀሩት መሞቱ ተሰማ፡፡ ከርሱም ቀጥሎ ኃላፊነቱን የተቆናጠጠው “ተጋዳላይ” ክንፈ ገ/መድኅን በግንቦት 4/1993 ዓ.ም በጎልፍ ክለብ ተገደለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ክስተቶች ተደማምረው፣ የኢትዮጵያን የደህንነት መሥሪያ ቤት የሚመለከቱ መረጃዎች ከኃላፊዎቹ ጋር ተቀበሩ፡፡ የኃላፊዎቹንም ፍጻሜ ያዩት የመረጃ መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች “ጎመን በጤና” ብለው እንዲታቀቡ ጥላውን አጠላባቸው፡፡
ሁለተኛውም ምክንያት ከባህላችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ በብዙዎቹ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች አኗኗር ውስጥ “አይተኻልን?-አላየኹም!” ሰምተኻልን?-አልሰማኹም!” በል የሚል የመረጃና የደኅንነት መግቻ ጥብቅ ሕገ-ድንብ አለ፡፡ ይህ ሕገ-ደንብ ከማንም በላይ የሚጠብቀው የተጠያቂውን ግለሰብ ደኅንነት ነው፡፡ “ሰውን ማመን ቀብሮ ነው!” ያለችውን ቀበሮ ኢትዮጵያዊት ሳትሆን አትቀርም፡፡ “…ልቡ ዘጠኝ፣ ሰምንቱን ሸሽጎ አንዱን አጫወተኝ!” የተባለው ተረት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሳይሠራ አይቀርም፡፡ ያም ባይሆን፣ ብዙዎቹ “ምስጢር፣ የባቄላ ወፍጮ አይደለም” ብለውም የሚያምኑ በመሆናቸው፣ “አይተው-ላለማየትና ሰምተውም-ላለመስማት” ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም የተነሣ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለበርካታ ዘመናት ያህል፣ ምስጢር-ጠባቂነት የግለሰቦች ባህሪ ከመሆንም አልፎ የወል ባህልም ለመሆን ችሏል፡፡
ወደዋናው ትኩረታችን እንመልስ፡፡….“ማን ይናገር የነበረ…..የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”፣ የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ ዋናው የትምህርት ጥናታቸው ኤኮኖሚክስ ነው፡፡ በ1951 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የኤኮኖሚክስ ዲግሪያቸውን በኦክስቴንሽን እያጠኑ ሳለ ከሻለቃ ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተዋወቁ፡፡ ሁኔታውን እንዲህ ያስታውሱታል፣ “በወቅቱ የምሰራው በአሜሪካን የማስታወቂያ ክፍል (USIS) ነበር፡፡ ደቡብ የመን ደርሶ የመጣውን ጓደኛዬን አዲስ መጽሐፍ ገዝቶ አምጥቶልኝ ነበር፡፡  በሥራ ቦታዬ ላይ ፋታ ሳገኝ ለማንበብ ከጽሕፈት ጠረንጴዛዬ ላይ አስቀምጠው ነበር፡፡….