Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ይድረስ ለነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን –ከያህያ ይልማ

$
0
0

አሁን ያለው የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች ምን እንደሆኑ በውል ተመልክቶ በተቃራኒው ምን ዓይነት የትግል መስመር እንደሚያስፈልግ እኔ ያህያ ይልማ የሚከተሉትን ቁምነገሮች ሳስቀምጥ የሌሎቻችሁም አስተያየት ውሸት የሌለው እና ህሊናዊ ተጠየቅ ባለበት መልኩ እንዲሆን እያስገነዘብኩ በደስታ እጋብዛችኋለሁ::

1. የሕወሐት ሥርዓት ችግሮች

tplf-rotten-apple-245x300ሀ. የሕወሐት መስራቾች ወደ ትግል ለመግባት ያሰቡት እና የገቡት የንጉሱን ስርዓት ብሎም የአማራውን ገዥ መደብ በተለይም የሰሜን ሸዋን የበላይነት ተዋግቶ በማስወገድ የወልቃይትንና የራያን ለም መሬቶች አስገብቶ ታላቋን ትግራይ መመስረት አልሞ ሆኖ እያለ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ በማውረድ በምትኩ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አሰፈንኩ እያሉ ያጭበረብራሉ:: እዚህ ላይ የማይካድ ሐቅ አለ:: የሕወሐት ተራ ታጋዮች በቆራጥነት ተዋግተዋል፣ ስርዓጥ አልበኛ ከነበረው ከአምባገነኑ ደርግ አንጻር የሰራዊታቸው ዲስፕሊን የሚደነቅ ነበር፣ የመጨረሻ ደባቸው ምን እንደሚሆን በትክክል ባይታወቅም እንዲሁ በምንረዳው ሐሳባቸውን ከመገንጠል ወደ ኢትዮጵያን መምራት አስተሳሰብ ቀይረውም ነበር:: እነዚህ ሁኔታዎች በትግራይ እና በሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ የሚኖሩ ገጠሬዎች እንዲደግፏቸውና አብረዋቸው እንዲሰለፉ ዳርጓቸዋል:: እየፈራረሰ የነበረውን የወቅቱን ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ ዓለምን በብልጣብልጥነት የተው መስለው ከምዕራባዊያን ጋር ወዳጅነት መፍጠራቸውም በእጅጉ የጠቀማቸው አካሄድ ነበር::

ለ. የሀገር ድንበርን ከማስከበር እና የህዝቦችን አንድነት ከመጠበቅ አንጻር ሲነጻጻር የወረደ ቢሆንም ሕወሐት የአጼ ዮሐንስን ዘመን አምጥቸላችኋለሁ በሚል ስሜት ትግራዊያንን ተጠቀሙብኝ እያለ በሙስና የማይገባቸውን ሐብት እንዲያጋብሱ እያደረገ ይገኛል::

ሐ. የሕወሐት ስርዓት የለየለት ዘረኛ መሆኑን የራሱ አጋዥና ታዛዥ የሆኑት የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደህዴንና ሌሎች አጋር ድርጅቶችም ተረድተውት ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ጊዜ እየጠበቁ ይገኛሉ:: ለዚህም ማስረጃ ጦሩና ደህንነቱ እንዲሁም ወሳኝ የመንግስት አውታሮች በሕወሐት ብቸኝነትና የበላይነት ተጨንፍረው ይገኛሉ::

መ. ሕወሐቶች በትግል ወቅት ያልነበራቸውን ጭካኔነት በአሁኑ በሰለጠነ ዘመን እንዴት ሊተገብሩት እንደቻሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ዜጎችን ሲያስሩ፣ ሲያንገላቱና ሲገድሉ መመልከት የተለመደ ተግባር ሆኗል::

ሰ. የሕወሐት ስርዓት ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን ጨለምተኝነትንና ተስፋቢስነትን አስፍኗል:: መማር ትርጉም አጥቷል፣ የመኖር ዋስትና ጠፍቷል፣ ሀላፊነት ያላቸው ሰዎች በውሸት የተሞሉ በመሆኑ ውሸታቸውን እየነዙ በኢትዮጵያዊያን መካከል መተማመን ጠፍቷል፣ ከፋፍሎ የመግዛት ስልትን አጠናክረው ስለቀጠሉበትም ኢትዮጵያዊያን በጎሪጥ እንዲተያዩ ዳርጓል::

ረ. የሕወሐት ስርዓት ሉዓላዊነትን ከማስከበር እና ከማስጠበቅ ይልቅ ስልጣንን የሚያስቀድም በመሆኑ በድንበራችንና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ላለው አሳፋሪ ውርደት ተጠያቂ ነው::

ሸ. የመሰረተ ልማት አውታሮች እየተዘረጉ ቢታዩም እንዴት ነው የሚዘረጉት፣ ጥቅሙስ ለህዝቡ እየደረሰ ነው ወይ ተብሎ ሲታይ መልሱ ተቃራኒ ነው:: የመሰረተ ልማት አውታሮቹ የሚገነቡት ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ እንኳ ልትከፍለው የማትችለው ወደ ፵ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የብድር እዳ እንድትሸከም ሆና ሲሆን ከዚሁ እዳ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በፖለቲካ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ለማፈኛ ሆኖ ከማገልገል በተረፈ በሕወሐት ባለስልጣናት እየተዘረፈ የሚገኝ መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ::

ቀ. በአጠቃላይ የሕወሐት ስርዓት ለዚህ ዘመን የማይመጥን ፍጹም አምባገነን ዘረኛ ስርዓት ነው:: ህዝቡም ይህን በደንብ ስለሚገነዘብ ሕወሐትን እንደ ዘራፊ ቡድን እንጂ እንደ መንግስት አይመለከተውም::

በመሆኑም የሕወሐት ስርዓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መወገድ ያለበት የኢትዮጵያዊያን ካንሰር ነው:: ከዚህ በመነሳት የሕወሐት ስርዓት በመሳሪያ የታጀበ ህዝባዊ አመጽን በማቀጣጠል ሊወገድ ይገባዋል::

2. ሕወሐትን ለማስወገድ የሚያስፈልጉ የትግል መስመሮች

ሀ. ሰላማዊ ትግል እያሉ ጊዜን ከማጥፋትና ዜጎች እንዲሰቃዩና እንዲገደሉ ከማድረግ አሁን ባለው ሁኔታ የሕወሐት ስርዓትን ለማስወገድ የሀይል አማራጭ መጠቀም ብቻ መሆኑን ማወቅና ከልብ ማመን ነው::

ለ. ከታሪክ እንደምንረዳው እንኳንስ አምባገነኑ ሕወሐት ይቅርና ዴሞክራስያዊ የሆኑ ስርዓቶችም ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ይሞታሉ:: ከዚህ አንጻር ሕወሐት ተወልዶ ሲያድግ ተመልክተናል:: አሁን ደግሞ የህዝብ እሮሮ በርክቶ ወደመሞቻው ጉዞ ላይ ይገኛል:: ይህንን መረዳትና የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ሕወሐት ማስወገጃ ጊዜው አሁን መሆኑን መገንዘብና መነሳት ያስፈልጋል::

ሐ. ተስፋ ሰጭ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ሀይል ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ መደገፍ፣ ቅስቀሳ ማካሄድና መቀላቀል:: አርበኞች ግንቦት ሰባትን መቀላቀልና ማጠናከር የሚጠቅመው ሕወሐትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሕወሐት ከተወገደ በኋላም ሳይታወቅ የሕወሐት ዓይነት ቡድን ሳይፈጠር ሉዓላዊነት የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ስለሚጠቅም ነው:: የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖቶች እንዳይጨቆኑብን ካሰብን ክርስቲያኖችና እና ሙስሊሞች የሆን በሙሉ አርበኞች ግንቦት ሰባትን መደገፍና መቀላቀል ነው:: የብሔር ጭቆና አለ ብለን የምናምንም አላስፈላጊ የቃላት አተካራን ትቶ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሀይል መሆንና ውሳኔዎችን በጋራ የምናስኬድ መሆን:: ድጋፉ ከተለያየ አቅጣጫ የማይመጣ ከሆነ ግን አርበኛች ግንቦት ሰባት ጎንደሬ ወይም ሰሜን ሸዋ ወይም ጎጃሜ ወይም ወሎየ የበዛበት ወይም አንዱን ሀይማኖት ብቻ ከፍ አድርጎ የሚመለከት ይሆንና በጋራ ወሳኝ ከመሆን የቡድኑን ይሁንታ የምንጠብቅ እንሆናለን:: በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና በፍትህ የሚያምነው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መዳፍ እንደገባ ሁሉ አሁን በስም ከምናውቃቸው ታጋዮች የድሉን መጨረሻ ለማየት የሚታደሉት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ:: ይህ ማለት የሁላችንም ተሳትፎ ከሌለ ከድል በኋላ የምናየው አርበኛች ግንቦት ሰባት መልኩን ቢቀይር ችግሩ አሁን ያለመሳትፋችን ውጤት ነው የሚሆነው:: ስለሆነም አሁን የምናደርገው ተሳትፎ ከኢትዮጵያችን ነጻ መውጣት ጋር ተያይዞ ለሚኖረው የህልውናችን፣ የማንነታችንና የአብሮነት ውሳኒያችን አካል መሆኑን ተገንዝበን ከአርበኛች ግንቦት ሰባት ጎን መቆም::

መ. አርበኛች ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት ትግሉን እያፋፋመ ጎን ለጎን ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል:: ማንፌስቶው የሚከተሉትን ሶስት ወሳኝ ጉዳዮች ቢያካትታቸው እሻለሁ::

1. ኢትዮጵያ ክብሯ ከፍ ያለች አገር ሆና እንድትቀጥል ህጋዊ ሰውነት ያለው ማንኛውም ተቋም መለሰ ዜናዊና ደቀመዝሙሮቹ እያላገጡ እንዳየነው የኢትዮጵያን ታሪክ የማንቋሸሽ ስራ ነውርና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ትኩረት ማድረግ::

2. ሕወሐት ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች እያለ ትርጉሙ ላገሬው ግልጽ ያልሆነን ማደናገሪያ እንደተጠቀመበት ሳይሆን በቀናነት ከምር ራስን በራስ የማስተዳደር ተግባራዊነት አስፈላጊ ነው:: ለዚህም ፕ/ር መስፍን ከጻፏቸው መጽሀፍት መካከል «ኢትዮጵያና የመንግስት አስተዳደር» [ካነበብኩት ጊዜው ስለረዘመ የመጽሀፉ ትክክለኛ ርዕስ የጠቀስኩት ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም] በሚለው እንደተመራመሩት አካባቢያዊ ስሜቶች የሚንጸባረቁባቸው ማህበረሰቦች የራሳቸው አስተዳዳሪዎች ኖሯቸው ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግስት መሆን:: ለምሳሌ የተንቤን፣ የአድዋ፣ የመቀሌ፣ የራያና የጁ፣ የላስታና ዋግ፣ የደላንታና ደቡባዊ ወሎ፣ የከሚሴ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋ፣ የሐረሪና ድሬዳዋ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የአርሲ፣ የሀድያ፣ የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የባሌ፣ የወለጋ፣ የቤንችማጅ፣ የሐመር፣ የሙርሲና የቱርሲ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ወዘተ. የራሳቸው አስተዳደር ኑሯቸው ተጠሪነታቸው ለማዕከላዊ መንግስት እንዲሆን ማድረግ አንድ ነን በሚል ሽፋን የሚከሰቱ ዘረኛዊ የአስተዳደር በደሎችን በእጅጉ ለመቀነስ ይረዳል:: አካባቢን ለማልማትም ከልብ ተነሳሽነት እንዲኖር ይረዳል::

3. ታሪካዊ በደሎች እንደነበሩ አምኖ ሀገራዊ እርቅ እንዲኖር ቁርጠኝነትን ማሳየት::

ሠ. ሕወሐትን ለመጣል የሚደረገው ትግል ከተከማቸው መሳሪያ አንጻር አልጋ ባልጋ የሚሆን ባይሆንም እንደ ድሮው በቆራጥነት የሚታገል ታጋይ የሌላቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ቁርጠኝነት የነበራቸው አርጅተው በሙስና ተዘፍቀው ከመዋጋት ይልቅ ሁሉም አዛዦች ሁነው ያሉበት ወቅት ነው:: እንተማመንበታለን የሚሉት እንደ አግአዚ አይነት ያለው ጦርም ቢሆን እንኳ መሳሪያ ባልያዘ ሰላማዊ ዜጋ ካልሆነ በስተቀር መልስ የሚሰጥ ታጋይ ጋር የመዋጋት ሞራል የለውም:: መልቀምቀም የለመደ ስለሆነ ሞትን የሚጋፈጥ አይደለም:: ረባም አረባ ድሮ የሚሰብኩበት አይዲዮሎጂ ነበራቸው:: አሁን ግን እነሱን ግራ አጋብቶ ሌላውንም ግራ ያጋባው አብዮታዊ ዴሞክራሲ በማንም የተተፋ ስለሆነ የሞራል መቀስቀሻ የላቸውም:: አጭበርባሪና ውሸታም መሆናቸው ስለታወቀ አዲስ ሀሳብ እናምጣ ቢሉም የሚቀበላቸው የለም:: ከሕወሐቶችና ጥቅመኛ አለቆች ውጭ ያለው ተራው ወታደር እጅ ለመስጠት የሚዘጋጅና በነሱ ላይ አዙሮ መተኮስ የሚችል ሀይል ነው ያለው:: ስለሆነም የትግሉ መራራነት በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው::

ረ. ትግልን ለማካሄድ ምክኒያት ማብዛት ወደ ኋላ ያስቀራል:: ለምሳሌ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከጅምሩ ህብራዊ እንደሆነ ብንረዳም መሰረቱ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ህዝብ ነው:: ድርጅቱን ኦሮሞዎችና ነጻነትን የሚሹ ሌሎች አካሎች መሰረቱ በአማርኛ ተናጋሪው በመሆኑ መሸሻ ምክኒያት ማድረግ የለባቸውም:: ከላይ እንደጠቀስኩት ካሁኑ መሳተፍ የራስን ሃሳብ ውጤት እንዲኖረው ለማድረግ ይጠቅማል:: ከዚህ በተጨማሪ አማርኛ ተናጋሪው በሕወሐትና ሆድ አደር አጋር ፓርቲዎች ሲገፋና ፍዳውን ሲያይ እንኳ እልህ ተጋብቶ የራሴ ሳይል ለኢትዮጵያ ብሎ ነው ሲጮህና ሲታገል የኖረው:: ታዲያ ስተት ካለ እንተራረም እንጂ ማለት ኢትዮጵያዬ ማለቱ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው የምቆመው ማለቱ ድጋፍ ያሰጣል፣ አይዞህ ያስብላል እንጂ በጥርጣሬ ያስተያያልን ? የሕወሐትን ከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካን መቸም ሁላችንም ጠግበነው አንገሽግሾናል:: እና ለምኑ ብለህ ነው ወገኔ የሚልህን የምትርቅ:: ታሪካዊ ስህተቶችንም እንደምንተራረም መስመር እየዘረጋን ነው:: ያለፈው አልፏል፣ የሆነው ሆኗል ለኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲና ለነጻነት ስንል ዛሬ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጎን ቆመን ለአገራችን ካንሰር የሆነውን ሕወሐትን እናስወግድ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!


አንድ አስገራሚ ታሪክ ከጦር ግንባር –ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

$
0
0

arbegnoch
ወጣት ለአከ ይባላል:: የ21 ዓመት ወጣት ነው:: የትህዴን ተዋጊ ወታደር ነው:: በርከት ያሉ የማጥቃት ወታደራዊ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል:: ….በ2006 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በየካቲት ወር በአንዱ ዕለት ነው:: የሱ ምድብ ጋንታ ግዳጅ ተሰጥቶት ወደ ትግራይ መሬት ይገባል:: ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ይገጥማል:: ለሰዓታት በዘለቀው በዚሁ ውጊያ ለአከ የተሰለፈበት የትህዴን ሃይል የማጥቃቱን የበላይነት ይይዛል:: እነ ለአከ በርካታ የህወሀት ታጣቂዎችን እየማረኩ ነው:: …..

….ለአከ በውጊያው መሃል አንድ የህወሀት ታጣቂ መሳሪያውን እንደያዘ ሲሸሽ ተመለከት:: ተከተለው:: ከዚያም መሳሪያውን አስቀምጦ እጅ ወደ ላይ እንዲል አደረገው:: ታጣቂው እንደተባለው አደረገ:: ፊቱን እንዲያዞር አዘዘው:: ፊቱን አዞረ:: ….ለአከ ድንግጥ አለ:: የሚያየውን ማመን አቃተው:: ….ወላጅ አባቱ ናቸው::

እኔ..” አባትህን ስትማርካቸው ምን ተሰማህ?”
ለአከ..” ምን ላድርግ? የዓላማ ጉዳይ ነው::”

ለአከ የማረካቸውን አባቱን ይዞ ወደ ካምፕ ተመለሰ:: አባት ከትህዴን ጋር መቆየት ወይም ወደ ቤተሰብ መመለሥ የሚሉ ምርጫዎች ቀረቡላቸው:: ወደ ቤተሰብ መመለሱን መርጠው ምክር ተሰጥቶአቸው ሄዱ::

እኔ..” አባትህ የማረካቸው ወታደር የእሳቸው ልጅ መሆኑን ሲያውቁ ምን አሉህ?
ለአከ..” ..’በህይወት አለህ? እርማችንን አውጥተን ነበር’..አለኝ”
አባትና ልጅ በተቃራኒ ቡድኖች የተሰለፉበት ታሪክ:: ለአከ “ከዓላማ የሚበልጥ ምንም ነገር የለም” የሚል መልስ ከአፉ አይጠፋም::

‹‹አሸባሪዎቻችን›› ሲኖ ትራኮች ብቻ አይደሉም!! –ለ85 በመቶ የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ሆኖ እርምጃ ያልተወሰደበት አንድ ብቻ ምስጢር!!

$
0
0

ለሥራ ጉዳይ ወደ ጎጃም ስጓዝ ያየሁት ነገር ትኩረቴን በጣም ሳበው፡፡ ሁሉም እግረኞች ግራቸው ይዘው ነው የሚጓዙት፡፡ ቆም ብዬ አካባቢዬን ስቃኝ ቀኜን ይዤ የምጓዘው እኔ ብቻ ነኝ፤ ሁሉም እግረኛ ግራውን ይዞ ነው የሚጓዘው፡፡ ከቀናት በኋላ በአንድ የገበያ ቀን የወንበርማ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ሸንዲ ከተማ ቢጫ ቲሸርት የለበሱና ፊሽካ የያዙ ወጣቶች ገበያተኞችን ግራቸውን እንዲይዙ ሲያደርጉ ተመለከትኩ፡፡ እኔም አንዱን ወጣት ጠጋ ብዬ ስለሁኔታው ጠየኩት፡፡ በጎ ፍቃደኞች እንደሆኑና ሁሌም ቅዳሜ ሰውን እንደሚያስተምሩ ነገረኝ፡፡

sinotruck accident addis abab

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ፌስቡክ ላይ የሚገርም ምስል አየሁ፡፡ ከላይ ጽሑፍ አለ ከታች ፎቶ፡፡ ናይጄሪያ ብሎ ቦኮሃራም ይላል፡፡ ሱማሊያ ብሎ አልሸባብ ይላል፡፡ ሶሪያ ብሎ አይሲስ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ብሎ ፎቶ ተለጥፏል፡፡ ፎቶውም ቀደም ሲል ‹‹ቀይ ሽብር›› አሁን ደግሞ ‹‹ድሮኖቹ›› (The Drones) ማለትም ‹‹ሹፌር አልባዎቹ›› እየተባለ የሚሽሟጠጠው የሲኖትራክ መኪና ፎቶ ነው፡፡ የእኛ ሀገር አሸባሪ ይኸው ሲኖ ትራክ መሆኑ ነው፡፡ ሌሎቹ መኪናዎቹስ እያሸበሩን አይደለምን? እስኪ ዛሬ ስለ ትራፊክ አደጋ ልፃፍ፤ እናንተም አንብቡ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!

የመኪና አደጋ ሁኔታ ቅኝት

ለእንደ ኢትዮጵያ ላሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት መኪና ዋነኛው የመጓጓዣ መንገድ ነው፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ 80 ከመቶ የሚሆነው ሰው እና ዕቃ የሚጓጓዘው በመኪና ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመጣ ደግሞ በከተሞች መሀከል ከሚደረጉ የሰዎችም ሆነ የዕቃዎች መጓጓዝ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነው የሚካሄደው በመኪና ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመኪና መጓጓዝ ውስጥ አደጋ የመፈጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት ግምት መሰረት በዓለም ላይ በመንገድ ላይ በሚደርሱ የመኪና አደጋዎች በየዓመቱ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን 50 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳቶች ይዳረጋሉ፡፡ በዓለም ላይ ያለውን የአደጋ ቁጥር የመጨመር ሁኔታን ያጤኑት ደግሞ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ይላሉ፡፡ ናድ፣ ቺሾልም እና ባከር የተባሉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ2020 የትራፊክ አደጋ ከኤች.አይ.ቪ እና ከቲቪ ቀጥሎ 3ኛው ገዳይ ይሆናል፡፡

ይህን ሁኔታ በአንክሮ ስንቃኘው ደግሞ የትራፊክ አደጋ የሚበዛው በሰለጠኑትና ብዙ መኪና ባላቸው ሀገራት ሳይሆን ጥቂት የመኪና ቁጥር ባላቸው ታዳጊ ሀገራት ነው፡፡ ከዓለም ህዝብ ውስጥ 81 ከመቶ የሚሆኑ የሚኖሩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሲሆን በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ መኪናዎች በዓለም ከሚገኙ መኪናዎች ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች በብዛት የሚገኙት በእነዚህ ሀገራት ነው፡፡ እንደ ሙራይ እና ሎፔስ ስሌታዊ አገላለፅ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት በትራፊክ አደጋ ምክንያት በቀን ውስጥ 3 ሺ ሰዎች ይሞታሉ፣ ሌሎች 30 ሺ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ግምት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 227,835 እግረኞች፣ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 165,501 እግረኛ እና ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 22,500 እግረኞች በየዓመቱ በመኪና አደጋ ምክንያት ይሞታሉ፡፡

እንደ አንድ ዝቅተኛ ገቢ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ገፈቶች ቀማሽ ነች፡፡ ከቤቱ ሳይወጣ ሬዲዮ የከፈተ ሰው እንኳ ቢያንስ አንዴ ስለ አንድ የትራፊክ አደጋ ይሰማል፡፡ ጥናታዊ መረጃ ለማቅረብ ያህል እንኳ ዳንኤል አድማሴ፣ ታከለ ይርጋ እና ብሩክ ዋሚሽ የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2010 ባሳተሙት የምርምር ወረቀት እ.ኤ.አ በየካቲት እስከ ነሐሴ 2007 ወደ ጥቁር አንበሳ በአጥንት ስብራት ምክንያት ከገቡት 422 ታካሚዎች ውስጥ 49.7 ከመቶ (202 ታካሚዎች)የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ15-25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ በሬዲዮና በቴሌቪዝን የሚነገረን በግርድፉ ሲሆን ጥናቶቹ የሚነግሩን ደግሞ ወጣቶች እና እግረኞች ከፍተኛው ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ተወልደ መኮንን የተባለ ተመራማሪ እ.ኤ.አ በ2007 በሰራው ጥናት በመኪና አደጋ ከሞቱ ሰዎች ውስጥ 51 ከመቶ የሚሆኑት እግረኞች ናቸው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ ደግሞ በሀገሪቱ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የሚደርሱባት ከተማ ነች ብሎም ከሟቾች ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ሟቾች እግረኞች ናቸው፡፡

 

ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ?

ሀገራችን ውስጥ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ብዙ ናቸው፡፡ ጥያቄው ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ የሚለው ነው፡፡ እዚህም እዚያውም የተሰሩ ጥናቶች መንስኤ የሚሏቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

በቅርቡ ከተሰራ ጥናት ለመጀመር ያህል እ.ኤ.አ በ2014 ኃይሌ መኮንን እና ደመቀ ላቀው የተባሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በባህርዳር ከተማ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን አጥንተዋል፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ የሚያሳዩት ባህሪ እና የሹፌሮች የወንበር ቀበቶ አለማሰር በትራፊክ አደጋዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳይተዋል፡፡ ዝርዝር ውጤቶችን ስንመለከት ደግሞ፡-

– 55.5 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የተከሰቱት ከ30 ዓመት በታች ዕድሜ ባላቸው ሹፌሮች ነው፤

– 42.2 ከመቶ የሚሆኑት አደጋ ያደረሱ መኪናዎች ለረዥም ዓመት አገልግሎት የሰጡ ናቸው፤

– 69.8 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የደረሱት ለእግረኞች ቅድሚያ ባለመስጠት ነው፤

– 55.6 በመቶ የሚሆኑ ሹፌሮች የወንበር ቀበቶ የሚጠቀሙት አልፎ አልፎ ነው፤

– 57.8 በመቶ የሚሆኑ አደጋዎች የደረሱት ሹፌሮች ሞባይል እያነጋገሩ ነው፤

– 66 ከመቶ የሚሆኑት ሹፌሮች እግረኞች የተሳሳተ የመንገድ ማቋረጫ ይጠቀማሉ ብለው ያምናሉ፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባት ሀገር፣ አዲስ አበባ ደግሞ 60 ከመቶ የሀገሪቱ አደጋ የሚከሰትባት ከተማ በሚል መነሻ በአዲስ አበባ ጥናት ያደረገው ተወልደ መኮንን የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝቷል፤

– አብዛኛዎቹ አደጋዎች የደረሱት በመኖሪያ አካባቢዎች ነው፡፡

ኢብራሂም ሃሰን እና ጓደኞቹ እ.ኤ.አ በ2011 350 ሾፌሮችን በማካተት ስለመቀሌ ከተማ የትራፊክ አደጋ ጥናት ሰርተው የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝተዋል፡፡

– 233 ሹፌሮች አደገኛ የአነዳድ ባህሪ አላቸው

– 100 ሹፌሮች ስለመሰረታዊ የትራፊክ ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ ነው

– 148 ሹፌሮች እያሽከረከሩ ሞባይል የመጠቀም ልምድ አላቸው

– 28 ሹፌሮች ከጠጡ በኋላ የመንዳት ልምድ አላቸው

– 77 ሹፌሮች ከዚህ በፊት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል

– ሁሉም የባጃጅ ሹፌሮች፣ 62.6 ከመቶ የሚሆኑት የቤት መኪና የሚይዙ እና 37.4 ከመቶ የሚሆኑት የታክሲ ሾፌሮች በሚያሽከረክሩበት ሰዓት የወንበር ቀበቶ አይጠቀሙም፡፡

ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክስ አሶስየሽን በ2012 ባወጣው የምርምር ማብራሪያ (research brief) የሚከተሉትን ጉዳዮች በመንገድ ላይ ለሚከሰቱ የትራፊክ አደጋ ምክንያቶች ናቸው ብሎ ከተለያዩ ምርምር ውጤቶች እንደተገኙ የገለፃቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ደካማ የመንዳት ክህሎት

– ‹‹ለእግረኛ ቅድሚያ ስጥ›› የሚለውን ህግ አለማክበር

– ከተፈቀደው የፍጥነት ገደብ በላይ ማሽከርከር

– በዕቃ መጓጓዣ የተሰሩ መኪናዎችን ለሰዎች ማጓጓዣነት መጠቀም

– የትራፊክ ህጎችን አለማክበር

– ደካማ ቴክኒካዊ ብቃት ያላቸውን መኪናዎችን ማሽከርከርና ለመኪናዎች በቂ ጥንቃቄ አለማድረግ

– የመኪና መንገዶች በእንስሳትና በእግረኞች መያዝ/መጨናነቅ

– እግረኞች ስለትራፊክ ህጎችና ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ መሆን

– የትራፊክ ህጉን በተግባር ያለማዋል

– ከመንገዶች ጥራትና ዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች

– የመኪኖች መናኸሪያ አለመኖር

– በቂ የፓርኪንግ ቦታ ያለመኖር ችግር

 

ምክንያቶቹ ተለይተዋል ካልን ምን የእርምት እርምጃ ተወሰደ?

የሚመለከታቸው መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ በሀገር ደረጃ በመንገዶች ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ለመቅረፍ እ.ኤ.አ ከ1997 ጀምሮ የመንገድ ዘርፍ እድገት ፕሮግራም መንግሥት ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ዋና ትኩረቱም 3 ጉዳዮች ሲሆኑ እነሱም ሀ/ ዋና ዋና መንገዶችን ማሻሻልና ማሳደግ ለ/አዳዲስ መገንባት እና ሐ/ መንገዶችን በተከታታይ ጥገና መስጠት ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ ፖሊሲዎችን በማውጣት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በጀ የሚያሰኙ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ ለዚህ ጥሩ አብነት የሚሆነን ደግሞ እ.ኤ.አ በ2011 የወጣው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ፖሊሲ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የተሞከሩ ሂደቶችን፣ በሂደቱ ውስጥ የታዩ ችግሮችን እና የተሻለ ውጤት ለማምጣት መከወን ስላለባቸው ተግባራት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ሞባይል እያወሩ ማሽርከርና ቀበቶ የማሰር አስገዳጅ ደንቦች ተጠቃሽና ቀበቶ የማሰር ጉዳዮች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው የዜብራ መንገድ አጠቃቀም ህጉም ከባድ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን እግረኞችም በዜብራ መንገድ ሲያቋርጡ በተገኙ ጊዜ የሚጠቀሙበት አሰራርም ተጀምሮ ነበር፡፡

የሚዲያ ተቋማትም ሁኔታውን ከመዘገብ አንስቶ ህብረተሰቡን በተለያዩ ዘዴዎች እስከማስተማር ያሉ ወሳኝ ተግባራትን እየወከኑ ነበር፤ ናቸውም፡፡ በተለያዩ የሙያዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችም የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ‹‹አሽከርክር ትደርሳለህ፤ ረጋ ብለህ›› በማለት ያቀነቀነው ሞገስ ተካ ለዚህ ምርጥ አብነት ነው፡፡ መፅሐፍ በመፃፍና የተለያዩ የሚዲያ ተቋማትን በመጠቀም ያለመታከት አደጋዎችን ከዘገብ እስከ ትምህርታዊ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ እየሰራ ያለው ሥራ ከፍተኛ ምስጋና የሚቸረው ግለሰብ ነው፡፡

የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን በበኩሉ የመንጃ ፈቃድ አሰጣጡን እስከመቀየር የደረሰ መሰረታዊ የእርምት እርምጃ ወስዷል፡፡ በቅርቡ ደግሞ በሲኖትራክ መኪና የሚደርሱ አደጋዎች ላይ ጥናት እንደሚደረግ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ዘግበውት እሰይ ብለናል፡፡

የእርምት እርምጃዎቹ ውጤታማ ለምን አልሆኑም?

እላይ የጠቀስኳቸውና ያልጠቀስኳቸው የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ይህ በራሱ መልካም ነገር ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን እየደረሱ ያሉ አደጋዎች ከመቀነስ ይልቅ እየጨመሩ እንደሆነ ነው እያየንና እየሰማን ያለነው፡፡ ማስረጃ ለመስጠት ያህል እንደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሲየሽን ማብራሪያ እ.ኤ.አ ከ2003/2004 እስከ 2010/11 በትራሪክ አደጋ የደረሰው የሟቾ ቁጥር በ6 በመቶ፣ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በ4.5 በመቶ እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በ3.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

እርምጃዎች እየተወሰዱ የአደጋው ሁኔታ አሁንም እየጨመረ የሚመጣ ከሆነ ለምን ብሎ መጠየቅ እጅጉን ወሳኝ ነው፡፡ ውጤታማ የሆኑ እርምጃዎች ደግሞ ከውጤታማነታቸው ጀርባ ያለውን ምስጢር ማጤኑ አስፈላጊ ነው፡፡ በእነዚህ መነፅሮች ውጤታማ እና ውጤታማ ያልሆኑትን ተግባራት በማነፃፀር ትምህርት መውሰዱ እና የተሻለውን መተግበሩ ለነገ የሚባል አይደለም- ሰው እያለቀና ንብረት እየወደመ ነውና!

ቀደም ብየየ የጠቀስኳቸውንም ሆነ ያልጠቀስኳቸውን የጥናት ውጤቶችን በጥሞና ያጤነ ሰው የሚገነዘበው አንድ አብይ ጉዳይ አለ፡፡ አብዛኛዎቹ የአደጋ መንስኤዎች ከሰዎች ባህሪያት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ከሹፌሮች፣ ከእግረኞች፣ ከሕግ አስከባሪዎች፣ ከባለንብረቶች፣ ወዘተ፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ ከመኪናዎች እና ከመንገዶች ሁኔታ/ችግር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ቀደም ብዬ የጠቀስኳቸው ናድ፣ ቺሾልም እና በከር የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2009 በሰሩት ዓለም አቀፍ ጥናት እንዳገኙት ደግሞ 85 ከመቶ ለሚሆኑት አደጋዎች መንስኤ ከሰዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከመንገድ ጋር እና ከመኪናዎች ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ለቀሪ 15 ከመቶ አደጋዎች መንስኤ ሆነዋል፡፡

እናም የሚወስዱት የእርምት እርምጃዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንዳ መሰረታዊ መርሃቸው ከሰዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎችን መቅረፍ ላይ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት ግን ከመንገድና ከመኪናዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎችን መተው አለባቸው ማለት አለመሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይልቁንም ሁሉንም ችግሮች ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሱ አብላጫውን ትኩረት ሰዎች ጋር ከተያያዙት ላይ ማድረግ አዋጭ ነው፡፡ ውጤታማ የሆኑት እርምጃዎችም ይህንን ነው የሚያሳዩን፡፡ የጎጃሙ ሁናቴ ለዚህ ዓብይ ምሳሌ ነው፡፡ እግረኞች ላይ አተኩረው ሰሩ የትራፊክ አደጋዎችን ቁጥርም በእጅጉ ቀነሱ፡፡ ያ ማለት ግን የመኪኖችን ዓመታዊ ፍተሻ እና መንገዶችን ምቹ ማድረጉን አቆሙ ማለት ሳይሆን ትኩረታቸውን በእግረኞች ላይ በማድረግ ሁሉንም እርምጃዎች ጎን ለጎን ከወኗቸው ማለት እንጂ!

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አነስተኛ ወይም ከሚጠበቀው በታች ናቸው፡፡ ይህም ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፖሊሲ ውስጥ የሚመለከታቸው አካላት ስለ ትራፊክ ያላቸው ዕውቀትና አመለካከት ወሳኝ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ በመቀጠልም በዚህ ረገድ ከበፊቱ የተሻለ ሥራ እየተሰራ ቢሆንም የማያረካ፣ ቀጣይነት የሌለው እና በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገደበ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ፖሊሲው የተለያዩ ምክንያቶችን ከጠቆመ በኋላ ደግሞ እግረኞችም ሆኑ ሹፌሮች የትራፊክ ሕጉን አያከብሩም የሚል ድምዳሜ ያስቀምጣል፡፡ ሕግ አስከባሪ አካላትም ሕጉን አይተገብሩም ይላል፡፡ እነዚህ የተጠቀሱት ነገራት ሁላ የሚያሳዩት ከሰዎች ጋር የተያያዙ ችግሮች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

በቅርቡ ይወሰዳል በተባለው አስደሳች እርምጃ ውስጥም የዚህ አይነት የትኩረት ስህተት ይታያል፡፡ በሲኖትራክ መኪና የተከሰቱ አደጋዎች ላይ ጥናት ይደረጋል የሚለው ሃሳብ ሲብራራ የጥናቱ ትኩረት በዋናነት በመኪናዎቹ ቴክኒካዊ ምርመራ ላይ እንደሚሆን ነው የተነገረው፡፡ ይህ መደረጉ በራሱ ጥሩ ሆኖ እያለ አሁንም የተዘገና ነገር ይታያል፡፡ ስንቶቻችሁ አጋጥሟችሁ እንደሆነ ባላውቅም አንዳንድ የሲኖትራክ ሹፌሮች ከፊታቸው የሆነ መኪና መንገድ ሲዘጋባቸው በመስኮት በኩል አንገታቸውን አውጥተው ‹‹ወዮልህ፣ መጣሁብህ፣ እላይህ ላይ እንዳልወጣ›› ሲሉ እንሰማለን፡፡

ታዲያማ የመኪናው ሁናቴ ተፈትሾ፣ ችግር ከተገኘበትም ተስተካክሎ፣ የሹፌሮቹ ባህሪ ካልተቀየረ ችግሩ ይቀንስ ይሆን እንጂ መቸ ይቀረፍና? የእግረኛ ማቋረጫውን በቅርብ ርቀት እያዩ በመሀል የሚያቋርጡ እግረኞች ባህሪ ካልተለወጠ የተስተካከለ መንገድና ጥሩ ብቃት ላይ ያሉ መኪናዎች ቢኖሩንም አደጋውን የመቀነስ ሁኔታችን ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል? ለእግረኞች ቅድሚያ የሚሰጥ ሹፌር መንገደኞችን ሲያሳልፍ ሌላ ግድ የሌለውና ያልተረጋጋ ሹፌር እየተሻገሩ ያሉትን መንገደኞች ገጭቶ እንደገደለ የሰማነው በቅርቡ አይደለምን? ለጥ ባለ የአስፋልት መንገድ የሚሄድ ከባድ መኪና ለቁጥር የበዙ ግመሎችን የረጋገጠው ግመሎቹን ባለቤታቸው ወደ መንገድ ስላስገባቸው አይደለምን?

ትራፊክ የሚገጩ ሹፌሮች፣ ጋቢና ውስጥ ትራፊክ ተቀምጦ ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት የሚያሽከረክር ሹፌር፣ የተሳፈሩበት መኪና እየተንቋቋና የመበላሸት ድምፅ እየሰሙ የማይናገሩ ተሳፋሪዎች፣ በዕቃ  መጫኛ መኪና ሰዎችን የጫነ መኪና ሰላምታ ሰጥተው የሚያሳልፉ ትራፊኮች፣ ከተገዛ ሁለት ቀን የሖነው አዲስ መኪና ደረጃ አንድ በሆነ መንገድ ጠጥቶ ሲያሽከረክር የተገለበጠ ግለሰብ፣ መንገድ ለማሳጠር በእግረኞች መንገድ የሚነዱ ሹፌሮች፣ መፍጠን ልምድ አድርገውት ምንም የሚያስቸኩል ሥራም ሆነ ቀጠሮ ሳይኖራቸው የሚካለቡ ባለመኪኖች፣ ሕግ መጣስ ልምድ ሆኖባቸው የትራፊክ መብራት እየበራ የሚጥሱ፣ በህይወታቸው የራስ ወዳድነት ባህሪያቸው በመጉላቱ ቅድሚያ ለራሳቸው እንጂ ለሌሎች መስጠትን የሚጠሉ እልኸኛ ሾፌሮች፣ መቅደምን እንጂ መቀደምን የማይወዱ፣ ወዘተ… በምናይበት ሁናቴ የሰዎችን ባህሪ መለወጥ ላይ ትኩረት ያላደረገ እርምጃ ምን ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል?

በአጠቃላይም እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎችን እያደነቅን፣ እንዲቀጥሉም እየጠየቅን በቀጣይ ግን ትኩረታችንን በዋነኞቹ የችግሮቹ መንስኤዎች ማለትም በሰዎች ባህሪ ለውጥ ያመጣልና የሚመለከታቸው አካላት ያስቡበት ባዮች ነን፡፡ ያለበለዚያ ግን ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ እንደሚሉት ብሂል ሆኖብን ታጥቦ ጭቃ እንዳንሆን ያሰጋል፡፡ ለዛሬ አበቃሁ፡፡ የሳምንት ሰው ይበለን፡፡ ቻው!

‹‹አሸባሪዎቻችን›› ሲኖ ትራኮች ብቻ አይደሉም!!

ለ85 በመቶ የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ሆኖ እርምጃ ያልተወሰደበት አንድ ብቻ ምስጢር!!

ለሥራ ጉዳይ ወደ ጎጃም ስጓዝ ያየሁት ነገር ትኩረቴን በጣም ሳበው፡፡ ሁሉም እግረኞች ግራቸው ይዘው ነው የሚጓዙት፡፡ ቆም ብዬ አካባቢዬን ስቃኝ ቀኜን ይዤ የምጓዘው እኔ ብቻ ነኝ፤ ሁሉም እግረኛ ግራውን ይዞ ነው የሚጓዘው፡፡ ከቀናት በኋላ በአንድ የገበያ ቀን የወንበርማ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ሸንዲ ከተማ ቢጫ ቲሸርት የለበሱና ፊሽካ የያዙ ወጣቶች ገበያተኞችን ግራቸውን እንዲይዙ ሲያደርጉ ተመለከትኩ፡፡ እኔም አንዱን ወጣት ጠጋ ብዬ ስለሁኔታው ጠየኩት፡፡ በጎ ፍቃደኞች እንደሆኑና ሁሌም ቅዳሜ ሰውን እንደሚያስተምሩ ነገረኝ፡፡

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ፌስቡክ ላይ የሚገርም ምስል አየሁ፡፡ ከላይ ጽሑፍ አለ ከታች ፎቶ፡፡ ናይጄሪያ ብሎ ቦኮሃራም ይላል፡፡ ሱማሊያ ብሎ አልሸባብ ይላል፡፡ ሶሪያ ብሎ አይሲስ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ብሎ ፎቶ ተለጥፏል፡፡ ፎቶውም ቀደም ሲል ‹‹ቀይ ሽብር›› አሁን ደግሞ ‹‹ድሮኖቹ›› (The Drones) ማለትም ‹‹ሹፌር አልባዎቹ›› እየተባለ የሚሽሟጠጠው የሲኖትራክ መኪና ፎቶ ነው፡፡ የእኛ ሀገር አሸባሪ ይኸው ሲኖ ትራክ መሆኑ ነው፡፡ ሌሎቹ መኪናዎቹስ እያሸበሩን አይደለምን? እስኪ ዛሬ ስለ ትራፊክ አደጋ ልፃፍ፤ እናንተም አንብቡ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!

የመኪና አደጋ ሁኔታ ቅኝት

ለእንደ ኢትዮጵያ ላሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት መኪና ዋነኛው የመጓጓዣ መንገድ ነው፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ 80 ከመቶ የሚሆነው ሰው እና ዕቃ የሚጓጓዘው በመኪና ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመጣ ደግሞ በከተሞች መሀከል ከሚደረጉ የሰዎችም ሆነ የዕቃዎች መጓጓዝ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነው የሚካሄደው በመኪና ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመኪና መጓጓዝ ውስጥ አደጋ የመፈጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት ግምት መሰረት በዓለም ላይ በመንገድ ላይ በሚደርሱ የመኪና አደጋዎች በየዓመቱ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን 50 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳቶች ይዳረጋሉ፡፡ በዓለም ላይ ያለውን የአደጋ ቁጥር የመጨመር ሁኔታን ያጤኑት ደግሞ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ይላሉ፡፡ ናድ፣ ቺሾልም እና ባከር የተባሉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ2020 የትራፊክ አደጋ ከኤች.አይ.ቪ እና ከቲቪ ቀጥሎ 3ኛው ገዳይ ይሆናል፡፡

ይህን ሁኔታ በአንክሮ ስንቃኘው ደግሞ የትራፊክ አደጋ የሚበዛው በሰለጠኑትና ብዙ መኪና ባላቸው ሀገራት ሳይሆን ጥቂት የመኪና ቁጥር ባላቸው ታዳጊ ሀገራት ነው፡፡ ከዓለም ህዝብ ውስጥ 81 ከመቶ የሚሆኑ የሚኖሩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሲሆን በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ መኪናዎች በዓለም ከሚገኙ መኪናዎች ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች በብዛት የሚገኙት በእነዚህ ሀገራት ነው፡፡ እንደ ሙራይ እና ሎፔስ ስሌታዊ አገላለፅ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት በትራፊክ አደጋ ምክንያት በቀን ውስጥ 3 ሺ ሰዎች ይሞታሉ፣ ሌሎች 30 ሺ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ግምት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 227,835 እግረኞች፣ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 165,501 እግረኛ እና ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 22,500 እግረኞች በየዓመቱ በመኪና አደጋ ምክንያት ይሞታሉ፡፡

እንደ አንድ ዝቅተኛ ገቢ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ገፈቶች ቀማሽ ነች፡፡ ከቤቱ ሳይወጣ ሬዲዮ የከፈተ ሰው እንኳ ቢያንስ አንዴ ስለ አንድ የትራፊክ አደጋ ይሰማል፡፡ ጥናታዊ መረጃ ለማቅረብ ያህል እንኳ ዳንኤል አድማሴ፣ ታከለ ይርጋ እና ብሩክ ዋሚሽ የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2010 ባሳተሙት የምርምር ወረቀት እ.ኤ.አ በየካቲት እስከ ነሐሴ 2007 ወደ ጥቁር አንበሳ በአጥንት ስብራት ምክንያት ከገቡት 422 ታካሚዎች ውስጥ 49.7 ከመቶ (202 ታካሚዎች)የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ15-25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ በሬዲዮና በቴሌቪዝን የሚነገረን በግርድፉ ሲሆን ጥናቶቹ የሚነግሩን ደግሞ ወጣቶች እና እግረኞች ከፍተኛው ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ተወልደ መኮንን የተባለ ተመራማሪ እ.ኤ.አ በ2007 በሰራው ጥናት በመኪና አደጋ ከሞቱ ሰዎች ውስጥ 51 ከመቶ የሚሆኑት እግረኞች ናቸው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ ደግሞ በሀገሪቱ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የሚደርሱባት ከተማ ነች ብሎም ከሟቾች ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ሟቾች እግረኞች ናቸው፡፡

ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ?