የመሥሪያ ቤቱ ዳይሬክተር… በአንባቢነቴ ይደነቅ ነበርና ጠጋ ብሎ አርእስቱን ቢመለከት “ዳስ ካፒታል” የሚል ሆኖ ያገኘዋል፡፡” በዚህም ሳቢያ አቶ ብርሃኑ በኮሚኒስትነት ተጠርጥረው ወደሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ይወሰዳሉ፤ ሻለቃ ወርቅነህም ዘንድ ይቀርባሉ (ገጽ-18)፡፡ (መግቢያችን ላይ የተጠቀምናት፣ “እድል አጋጣሚ፣ ለሰው ልጅ ስትመጣ” የምትለው የከበደ ሚካኤል ስንኝ በትክክል ደርሶባቸዋል፡፡) ደራሲው ከተጠረጠሩበትም የኮሚኒዝም ስርፀት ጣጣ ነፃ ቢወጡም ቅሉ፤ ወደUSIS ተመልሰው እንዳይሠሩ ይደረጋሉ፡፡ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ፣ ከኤኮኖሚክስ ጥናታቸው ልቆ የነገረ-መረጃ ሥራቸው ጨምሯል (ገጽ-19)፡፡
“መረጃ አይናቅም፤ አይደነቅም!” በሚለው መሠረታዊ የነገረ-መረጃ ንድፈ-ሃሳብ የሚያምኑት ደራሲ ብርሃኑ አስረስ፣ ሴራውን (መፈንቅለ-መንግሥቱን)ና በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩትን የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የአስተዳደራዊ ኩነቶች በገለልተኛነት ለመተንተን ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ ነው፡፡ የስዒረ-መንግሥቱ ጠንሳሾች፣ “በህዝቡ ላይ የመታየውን የፍርድ ጉድለት፣ የአስተዳደር በደልና የኤኮኖሚ ድቀት እያስጨነቃቸውና ሰላም እየነሳቸው ስለሄደ፣ አማራጭ መፈለግ ግድ እየሆነባቸው መጣ” ይላሉ(ገጽ፣ 151)፡፡ ነገር ግን፣ በኅዳር 29/1953 ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ በሌ/ኮሎኔል ወርቅነህ በኩል የላኳት ቴሌግራም ያለጊዜው እሳት መጫሯን ያትታሉ (ገጽ-151/2)፡፡
በገጽ 81 እና 82 ላይ እንደገለጹት ሁሉ፣ ሻለቃ ወርቅነህን ለለውጥና ለመሻሻል ያነሳሱትን አምስት ምክንያቶች ዘርዝረዋል፡፡ እነርሱም በኮሪያ ዘመቻና በቶኪዮና ሴኡል የህክምና ጉብኝቱ እንዲሁም በሲዊድን ቆይታው ወቅት በገሃድ ያያቸው መሆናቸውን ያብራራሉ፡፡ ከግርማዊነታቸውም ጋር በተለያዩ አገሮች ሲሄድ ባወቃቸው ኩነቶች ተገፋፍቶ እንደሆነም ያወሳሉ፡፡ የኢትዮጵያንና የሕዝቧንም እድገትና ብልጽግና ያጫጨው “የመሬት ስሪት/ፖሊሲው” ጉዳይ መሆኑን ሌ/ኮሎኔል ወርቅነህን ዋቢ አድርገው ያትታሉ (ገጽ-91/2)፡፡ ኮ/ል ወርቅነህ ባቀረበው የመሬት ስሪት/ፖሊሲው ጥናታዊ ማስታወሻ እንደጠቀሰው፣ “የመሬት ይዞታው ጉዳይ አንደጋንግሪን እየገዘፈ መጥቶ መንግሥትን የሚያናውጥ ሕዝብንም የሚያፋጅ ቀውስ እንደሚያመጣ” ማስረዳቱን ያስታውሳሉ፡፡ በአሁኑም ጊዜ፣ “በዓለም ላይ ርስት የለሽ ሕዝብ ያለባት ብቸኛ አገር (ከኮሚኒስት አገሮች በቀር) ኢትዮጵያ ሳትሆን አትቀርም፤” ይላሉ(ገጽ-92)፡፡ አያይዘውም፣ “ሰው በሰውነቱ እኩል ሆኖ የተፈጠረ ስለሆነ፣ የአገሩ የተፈጥሮ ሀብት ከሆነው መሬት ድርሻ ሊኖራ ይገባል፤….” የሚል አቋም የነበራቸውን አፄ ኢያሱ አድያምሰገድን የመሬት ስሪት ደንብ ያቀርባሉ (ገጽ-121)፡፡ አፄ ምሊልክም አዲስ አበባን ሲቆረቁሩ ይዘውት የነበረውን ፍትሀዊ የመሬት ስሪት ደንብ ያወሱና፣ የምኒልክ ሹማምንት ግን “ከሕዝብ ተለይተው መሬት ለነርሱ ብቻ እንደተፈጠረ ወደ ማድረጉ አዘነበሉና ራሳቸውን ብቻ በማበልፀግ የማኅበራዊና የኤኮኖሚያዊ ኑሮውን ደረጃ ልዩነት አሰፉት፤” ሲሉ ይወቅሳሉ (ገጽ-125)::