ሀገራችን ውስጥ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ብዙ ናቸው፡፡ ጥያቄው ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ የሚለው ነው፡፡ እዚህም እዚያውም የተሰሩ ጥናቶች መንስኤ የሚሏቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

በቅርቡ ከተሰራ ጥናት ለመጀመር ያህል እ.ኤ.አ በ2014 ኃይሌ መኮንን እና ደመቀ ላቀው የተባሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በባህርዳር ከተማ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን አጥንተዋል፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ የሚያሳዩት ባህሪ እና የሹፌሮች የወንበር ቀበቶ አለማሰር በትራፊክ አደጋዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳይተዋል፡፡ ዝርዝር ውጤቶችን ስንመለከት ደግሞ፡-

– 55.5 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የተከሰቱት ከ30 ዓመት በታች ዕድሜ ባላቸው ሹፌሮች ነው፤

– 42.2 ከመቶ የሚሆኑት አደጋ ያደረሱ መኪናዎች ለረዥም ዓመት አገልግሎት የሰጡ ናቸው፤

– 69.8 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የደረሱት ለእግረኞች ቅድሚያ ባለመስጠት ነው፤

– 55.6 በመቶ የሚሆኑ ሹፌሮች የወንበር ቀበቶ የሚጠቀሙት አልፎ አልፎ ነው፤

– 57.8 በመቶ የሚሆኑ አደጋዎች የደረሱት ሹፌሮች ሞባይል እያነጋገሩ ነው፤

– 66 ከመቶ የሚሆኑት ሹፌሮች እግረኞች የተሳሳተ የመንገድ ማቋረጫ ይጠቀማሉ ብለው ያምናሉ፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባት ሀገር፣ አዲስ አበባ ደግሞ 60 ከመቶ የሀገሪቱ አደጋ የሚከሰትባት ከተማ በሚል መነሻ በአዲስ አበባ ጥናት ያደረገው ተወልደ መኮንን የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝቷል፤

– አብዛኛዎቹ አደጋዎች የደረሱት በመኖሪያ አካባቢዎች ነው፡፡

ኢብራሂም ሃሰን እና ጓደኞቹ እ.ኤ.አ በ2011 350 ሾፌሮችን በማካተት ስለመቀሌ ከተማ የትራፊክ አደጋ ጥናት ሰርተው የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝተዋል፡፡

– 233 ሹፌሮች አደገኛ የአነዳድ ባህሪ አላቸው

– 100 ሹፌሮች ስለመሰረታዊ የትራፊክ ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ ነው

– 148 ሹፌሮች እያሽከረከሩ ሞባይል የመጠቀም ልምድ አላቸው

– 28 ሹፌሮች ከጠጡ በኋላ የመንዳት ልምድ አላቸው

– 77 ሹፌሮች ከዚህ በፊት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል

ኑ! ወደ እውነት –ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

„አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ“ – ሙግት።

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

 

Cry Ethiopia in Saudiወደ እርሱ ከመግባቴ በፊት በዝና ዬማውቀውና የማከብረው ወንድሜ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ „ለውስጤ“ መልስ ሰጥቶበታል። የመልስ መልስ – እራሱን አስችዬ አላስፈለገኝም። ጹሑፉ ቅን ስለሆነ። ፍርድና ዳኝነቱን ደግሞ የጋራ ታዳሚዎቻችንም  – አሉ። መማር ያለብኝን ግን ከልምድ ዘለቅ ወንድሜ –  የምማርባቸውን ዘርፎች – እፈቅዳለሁ። የአንተን እኔ ወስጄ አንተ የእኔን ሙሉውን ውድቅ ብታደርገውም እንኳን ግድ አይሰጠኝም። ማንበብህ ብቻ – ይበቃኛል። መደማመጡ ነው – ነገን የሚያድነው። ጥቂት ነገሮች ተንጠልጥለው እንዳይቀሩ ትንሽ ልበል፤ ከዕለቱ እርእሴ ጋርም ተቀራራቢ ነው። አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ዴሞክራሲን በቲወሪ ሳይሆን እዬኖረበት እያለ በነፃነት ላይ ሆኖ፤ መሃያውን ከሌላ አካል እያገኘ ነው ዬጎጥ ፖለቲካ ፍለጋ – የሚማስነው። ለዛውም ሊተረጎም የማይችል ረቂቅ መክሊት ካላቸው የሙያው አዛውንታት ጋር እዬሠራ – እያዬ፤ ሀገራዊ መከራውን እዬሰማ – እያለ፤ ጭራሽ በሰለጠነው ሙያ በጋዜጠኝነት ሥም ሲሆን ደግሞ – ያማል፤ እያወቀ ነው የሚያደርገው። እኔ ወጣት ከነበርኩበት ጋር ለማነፃጸር ግን ዘመኑም ሆነ የኃላፊነት ደረጃው፤ እንዲሁም የሙያው ዓይነቱም በፍጹም ሁኔታ – አይገናኝም። የሆነ ሆኖ የእኔ አባት „ለሰው ልጅ“ ጥብቅና መቆምህን እጅግ አደንቃለሁ – አከብርማለሁ። እንዲያውም አዲስ ፕሮጀክት ጅምር ላይ ነው። አዲሷ እንቡጢጣ ብሎጌ „ነገና የተፈጥሮ ሥጦታ እንዴት ይታረቁ“ የሚል አምክንዮ – አለው። በርከት ያሉ ተያያዥ ንድፎቼንም ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ – ልኬያለሁ። የፖሊሲና የበጀት ጥያቄ ስለመሆኑም መልስ – ሰጥተውኛል። ነገር ግን ባጀትም ፖሊሲም ሳይስፈለግ አዬር ላይ ክርክሩን በትንሹ መጀመር – ይቻላል። እርግጥ የቀረኝ የቪዲዮ ተግባር – አለብኝ፤

ሌላው — የአንተ ሃሳብን የደገፈ ወይንም ጎሽ ያለ ሌላ ጹሑፍም – አይቻለሁ። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ለፋሺዝም ቃል አቀባይ ጥብቅና – አልቆምም። ዬአሜሪካ ድምጽ ዬአማርኛው ክፍል ቢሆን እንደ ታላቅነቱ – አንጋፋነቱ፣ ተከባሪነቱና ተደማጭነቱም እንዲሁም ተወዳጅነቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ፤ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖለቲካዊ አጀንዳ ፍላጎት አስፈፃሚዎችን፤ ዓለምአቀፍ የነፃ ሚዲያ ሥነ ምግብር የማይከተሉ ከሆነ እርምጃ መውስድ – ይኖርበታል። ደረጃውን የጠበቀ አመራር ሊኖረው – ይገባል። ሃግ በዛም ገለማም ሊሉትም  – ይገባል። ለራዲዮ ፋና ቅርንጫፍ ማህያ እዬከፈለ ሊያቆስለን – አይገባም። ከዚህ ላይ አንድ ብጣቂ ማጣቀሻ ላስታውስህ እሻለሁ የሥነ ጥበብ ኮርስ እወስድ በነበረበት ጊዜ በሸበጥ ጫማ ምንም የመማሪያ ቁሶችን ሳይዝ ተከርችሞ ገብቶ ተከርችሞ የሚወጣ አንድ ወጣት ነበር። ሌላ ጊዜ ፋቲኩን ለብሶ – አገኘሁት። ስለሰው መጠዬቅ የእኔ ዓለም ስላልሆነ ሰላምታ ተለዋውጠን የነገረኝን አድምጬ – ተለያዬን። እነሱ ለዘራዊ ድርጅታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ሥነ ምግብር – አላቸው። ስለዚህ ለፋሽስት ፋቲክ ዋቢነት – አይመችኝም።  „አመጽ“ የሚለውን በሚመለከት – ውሳኔን – ሃሳብን አልቀበለም ማለት እንቢኝ ብሎ ወይንም አሻምን ተቀብሎ ቤት መቀመጥ አመጽ – አይደለም። ሃሳቡን ዓላማውን ውሳኔውን አልተመቸኝም፤ አልተቀበልኩትም ብሎ ያልመቸውን ሃሳብ፣ ዓላማ፣ ውሳኔ ለመታገል መንፈሱን አሸፍቶ አደባባይ ፊት ለፊት መውጣት ደግሞ በሃሳቡ በዓላማው በውሳኔው ላይ „ማመጽ“ ነው። የግድ የብርት ኳኳቴ – አያስፈልገውም። ሃሳብና ሃሳብ ነው የሚፋጩት – የሚቧከሱት። ይኸው እኔና አንተ በብዕር እንፋለም የለም? እንደዛ …..

እናትዬ – የአቤን ተዎው …. አላወቀበትም። አጠረ! ያልገባህ ነገርም እንዳለ ገልጸኽልኛል። አቤን ከውስጥ አድርገህ – ሊታይህ አይችልም። የሀገራችን የፖለቲካ ጉዳይም ይኸው ነው። በውስጥ ያለውን ጽንስ ውጪ አድርጎ የመተንተን አቅም – ማነስ። ሰፍ የምትልለትን አምክንዮ ሆነ የምትጠላውንም ቢሆን ሞጥጠኽ ከውስጥህ ወጣ አድርገህ – ለዓፄ  ዕንባ ዳኝነቱን ብትፈቅድ ከወቅት፣ ከውጪያዊና ውስጣዊ፤ ከብሄራዊና ዓለምአቀፋዊ ተጫባጭ ሁኔታ ጋር ያለውን ተዛምዶና ተቃርኖ ሚዛን ላይ – ማስቀመጥ ያስችላል። ለማንኛውም አቤዋን በሚመለከት በቅንጅት ጊዜ አይበት የነበረው የበዛ ቅንነት ዛሬ ማዬት – አልቻልኩም። እልህና ውድድር ግን እያዬሁበት ነው። አንድ አቅጣጫ ብቻ እእ፤ ተቆርቋሪነትን – ለማስደሰት ሆነ ከተፈለገ ለናሙና ዘሃበሻን ማዬት – ይቻላል። የተቋረጥነውን ሁሉ ነው እቅፍ ድግፍ አድርጎ በአክብሮት – የያዘን፤ ለዛውም ማንና ምን እንደሆን ሳያውቀን – አብሶ እኔን በሚመለከት በጎንዬሽ ያለበትን ጫና ሁሉ ጥሶ መለኪያውን ኢትዮጵዊነትን ብቻ መሆኑን አሰተማረበት። የጎደለውን እያዩ – መደጋገፍ፤ ቀዳዳን – መድፈን፤ ስሱን – ቦታ ፈልጎ መጠገን። ዕንባን አይዞኽ – ይላል። ሁሉ ሰው አንድ ቦታ ላይ መታጨቅ – የለበትም። ብዙ ሰው ያልደረሰባቸው ክፍት የሥራና የኃላፊነት ቦታዎች አሉ። በተረፈ እናትዬ እግዚአብሄር ይስጥልኝ – ያክብርልኝም። ለዚህ ያበቃን ዘሃበሻ ድህረ ገጽንም – አመሰግናለሁ። እንዲህ ዓይነት ክርክሮችና ሙግቶችን መፍቀዱ ህይወት ነውና። ለነገም – ተቋምነት። አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ከተማረበት በፍቅር እብድ የሚልለት ማንፌስቶ የሚያደርገውን መራር ሃዘን የእህቱን፤ የነገን ጽንስ የጮርቃውንም ፍርጃ ፍዳና ስቃይ በዚህ ሊንክ ቢያደምጠው ደስ – ይለኛል። ሌላም አያስፈልገወም ወደ ብሄራዊነት – ለመምጣት። “Esat Menalesh Meti – Ethiopian Women and the struggle for freedom …”

http://ethsat.com/video/2015/05/18/esat-menalesh-meti-ethiopian-women-and-the-struggle-for-freedom/

ባዘገዬውም ሰላምታውን – እንዴት ናችሁ – ቤቶች! ሰሞኑን በጠ/ሚር ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ላይ ወክ እንዲህ ልል አሰኝቶኝ ሳለ፤ የተከበሩ ጸሐፊ አቶ ይገርም ዓለሙ ጹሑፍ ገጠመኝና ኃይለ – ቃሏን ብቻ ነጠል አድርጊ አውጥቼ ጠረጴዛዬ ወለል ላይ አስቀምጬ – እንድንፈታተሽ – ፈቀድኩኝ።

መግቢያ በር

እልፍኝ  ዬሙግት –  ዝመት ላሰኘው ሃሳብ፤

„ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት – ይገረም አለሙ” ዋው¡

“ወያኔዎች ትናንትም ሆነ ዛሬ አላማ ፍላጎታቸው ስልጣን ነው ከራስ ጥቅም ያለፈ አላማም አጀንዳም ያላቸው አይደሉም” ምን? በህግ አምላክ!

“እኛ መጠራት ያለብን እሱ ነኝ በሚለው ማንነቱን በማይገልጸው ሳይሆን ለማንነቱ በሚመጥነው ለግብሩ መገለጫ በሚሆን መጠሪያ መሆን አለበት፡፡ አሁን ልማታዊ መንግሥት እያለ ራሱን እየጠራ ነው ታዲያ እኛ በዚህ  እንጠራዋለን?“ ዖዬ!

“ሁለተኛው ግንባር የሚለው ነው፡ከመጠሪያው ጋር ሊቀራረብ የሚችለው ህወኽት ነው እሱ ደግሞ ግንባር አይደለም፤ ግንባሩ  ኢህአዴግ ነው፡፡ እሱን በጥቅሉ የትግሬ ነጻ አውጪ ለማለት ተፈልጎ ከሆነ ደግሞ ወያኔ ሀገራዊውን የፖለቲካ ትግል የጎሳ ትግል ለማድረግ ሌት ከቀን የሚማስንበትን ስራ እያሳካንለት ነው ማለት ነውና አደጋ አለው፡፡” ህም!

“የወያኔ ስብከትና ማስፈራራያ ያልበገራቸው በርካታ ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞው ጎራ ጥንቃቄ የጎደለው ተግባር ያለፍላጎታቸው ወያኔን ለመደገፍ  መገደዳቸው የአደባባይ ምስጢር ይመስለኛል፡፡ የሚወዱትን ሲያጡ እንደሚባለው ሆኖባቸው፡፡” ኦኦ!

ምንጭ —- http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44875

እንዴት አሉልኝ የተከበሩ ጸሐፊ አቶ ይገርም ዓለሙ። እኔ ኦድዮን ወይንም ራዲዮን ከማድመጥ ፍቀረኛነቴ እነዛን ማራኪ፣ ታይተው የማይጠገቡ ፍልቅ የብቻችን ጠረናችን የሆኑትን – ፀሐያዊ ፊደሎችን እያዬሁ ማንበብ ነው የሐሤቴ ቅምረቱ፤

የ40 ዓመቱን ሥያሜ በተለጣፊ ሥያሜ ይቀዬር ነው የጹሑፎዎት – እድምታው። ይህ በቀጥታ የሚወስደን ወደ አቶ ገብሩ አስራት ቲወሪ ነው። እኔ ደግሞ የአቶ ገብሩ አስራት ቲዎሪ ከማይመቻቸው ሰዎች አንዷ – ነኝ። የደም ሥርን በጥሶ „ገድሎ እግዚአብሄር ይማርህ“ ዓይነት ስለሚሆን በትግራይ መሳፍንት የመሬት ወራራ እንኳን ትንትና ለመስጠት ድፍረት – ስለሚያንሳቸው – ግጥሜ አይደሉም፤ ይበሉ ወገኔ ላነሱት ነጥብ እንዲህ ልሞግትዎት ….. ስለ መለሲዝም ፋሺዝም ጎጣዊ ዶክተሪን ትርፋ ትርፎች፤ እርግጥ ተዘርዝሮ ስለማያልቅ በጥቂት ጭብጦች ዙሪያ ብቻ —

„የልማታዊ መንግሥት“ በለው! ይህም በራሱ አቅሙ – አይደለም። ያለማው አካባቢ ካለ ጥብቅና – ይቆምለት። ምን አልባት በልጥፍነት ወይንም እንደ ፍሉ ማርኬት ይጠቅማል ካሉ የተከበሩት ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ  ምርጫው – የእርስዎ ይሆናል።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ፤ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር  / The Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) (Ge’ez: ህወሓት), https://en.wikipedia.org/wiki/Tigrayan_People’s_Liberation_Front ይህ የወያኔ ሃርነት ግንባር ትክክለኛ መጠሪያ መለያ ሥሙ ነው። ዓለም የሚያውቀው። ለምን እንደሚቆላመጥ፤ ደፍሮ ለመጥራት ጭንቅ የሚሆንበት አምክንዮ አብርን ስለኖርን በሚገባ አሳምሬ – አውቀዋለሁ። ለሥሙም ጥገና መጠለያ – ይፈለግለታል፤ ለበደሉ ደግሞ መሸሸጊያ – ግርዶሽ ነገር – ጉድብ። በዚህ ማንፌስቶ በነቂስ ከማህል እስከ ደንበር አንገቱ ቀና ብሎ የሚሄደው ጥቂቱ አንገቱ ተስብሮ ጎብጦ ለመሄድ ያልተፈቀደለት ደግሞ – ዕልፉ ነው። ለዚህም ነው ይህ ዬቅብረት ማንፌስቶ በጥገና ሳይሆን ከሥሩ መነቀል እንደለበት በፅናት እማምነውም።

ክቡርነተዎት – እንደሚሉት ድርጅቱ በሥም ብቻ የቀረም አይደለም። ለሥልጣን ብቻም አይደለም። ተልዕኮና ግብ ነበረው አለውም። የእርስዎ ትንተና ደግሞ ተልዕኮው ምንም አላሰም አልቀመሰም ነው የጸሑፎዎት ነገርዬው፤ እንኳንስ እኛ ያልተወለዱን – ያውቁታል። በሌላ በኩል ተበድላችሁም – ተቀጥቅጣችሁም – ተገፍታችሁም – የገፋችሁን የቀጠቀጣችሁን ዋጥ አድርጋችሁ የተገላቢጦሽ ይቅርታ መጠዬቅ አለባችሁም – ወይንም አትነካኩት – ይመስላል። እኛ የዚህ አጥፊ ሥም አፍቅሮት የለንም፤ ድርጊቱ ግን ከተነሳለት ዓላማ ፈቅ ሳይል በቁርሾ ኢትዮጵያን ሲያነዳት ነው – ያዬነው። ሥሙን ቢቀይር እንኳን የለበጣ ነው የሚሆነው – ማባጨል።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ ለታላቋ ትግራይ ህልሙ“ ለ24 ዓመት ዬበታችነት ስሜታዊ ህመሙን ለማስታገስ ቀጥቅጦ፣ ጨቅኖ በበቀል የገዛበት ብሄራዊ ማንነትን – የገነዘበት፤ ታሪክን – የገዘገዘበት፤ ትውፊትን – ያረደበት፤ ሰንድቅዓላማን እግር ከወርች ያሰረበትን ሂደት በስማ በለው ሳይሆን በዕድሜያችን ያዬነው በደም የጨቀዬ ሃቅ ነው። የተመሰረተበት የተደራጀበት ዓላማውና ተግባሩ ለአንድ አካባቢያዊ ስሜት ልዕልና ልቅና አለቅነት ወይንም ንጉሣዊ መሳፍንታዊ ሥርዓት ነው። ከዘርም – ዘር፤ ከመሬትም – መሬት በላይ በማደረግ እጅግ በተንጠራራ በተወጠረ ትዕቢታዊ – ትምክህት በዘረኝነት ስሜት። ጀርሞኖች ናዚዝም አካላቸው እንደ ነበረ – ያምናሉ። ግን በመጸዬፍ ነው። የኛዎቹ ደግሞ የተገለበጠ ነው። አብዛኞቹ ሲከበክቡት ነው – የሚታዩት። በለስ የቀናው የመንደር ድርጅት ያስገኘው ብጣቂ ብናኝ ነገር ለትግራይ ህዝብ ምንም የለም የምትሉት ነገር ካለ፤ አንድ ሁለት ተብሎ ይቅረብና በዛም ነጥብ ዙሪያ መከራከር ዲቤት ማደረግ – ይቻላል። ምላሱን የተጠቆረ የለም። አቅም አለን!

ወያኔ „ሀ“ ብሎ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ዕለት ጀምሮ የውጭ ሀገር ጸሐፊዎች በሚጽፏቸው ታሪክ ቀመስ መጸሐፍት ሁሉም ባህሉ የትግራይ ነው። ዕምነቱም – የትግራይ ነው። ትውፊቱም – የትግራይ ነው። ድንቅነቱም – የትግራይ ነው። ከመገልገያ አቅም እንኳን። ይህን በቅርበት ካሉ የውጭ ሀገር ቤተመጸሐፍ ጎራ ይበሉና – ይቃኙት። የአራስነት ቆይታ – የትግራይ፤ ክርስትና – ትግራይ፤ ሠርግ – የትግራይ፤ እንጀራ – ትግራይ፤ ቡና – ትግራይ፤ ድልህ – ትግራይ መሪ ትግራይ ጳጳስ ትግራይ …. ምን ያልተወረረ ነገር አለና። ኢትዮጵያ በመንፈስ – ተደምስሳለች። በተክለ ሰውነት በመዳፋችን ውስጥም – አይደለችም። ዕሴት አልባነቷ በረቂቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። ትግራይ አካላችን ነው በራሱ የነበረው እራሱ ይበቃውም ነበር። የብሄራዊነት ሃብታት ትሩፋትን እንዲህ በጠራራ ፀሐይ ተዘርፎ – ሳይሸለም። ባለፈው ወር CNN ሰፊ ሽፋን የሰጠው ዝግጅት – ነበረው። ትግራይ ላይ ነው የተጀመረው ደቡብ ደርሶ ማህል ሀገር ተንሸራሽሮ ትግራይ ላይ – ሰከነ። ማህል ሀገር ሳይቀር ተጠያቂዎች በሙሉ …. እሱ – በእሱ። ውዶቼ ዝም ብላችሁ ነው አምታዩት — ወይንም ልብ ሰጥታችሁ ትመለከቱታላችሁ ….? ጥቋቁር ነገሮች እኮ – ናቸው። በደሉም የሚገባን ከውስጥ ሆነን ማዳመጥ ስንችል ብቻ ነው። ወጣ ገብ አቋምም የማይኖረን ተጨባጭ መረጃዎችን ቀረብ አድርገን ጠረናቸውን ዬእኛ ብለን ማሽተት ስንችል ብቻ ነው። በስተቀር የተቆራረጠ ፍላጎት ነው የሚኖረን —- ይህም ብቻ አይደለም። ነገም መፍትሄ አመንጭነቱ ኮሳሳና የተደበቀ ነው – የሚሆነው። የተበደለ መካስ – አለበት። ቢያንስ ይቅርታ ሊጠዬቅ – ይገባዋል። በጀምላ ንግድ ከሆነ ግን ተመልሶ – እንቦጭ ነው።

የሥልጣን ክፍፍሉ፣ የልማት ሥርጭቱ ሚዛናዊነት ቀርቶ በነቂስ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ያልታዩ ያልተወለዱ ጽንሶች ሳይቀሩ  በቁርሾ በቂምና በበቀል ያልተቀጠቀጠ አካባቢ ዞን ክፍል ተቋም አለ ብሎ ለመናገር ከሃቅ ጋር ዬመፋለም ያህል – ይሆናል። የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባልነት ትግሬነት ብቻ ነው። ይህም ብቻ አይደለም በሌለች ድርጅቶችም በድርብ አባልነትና አካልነት የተፈቀደ ነው። ይህ ደግሞ የትም አካባቢ ለሚኖር ሁሉ ልዩ መለያ፤ የተዋረድ ሥልጣን መከትከቻው ነው። አሁን በምርጫው ከአረና በሰማዕት ታንቆ ያለፈው ሲቲት ሁመራ ላይ ነው። በዚህ አካባቢ የሚወለዱ ልጆች ሥም የምናውቀው የጎንደር ከወልቃይት ከጠገዴ ከቃብቲያ ከአዲረመጽ ሥሞች – ጋር ተመሳሳይ ነው። ለማንኛውም ኢትዮጵያን ሌላ የውጭ ሀገር ቅኝ ገዢ ገዝቷት ቢሆን እንኳን ሊታይ የማይችል የአድሎዊነት ዬመገለል ሰቆቃ ዘመን ነው። ልዕልት ኢትዮጵያን የውጭ ሃይሎች ቢይዟት እንኳን ሊደርስ የማይችል መከራና ፍዳ ያስተናገደችበት ግፋዊ የጠቀራ ዘመነ፤ ህማማታዊ የፍዳ ዘመኗ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለእኛ ምናችንም አይደለም – መጠለያ ጥግ ለሆናቸው ደግሞ – ትንፋሻቸው። ዲታዎችም ናቸው፤ ማንስ ነክቷቸው? እነሱ እራሳቸው ለተገፋው ዜጋ ይለፎች ወይንም ልዩ ቪዛዎች ናቸው – ለማኖር።  …. እባካዎትን የማከብረዎት በቅርፊቱ ሳይሆን ውስጡ ለውስጥ መንገዱንም ይድፈሩትና – ይሂዱበት።

„መንግሥት“ የሚለው እራሱ ለእኔ – አይመቸኝም። ኢትዮጵያ መንግሥት የላትም። ብዬም ጽፌ አላውቅም። ስለምን? ብሄራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንፃር አቅሙ ስላልሆነ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሌሎች ሀገሮች ገልብጦ ላወጣው ህግ እንኳን ተገዝቶ – ስለማያውቅ። ሥርዓቱም ሆነ አስተዳደሩ ለናሙና የሚመስለው አንዳችም ሀገር – ስሌለ። አንድ መንግሥት የኃላፊነትና ዬተጠያቂነቱ ህግ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅሙ ከራሱ መጀመር መቻል አለበት። ቃሉን በሚመለከት በአለም ሸበላ ቃሎች ሁሉ በገፍ ወደ ኢትዮጵያ በስደት – ገብተዋል፤  በአንቀፃትም ቅኝ – ተገዢነት። ቀሰማው ግን በማንነቱ ውስጥ ተቀብሮ – ቀርቷል። ያ ማንነቱ የቆመለት „ዬታላቁ ትግራይ ራዕይ ነው።“ ሌላውን ግን እንደ አደስ በመደቆስና – በመፍጨት። ስለዚህ እኔ ባይገርመወት የጎጥ አስተዳደር ወይንም ሥርዓት እያልኩ ነው እምጠራው ….. „አስተዳደርም“ መጥኖት አይደለም፤ ትንሽ ቢቀርብ ብዬ በማጠጋጋት ወይንም በማሸጋሸግ – እንጂ፤

እንደሚያውቁት ሦስቱ የመንግሥት አደረጃጀቶች አሉ። ፌድራሊዝም፣ ወጥ ወይንም ኮንፈዴሬሽን። ከነዚህ ውስጥ ሥሙን መያዝ አይደለም ቁም ነገሩ። ቁምነገሩ የሥልጣኑ ምንጭ የህዝብ ፈቃድና የህዝብ ባለመብትነት ከህይወቱ ከውስጡ በመሆን በድርጊት ሲቀልም ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የምትማራው በመለሲዝም – ሄሮዲዝም ፋሺዝም – ዶክተሪን ነው።

„ግንባር“ ተለጣፊ ናቸው። ውህደት – የላቸውም። በውህደት የተቀረጸ ደንብና ፕሮግራም – የላቸውም። ሥልጣኑንም፤ መንፈሳዊ ሃብቱም፤ ቁሳዊ ምንጩም ወደ አንድ የተማከለበት ሆኖ ነው – የሚገኘው። የአፈሯ ቡቃዬ ነኝ የሚል ማንኛውም ዜጋ ድራሹ እስኪጠፋ ድረስ በተገኘው የሚወቃበት – ባለ ሎቲዎች ግን አብዛኞቹ ተለይተው እጬጌ የሆኑበት … የክትና የዘወትር፤ ወርቅና ነሃስ በጎጥ ግንብ የተለዬበት። ቢመርም የ24 ዓመት የጨለማ ዘመን ሸክም ነውና መዋጥ ግድ – ይላል። ተጠያቂው ደግሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንጂ ሌላ ከቶ ሊሆን አይችልም። ደጋፊውም ቢሆን ትራሱ እሱ – በእሱ ነው። አንዲት ኢትዮጵያዊ ሴት ከትግራዊቷ ሴት ጋር እኩል ተቀባይነት – የላትም። ብቃት አይደለም መለኬያው፤ ዜግነትም አይደለም፤ መንደር – እንጂ —-

በዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነፃ ውጪ አስተዳደር እያንዳንዱ የእንቅስቃሴ ነጥብ በመርዝ የተበከለ ስለሆነ ሌላ የሰከነ የመንፈስ አብዮት የሚጠይቅ ተግባር ከፊት ለፊት ብሄራዊ ነፃነት ፈላጊውን ህዝብ – ይጠብቀዋል። ወንድሜ ሆይ!  ይህ የሚጎረብጠዎት ከሆነ ይህን ይስሙት ሳይሆን – ያዳምጡት።

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2015/02/03/u-s-policy-ethiopia-a-failed-state-documentary

በማድመጥና በመስማት፤ በማዬትና በመመልከት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ማዬት ዓይን ያለው ሁሉ – ያያል፤ መመልከት ግን ህሊና ያለው ብቻ ነው የሚያስተውለው። ማድመጥም ጆሮ ያለው ሁሉ ይሰማል፤ ማድመጥ ግን ልብ ያለው ብቻ፤ 24 ዓመት ሁሉን በተደሞ የመረመሩት ሥልጡኑ የአውሮፓ ማህበረሰብ „የትግሬ መንግሥት“ ብለዎታል አቅም ካለዎት እሱን – ይሞገቱት። እኔም ለዬትኛውም ድርጅት ስጽፍ የአንድ መንደር ድርጀት አይልኩ ነው – „ቁርጥ ያጠግባል“ ይላል ጎንደሬ።

የአንድ ሀገር ህዝብ መለያው ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ያለው መልክዕምድራዊ አቀማመጡ ነው። በሥሩ ያሉ ለአስተዳደር እንዲያመች ተብለው የሚደራጁት አካባቢያዊ ቤተ – አካሎችም በዚህው ተፈጥሯዊ ሥር ነው የሚታደሙት። ዛሬ ያነ አለ ወይ ሲባል – ፈልሷል። „ለታላቋ ትግራይ ህልምና ራዕይ“ ሲባል …. ተፈጥሯዊ ደንበሮች ተጥሰው ታላቅ የቅረስ ዘረፋና የታሪክ ቅጥፈት – ተከውኖበታል። ለምን? ይህ የሆነበት ምክንያት በፌድራሊዝም አደረጃጀት አንድ አካባቢ በአቅሙ ልክ ነው የአስተዳደር ውክልና ማግኘት – የሚችለው። የሥልጣን ደረጃውም – የሚዋቀረው። ስለዚህ ቀደም ባለው የትግራይ ክ/ሃገር ትግራይን በራሷ የኢኮኖሚ አቅምና ጥሪት አውጥቶ እራሷን ችላ እንድትቆም የፌድራሊዝም ተጠሪ ሊያደርጋት – አይችልም። የኢኮኖሚ አቅም ምንጭ ደረጃው ዝቅተኛ ስለሆነ፤ ስለዚህ አባል ሳትሆን ግን ተሳታፊ ብቻ እንድትሆን ሊያደርግ የሚችል የውክልና ሁኔታ መምጣቱን የሚውቁት ሄሮድስ መለስ ዜናው ቋንቋን መከለያ አደረጉት። …. ይህም የሚሠራ አይደለም። ለምሳሌ ጎጃም ቤተ – አገው አለ፤ ወሎም – እንዲሁ። ቋንቋ ይሁን ሲባል እነዚህን እንዴት አንድ ላይ ማደረግ ይቻላል? ተፈጥሯዊ መነሻ መሬታቸው በጣም – የተራራቀ ነው። ይህ በቤተ አገው ላይ አልሰራም። በትግራይ የመስፋፋት የወረራ ህልም ላይ ግን – ሠርቷል። ሌላም ምሳሌ ቤተ – ቅማንት ጭልጋ አውራጃና ጎንደር አውራጃ አለ። አሰፋፈራቸው ግን አንድ ላይ ለማድረግ – አይመችም፤ በሌላ በኩልም ጎንደር ከዕርዕሰ ከተማው ዙሪያ ያሉትና የጭልጋዎች ሥነ ልቦናዊ ሁኔታም ያደጉበትን አካባቢያዊ ሁኔታን የተቀበለና የለመደ ሆኖ – እናገኘዋለን። እኔ ሁለቱንም ቦታዎች አሳምሬ ማውቅ ብቻ ሳይሆን ኑሬ ሠርባቸዋለሁ – ለዛውም እያንዳንዱን የገጠር ጣቢያ። በብሄረሰብነት ለማጠቃለል የወሰን የደንበር ቅርበት ፈጽሞ – የላቸውም። አንዱ መተማ በር ሌላው ወገራ በር ነው። ሥነ ልቦናቸውም – እንዲሁ። ስለዚህ በዚህም አያስኬድም፤ አሜሪካ ከ100 አመት ላለነሰ በእንግሊዝ ቅኝ ነበረች። ፌድራሊዝምን ስትገነባ ከዚህ ሀገር ከዚህ ዘር አልተባለም፤ ህዝቡ በለመደውና ተሳስሮ በቆዬው ትውፊታዊ ዕሴቱ ላይ ነበር የቀጠለው፤ ይህም በመሆኑ ዛሬ ከሀገሯ አልፋ አሜሪካ የዕልፎች መጠጊያ ባለጸጋ ሀገር ሆነች። የህዝብን ስሜት የዋጠ እርምጃ ትውልድን ከፍርሰት – ያድናል።

ዬፌድራሊዝም አደረጃጀት ከሌሎች ሀገሮች – የተቀሰመ ሲሆን፤ ሲቀሰም ግን ለራስ እንዲያመች ሆኖ – ተቀልብሷል። ጀርመኖችም ፌድራሊዝምን ሲያደራጁ የነበረው አካባቢያዊ ስሜትና ቅርስ፤ ትውልዳዊ ትስስር፤ ተፈጥሯዊ ደንበሮች ንክት ሳይሉ ነበር የከወኑት። ቋንቋቸው አንድ ቢሆንም ዘይቤው የተለያዬ ነው። በባህላዊ አለባበሳቸውም የተለዩ አሉ። ግን ሁሉንም ሳይናድ ነበር የተከወነው። ዛሬ ያን የጨለማ ዘመን አልፈው የአውሮፓ ጭንቅላት መሆን የቻሉትም በዚህ አመክንዮ ውስጥ ብልህ የሆነ ሥልጡን ተግባር በመከወናቸው ነው። ህዝቦች ቀድመው በኖሩበት፣ በተዋህዳቸው በሚያውቁት አካባቢ ሥነ ልቦናቸው ጫና ሳይኖርበት፤ ሳይከፋቸው እንዲኖሩ በቅናዊ አስተዳደር ነው በሌሎች ሀገሮች – የተደራጁት። ይህን ቁልጭ ባለ መልኩ ከጀርመን ሆነ ከአሜሪካ የፌድራሊዘም የአደረጃጃት ታሪኮች ማዬት ይቻላል።

ሰሞኑን ጠቅላይ ሚር/ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያጎረሷቸውን ሲነግሩን ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵውያን ላይ ያለውን የመብት መደፍጠጥ ሲያቀርቡ ሃስት በማለት ሲያቅራቸው፣ ሲያጣጥሉ ባዳመጥንበት ጆሮ ዛሬ ደግሞ ከ100000 ላለኑሱ የኤርትራ ወጣት ስደተኞች በተቆርቋሪነት የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ያቀረበው ሪፖርት እውቅና ሲሰጡ በተመሳሳይ ምላስ – አዳምጠናል። ኢትዮጵያ ላይ ሲሆን – አይሰራም። የፌድራሊዝም አከላልም – እንዲሁ ነው። ሙልጭ ያለ ቅጠፈቱ በእያንዳንዱ አመክንዮዊ ጉዳይም ትግራይን በማላቅ በማስመቸት ነው። ስለዚህ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ለትግራይ ምንም አላደረገም – የሚለው መከራከሪያው ደመ ነፍስ ነው። ግጥም አድርጎ የፈለገውን ከውኗል። መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ጥበቃ በተለዬ ሁኔታ – ተከናውኖበታል። ይህ በቀላሉ ሊታይ የሚችል አይደለም እጅግ – ረቂቅ ነው። ከጠባብ ቤት ሰፊ ቤት የበለጠ – ይደላል፤ ከኢትዮጵያዊ ዜግነት ይልቅ ዛሬ ትግሬነት አልጋ ባልጋ ነው። ሌላው ቀርቶ ቋንቋውን መናገር ልዩ ሽልማት – ያሰጣል። ከአዲስ አባባ ወይንም ከጎንደር ተነስተው ለክርስትና ትግራይ ድረስ መሄድ የተለመደ – ሆኗል። ካለው ተጠጋ … እንዲሉ ሆኖ እዬታዬ ነው። ለደጅ ጥናት። እኔ ይሄንን ዘመነ የትግራይ መሳፍንት እለዋለሁ።  እኔ በጣም እማወቀው ዲታ ሰው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣን እንደያዘ አክሱም ጽዮን – ሄዷል፤ ደጅ ጥናቱ ለማይገሰሰው የመዳህኒዓለም ቤት – አይደለም።

… እእ ደጅ ጥናቱ ለትግራይ ነፃ አውጪ አስተዳደር ግብር ለማስገባት ነበር፤ ምክንያቱም ከዛ በፊት መሄድ ይቻል ነበር። እንደ ቁልቢው ጉዞ …. ሰው እሱነቱን እያወጣ እዬጣለ በራሱ ላይ የሥነ ልቦና ጥቃት ሁሉ ፈቅዶ ፈጽሟል – የብሄራዊነት – ንደት፤ ይህም ብቻ አይደለም ዕድምታው ማንነትን በፈቃዱ – ይሸረሽራል። እራሱን – ይሸጣል – ይለውጣል። የመንፈስ ወራራ፤ የታሪክ ወራራ፤ የመሬት ወራራ፤ የትውፊት ወረራ – የሃብት ወረራ – ገኗል፤ በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘር ቆጥሮ መጠጋት የመኖር ህልውና ጉዳይ  ሆኗል። „ከትግራዊነት ጋር ተጋብቶም ተዋልዶም ክርስትናም ተናስቶም ብቻ በሆነ ክር ከዘመንተኛው ጋር ተዛምዶ መኖር ነው መስፈሪያው – ልኩ፤ ቀና ብሎ እንዲሄድ የሚያደርግ ልዩ ጆከር“ ይህን እውነት ዳጡት ነው የእርስዎ አምክንዮ …. እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ደግሞ – አስፈንጥረዋለሁ። አላስጠጋውም! አንድ ቀን ብርሃን የወጣ ዕለት ድህነት – ምህረት – ይቅርታ ማውረድ የሚቻለውም ዕውነቱን ስንደፍር ብቻ ነው። እንደጎበጥክ የአንጀትህ ሴል እንደረገፈ ተሸከም ግን ሌላ የጭንቅ ዘመንን – ይተካል። ቢያንስ የመንፈስ – ካሳ፤ የተቀጠቀጠው መንፈስ እንዲያገግም ጥንቃቄነት ያልተለዬው የአያያዝ ልዩ ጥበብና እንክብካቤ – ብልህነትም ያስፈልገዋል። ድርድር ሊደርግባቸው በማይገቡ የመሬት ጉዳዮች ላይ ቁልጭ ያለ ግልጽነት ያለው በህግ የተደነገገ ደንበር መሥራት ግድ – ይላል። በስተቀር አይቀሬው – አይቀሬ ይሆናል።