በመጨረሻም፣ ከበድ ያለና ጥንቃቄን የሚሻ ትንታኔ ለአንባቢያኑ ያቀርባሉ፡፡ “የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ድልድል እንዳጠና ሌ/ኮሎኔል ወርቅነህና አቶ ገርማሜ ንዋይ አዘዙኝ” ይላሉ (ገጽ-119)፡፡ ገርማሜ የኢትዮጵያን የመሬት ወረራ ያመሳሰለው ለመጀመሪያ ዲግሪው መመረቂያ ጽሑፉ ሲያዘጋጅ ካጠናው ከኬንያው የ“ማው ማው” ንቅናቄ ጋር ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከላይ የተገለጹትን የአፄ ኢያሱንና የአፄ ምኒልክን የመሬት ስሪት ድልድል ሲረዳ፣ “ድሮ ከነበረው ስሜቱ መለስ” ብሎ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ ሆኖም፣ “ገርማሜ ነዋይ፣ እነዚህ ከመሬት ባገኙት ኤኮኖሚ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂቶች፣ የፖለቲካ ስልጣኑንም በመጨበጣቸው በሕዝቡ ላይ ይደርስ ለነበረው የአስተዳደር በደልና የፍትሕ መጓደል በዋናነት ተጠያቂ አድርጎ ያቀርባቸው” እንደነበርም አትተዋል (ገጽ-126ና 139)፡፡ በተመሳሳይ ኹኔታም፣ በገርማሜ ታላቅ ወንድም በብ/ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ ይመራ የነበረውንም የክብር ዘበኛ አምርሮ ይጠላው እንደነበር በገጽ-266 ላይ ዘግበዋል፡፡ ገርማሜ እንዲህ አለ፤ “የክብር ዘበኛ… በመፍረሱ ደስ ብሎኛል፡፡…. ያ ሠራዊት ጀግና ነው፡፡ የታወቀ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የፈለገውን ነገር ማድረግም ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን፣ በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ያለው ታማኝነት ከፍ ያለ ስለሆነ ሳይዋጋ ቀረ፡፡…. ሠራዊቱ አንድ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተነሳ ሲባል ሄዶ ያፍናል፡፡ ስለዚህ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሆኑ ማንኛውም ሰው (ድርጅት) በተቃውሞ መንቀሳቀስ ወይም የልቡን ተናግሮ ሀሳቡን መግለጽ ስላልቻለ፣ ይህ ሠራዊት ከተበተነ በኋላ ለተቃውሞ እንቅስቃሴ ይነሣሣል፡፡ ዓላማውም ውጤት እንዲያገኝ ይረዳል….፡፡” ከአራት ዓመታትም በኋላ ገርማሜ ነዋይም እንደተነበየው ሆነ፡፡ በ1957 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች አመጽ  እየበረታ ሄደ፡፡