ለነገሩ ተዘርዝሮም አያልቅም ጥቂቶችን ግን እንሆ ====

  • ዛሬ ከጣና ለተሳበው የኤሌትሪክ አገልግሎት መብራቱ ለትግራይ ነው። ዘበኛው በተራ ሌትና ቀን የሚጠብቀው ግን በመስመሩ የሚልፍባቸው ደሃ ጨርቅ ለባሾች ገበሬዎች – ናቸው – እነ መከረኛ። ጨለማ ውስጥ በእንጨት ጭስ ብልጫታ እንደ ዛሬ ሺህ ዓመታት ይኖራል – የሁሉም ነገር መፈተኛው፤ ቢያንስ መብራት ይዞ ማብላቱን እርሰዎ እንደ ሰው ምን ይሉታል? !!!!! ?
  • የአባይ አጀንዳ አበቃለት መሰል፤ ጭጭ ሆኗል፤ እሱም ቢሆን የራሱ ትዕይንት ተቀመሮለት የተከወነ ነው። አባይን እስከ ምንጩ ለመቆጣጠር —-
  • ማትሪክን አልፎ ለመግባት „ትግረኛ ቋንቋ“ አብይ መሥፈርት ነው። + ሆነለት ማለት ነው።
  • ዬመተማ ወደብነት ለሱዳን ግንኙነት – ይህም የእግር እሳት – ስለሆነ፤ ቀጥታ ወደ ትግራይ የሚገባ መስመር ከመንፈስ አልፎ መሬት ላይም የወረደ ተግባር እዬሆነ ነው ….
  • የኢፍርት ህዝባዊ ሃብትነት ብሄራዊ ሲሆን ጥሪቱ ተሟጦ ዬት ላይ እንደ ሆነ ልበዎት – ያውቀዋል። ቀድሞ ነገር አንድ ሀገርን የሚመራ ድርጀት ከብሄራዊ ሃብት ማፊሪያ ውጪ ይፋ የሆነ ግንጥል የኤኮኖሚ ተቋም ሲኖር የወያኔ ሃርነት ትግራይ በዓለም የመጀመሪያው ነው።
  • ሰሞኑን ትንሽ ገጭ ገው ቢኖርበትም፤ ከጁቡቲ ትግራይ አሰብን አቋርጦም ከአዲስ አበባ ጁቡቲ የነበረወን የንጉሦች ንጉሥ የዓጤ ሚኒሊክን ጥሪት ለመፋቅ የታሰበ ሌላው ጉዳይ ነው፤
  • በትምህርት ዘርፍ ዛሬ ማዬት አይቻልም ትምህርት የረጅም ጊዜ ሂደት ውጤት በመሆኑ (education) ፤ በዚህም ዘርፍ ኮንፒተራይዝድ የማደረጉ ተግባር መሬት ላይ እዬወረደ ነው ….
  • ለማናቸውም ናሙናዊ እድገት ዬልምድ ልውውጥ ትግራይ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል …. ሌሎች ለምስልና ለሽፋን ነው፤
  • ለተቋማት ምስረታም ሩጫ ማራቶን ሽልማቱ ያው ለትግራይ ነው ….. የአሸናፊዎች አሸናፊ ተወዳዳሪ አልቦሽ።
  • ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አቅጣጫቸው ወደ ትግራይ ነው …..
  • በስፖርት፤ በባህል፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ በከፍተኛ የትምህርት የውጪ ሥልጠና፤ ቅድሚያ ኢትዮጵያዊ ዜግነት አይደለም። ትግራዊነት ነው፤ ዛሬ ሯጭ ከደቡብ ብቻ አይደለም – ትልቁ የሥልጠና ማዕከል ትግራይ ላይ ነው።
  • ቶሎ ጉዳይን በማስፈጸም፤ ቶሎ መረጃ በማግኘት፤ ተሎ ተደማጭ በመሆንም፤ ቶሎ እውቅና በማግኘት የተሻለ አክሰስ ያለው የትግራይ ተወላጅነት ነው።
  • ታሪክ ባህል ጉብኝት ሁሉም ማዕከሉ – የትግራይ ነው። ….
  • አቤት! ስንት የቲያትር የፊልም ተዋናዮች ፈሩ …. „ቅመሞች“ ካለነሱ ቅስቅስ የሚል አንድም ፕሮጀክት – የለም። አላበደም አንድ የፕሮጀክት ማናጀር ከእነሱ ውጪ ….
  • ከስሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከላይኛው ማዕከለዊ መዋቅር እስከ ገጠር የከተማ ሱቆች ድረስ ሁሉም የሃብት ቁጥጥር በአንድ ጎሳ ሥር የተጠቃለለ ነው። የእኛም ስጋት ይሄው ነው። እንደ ሰው ለምናስበው፤ አንድ ነገር ቢፈጠር በአግባቡ ማስተዳደር ካልተቻል ቅድመ ሁኔታውን በላቀ ሥልጡን አማራር ማስተዳደር ካልተቻለ መከራው እጅግ አሰቃቂ እንደሚሆን – ስጋቱ እንቅልፍ አልባ – ያደርጋል። የቂም ውርርስን ሰብዕናችን – ስለሚጸዬፈው። የነገ ኢትዮጵያ መከራው በቁርሾ እንዳይወራረድ በመቻቻል እንዲሰክን – እንሻለን። ግን ዛሬ ያለውን ሃቅና በደል በመረገጥ – አይደለም። ለበደሉ መታመንን አብዝቶ ይጠይቃል ዘመኑ – መከራን ለተቀበለ መንፈስ ታማኝነት ይጠይቃል – በአንክሮ።
  • ብዙም እሩቅ አይደለም በቅርቡ አዬር መንገድ ካሰለጠናቸው 50 ቴክኒሻኖች 48ቱ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ይህ ለናሙናነት እንጂ የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባላት የዬትኛውም ቦታ አዛዥ ናዛዥ እንሱ ናቸው። ለድርጀቱ አባልነት ፈቃድ የሚሰጠው ደግሞ መስፈርቱ „ትግሬነት“ ነው። ከቶ ይህ ከስታስቲክ ውጪ ሆኖ ይሆን – ለርስዎ?
  • የደረጃ እድገት፤ ለሁለተኛ ለሦስተኛ ቀጣይ የትህርት ዕድል፤ የአክስዮን ድርሻ ስንቱ ይዘረዘራል …. ነጭ ለባሾች እነሱ ናቸው።
  • በተገኙባቸው ድርጅቶች መዋቅሮች ፈቃድ መዋቅራዊ መንግስታዊ አይደለም የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባልነት ብቻ ነው። ማናጀሩ የሌላ አካባቢ ሰው ከሆነ „ፎቶ“ ብቻ ነው የሚሆነው። አንዱ ብቻ ብዙ የተከማቸ ሥልጣን አለው – ተራው ካድሬ ማለት ነው። ካድሬ ባይሆንም። ….. ሌላው ደግሞ የበይ ተመልካች እንዲሆን እንኳን አልፈቀድለት ብሎ – በሳንጃ፤ ጎራዴውም አልበቃ ብሎ – በማደንዘዣ ….
  • የኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድነት ወሳኝ ጂኦ ፓለቲካል መልካምድራዊ አቀማመጧን እንዲለወጥ በማድረግ ክብሯን ሲቀንሱ ኤትርትራ የምትባል ሀገር ፈጥረው ነው። ጸሑፎዎት ይህን መሰረታዊ ጉዳይ በአግድሞሽም ይሁን በሰቃዊነት ዘሎት አልፏል፤ ዛሬ ደግሞ እነሱዎ ለሠሩት ኡኡ ሲሉ ይደመጣሉ፤ ኢትዮጵያ ግን አምላክ አላት ሰው ሠራሽ ሴራን የጨው ውሃ የሚያደርግ። አናቆራቸው።

ለኢትዮጵያ ህዝብ ለገጠሩም ለከተማውም መሬት የደም – ቧንቧው ነው። በዚህ ዘርፍም ተመሳሳይ የተዛባ ስርጭት ነው የሚታዬው፤ ከዚህም አልፎ ሰፊ መሬት ተቆርሶ ከወሎና ከጎንደር ወደ ትግራይ ተክልሏ። ትናንት አባቶቻችን ሲነገሩን እስከ ሃይቅ እስከ ባህርዳር የጎንደር ነበር ይባል ነበር። ጋብቻውም እንዲሁ። ዛሬ ያ ተርስቷል። አሁንም ከሁለቱ ክ/ሀገሮች የተዘረፉ መሬቶች ተረተረት እንዲሆኑ እዬተፈለገ ነው። ልምምድ – እዬተደረገባቸው ነው። የአነ አቶ ገብሩ አሥራት ቲወሪም ይሄው ነው „ህዝብን እዩ“ ይሉናል ማላገጥ።:፡  አሁን ጎንደር የፌድራሊዝም ደረጃ ይሰጠኝ ብትል – አትችልም። ለምን የኢኮኖሚ አቅሟ – አይፈቅድም፤ ጎንደር ስሜኑ አራት አውራጃዎች ነበሩት ጭልጋ – ወገራ – ጎንደር – ስሜን አራቱም አውራጃዎች ተቀራምተዋል፤ በጭልጋ አውራጃ በኩል መተማ ለጉምዝና – ለሱዳን፤ ወገራ – ስሜን – አውራጃና ከጎንደር አውራጃም ዬአርማጭሆ አካባቢ ለትግራይ – ተስጥቷል፤ ዩኒስኮ በቅርስነት የመዘገበው ፋሲል ግንብ ብቻውን ኤሉሄ እያለ ነው። በተከበሩ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ስልታዊ የማፈግፈግ ሂደት የዳነው ፋሲል ግንብ ዛሬም የስጋት ምንጭ ነው – ለሥርጉተ። ፈንጅ ይቀበርበት ይሆን ወይንስ ያ የቅርስ የታሪክ ጌታ ዘመኑ በምን ይጠቃለል ይሆን? ዕንቅልፍ የሚነሳኝ ጉዳይ ነው። ማፍለስ ነውና የወያኔ ሃርነት ትግራይ – ተልዕኮ፤ ተዘርዝረው የማያልቁ ተጽፈው ያማይዘለቁ የተዛነፉ ግፎች – ተፈጽመዋል። አልተጠቀመም የትግራይ ህዝብ ለማለት በፍጹም – አይቻልም። የጥንታዊ ቤተ ክርስትያን ቅርሰ ቅርስማ ስንቱ …  አጋፏል – እስኪበቃው። አንዲት ነገር ግን ከትግራይ ንክች – አላለችም። ከቅርሰም ከትውፊትም።ማን ደፍሮ! አፋርም – ያሰጋዋል – ካልበረታ። የሰው ዘር ምንጭነቱ የበታችነት ስሜት ለሚያናውዘው የጎጥ ድርጅት የእግር እሳት ነውና። እነዛ በዬቦታው አሉ የሚባሉት ዲታዎች እኮ ዘረ መነሻቸው – ትግራይ ነው። አንዱ ሲዳላው ሲመቻው ቤተሰቡም ቀና ይላል። በአማካኝ አምስት ሰው ይዞ – ይበላል። ለነገሩ እነሱም – አይሉም፤ ምን አልባት ቁስለኛ ላልሆነ ሰው ባዕዱ ሊሆን – ይችላል። ቀን አይቶ የማይከዳው ንጉሥ ዕውነት ግን ይሟገታል – ታሪክም ጥብቅና ይቆማል። ወገኖቼ ሁመራና መተማ ማለት እኮ ካሽ ክሮፕ እኮ cash crops ነው። ዶላር እኮ ነው የሚታፈሰው። ተዝቆ የማያልቅ የሃብት ክምችት ነው ያለው ከዛ። ግን በዕብሪት ተዘረፈ። ሥነ – ልቦናውም በጩቤ ተዘለዘለ።

ለዚህም ነው ከዚህ አቋም ለዬት ብለው የሚወጡትን እጅግ ጥቂት የትግራይ ልጆችን እንደ ብርቅና እንደ ድንቅ የሚታዩት። ወደ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲም ሲቀላቀሉ እንደ ሌላው አይደለም። ተነጥፎ ተጎዝጉዞ በተለዬ ሥርዓትና ወግ ነው። ለምን? ከህሊናዎት ጋር ቁጭ ብለው ይፋረዱ ….. የነገይቱ ኢትዮጵያ ይህን የተዛበ ሥርጭት፤ አካለ ጎደሎ የሆነ ዬአያያዝ ክርጭጭት ማስወገድ-  ይኖርባታል። አንድ ዜጋ በሀገሩ እኩል ነው። አንድ ዜጋ በሀገሩ እኩል መብትና ግዴታ አለበት። ለዜግነት የክትና የዘወትር የለም። ይህ በተራ ቀላጤ ሳይሆን በህግ ሽፋንነት ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ የሰብዕ መብት ነው። በመዋቅር አስፈጻሚነት እዬተከወነ ያለው አድሎዊና አግላዊ ሥርዓት መልክ ሊያስይዝ የሚችል፤ በዚህ የዘበጡ ጉዳዩች ላይ ደፍሮ እርምጃ መውሰድ የሚችል ሥርዓት ነው እኔን የሚናፍቀኝ ….. ህግ የሚዳኘው። እራሱም በህግ የሚተዳደር ግልጽነት ተክለ – ቁመናው የሆነ በስተቀር „አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ“ ነው የሚሆነው …

አዎን ገዢያችን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ወይንም ግንባር ህወሃት ነው። እኛ ኢትዮጵውያን ባሪያዎች እነሱ ደግሞ ዘመን ላይ ያንጠለጠላቸው – ጌቶቻችን ናቸው። ዛሬ የባሬያና የጌታ፤ የጌታና የሎሌ ሥርዓት ነው ያለው …. ከባርነት ነፃ ለመውጣት መጀመሪያ በችግሩ ላይ ግልጽነት ያለው ያልተደበሰበ አጋሰስ ያልሆነ አቋም ሊኖርን – ይገባል። ድፍርስ በሽታ ነው። የተበደለውን ህዝባችንም ባናስከፋው ጥሩ ነው። ቢያንስ ለተቀጠቀጠው መንፈሱ ጥብቅና መቆም – የአባት።

አዎን እርግጥ ነው። ዘመናዮች በሚታይ ነገር ማለቴ ነው ጥቂት የትግራይ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ፤ በማይታይና በረጅም የማደራጀት መልሶ – ዬማቋቋም፤ በተረጋጋ የማስልጠን ተግባር ሲታይ ደግሞ እስከ ልጅ- ልጅ ሊዘልቅ የሚችል የትግራይን ህዝብ በተጠቃሚነት ሊስቀጥል የሚችል ዘርፈ ብዙ አልሚ ፕሮጀክቶች ሌትና ቀን እዬባተሉበት ነው – በኢትዮጵውያን ሃብት። እርግጥ ዛሬም ትግራይ ላይ በባዶ በእግራቸው የሚሄዱ ገበሬዎች ሊኖሩ – ይቻላሉ፤ በመሸታ ሊተዳደሩ የሚችሉ ሴት እህቶቻችን ሊኖሩ ይችላሉ። ዘለግ ብለው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን፤ የተጣሉ መሰረቶችን ስናይ ግን ከደቡብ አፍሪካ የተመክሮ ማሳ መማር ያለብን – ይመስለኛል። ዛሬ ዬናዬው የሃቅ ወርቅ አለ። እንደገናም ዛሬ የናዬው ከ20፣30 ዓመት በኋላም የሚታዮ ምጥቀቶች አሉ። ለማናቸው ነገር ለመንፈስ – ለሥነ ልቦና በዬነጥብ ጣቢያው ይህንን ተልዕኮ ጥበቃ የሚያደርግ ጥግ ይዘው የተቀመጡ ግን በአግባቡና በውል የተደራጁ የቀደሙ ደጀኖችም – አሏቸው። በተቃዋሚነት – ሥምም። የኛው የተቀጠቀጠው መንፈስ ደግሞ አውላላ ሜዳ ላይ ነው ያለው። ሳሩን እንጂ ገደሉን – አላዬም። መሰናዶውም – እንብዛም ነው። ባሊህ ባዩም – እስተዚህም ነው። አንደኛው እንዲህ አይነት መንፈስን የሚያዝሉ ጹሑፎች እና በማር የተለወሱ መርዝ የሚተፉ መጸሐፍቶች ናቸው። እኔ የልጆችን መጸሐፍት ስጽፍ እንዴት ተጨንቄ እንደፃፍኩት፤ ምን ያህል ጊዜም እንደበላብኝም – አውቃለሁ። እኛ ባለፍነበት ንትርክ እነሱ ማለፍ ስለለባቸው ነበር ያን ያህል በጥበብ ድክም ብዬ – የሠራሁት። የልጆች ራዲዮ ዝግጅቴም እንዲሁ ፍቅርን – ለማውረስ ይተጋል። ለማንኛውም አስከ ዛሬ ከአጠገባቸው ድርሽ ያላልንባቸው ያላዬናቸውም የተኛንባቸው ሃቆችን ቢያንስ ዛሬ ዓይናችነን ከፍተን ማዬት – ይኖርብናል። የተበደልን – ወገኖች። ለዚህም ነው እኔ የጥገናዊ ለውጥ ግጥሜ – የማይሆነው። ጎጠኝነት ከሥሩ በህግ መነቀል – መታገድም አለበት ባይ ነኝ። ሀገረ አሜሪካን ያዳነውም ይሄው ነው። ጀርመን ውስጥም፤ አፈንግጠው ሊወጡ የሚችሉ ረባሽ መንፈሶች በህግ ቀደመው – ስለታሠሩ። እርግጥ መታሠራቸው ብቻ በቂም አይደለም፤ ጥበቃ የሚያደርግ የህግ አስፈጻሚ፣ የቁጥጥር አካሉ የመሰረቱ አስኳል ህዝባዊ መሆን – ይኖርበታል። የቃላት ድርድር ሳይሆን ከእብለት ጋር የማያድም ወይንም የማይደራደር – ልቅና። ፖለቲካና የሰው ልጅ መብት መከበር ለአንድነታቸውም ለልዩነታቸውም ዘርፍ አለው። ብልሆች ብቻ ያውቁታል። የፖለቲካ ትርፍ የሰብ ውስጥን ማፍካት ካልቻለ ንቃቃት – ያስከትላል።

የነፃነት ትግሉ በሥነ ልቦናዊ ዘርፍም ጥበቃ ማድረግ – ያስፈልገዋል። እኔ እርስዎ የጻፉት ጹሑፍ የፈንጅ ያህል ነው – ያቆሰለኝ። አይደለም – ሌላውን። እያቅለሸለሸኝ ነው – ያነበብኩት፤ ስለምን? በአጋጣሚዎች ምክንያት ብዙ ነገሮችን በጥልቀት ስለማዳምጣቸው። እርግጥ ነው እማደንቀው አቋም አለዎት – በቀደምቶቹ ጹሑፎዎት፤ በዚህ ፁሑፍ ግን መገናኘት አይደለም መቀራረብ የሚያስችል አቋም የለኝም። እና ደግሞ ተግቼ – እታገለዋለሁ። ሚዘኑን የሳተ ትንተና ነውና። ውሎው ጦር ሜዳ ነበር – የብዕሩ ማለቴ ነው። የሆነ ሆኖ በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚ የሆነውም ቢሆን የሚበልጥበትን መምረጥ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን – ያደርገዋል። በዚህ የመከራ ዘመን መከራን የመረጡ፣ እስራትና እንግልትን የመረጡ እጅግ ጥቂት – ደሞቻችን አሉ። እንደነሱ መሆን መቻልን አብዝቶ ዘመኑ – ይጠይቃል። አንስቼ የማልጠገበው ዬውዴን ዬአብርሽን አርያነት መከተሉ መንገዱ ይህ ብቻ ይመስለኛል – መፍትሄውም። ጎጠኝነትህ ከረፋን – ኢትዮጵዊነታችን ይበልጥብናል፤ ከብዙሃን መከራ ጋር መኖር ይሻለናል ማለት – አለባቸው። ድሎት ያገኙባቸው አመክንዮችንም ቢሆን የእኛ አይደሉም የዘረፋ ነው፤ ለሥጋም ለነፍስም የማይሆን በማለት …. መሞገት ይኖርባቸዋል – የአካባቢው ተወላጆች፤ … በተዘረፈ ሃብትና ንብረት ዬወርቅና የጨርቅ መተያያ ቅብጥና ቅልጥ ዘመኑን ከሚያደርጉት፤ በዬሾጎሬው በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽሙትንም በደልንም – ቢያስታግስት። ጭንቅላት መፈጥፈጥ ልጅ -አያወጣም። የሁሉም ዳኛ ደግሞ አለ ከላይ። ወደ ላይ የሚረጭ ዕንባ፤ ቀን እንደ ጠቆረ አይቀርም – ያልፋል። ይህም ያልፋል፤ ያ እንዳለፈው ሁሉ፤ ለማንኛውም  ….. ተለይተው ገፍትረው መውጣት – ይኖርባቸዋል። ተለይቶ ሲወጣ ግን በተጋደመ ወይንም በተጣነነ ወይንም በተንጠባጠበ ዕሳቤ ሳይሆን ቁልጭ ካለው ሃቅ ጋር ፊት ለፊት መተያያት በመቻል – ድፍረት።

መውጫ በር

በጣም ክብካብ የሚደረግላት እንደትነካ የምትሻ ጉዳይን ወኔን – ትሻለች። ስንደፍራት መዳህኒትና ፈውስ ናት። በስተቀር ነቀርሳ ትሆናለች። ዬነቀርሳነቷ ዘመን ተሻጋሪነቱ አይቀሬ ነው። ….  ቀደም ብዬም ለሌላ ጉዳይ ለንጽጽር ያቀረብኩት የአንድነቱ ልዑል የአባ አሉላ ነጋ ልጆች ዬህብረ ብሄር ፓርቲን ሊቀላቀሉ ሲመጡ ብርቅ – ሲሆኑ በተደጋጋሚ – አይቻለሁ። ይነጠፋል – ይጎዘጎዘል። ሚዲያው ሁሉ  ውደሳውን ተቀብሎ – ያስተጋባል። ሥርጉተ ደግሞ – ትስቃለች። ስለምን? ይህ እኔ ለአንድነቱ ልዑል ለአሉላ አባ ነጋ ልጆች ክብር – ስለማይመስለኝ። ኢትዮጵያዊነትን ‚ሀ‘ ብሎ መጀመር ዓይነት ስለሚሆን ፊኖሚናላዊ አምክንዮው ድንብስ – ይሆንብኛል። እንደገናም ዬግንዛቤ ደረጃውም ቢሆን ልል ሰብዕናን – ይጋብዛል፤ ስለዚህ ሊቀበሉትም ሆነ ሊደሰቱበትም አይገባም – ባይ ነኝ። ስለዚህም አንቴናቸውን ወደ ቀደምቱ ቢያደርጉ ብዙ ነገር ያተርፋሉ – እላለሁ። ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና። ጣዕሙም – ለዛውም – ውበቱም – ልቅናውም ፍጹም ነው ኢትዮጵያዊነት! ኢትዮጵያ ሁሉንም ናት! ዛሬ ከእጃችን ወጥታለች …. ሁነን እንሁንላት!-  ትግሉ ለዚህ መሆን አለበት። ከውስጣችን ይክፋን – ስለእሷ!

ስማንም አይነም ዕውነት አርበኞች አሏት፤ እውነት ገበሬዎች አሏት፤ እውነት ደጀን ናትና በእሷ መሪነት ፍልሚያው ይቀጥላል። ኑ እስኪለን ድረስ ለታሪክና ለትውልድ በሚበጅ መልኩ ታሪካችን አደራጅተን ማለፍ ግድ  -ይላል። ኑ ወደ እውነት፤ በመጨረሻ – ዘመናይነቱ ሆነ መረማማጃው በቁስል ላይ ባይሆን መልካም ነው።

የኔዎቹ ለነበረን ሸበላ የመደማማጥ ጊዜ አከበርኳችሁ። መልካም ሰንበት! ቸር – ያሰማን።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ኑ ወደ እውነት!

የትግራይ ፋሽዝም ገለማኝ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (ክፍል ፫) አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

 

ረቡዕ፤ ሰኔ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህቱረት ( 6/17/2015 )

የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል አራማጆች፤ ከሌሎች ሰላማዊ ትግል አራማጆች የምንማረው

በክፍል አንድ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ገልጫለሁ። በክፍል ሁለት ደግሞ፤ ስለሰላማዊ ትግሉ ያለንን ግንዛቤ አሳይቻለሁ። በዚሁ በሶስተኛው ክፍል ላይ፤ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሰላማዊ ትግል፤ ከሌሎች ከዚህ ቀደም የሰላማዊ ትግል ካካሄያዱ ሀገሮች የምንማረውን ተመክሮ እዘረዝራለሁ። ሰላማዊ ትግሉ፤ ዕለት በዕለት በገዥው ወገንተኛ አምባገነን ገዥ መንግሥት ፊት ኑሯቸውን በመምራት፤ በመንግሥታዊ መዋቅሩ ከተሰገሰጉት ካድሬዎች ጋር የሚላተሙ ኢትዮጵያዊያን፤ ትኩረታቸው ውስን ሆኖ፤ በጠባብ ጥያቄያቸው ዙሪያ ተጠምደው፤ በትምህርት ቤታቸው፣ በገበያ አዳራሻቸው፣ በእርሻ መስካቸው፣ በመሥሪያ ቤታቸው፣ በሚሠሩበት ፋብሪካ፣ በቀበሌያቸው፣ በገበሬ ማህበራቸው፣  ወታደሮች ለግዳጅ በተሰማሩበት ቦታ፤ ለኒሁ ውስን ጥያቄዎች መልስ ፍለጋ ሲሯሯጡ፤ በቦታው ተገኝቶ እኒህን ጥያቄዎቻቸውን ሀገራዊ ይዘት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። እኒህን ውስን የአካባቢ ጥያቄዎች፤ በሀገራዊ ራዕዩ ቦታ ሠጥቶ፤ መታገያ ዕሴቶች ሆነው፤ ሕዝባዊ መነሳሳት እንዲከተል ማድረግ ነው። የገዥው ክፍል እንዲህ ባለ በጉልበት የመግዛት ሂደት ሲሰማራ፣ ድህነት በሀገራችን በነገሠበት ወቅት፣ ሙስና በገዥው ክፍል ውስጥ ባህል ሆኖ ሲደራ፣ አድልዖ የዕድገት መሰላል በሆነበት አስተዳደር፣ ሕዝቡን በመርገጥ ግፉን ሲያበዛ፤ ሕዝቡ እምቢ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ማመጹ፤ የሕልውና ጉዳይ ነው። ለዚህም ሕዝቡ እምቢተኛነትን ይዟል። ትክክለኛ ላልሆነ አሠራር ተባባሪ አልሆንም ብሏል። ሰላማዊ በሆነ እምቢተኝነት፤ የኅብረተሰቡን የፖለቲካም ሆነ የማንኛውም የአስተዳደር በደል ምንጭ አጥፍቶ፤ ትክክለኛ የሆነ ሥርዓት ለማምጣት ተነስቷል። እኒህ ሰላማዊ ታጋዮች፤ ሕዝቡን በማስተማር፣ ከፍተኛ ሕዝባዊ መዋቅር በመዘርጋትና ሕዝቡን በማነሳሳት፤ አጠቃላይ መሬት አንቀጥቃጭ ንቅናቄ ለማስከተል ቆርጠው ተነስተዋል። ታዲያ ከሌሎች የሰላማዊ ትግል ካካሄያዱ ሀገሮች፤ ምን ተመክሮ እንቀስማለን። ይህን ለመመለስ ነው ይህ ጽሑፍ የሚጥረው።

ሰላማዊ ትግል፤ በአመጽ ያለውን ገዥ ክፍል ለማስወገድ በመሰለፍና፤ ያለውን እንዳለ ተቀብሎ በመኖር መካከል ያለ የሕዝብ ይሄስ በቃ የማለት እርምጃ ነው። ያለውን ተቀብሎ ባለው ሥርዓት ሥር ለመኖር መወሰን አንድ ነገር ነው። ባንጻሩ ደግሞ፤ ያለውን ሥርዓት አውግዞ፤ ያንን ለመለወጥ ነፍጥ አንግቦ መነሳት ሌላው ነገር ነው። በመካከል ያለው ሰላማዊ ትግሉ ነው። ይህን ትግል፤ ከሕንድ እስከ አሜሪካ፣ ከፖላንድ እስከ ጓቴማላ፣ ከደቡብ አፍሪቃ እስከ በርማ፣ ከፊሊፒንስ እስከ ጀርመን፣ ከቻይና እስከ ቼዝ ድረስ፤ ታጋዮች አካሂደውታል። በርግጥ በቻይናና በበርማ ግፈኛ የሆኑ አምባገነን ገዥዎች፤ አረመኔነት በተመላበት መንገድ፤ የሕዝቡን አመጽ ለጊዜው አዘግይተውታል። እኛ፤ ከተሳኩትም ሆነ ካልተሳኩት የምንማረው አለ።

መሠረታዊ የሰላማዊ ትግሉ ማሽከርከሪያ፤ የገዥውን ክፍል ውስጣዊ ችግሮች በማባባስ፤ ቅራኔውና ውጥረቱ በታጋዩ ክፍልና በገዥው ክፍል መሆኑ ቀርቶ፤ በገዥው ውስጥ እንዲካረር በማድረግ፤ ግልብ ሆኖ እንዲፈረካከት መቦርቦር ነው። ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ፤ የሰላማዊ ትግሉ አራማጆችና ባለስኬቶች ነበሩ። ከነዚህ አዛውንት ሰላማዊ ታጋዮች ብዙ የምንማረው ትምህርት አለ። ዋናው ቁምነገር፤ የነዚህን ግዙፍ ሰላማዊ ታጋዮች ግብር በማጥናት፤ ለኛ ሀገር ተስማሚ በሆነ መንገድ፤ ተመክሯቸውን መጠቀም ነው። እኛ በያዝነው ትግል፤ ዋና ገዥ ፍልስፍናችን ምንድን ነው? ሀገራችን ያለችበት አስጊ ሁኔታ የሚቀየረው፤ ሁላችን ታጋይና ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተሰልፈን፤ በአንድ ራዕይና በአንድ ድርጅት ስንታገል ነው። ታግለን ደግሞ መመሥረት ያለበት፤ ሁላችንም የሚወክል የሽግግር መንግሥት ነው። ሰላማዊ ትግሉ፤ ያላማራጭ ባሁን ሰዓት ላለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ብቸኛ መንገዱ ነው። ለምን?

አንድ ማዕከል ያለው ትግል ባገራችን በሌለበት ሁኔታ፤ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሞሉባት ኢትዮጵያ፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በትውልድ ሐረግ፣ በንብረት ብዛት፣ በአካባቢ ብልጽግናና በመሳሰሉት መለያያ መንገዶች ያለን መሆናችን አንዱ ምክንያት ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በተለይም የትውልድ ዘር ቆጠራ ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች የተስፋፉበት፣ የተለያዩ የትግል መስኮችና ግቦች የፖለቲካውን ምኅዳር ያጣበቡበት ሀቅ ሌላው ምክንያት ነው። አምባገነኑ ወገንተኛ ገዥ ተወግዶ፤ የነገዋ ኢትዮጵያ የሁላችን እንድትሆን አስተማማኝ የሆነ የትግል ስልት ማስፈለጉ፤ ሌላው ምክንያት ነው። ብዙ ታጋይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ትግሉ፤ ለሌላው ሳይሆን ለራሳቸው ሲሉ መምጣታቸው፤ አስፈላጊና ወሳኝ ነው። ይህ ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው። ባሁኑ ሰዓት፤ በገዥው ቡድን መካከል፤ መለስ ዜናዊን የመሰለ፤ ሁሉን ሥልጣን ጠቅልሎ በጁ የጨበጠ አንድ አምባገነን በሌለበት ወቅትና፤ እያንዳንዳቸው የራሳቸውን ወገን ለማጠናከር በሚሯሯጡበት ሰዓት፤ በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለማስፋትና ጥርጣሬ እንዲገባባቸው ለማድረግ፤ ግፊት ከሕዝቡ ያስፈልጋል። ሰላማዊ ትግሉ ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፤ ለዚህ የገዥው ተጨባጭ እውነታ፤ አጣዳፊና ተግባራዊ መደረግ ያለበት ግዴታ ነው። ባሁኑ ሰዓት በታጠቀ ኃይል ከመፈረካከታቸው ይልቅ፤ በመካከላቸው በሚፈጠረው ቅራኔና ሽኩቻ፤ የበለጠ መዳከማቸው አመኔታ አለው። እናም ይሄን ለማባባስ አንድ የሚያደርጋቸውን ሳይሆን የሚሰነጣጥቃቸውን መምረጥ አለብን። እናም ሰላማዊ ትግሉ ይሄን ለማድረግ ይረዳናል። የሱማሌና የዩጎዝላቪያ ሀቅ፤ በላያችን ላይ ከብዶ ሊያንዣብብ ያስፈልጋል።

በርግጥ ሰላማዊ ትግሉን መምረጥ ማለት፤ የማህተማ ጋንዲን ወይንም የማርቲን ሉተር ኪንግን ተግባር በቀጥታ መቅዳት ማለት አይደለም። የኛ ሀገር የፖለቲካ ሁኔታና ያለው ተጨባጭ ሀቅ ገዥ ነው። ለጋንዲና ለማርቲን የሃይማኖት መሠረት ዋና ትክላቸው ነበር። በርግጥ ኢትዮጵያዊያን፤ ሃይማኖተኞች ነን። በክርስትያንም ሆን በእስልምና ተከታዮች ዘንድ፤ ለሌሎች ጠበቃ ሆኖ መቆምና ግፍን መቃወም ባህላችን ነው። ሰላምታ አለዋወጣችን እንኳ፤ አንገታችንን ዝቅ አድርገን በመድፋት፤ ሰላምታ ከምንለዋወጠው ሰው ራሳችንን አሳንሰን ነው። አስደጋጭ ሁኔታ ሰፈጠር፤ ለፀሎት ወደ ቤተ ክርስትያንና ወደ መስጂድ መሮጣችን እውቅ ነው። አብሮ ለጸሎት ወደ ቤተ እመነት መሄድና አብሮ መጸለይ የተለመደ ነው። እንግዲህ ይህ ብዙ የሚያመሳስለን ሁኔታ መኖሩን ይመሰክራል። ለነሱ ዋናው እምነታቸው፤ ገዥውን ክፍል ተገዥ ለማድረግ ሳይሆን፤ ሁሉም እኩል የሚሆንበት የወደፊት እንዲፈጠር ማድረግ ነው። ይሄ በቅኝ ግዛት ትማቅቅ ለነበረችው ሕንድ፤ ምን ያህል እንደሠራ ማየቱ ቸግሮኛል። እንግሊዞች ወጥተው ሕንዶች የራሳቸው መንግሥት እንዲመሠርቱ የታገለው ጋንዲ፣ ይሄን መስበኩ ለኔ ገርሞኛል። ባንጻሩ ማርቲን ምርጫ አልነበረውም። ኔልሰን ማንዴላም ቢሆን ምርጫ ስላልነበረው፤ በአውሮፓውያንና አሜሪካውያን፤ ለውጡ ዘምዶቻቸውን እንደማይጎዳና ጥቁሮቹን ባሉበት የድህነት ሰቆቃ እንዲማቅቁ መደረጉን ተገዶ ተቀብሏል። ወራሪንና እንደወራሪ የሚገዛን ቡድን፤ አስተናግዶ እኩል ለማድረግ፤ የሀገራችን ሀቅ አያመችም።

ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች አሉ። ሰላማዊ ትግሉ መማርና መመራመርን መጠየቁን ያምኑበት ነበር። ለነሱ እውነተኛ እውቀት ማለት፤ በቦታው በተጨባጭ ያለውን ሀቅ ተገንዝቦ፤ ሂደቱን በማስላት፤ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በማካተት፤ ወደ መሠረታዊ ዋና ግቡ መጓዝ ማለት ነበር። ደጋግሞ ስለሰላማዊ ትግሉ ምንነት መስበክና ማስተማር የመሪዎቹ ኃላፊነት መሆኑን አስምረውበታል። የሰላማዊ ትግሉ በተግባር ላይ ስለመዋሉ እውነተኛነት፤ ጽኑ እምነትና ቆራጥነት ግድ ነበሩ። በጋጠ ወጦችና በገዥው ታጣቂዎች ለደረሰባቸው ጉጥጫና ግፍ፤ የአካል፣ የመንፈስና የንብረት ጥቃት፤ መልሳቸው ግልጽ ነበር። “ያነገትኩት እውነት፤ ክቡርና ጠንካራ ስለሆነ፤ ውሎ አድሮ፤ አቸናፊ ነኝ!” ነበር። የዚህ ትግል መሪዎች፤ የአእምሮ ነፃነት ያላቸውና ለግል ተጠቃሚነት ቦታ ያልሠጡ መሆን አለባቸው ብለዋል። በሰላማዊ ትግል የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ማሟላት፤ ትክክለኛ ተግባር ነው ብለው አምነዋል። ከማንኛውም ቦታ የሚመጡ የተለያዩ ሃሳቦችን ለማዳመጥና ለማመዛዘን ፈቃደኞች ነበሩ። የሰላማዊ ትግሉ ሂደት፤ ለኅብረተሰቡ ኑሮ፤ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ነው። እናም ከትግሉ ስኬት በኋላም አገልጋይ የሚሆኑ ባህሪና ጥበቦችን በሥልጠናና በተግባራዊ ልምድ ማዳበር ይጠቅማል። ለሚከተለው ሰላምና ብልጽግና፤ በተለይም ከጦርነት እሽክርክሪት ለመውጣት መሠረት ነው። እብሪትና ድንቁርና፤ ጦር ወደ መምዘዝና ካንተ መቼ አንሼ ወደሚል ያመራሉ።

የሕዝቡ የነፃነት ፍላጎት አይሎ፤ በየቦታው እምቢተኝነቱን ሲያሰማ፤ የገዥው ወገንተኛ አምባገነን መንግሥት ሁለት ምርጫ ብቻ ከፊቱ ይደቀናሉ። እኒህ ወሳኝ የሆኑ ምርጫዎች፤ የገዥውን ቡድን አረመኔያዊ ግፍ፣ የሕዝቡን አጸፋ አመላለስና የወደፊቱን የሀገራችን ሕልውና ይወስናሉ። የመጀመሪያው ለሕዝቡ እምቢተኝነት ተገዝቶ፤ የሕዝቡን ፍላጎት ለሟሟላት እሽ ማለት ነው። ሁለተኛው፤ በእብሪት ተሞልቶና እኔ ገዢ ነኝ፤ እኔ ብቻ ያልኩት መፈጸም አለበት በማለት፤ ጉልበቱን ተጠቅሞ የሕዝቡን እምቢተኝነት በጭካኔ ለመቅጨት ሠይፉን ከአፎቱ መምዘዝ ነው። የመጀመሪያው እንደሂደቱ የሚመለስ ሲሆን፤ የአምባገነኖች መጨረሻ እንዳስገነዘበን ግን፤ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች፤ የሁለተኛው ምርጫ ነው የተለመደው። የሕዝቡ የአጸፋ መልስ፤ የገዥውን የእብሪት ጉልበት መቋቋምና የበላይነቱን መውሰድ ይጋብዛል። ያኔ የሕልውና ግዴታ ቦታውን ይወስዳል። በመኖርና ባለመኖር መካከል የሚቀመጥ መርጫ፤ በማናቸውም መንገድ መኖርን ይዞ መነሳቱ፤ አጠያያቂ አይደለም።

በአራተኛው ክፍል፤ ከየት እንጀምር የሚለውን ተግባራዊ ጉዳይ ይዞ ይቀርባል።

eskemecheeske.meche@yahoo.com  http://nigatu.wordpress.com

እኔና ስርጉተ–  አልተግባብቶም        ይገረም አለሙ

$
0
0

በቅድሚያ እህቴ ስርጉተ ለአስተያየትሽ አመሰግናለሁ፡፡ ሁለት ገጽ ጽሁፌ እያንገሸገሽሽ አንብበሽ በተረዳሽውና በገባሽ መልክ  በጨዋ አቀራረብ አስተያየት በመስጠትሽ፤- እኛ ኢትዮጵያውያን በእጅጉ ከሚጎድሉን በርካታ ነገሮች አንዱ ይህ ነው፤ በጽሞና መነጋገር ሀሳብ መለዋወጥ መደማመጥ አለመቻል፡፡ ሀሳብን በሀሳብ ከመሞገት ይልቅ ፈጥኖ ዘለፋና ፍረጃ፤

እህቴ  በጽሁፏ መጀመሪያ ሀይለ ቃሏን ብቻ አውጥቼ ጠረጴዛየ ላይ አድርጌ ፈተሸኳት ስትል በጥሞና አንብባዋለች በሚገባም  ተረድታኛለች የሚል ስሜት አድሮብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን 6 ገጽ የፈጀውን ሀሳቧን አንብቤ ስጨርስ እንደገባኝ ሀይለ ቃል ብላ ያወጣቻቸውን ብቻ ይዛ  በእነኛ ላይ ተመስርታ አቶ ገብሩ አስራትን እያሰበች (ርሷ እንዳለችው) ሌላውን የጽሁፉን መልእክት በትኩረት ባለማየቷ  ያነበበችው በሀሳቧ ታወጣ ታወርድ ከነበረው  የተምታታባት ይመስላል፡፡ ይህም በመሆኑ ጽሁፉ የማይለውን ትርጉም በመስጠት በሀሳብ ሳንለያይ ተለያየን፤ አንድ ቋንቋ እየተናገርን ሳንግባባ ቀረን፡፡

በሀሳብ መግባባት ሲቻል መልካም ነው፡፡ ካልሆነ ደግሞ ላለመግባባትም መግባባት ጥሩ ነው፡፡ አንድ አይነት ሀሳብ እያንጸባረቁ አለመግባባት ያለመደማመጥ ውጤት በመሆኑ ምን አልባት ሀሳቤን በትትክል አልገለጽሁ ይሆን እንዴ ብዬ ጽሁፌን እንደገና አነበብኩት፡፡ ግና ስርጉተ የፈንጅ ያህል ነው ያቆሰለኝ ያለችውን ትርጉም የሚሰጥ ቃልም ሆነ አረፍተ ነገር ማግኘት አልቻልኩም፡፡ እናም ሲሆን ለመግባባት ከልቻልንም ላለመግባባት መግባባት መደማመጡ መልካም ነውና ከረዥሙ ጽሁፍ ትንሽ ማሳያዎችን በመጥቀስ  ሀሳቤን ግልጽ ለማድረግ ልሞክር፡፡

1-„የልማታዊ መንግሥትበለው! ይህም በራሱ አቅሙአይደለም። ያለማው አካባቢ ካለ ጥብቅናይቆምለት። ምን አልባት ብላለች ስርጉተ፡ ይህ ብቻውን የእኔ ጽሁፍና ስርጉተ እንዳልተገናኙ በቂ ማሳያ ነው፡፡ ምንም ማብራሪያ ሳያስፈልግ በጽሁፌ የገለጽኩትንና ይህን ለማለት ያበቃትን ዐ.ነገር  ደግሜ ላስፍረው፤ “አሁን ልማታዊ መንግሥት እያለ ራሱን እየጠራ ነው ታዲያ እኛ በዚህ  እንጠራዋለን?” ነው የሚለው የእኔ ጽሁፍ፡፡ ለራሱ በሰጠው ግብሩን በማይገልጽ መጠሪያ ልንጠራው አይገባም እያልኩ ስርጉተ ያለማው አካባቢ ካለ ጥብቅና ይቆምለት በማለት ልማታዊ መንግሥት ተብሎ ይጠራ እንዳልኩ አድርጋ ነው የተረዳችው፡፡

2-እኔ እርስዎ የጻፉት ጹሑፍ የፈንጅ ያህል ነውያቆሰለኝ። አይደለምሌላውን። እያቅለሸለሸኝ ነውያነበብኩት፤ ስለምን? በአጋጣሚዎች ምክንያት ብዙ ነገሮችን በጥልቀት ስለማዳምጣቸው በማለት እኔ ወያኔ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን በደልና ጥፋት እንደማላውቅ ወይንም ወደ ጎን አድርጌ በደጋፊነት አንደተሰለፍኩ ገምታኛለች፡፡ ጽሁፌ ውስጥ የትኛው አገላለጽ ይህን ትርጉም እንደሰጣት አልገባኝም፡፡ ብታሳየኝ ጥሩ ነበር፡፡

ስርጉተ በሰፊው የገለጸችውን የሰው ልጅ ሊሰራው የማይገባ እርኩስ የሆነ የወያኔ ተግባር አውቃለሁ፡፡ የማውቀው ደግሞ  በስማ በለው ሳይሆን እየኖርኩበት በራሴ ጭምር ደርሶም እየደረሰም ነው፡፡ ማወቅ ብቻ ማውገዝ ብቻ አይደለም ስልጣን ጨብጦ የጫካ ርኩስ ተግባሩን ከቤተ መንግሥት ሆኖ መፈጸም ከጀመረበት ግዜ አንስቶ ከሰላማዊ ታጋዮች ጋር ተሰልፌ የታገልኩ ነኝ፡፡እናም በወያኔ ማንነት ምንነትና እንዴትነት ላይ ልዩነት ሳይኖረን ነው ያልተግባባነው፡፡

3- የነገ ኢትዮጵያ መከራው በቁርሾ እንዳይወራረድ በመቻቻል እንዲሰክንእንሻለን። ይህ የስርጉተ አባባል የእምነቴ መሰረት በጽሁፌ የተገለጸው ሀሳቤም ማጠንጠኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው አልተግባብቶም ለማለት የበቃሁት፡፡ትግሉ ወያኔን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ ልጆቿ በፍቅር በሰላም በእኩልነትና በነጻነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ከሆነ ዛሬ የምንናገረው የምንጽፈውም ሆነ ተግባራዊ የምናደርገው ይህን ያነዘበ መሆን አለበት፡፡ እናም ስርጉተ እንዳልሽው የነገ ኢትዮጵያ መከራው በቁርሾ እንዳይወራረድ በመቻቻል እንዲሰክን ከመሻት ባለፈ እውን እንዲሆን  ከተመኘን ወያኔና ትግረኛ ተናጋሪ ወገናችንን ለያይቶ ማየት  ይበጃል፡፡

4 በዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነፃ ውጪ አስተዳደር እያንዳንዱ የእንቅስቃሴ ነጥብ በመርዝ የተበከለ ስለሆነ ሌላ የሰከነ የመንፈስ አብዮት የሚጠይቅ ተግባር ከፊት ለፊት ብሄራዊ ነፃነት ፈላጊውን ህዝብይጠብቀዋል። ወንድሜ ሆይይህ የሚጎረብጠዎት ከሆነ…….