አቶ ብርሃኑ፣ ለመጽሐፋቸው ዋና መነሻ የሆኗቸውን ሃሳቦች ያገኙት በድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆናቸው ነው፡፡ ደራሲው፣ እዚህም-እዚያም ተሰባጥረው የሚገኙትን የ1953ቱን ስዒረ-መንግሥት መነሻና መድረሻ “ማን ይናገር?…የነበረ!” እና “የታኅሣሡ ግርግር”ባሉት ሃይለ-ሃሳብ አደላዳይነት በፈርጅ-በፈርጁ ሊደለድሉት ጥረዋል፡፡ ሙከራቸውም ፈሩን ያለቀቀ ነበር፡፡…. በአስተሳሰባቸውና በአቀራረባቸውም የገለልተኛነት ስፍራን ለመውሰድ ተግተዋል፡፡ በመፈንቅለ-መንግሥቱ ሴራ ተሳትፏቸው የተነሣ ለአምስት ዓመታት ያህል ቢታሰሩም፣ የእልህና የስሜታዊነት ጥገኛ ለመሆን አልፈለጉም፡፡ ከዚህም ከዚያም ብለው ጠቃሚ የሆኑትን ሃሳቦችና ነጥቦች ተፈላልገው በማጠናቀር የዐይን እማኞችን ሃቲት ለማካተት ተግተዋል፡፡ ይሁንና፣ ምንም  የገለልተኛነት መንገድን ለመውሰድ ቢሞከሩ እንኳን፣ በአለቃቸው/በወዳጃቸው በሌ/ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ  ተጽእኖ ስር ከመውደቅ አላመለጡም፡፡ “የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች” የሚለው ምዕራፍ ሥር “ወርቅነህ ገበየሁ (?-1953)” የሚለው ንዑስ-ርዕስ የደራሲውን የሃሳብ አካሄድና የአስተሳሰብ ፈለግ በይበልጥ የሚመሰክር ነው፡፡ ደራሲው ንጉሠ ነገሥቱንና ሌሎችንም ሰዎች የሚያዩት በእነርሱ ዐይን ነው፡፡ ለአብነትም ያህል ገጽ-85፣ ገጽ-92፣ ገጽ-102፣ ገጽ-111/2፣ ይጠቀሳሉ፡፡ በገጽ-145ና ገጽ-342 ያሉትን አተያዮች ደግሞ በብ/ጄኔራል መኮንን ደነቀና በመቶ አ/ በቀለ አናሲሞስ በኩል ነው ያስተላለፉት፡፡ ይኼንንም ያደረጉት ይሆነኝ ብለው ነው፤ ከስሜታዊነት ለመራቅ፡፡
በተጨማሪም፣ ደራሲው በመፈንቅለ መንግሥቱ ተሳታፊ የነበሩትን ዋና ዋና ተዋንያን እስር ቤት ሳሉና ከወህኒ ቤትም ከወጡ በኋላ ተከታትለው በማናገር የተበታተኑትን ምስጢራዊ መረጃዎች አጠናቅረውና አስፋፍተው በመፃፍ አንድ ጉልህ-ፈር ቀደዋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲያም፣ የተለያዩ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የፖለቲካ ሳይንስ አጥኚዎች፣ የሥነ-ጽሑፍና የትውን ጥበባት ቀማሪዎች ስለጉዳዩ በየፊናቸው ለመተርጎም የሚያስችላቸውን ግብዓት አግኝተዋል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ ምስጢራዊ ሰነዶችና መረጃዎችም እንደምን ሊገኙ እንደሚችሉ መላና ዘዴውን ገልጠዋል፡፡ ለውጥ እንዴት ያለነውጥ ሊመጣ እንደሚችል ተሞክሯቸውንም አካተዋል፡፡ በምዕራፍ 1ና በምዕራፍ 9 ስርም ያሉት ሁለቱ ሃተታዎች ይኼንን የደራሲውን የሕይወት ተሞክሮና ዕጣ-ፈንታ ይተርካሉ፡፡ የሚደንቀው ነገር፣ ደራሲው “እኔ-በዚህ ወጥቼ፣ እኔ በዚህ ወርጄ!” ከሚለው የንፉግ ትችት የራቁ መሆናቸው ነው፡፡