የእኔኑ ሀሳብ የደገመ ሀሳብ እንደምን ይጎረብጠኛል፡፡ ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት የሱን መርዝ ማራባት ነው፤ ምክንያቱም አንድም እሱ ሥልጣን ፈላጊ አንጂ ነጻ አውጪ ስላልሆነ፡ ሁለትም አባባሉ ትግረኛ ተናጋሪ ወገናችንን በሙሉ ጠቅሎ ከወያኔ ጋር በአንድ ቅርጫት የሚያስገባና ሌላው ኢትዮጵያዊ ትግረኛ ተናጋሪውን ወገን አንደሚጠላ አድርጎ በመስበክ የርሱ ጋሻና ዋሻ ለማድረግ የሚሰራውን ሴራ ማገዝ የሚረጨውን መርዝ ማሰራጨት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ፈጣሪ ነብሳቸውን እንዳሻው ያድርጋትና አቶ መለስ መቀሌ ተኝተው በትግረኛ ቋንቋ “እኛ ከሥልጣን ብንወርድ ነፍጠኞች አንድ ቀን አያሳድሩዋችሁም” በማለት የረጩት መርዝ በምንም ምልኩ አላማቸውን አንዲያሳካ እኛ በማወቅም ይሁን በበደል ግፊት ተባባሪ መሆን የለብንም ነው የእኔ ጽሁፍ መልእክቱ፡፡ እርሱ በጥላቻ መርዝ የበከለውን እኛ በፍቅር እናጽዳው ነው፡፡ወያኔ ለሥልጣኑ እድሜ ሲል ለሚፈጥረው መለያየት እኛ በር አንክፈት መንገድ አንስጥ ነው፤እሱ ጎሰኝነትን ሲያቀነቅን እኛ ኢትዮጵያዊነትን እንዘምር ነው ሀሳቤ፡፡

4በሌላ በኩል ተበድላችሁምተቀጥቅጣችሁምተገፍታችሁምየገፋችሁን የቀጠቀጣችሁን ዋጥ አድርጋችሁ የተገላቢጦሽ ይቅርታ መጠዬቅ አለባችሁምወይንም አትነካኩትይመስላል። ስርጉተ በፍጹም– ይህን ትርጉም ይሰጣል የምትይውን ቃል ወይንም አረፍተ ነገር ብታሰይኝ ጽሁፌ ሀሳቤን በትትክክል አልገለጸም ብዬ ለመማር ያስችለኝ ነበር፡፡ ከዚህ የሚያልፍ ከሆነም ይቅርታ ለመጠየቅ ፡፡ ወያኔ የትግሬ ነጻ አውጪ መባሉ ይበዛበታል ግብሩን አይገልጽም ለሥልጣን ሲል ሕዝብ ቢያልቅ ሀገር ቢፈራርስ ደንታ የሌለው ወያኔ እንደምን ነጻ አውጪ ይባላል ወዘተ ማለት እንዴት ሆኖ የዚህ አይነት ትርጉም ሊሰጠው እንደቻለ አይገባኝም ፡፡ በትንሹ የሀውዜንን እልቂት ፤የበደኖን የወተርንና የአርባ ጉጉን ጭፍጨፋ፤የወለጋውን አረመኔያዊ ግድያ ወዘተ ማስታወስ በቂ ይመስለኛል፡፡ እንኳን ይቅርታ ልንጠይቃቸው እነርሱ ልብ ገዝተው አገዛዛችንን ማሰመር አልቻልንም ባይሆን እንኳን አወራረዳችንን እናሳምር ብለው በደላቸውን  በንስሀ ለማስተስረይ ጥፋታቸውን በይቅርታ ለማወራረድ ቢፈቅዱ እንኳን በህግ ተጠያቂ ከሚሆኑባቸው ወንጀሎችና ጥፋቶች ነጻ ሊሆኑ አንደማይችሉ ነው የማምነው፡፡

5- ኢትዮጵዊነታችን ይበልጥብናል፤ ከብዙሃን  ጋር መኖር ይሻለናል ማለትአለባቸው

ትክክል፤-  ይህን ማድረግ የትግራይ ወገኖቻችንን ድርሻና ኃላፊነት ነው ስንል እኛ ደግሞ ወያኔዎች መጠቀሚያ ለማድረግ ሲሉ የሚነዙት አሉባልታና የሚረጩት መርዝ ሀሰት መሆኑን በተግባር ማሳየት ካልቻልን የምንለው ይሆን ዘንድ እንደምን ይቻላል፡፡ ለዚህ ነው ወያኔና ትግረኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ መለየት አለብን፤ በወያኔ ሥልጣን ላይ መኖር ተጠቃሚ ቢሆኑ እንኳን በወያኔ ከሥልጣን መውረድ ተጎጂ እንደማይሆኑ  አምነን ማሳመን ስንችል ነው  ከብዙኑ ጋር መኖር ይሻለናል  ከማለት አልፈው  አታለያየን በስማችን አትነግድብን ወያኔ ዘወር በልልን ማለት የሚችሉት፡፡

6-እኔ የልጆችን መጸሐፍት ስጽፍ እንዴት ተጨንቄ እንደፃፍኩት፤ ምን ያህል ጊዜም እንደበላብኝምአውቃለሁ። እኛ ባለፍነበት ንትርክ እነሱ ማለፍ ስለሌለባቸው ነበር ያን ያህል በጥበብ ድክም ብዬየሠራሁት። የልጆች ራዲዮ ዝግጅቴም እንዲሁ ፍቅርንለማውረስ ይተጋል።  ይህን ሳነብማ እኔና ስርጉተ የባቢሎን ዘመን ሰዎች የሆንን ያህል ተሰማኝ፡፡ አንድ ሀሳብ እያራመድን አንድ ቋንቋ እየተናገርን መግባባት የተሳነን፡፡ እኛ ባለፍንበት ንትርክ ማለፍ የለባቸውም፣  ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን፣  መለያየትን ሳይሆን ተነጋግሮ መግባባትን፣ በአንድ ሀገር ልጅነት ስሜት በፍቅር ተሳስቦ  መኖርን ማውረስ አለብን የምንለው ዘር ሳንመነዝር፣ የቋንቋ ገደብ ሳናበጅ፣ የሀይማኖት ልዩነት ሳንፈጥር ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሆነ  ወያኔን ነጻ አውጪ ማለት አይገባም በሚል የቀረበው ጽሁፌ ከዚህ አስተሳሰብ አይቃረንም፡፡አልተግባብቶ ሆኖ አንጂ፡፡

በመጨረሻም ወያኔን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት የሚደረገው የትኛውም ትግል ልንደርስበት የምንፈልገውን ግባችንን አሸጋግሮ በማየት ላይ የተመሰረተ በስሜት ሳይሆን በእውቀት የሚካሄድ በጥላቻ ሳይሆን በአላማ የሚመራ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነትና በፍቅር የሚያይ ሊሆን ይገባል፡፡

ወያኔ የሰው ልጅ ይሰራቸዋል ተብሎ የማይታሰብ ድርጊቶችን ፈጽሟል ፤ አሁንም ወደ ፊትም እድሜ እስከሰጠነው ድረስ ሥልጣኔን የሳጣኛል ብሎ የሚፈራውን ነገር ባየ በሰማ  ቁጥር ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም፡፡ የሰራውን ስናስታውስ አረመኔነቱ ሲታሰበን ያደረሰብን ቁስል ሲቆጠቁጠን ጥላቻችን መበረርታቱ ስሜታችን ለበቀል መነሳሳቱ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ እናም ለርኩስ ድርጊቱ የሚመጥን ተመሳሳይ ተግባር መፈጸም እንደሚገባን ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ክእነርሱ መሻላችንን የምናረጋግጠው፣ ለሀገርና ለሕዝብ የሚበጅ ራዕይ ያለን መሆናችንን የምናሳየው፣ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመሻታችን መገለጫ የሚሆነው  ይህን ስሜታችንን ገትተን የዛሬውን ድል ብቻ ሳይሆን የነገውን ውጤት አርቀን እያሰብን ለአላማችን ስኬት ስንታገል ነው፡፡ ደራሲ አያልነህ ሙላት በትያትር እንደገለጸው ኢትዮጵያ በጋሜ እንዳትቀር፡፡

በሰላማዊውም ሆነ በጠመንጃው ትግል በተቻለ መጠን የትግሉን ተሳታፊ ካልሆነም ደጋፊ ማብዛት፤ ብሎም የሚቃወምንና የሚጠላን መቀነስ ፤ በአንጻሩም የተቃራኒን(;ጠላትን)  ጎራ የሰው ኃይል ማሳሳት  ዋንኛ ስትራቲጂ ነው፡፡ ወያኔ ዘረኛ መርዙን የሚረጨው ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳውን የሚነዛው በትግራይ ክልል የተሰሩ ግንባታዎችን ወዘተ ጠዋት ማታ የሚነግረንና የሚያሳየን ትግረኛ ተናጋሪውን ወገን ጋሻውና ዋሻው ለማድረግ የያዘውን እኩይ ሴራ ለማሳካት ነው፡፡  ይህን ሴራ ማክሸፍና የረጨው መርዝ ጥፋት እንዳያደርስ ማድረግ የሚገባን እኛ ከወያኔ በተቃራኒ የተሰለፍነው ነን፡፡  ተግባራዊ የሚሆነው ደግሞ ጥላቻን በማሳየት ሳይሆን ፍቅር በመስጠት፣ ጠላቴ ብሎ በማራቅ ሳይሆን ወገኔ ብሎ በማቅረብ፤ የዛሬ ተጠቃሚ ሆነሀል ብሎ በመግፋት ሳይሆን ና ስለነገ አብረን ራዕይ ይኑረን በማለት ወዘተ ነው፡፡ስርጉተ የመንፈስ አብዮት የሚጠይቅ ተግባር ያልሽው መገለጫው ይህ ይመስለኛል፡፡

comment pic

 

ከደርግ የባሰ ግፍ በጎንደር

$
0
0

– የሚሊዮኖች ድምጽ

ወያኔ/ኢሕአዴግ “ብሶት ነው የወለደኝ” በሚል ደርግን በሚዋጋበት ጊዜ፣ መንገድ አሳልፎ ወደ መሃል አገር እንዲገባ ያደረገው የጎንደር ሕዝብ ነበር። በመላኩ ተፈራና በደርግ መከራን ያየና በመከራ የተማረረ ህዝብ፣ የተሻለ ሊመጣ ይችላል በሚል ነበር ወያኔን አሳልፎ ያስገባው።
ሆኖም ጎንደሬው ከደርግ የባሰ ግፍና መከራ እየደረሰበት ነው። ደርግ ያላደረገው በደል ህዝቡ እየተፈጸመበት ነው። ገበሬው ከምርታማ የጎንደር መሬት በኃይል እየተፈናቀለ ፣ ለአገዛዙ ቅርበት ላላቸው ኢንቨርስትሮች መሬቱ እየሰጠበት ነው። እሰ ሰሊጥ የመሳሰሉት የሚያበቅለው ለምለሙ መሬት በኢንቨርስተሮች ሕግ ወጥና ጸረ-ሕዝብ በሆነ መንገድ እየተወረረ ነው። ይሄን አይነት ዜጎችን ማፈናቀል ደርግ እንኳን ያልፈጸመው ግፍ ነው።
በምእራብ ወያኔ ገበሬዎችን ቀምቶ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ እየሰጠ ነው። ይሄንን በደርግ ጊዜ ያልታየ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥም መቆም ሳይሆን አገርን መሸጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
Gonder
ሕዝቡ ለመብቱ፣ ለክብሩ፣ ለነጻነቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ እየተደገደል፣ እየታሰረ፣ ክፍተኛ እንግክትና መከራ እየደረሰበት ነው። በኢትዮጵያ በሰለጠነ መልኩ በሰላም ለዉጥ እንዲመጣ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ብዙዎቹ ሲሰደዱ፣ ብዙዎቹ ወህኒ ወርደዋል። በአንድነት ፓርቲ ሥር በጎንደር ክፍል ሃግር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ጀግና ወገኖቻችን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1. ኣንጋው ተገኝ (ሰሜን ጎንደር)
2. አባይ ዘዉዱ (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
3. እንግዳው ዋኘው (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
4. በላይነህ ሲሳይ (መተማ ጎንደር
5. አለባቸው ማሞ (መተማ ጎንደር)
6. አለበል ዘለቃ ሃይማኖት አየና ( ውሮታው፣ ደቡብ ጎንደር)
7. ጸጋዬ ገበይየሁ (አርማጭሆ)
8. መምህርት ግዛው ( ሰሜን ጎንደር)
9. አውቀ ብርሃኑ (ጎንደር)
10. ማሩ አሻግሬ ( የአርማጭሆ ተወላጅ፣ የዞኑ የአንድነት አመራር – ቀይ የለበሰው))
11. አለላቸው አታለለኝ ( የሰሜን ጎንደር አንድነት ሰብሳቢ)
12. አስቴር ስዩም ( በጎንደር የምእራብ አርማጮሆ የአንድነት አመራር)

ጉደኛው አርከበ እቁባይ “ወደብ ልማት ያመጣል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ስለ ኢኮኖሚ ልማት ምንም የማይገባቸው ሰዎች ናቸው”አሉ

$
0
0

የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ግንቦት 20ን አስመልክቶ ከዘመን መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል። ከቀረበላቸው ጥያቄ መካከል ድርጅትና መንግሥታቸው ኤርትራንም ሆነ ወደቡንም አሳጥቶናል የሚሉ ወገኖች አሉና ለእነዚህ ወገኖች ምላሽዎ ምንድን ነው? የሚለው አንደኛው ነበር። እንዲህ ብለው መለሱ-
Arkebe Equbay
“ስለ ሕዝብ የማያነሳና የማያስብ ግለሰብ ወይም ቡድን ብቻ ነው ስለ መሬትና ወደብ የሚያነሳው። አገር ማለት ሕዝብ ነው። ስለሆነም ስለ ሕዝቦች በምናስብበት ጊዜ የኤርትራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ነው መወሰድ ያለበት።” በማለት የጀመሩት አርከበ ስለ ኤርትራ ህዝብ ፍላጎትና ስለድርጅታቸው አቋም እንዲህ ብለዋል “ የኤርትራ ሕዝብ ምን ይፈልጋል? ለብዙ ዓመት በጦርነት ውስጥ የቆየ ሕዝብ ነው፤ ከ30 ዓመታት በላይ። ከኢትዮጵያ መገንጠል እንፈልጋለን አሉ። 99 በመቶ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብ ነፃ ኤርትራን እንፈልጋለን አለ። ሕዝቡ ፍላጐቱን በድምፅ አረጋገጠ ማለት ነው። የሕዝቡ ፍላጐት ደግሞ መሟላት አለበት። ዴሞክራሲ ማለት ለሕዝብ መቆም ማለት ነው። ማነው የመጀመሪያ
አገር ኤርትራን እንደ አገር የተቀበለው? የኢትዮጵያ መንግሥት ነበር። ያ ሆኖ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል። ስለዚህ ያንን ያደረግነው ከሰላም፣ ከዴሞክራሲ፣ ከሕዝቦች መብት ማረጋገጥ አንፃር ነውና ይሔ መሆኑ ተገቢ ነው።”

ወደብን አስመልክቶ ግን አቶ አርከበ የሰጡት ማብራሪያ “የአሰብን ወደብ (ባለመጠቀም) የግመል መጠጫ ሆኖ ይቀራል (እናደርገዋለን?) በማለት ዝተው ከነበሩት ከአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር ጋር የሚመሳሰል ይመስላል። “እኛ ወደብ መች ቸገረን?” ያሉት አቶ አርከበ ወደብ ብቻውን ልማትን የማያስገኝ መሆኑን በመግለጽ ጥያቄውንም ሆነ ባለወደቢቷን ኤርትራን ከሶማልያ ጋር በመደመር ያናናቁ መስለዋል። እንዲህ ብለዋል-
“ግን ዋናው ነጥብ ምንድንነው ወደብ ልማት ያመጣል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ስለ ኢኮኖሚ ልማት ምንም የማይገባቸው ሰዎች ናቸው። በአካባቢያችን ሠፋፊ ወደብና የባህር ዳርቻ ያላቸው አገሮች እነማን ናቸው? አንዷ ሶማሊያ ናት። ሁለተኛዋ ማናት? ኤርትራ
ናት። ሁለቱንም እንያቸው በጥፋት ሂደት ያሉ አገሮች ናቸው። ሶማሊያ ግን አሁን በተሻለ እንቅስቃሴና
መረጋጋት ውስጥ ናት። ኢኮኖሚ ልማት በእነዚህ አገራት የለም። ስለዚህ ልማትና ዕድገትን የሚያመጣው ወደብና የባህር ዳርቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ያለ ማየት አስተሳሰብ ምንጭ ነው። እኛ ወደብ መች ቸገረን? በጂቡቲና በበርበራ መጠቀም እንችላለን። የኤርትራም ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል ብለን አንገምትም። በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን። የኬንያን ወደብ መጠቀም እንችላለን። ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ መስመር ለመገንባት ታቅዷል። የሱዳንንም እንጠቀማለን። ቢቻል ወደብ ቢኖረን ጥሩ ነበር ግን የሁሉም መቋጫና መፍትሔ እርሱ ነው ማለት አይደለም። የሚያመጣው መሠረታዊ ለውጥም የለም በእኔ እምነት።”


የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

አይበገሬዋ ጀግናዋ ርዕዮት!

በንጹሀን ዜጎች ላይ ስቃይን በመፈጸም ከሚታወቀውና ከአዲስ አበባ ከተማ እምብርት በስተደቡብ ምስራቅ ተንጣሎ ከሚገኘው እና በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ ከሚጠራው የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት (የኢትዮጵያ “ሮቤን ደሴት” ማለትም ነልሶን ማንደላ የታሰሩበት) ባልተጠበቀ ጊዜ የተለቀቀችው ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ ከማጎሪያው እስር ቤት በወጣች በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ቃለ መጠይቅ ሰጠች፡፡

reyot
ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ በማለት የዓላማ ጽናቷን በድጋሜ አረጋግጣለች፡፡

ርዕዮት በአምባገነኑ ገዥ አካል የ14 ዓመታት እስር ተበይኖባት ይህ እስር እንደገና ወደ 5 ዓመታት ከተቀየረ በኋላ 4 ዓመታት ከ17 ቀናት (1480 ቀናትን) በእስር ቤት አሳልፋለች፡፡

አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ እና በእርሱ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) የጸረ ሽብር ሕግ እየተባለ በሚጠራው ሰላማዊ ዜጎችን የማጥቂያ መሳሪያ የፈጠራ እና የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባት ነበር ወደ ዘብጥያ የተወረወረችው፡፡

ታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ለዘረኛው የጥቂት ነጮች ፈለጭ ቆራጭ አምባገነን ስርዓት ጭቆና አራማጆች እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር፣ “በማዘግየት በኩል ውጤታማ ልትሆኑ ትችላላችሁ፣ ሆኖም ግን ደቡብ አፍሪካ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ልታስቀሩት አትችሉም፡፡“

የርዕዮት ዋናው መልዕክት ማጠንጠኛውም ይኸው በታላቁ መሪ በኔልሰን ማንዴላ የተነገረው የአፓርተይድ ዓይነት ወሮበላ የዘራፊ አምባገነን ቡድን ስብስብ ለሆነው ለወያኔ ትክክለኛ የሆነ ገላጭ ድርጊት ነው፡፡ “ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡” ነው ያለችው፡፡

ትግሉ ይቀጥላል!

ማንዴላ ከዚህ በተጨማሪም እንዲህ ብለው ነበር፣ “እስር ቤት እራሱ ትዕግስትን እና ጽናትን የሚያላብስ ተዝቆ የማያልቅ ትምህርት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአንድን ሰው የአድራጊነት እና የመፈጸም ችሎታ የሚመዝን ፈተና ነው፡፡“

ርዕዮት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመውጣት በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ መስፈን ያላትን ለድርድር የማይቀርበውን ቁርጠኛ የሆነውን የዓላማ ጽናቷን በተግባር አረጋግጣለች፡፡ ይህንን ያደረግችው ግን እንዲሁ ከምንም ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ከፍላ ነው፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በየዕለቱ ውርደት፣ ለብቻ ተነጥሎ መታሰር፣ ዝቅተኛ አድርጎ የመመልከት እና ከሰብአዊነት የወረደ አስቀያሚ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡

ሆኖም ግን ጀግናዋ ርዕዮት ሁሉንም ነገር በጽናት ተቋቁማዋለች፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት የበቀል እና የሰይጣናዊ ጥላቻ መፈጸሚያ ከርስ ውስጥ ምርኮኛ ሆና ቆይታለች፡፡

በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ እጅግ በጣም አስቀያሚ የሆነውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነው አያያዝ የሚፈጸምባትን ስቃይ እየገለጸች ድምጿን ከፍ አድርጋ ስታሰማ ቆይታለች፡፡

ታጋሽ ሆናም በጽናት ቆይታለች፡፡

ለአራት ዓመታት እና ለ17 ቀናት ርዕዮት በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ እየደማ ሆኖም ግን ለአንዲት ቅንጣት ሰከንድ እንኳ ለአምባገነኖች ሳታጎበድድ በጽናት ግዳጇን የተወጣች ጀግኒት ናት፡፡

ርዕዮት እንደ አረብ ብረት እየጠነከረች የመጣች ጀግኒት ናት!!!