በታኅሣሥ 1953 ዓ.ም የተደረገውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከትሎም፣ በስድስት ኪሎ ገነተ-ልዑል ቤተ-መንግሥት አረንጓዴው ሳሎን ስለተገደሉት አስራ አምስት(15) ባለሥልጣናት አሟሟት ልከኛውን መረጃ ይሠጣሉ፡፡ ግድያውን የመራው ገርማሜ ነዋይ እንደነበረና ዋነኛው ነፍሰ-በላም እጩ መኮንን ነጋሽ ድንበሩ መሆኑን ይገልፃሉ (ገጽ-258 እና 266 ይመልከቱ፡፡) ብ/ጄነራል መንግሥቱ ነዋይ፣ “ኧረ ለመሆኑ ሚኒስትሮቹ እንዴት ሆኑ? ፈታችኋቸው? ልዑል ጌታዬስ? (አልጋ ወራሹስ) ማለታቸው ነው፤” ብለው ሲጠይቁ፣ ገርማሜ “እሳቸው እዛው ናቸው፡፡ ለሚኒስትሮቹ ግን የሞት ቅጣት ሰጥተናል፤” እንዳለ ይተርካሉ፡፡ የመጽሐፉም አንኳር ነጥብ ያለው እዚሁ ላይ ነው፡፡ በኮሚኒዝም ስርፀት ከሁለተኛው የእጩ መኮንንነት ኮርስ የተቀነሰው መርሻ ድንበሩና በኮሚኒስትነት ከወላይታ አውራጃ ገዢነቱ የተነሳው ገርማሜ ነዋይ፣ ዜጎችን ያለፍርድ በመግደል ለነሻለቃ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አርዓያ ሆኑ፡፡ ለሌሎችም “በዲሞክራሲ ካባ ስር፣ የማርክሲዝምና ሌኒኒዝምን ጃኬት” ለለበሱ ነፍሰ ገዳዮች አጽድቆት ሰጡ፡፡
ማጠቃለያ፤
“ማን ይናገር የነበረ…..የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”፣ የተሰኘው መጽሐፍ እጅግ የሚደነቅ የቋንቋ

Addis GudayVol 7. No. 178. Addis Ababa. (1)አጠቃቀምና የቃላት አሰካክን የተከተለ ነው፡፡ አልፎ-አልፎ የቀበልኛ ቃላትን ቢጠቀምም እንኳ፣ በግርጌ ማስታወሻ አማካይነት “ፍቻቸው” ተቀምጧል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያለው ጉድለት በዋናነት አንድ ነው፡፡ እርሱም፣ በአረንጓዳ ሳሎን ውስጥ በነገርሜ የተገደሉባቸው የራስ አበበ አረጋይ፣ የራስ ስዩም፣ የሜ/ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ የአቶ መኮንን ሀብተ ወልድና የሌሎችንም ባለሥልጣመናት ቤተሰቦች አለማናገራቸው ነው፡፡ ከዓመታት በኋላ፣ እነዚህ የሟቾቹ ቤተሰቦች ስለመፈንቅለ መንግሥቱ ያላቸውን ስሜትና እውቀት ሊያካትቱት ቢችሉ ምንኛ ዕጹብ-ድንቅ ይሆን ነበር፡፡ ከአቶ ብርሃኑ አስረስ አልገፉበትም እንጂ፣ ትልቅ ሙከራ አድርገው እንደነበር አያጠራጥርም፡፡ በ1953 ዓ.ም የፍትሕ ሚ/ር የነበሩትን ደጃ/ች ዘውዴ ገ/ሥላሴንና ብ/ጄኔራል መኮንን ደነቀን ለማነጋገር ያደረጉት ጥረት መልካም ነው፡፡ እጅግም የሚደነቅ ነው፡፡ በሰማኒያ ሦስት ዓመታቸው የተለያዩ ጫናዎችን ተቋቁመው ይኼንን የመሰለ ድርሳን ስላቀረቡልን ለአቶ ብርሃኑ አስረስ ያለኝን ምስጋናና ልባዊ አክብሮት በአንባቢያን ስም ይድረሳቸው እላለሁ፡፡ አንባቢያንም፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዋጋው ተፋፍቆ በእጥፍ ከምትገዙት፣ ዛሬውኑ መጽሐፉን በትክክለኛው ዋጋ “የግላችሁ አድርጉት!” በማለት ወንድማዊ ምክሬን አስተላልፋለሁ፡፡ ለአቶ ብርሃኑም መልካም ጤንነትና ሰላምን እመኛለሁ፡፡ (በተረፈ፣ በቸር እንሰንብት!)

በሳምናታዊው የአዲስጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 178 ላይ፣ በነሐሴ 18 ቀን 2005 ዓ.ም የወጣ ነው::

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>