ርዕዮት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለዓመታት ስቃይ እና ግፍ ስትቀበል ቆይታለች፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ፍርሀት ሳይጎበኛት በጽናት ቆይታለች፡፡

ጀግኒቱ ምንም ዓይነት ፍርኃት የለባትም ምክንያቱም ርዕዮት የዕጣ ፈንታዋ እመቤት ባለቤት እና የነብሷ መርከብ ካፒቴን ሌላ ማንም ወሮበላ ዘራፊ ሳይሆን እራሷ ናትና፡፡

ታዋቂው ገጣሚ ዊሊያም ኢርነስት ሄንለይ ከበርካታ ዓመታት በፊት “የማይበገሩ ጀግኖች” በሚል ርዕስ እንዲህ የሚሉ የግጥም ስንኞችን የቋጠሩት ለካስ ለእነ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ ለዞን 9 ጦማሪያን እና እንደ እነርሱ ላሉት ለሌሎች ጀግና የፖለቲካ እስረኞች ኖሯል፡

ጋርዶኝ ከነበረው ድቅድቁ ጨለማ፣
ጥልቀትን ከያዘው ከጉድጓዱ ወማ፣
ጥቁር ከለበሰው የመሬት ውስጥ ካስማ፣
አሻግሮ ከያዘው የምድር ላይ ማማ፡፡

ገብቸ በመሀል ሳንድዊች ተደርጌ፣
ባልፈጸምኩት ጥፋት ተጥዬ ከግርጌ፣
ሀበሳ ግፍ አየሁ ከጨቋኝ በርግጌ፡፡

እናም ፈጣሪዬን አምላኬን ላመስግን፣
ለመንፈሴ ጽናት ለሰጠኝ ብርታቱን፣
ከወገኔ ፍቅር እንዳይ በረከቱን፣
ግፍን ለማስወገድ ለመስበር መርገምቱን፡፡

በግፈኞች መዳፍ ስደቆስ ታፍኘ፣
ያለፍትህ አካል መጫወቻ ሆኘ፤
የይስሙላ ዳኛ መጨፈሪያ ሆኘ፡፡

አጥቸ ፍርድ ቤት፣
አቤት የምልበት፣
ፍትህ የማይበት፣
ግፍ የሚመታበት፡፡

ፍትህ ካደባባይ ከመንበሩ ጠፍቶ፣
አምባገነን ነግሶ ስርዓቱ ከርፍቶ፣
ህዝብን አተራምሶ ሀገርን አራቁቶ፣
ዜጋን አሰድዶ ወገን አስከፍቶ፣
በህዝቦች ጫንቃ ላይ ገኖ ተንሰራፍቶ፣
ለዘላለም ሊኖር ሁሉንም አጥፍቶ፣
በተንኮል በደባው ምሎ ተገዝቶ፣
አልሞ ተነስቷል ንጉስ ሊሆን ከቶ፡፡

ለማይበገረው ጠንካራው መንፈሴ፣
አምላክን ለመስግን በመርካቷ ነብሴ፡፡

በግፈኞች መዳፍ በወጥመድ ብወድቅም፣
ሰብአዊነት ክብሬ ቢጣስ ቢረገጥም፣
ብሩሁ አእምሮዬ አካሌ ቢቆስልም፣
ስሜንም ቢያጎድፉት ጥላሸት ቢቀቡም፣
ከዓላማዬ ጽናት አንዲት ጋት አልሸሽም፣
ግርፋት ስቃዩ ጡጫው ቢጨምርም፣
እራሴ ቢደማም አልተንበረከኩም፣
ተሰቃየሁ ብዬ አላፈገፍግም፣
ለጨቋኞች ደስታ አላጎበድድም፡፡

ከዚህ በላይ በቀል አድልኦ ጥላቻ፣
ስምን የማጠልሸት የሰይጣን ዘመቻ፣
ይፈጸማል እኮ በዕኩዮች ሽኩቻ፡፡

እናም የዘመናት ስቃይ ይቀጥላል፣
እኔን ግን መንፈሴ ቆራጥ ያደርገኛል፣
የወገኔ ፍቅር ያንገበግበኛል፡፡

ከምንጊዜም በላይ በሩ ቢጣመምም፣
የተንሸዋረረው ፍትህ ቢጓደልም፣
በኔ ላይ ደጋግሞ ቅጣት ቢቆልልም፣
ከዓላማዬ ፍንክች በፍጹም አልልም፡፡

የእራሴ እጣፈንታ ወሳኙ እራሴ ነኝ፣
ማንም አምባገነን የማይጨፍርብኝ፣
በዲያብሎስ መንገድ የማያስገድደኝ፣
የነብሴ መርከቡ ካፕቴኑ እራሴ ነኝ፡፡

አራቱ የዞን 9 ጦማሪያን ባስቸኳይ ይፈቱ፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥ አካል 5 ወጣት ጦማሪያንን እና ጋዜጠኞችን የህግ አማካሪዎቻቸው፣ እራሳቸው ግፉ የተፈጸመባቸው እና ወላጆቻቸውም ሳይቀር ምንም ነገር ሳያውቁ ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያው እስር ቤቱ ለቋቸዋል፡፡ ከሕግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ቤት ሲማቅቁ ቆይተዋል፡፡ ዴሞክራሲ እና ፍትህ በዓለም ላይ ሁሉ በአደባባይ እየሰፈነ እና እየለመለመ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በማጎሪያ እስር ቤት አስገብቶ እንደ እባብ የሚቀጠቅጥ፣ በንጹሀን ዜጎች ህይወት ላይ ቁማር የሚጫወት እና እንደፈለገ ወስዶ እንደ ጥጃ የሚያስርና የሚፈታ የዘራፊ ወሮበላ ቡድን ስብስብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ መታየቱ እጅግ ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ንጹሀን ዜጎች በወጡባት እግራቸው ነገም ተመልሰው የማይገበቡት ምን ዋስትና ሊኖር ይችላል! ምንም፡፡

የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ) “የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች የዞን 9 ጦማሪያንን ከሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በመስራት እና የማህበራዊ የግንኙነት መስመሮችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በመስራት ላይ ናቸው:: ቡድኑ በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ ጭቆና እና ማህበራዊ የፍትህ መጓደል ሲጽፍ የነበረ ሲሆን የእነዚህ ጦማሪያን ድረ ገጾች በሀገሪቱ ውስጥ በየጊዜው ይታፈኑ ነበር፡፡” በማለት ስለተናገረው ስለዞን 9 ጦማሪያን ነው እየጻፍኩ ያለሁት፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥ አካል ሁሉንም የውንጀላ ክሶች በመጣል ባልታሰበ ሁኔታ ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞችን ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለቋቸዋል፡፡

እስረኞቹ ለሌሎቹ ከአንድ ዓመት በላይ በግፍ ታስረው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት ንጹሀን ወገኖቻቸው እና ጓደኞቻቸው እንኳ በሉ ደህና ሁኑ ለማለት ጊዜ አላገኙም ነበር፡፡

ከማጎሪያው እስር ቤት የወጡት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የሚከተሉትን ያካትታል፡ ዘላለም ክብረት፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ኤዶም ካሳዬ ናቸው፡፡

ከማጎሪያው እስር ቤት የተፈቱት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ከእነርሱ ጋር በተመሳሳይ የፈጠራ ክስ ተመስርቶባቸው በማጎሪያው እስር ቤት የሚገኙት ሌሎች አራት ጓደኞቻቸው ለምን እንዳልተፈቱ ያሳሰባቸው መሆኑን እና የእነርሱ መፈታት ምሉዕ ደስታ ያልሰጣቸው መሆኑን ለህዝብ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ደህና፣ እንግዲህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሚስጥራዊ እንቆቅልሽ እዚህ ላይ ነው፡፡ በተመሳሳይ ውንጀላ ያሰራቸውን ዜጎች እውነት ባይሆንም እንኳ ተመሳሳይ ፍትህ የማይሰጥ በፖለቲካ ቡድኑ የሚጦዝ ድሁር የፍትህ አካል መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ ርዕዮት ዓለሙን የመሰለች ጀግኒት አለቻት፣

ሁሉም ሀገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚፈጠሩ ጀግኒቶች እና ጀግኖች በመታደል ላይ ናቸው፡፡

አሜሪካ በርካታ ጀግኖች እና ጥቂት ጀግኒቶች አሏት፡፡ አብዛኞቹ የአሜሪካ ጀግኒቶች ያልተዘመረላቸው ናቸው፡፡

አሜሪካዊት ጀግኒት ሐሪዬት ቱብማን እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ ባሮች ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ በማሰብ “የምድር ስር ባቡር” ማለትም ከባርነት ወደ ነፃነት ለመጥፋት የሚሞክሩትን የባርነት ተገዢዎች ህቡዕ በሆነ መልኩ በማደራጀት እና በማስተባበር የስብሰባ ቦታዎችን፣ የሚስጥር መንገዶችን፣ በመጓጓዣ ቦታዎች እና በሰላማዊ የህዝብ መኖሪያ ቤቶች በመጠቀም ትግሉ በተጠናከረ መልኩ እንዲካሄድ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1870ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አካባቢ ሱሳን ቢ.አንቶኒ የአሜሪካ ሴቶች የመምረጥ፣ የንብረት የባለቤትነት መብት እና ከዚህም በላይ በመሄድ የሰራተኞች ማህበር አባል እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን መብቶቻቸውን ለማስከበር አመራር ይሰጡ የነበሩ ጀግኒት ሴት ነበሩ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት “የሲቪል መብቶች ተከራካሪ የመጀመሪያዋ አመቤት” እና እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች ንቅናቄ እናት እያለ የሚጠራቸው ሮሳ ፓርክስ ቀላል የሆነውን ህዝባዊ እምቢተኝነትን እንደ ትግል ስልት በመጠቀም ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለፍትህ ሲካሄድ የነበረውን ትግል አቀጣጥለዋል፡፡ ከፊት ለፊት የተቀመጠችበትን የአወቶብስ መቀመጫ እንድትለቅ እና ወደ ኋላ ሄዳ እንድትቀመጥ የሚያዝዘውን የጨቋኞች ትዕዛዝ አሻፈረኝ፣ እምቢ በማለት ለሴቶች መብት መከበር ስትል የመጀመሪያዋ ሆናለች፡፡

ይህች ጀግኒት እንዲህ ብላ ነበር፣ “የለም፣ በፍጹም ከዚህ መቀመጫ አልንቀሳቀስም!“ በማለት ዜጎችን በጾታ ለሚከፋፍለው ሸውራራ የፖሊስ እና የፍትህ ስርዓት በአደባባይ በግልጽ ተናግራለች፡፡

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካ አሜሪካውያን ወዲያውኑ ትግሉን በመቀላቀል ከመብት ታጋዩዋ ጋር አብረው መዘመር ጀመሩ፡፡

“የትም አንንቀሳቀስም!/ልክ በውኃ አጠገብ እንደቆመ ዛፍ/ ህብረት ከእኛ ጎን ነው የተሰለፈው/እኛ ለነጻነታችን እንታገላለን/ ለልጆቻችን ስንል እንታገላለን/ ጠንካራ የሆነ ማህበር እንመሰርታለን/ጥቁሮች እና ነጮች በአንድነት ሆነን/ወጣቶች እና አዛውንቶች በአንድ ላይ በመቆም/ የትም አንንቀሳቀስም፣ የትም፡፡“

የአፍሪካ አሜሪካዊ ሴቶች ለሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ ትግል ዋና የጀርባ አጥንት ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ያልተዘመረላቸው ጀግኖቶች ናቸው፡፡

የዘመናዊ ሰብአዊ መብቶች ንቅናቄ እናት የሆኑት ኢሊኖር ሩዝቬልት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለሰብአዊ መብቶች ስምምነት መሰረት የሆነውን የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ በማርቀቁ ሂደት ከፍተኛ ኃላፊነትን ይዘው የነበሩ ብቸኛዋ ሴት ነበሩ፡፡

በእኔ አመለካከት ርዕዮት ዓለሙ የዚህ ዓይነት አብዮተኞች ቡድን አባል ናት ማለት እችላለሁ፡፡ እንደዚህ ያሉት ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሲቪል እና ሰለብአዊ መብቶች ዓይናቸውን ሳያራግቡ በመንፈሰ ጠንካራነት ታሪክን የሚለውጡ ደፋር፣ በአመክንዮ የሚያምኑ እና ለህዝብ ሲሉ መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ሴቶች ናቸው፡፡

እውነት ተናጋሪዋ፣

ርዕዮት “የኢትዮጵያ እውነት ተናጋረዊ ሴት” በመባል ትጠራለች፡፡

ዘመናዊው የአፍሪካ ታሪክ በሚጻፍበት ጊዜ እና በአፍሪካ አዳራሽ የዝነኞች ስም ዝርዝር ከአፍሪካ አዳራሽ ተዋራጆች ስም ዝርዝር ተለይቶ ሲጻፍ የርዕዮት ስም “በእሳት ውስጥ ተፈትነው ያለፉ” ከሚለው ከጀግኖቹ የክብር ስም ዝርዝር ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጻፍ ይሆናል፡፡

ርዕዮት ዓለሙ አራት ዓመታት ከ17 ቀናት በቆየው ጊዜ ውስጥ የመለስ ዜናዊን የገኃነም ቅጣት ተጋፍጣለች፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ወጣት የሆነችዋ የአረብ ብረቷ ሴት ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመውጣት ለዓለም ህዝብ እንዲህ በማለት አውጃለች፡

ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ እርሷን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በጉልበቷ እንድትንበረከክ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቧጠጠው አቀበት አልነበረም፡፡

የስነ ልቦና ስብራት ለማድረስ እና ያላትን ጠንካራ ተስፋ ለማዳፈን ለብቻዋ ለይቶ በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትታሰር አደረገ፡፡

ለህይወት አስጊ በሆነ በሽታ ተይዛ በነበረበት ጊዜ ህክምና እንዳታገኝ አበርትቶ ሰርቷል፡፡

ሴትነቷን እና ሰብአዊ ፍጡር መሆኗን ክደው ተንቀሳቅሰዋል፡፡

መንፈሷን ለመግደል የሞት ሽረት ትግል አድርገዋል፡፡

የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመባል በሚታወቀው እስር ቤት የጥላቻ እና የበቀል ቦታ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡

ሆኖም ግን በምንም ዓይነት መልኩ የርዕዮትን ቅስም መስበር ሳይቻላቸው ቀርቷል፡፡

አዕምሯዋን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

መንፈሷን መስበር አልቻሉም፡፡

ለመኖር ያላትን ምኞት ማጥፋት ሳይቻላቸው ቀርቷል፡፡

በኩራት ደረቷን ነፍታ በመቆም ለዓለም እንዲህ ትላለች፡

ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አሳሪዎቿ ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት እንድትወጣ ከማድረጋቸው ከደቂቃዎች በፊት አሁን እንዳለችው እንደምትሆን ነግራቸዋለች፡፡ ከማጎሪያው እስር ቤት እንድትወጣ አይፈቅዱላትም ምክንያቱም ከአራት ዓመታት በፊት ታደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ትግሏን እንደምትቀጥል ያውቃሉና፡፡

ርዕዮት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እንዲህ በማለት አስጠንቅቃለች፣ “ባላጠፋሁት ጥፋት ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳልጠይቅ ከማጎሪያው እስር ቤት ወጣሁ ብዬ ለህዝብ ስናገር መልሳችሁ ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ልታመጡኝ ትችላላችሁ፣ እኔ ግን በዓላማዬ ጸንቼ እቆያለሁ፡፡ ስለእኔ ከእስር መፈታት ሀሰት ብትናገሩ እውነቱን ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ እናገራለሁ፡፡“

በተለያዩ በርካታ አጋጣሚዎች የርዕዮት አሳሪዎች ይቅርታ ጠይቃ ነጻ ሆና እንድትወጣ የምትፈርምበትን ፎርም እያዘጋጁ ፈርሚ እያሉ በተደጋጋሚ ለምነዋታል፡፡

እርሷግን ወረቀቱን ወስዳ እንደምትጥለው ነግራቸዋለች፡፡

“ብረቷ ወይዘሮ ” እየተባለች እንደምትጠራው የንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር በህይወት ብትኖር ኖሮ እንዲህ እላት ነበር፣ “ማጊ እባክሽን ወደ ጎን ሁኝ፣ ቦታውን ለርዕዮት ልቀቂ!“

ርዕዮትን እና ሌሎችን ጦማሪያን እና ጋዜጠኞችን የፈቷቸው ለምንድን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ርዕዮት ለፍትህ ወይም ደግሞ ስለእርሷ የልብ ሀዘን መናገር እንድትችል እኔንም ጨምሮ አይፈቅዱላትም ምክንያቱም ተጻራሪ በሆነ መልኩ እነርሱ የሚያዝኑበት ልብም ሆነ መልካም ነገር የላቸውምና፡፡

ርዕዮት ከእስር ቤት ወጥታ ስትሄድ ጥርሳቸውን እንደሚነክሱ እና የሆድ ቁርጠት እንደሚይዛቸው ጥርጥር የለውም፡፡ ቢቻላቸው ኖሮ እርሷ በክፉ በሽታ ምክንያት ህይወቷ አልፏል በማለት ለዓለም ህዝብ ማሳወቅን ይመርጡ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ዕድል ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር አይደለችም፡፡

ይህንን ድርጊት ያደረጉት ለግንባር መሸፈኛ እና በዚህ ወር የሚመጡትን የኦባማን ልብ ለመማረክ ታስቦ የተደረገ ነው፡፡

ይህንን በማድረግ ለኦባማ ጥሩ ነገር እየሰሩ እንዳሉ ለማስመሰል የተደረገ የቅጥፈት ተውኔት ነው፡፡ የኦባማ ጉብኝት ርዕዮትን እና ሌሎችን የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ከሆነ የሚፈልጉት ነገር አይደለም፡፡

ኦባማ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ እናስብ፡ “ክቡር ፕሬዚዳንት ወደ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመሄድ የእርስዎን መሄድ የሚጠባበቁትን እና በግፍ በእስር ላይ እየማቀቁ የሚገኙትን እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን እና በሺዎች የሚቆጠሩትን ሌሎችን የፖለቲካ እስረኞች ሊጎበኙ ይችላሉን? በደርዘን በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ እባክዎትን ሄደው ለመጎብኘት ይችላሉን?“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በልካቸው የተሰፋ የማስመሰያ ልብስን በመልበስ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንደሚሉት የሰው ልጆችን መብት በመጣስ ታላቅ እና አስቀያሚ ሰይጣኖች ናቸው የሚሉትን በመተው ኦባማ ይኸ መንግስት እንደሚባለው አይደለም ብለው እምነት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ተዘየደ የሸፍጥ ስራ ነው፡፡ ከልብ እና ከፍቅር ያለመሆኑን አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርና የዓለም ህዝብም አሳምሮ እንደሚያውቀው ጥርጥር የለውም፡፡

አይዟችሁ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ምንም መጨነቅ አያስፈልግም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጠባቂ መላዕክት አሏቸው – ሱሳን ራይስ እና ዌንዲ ሸርማን በኦባማ ጉብኝት ሁሉ እየተከታተሉ የሚከላከሉላችሁ መላዕክት ናቸው፡፡ ወታደራዊ ማነጻጸሪያ ቃል በመጠቀም እናንተን ለመጠበቅ በቁጥር 1 በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሶስት ቢራቢሮ የሚመስሉ ፍጡሮች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አናት ላይ እያንዣበቡ በመዞር ይጠብቋችኋል ጠንቅቃቺሁ ተመልከቱ ፡፡

ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፣

ርዕዮት ዓለሙ በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ለአራት ዓመታት ከ17 ቀናት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ከቤተሰቦቿ፣ ከጓደኞቿ እና ከዘመዶቿ ተለይታ ቆይታለች፡፡

እናት እና አባቷ ብቻ እንዲያዩዋት ተፈቅዶ ነበር፡፡ (የእርሷ አባት ከሆኑት እና በተጨማሪም የሕግ አማካሪ ጠበቃዋ ከሆኑት አባቷ ጋር እንኳ የሕግ ምክር ውይይት እንዲያደርጉ አየፈቀድላትም ነበር፡፡)

ቢሆንም ግን ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

እርሷን የሚወዷት እና የሚደግፏት በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሺዎች የሚጠቆሩ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለሁልጊዜ በአዕምሯቸው እና በመንፈሳቸው ከእርሷ ጋር ነበሩ፡፡

በፌስቡክ ድረ ገጽ እና በማህበራዊ የመስመር የግንኙነት ዘዴዎች አማካይነት የሚጽፉላት ወጣት እና ቁጡ የሆኑ ወገኖች አሏት፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ታላቅ ክብርን ለሚያጎናጽፉ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ተሸላሚ እንድትሆን ስሟን በጥቆማ የሚሰጡ በርካታ ወገኖች ነበሩ፡፡

በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፡፡

ሌሎችም ለቁጥር የሚያዳግቱ እንደ እኔ ያሉ የእርሷን እና ሁሉንም በወያኔ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና ጀግኖች የማይበገሩትን የእስክንድር ነጋን፣ ዉብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አብርሃ ደስታን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን እና እንደ እነርሱ ያሉትን ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ጉዳይ የእራሳቸው የግል ተልዕኮ አድርገው የሚከታተሉ ወገኖች ነበሩ፡፡

ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህሊና ፍርድ አደባባይ በመቆም ስለ ርዕዮት ጥብቅና ቆሜ ስሟገት ታላቅ ክብር ይሰማኛል፡፡

በርዕዮት ጉዳይ ላይ በተለይም ወይም ደግሞ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና በአጠቃላይ በሰው ልጆች ላይ በወያኔው አምባገነን ገዥ አካል ስለሚፈጸመው ወንጀል በርካታ ትችትችን ጽፊያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 “ርዕዮት ዓለሙ፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ነጻነት ወጣቷ ጀግኒት“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ ላይ ርዕዮት ለምን እንደታሰረች ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

ርዕዮት እና ከእርሷ ጋር እንዲከላከል የተያዘው ውብሸት ታዬ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 በቁጥጥር ስር ውለው በስልክ እና በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ አደጋ ለመጣል የሚል የፈጠራ ክስ በወያኔው ስብስብ የሀሰት ውንጀላ ተፈብሮኮ ወደ መለስ የማጎሪያ እስር ቤት እንዲወረወሩ ተደረገ፡፡ ለወራት ያህል ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር በእስር ቤት ታጉረው ቆዩ፡፡ ሌላው ቀርቶ የግፍ ሰለባዎችን የሕግ ጠበቃዎች እንኳ እንዲጎበኟቸው አይፈቀድም ነበር፡፡

ርዕዮት በቁጥጥር ስር ለመዋሏ ትክክለኛው ምክንያት በዚያው ዓመት ሰኔ 17 በወጣ ፍትህ እየተባለ ይጠራ በነበረው እና በተከታታይ ከህትመት ውጭ ሆኖ በታገደው ሳምንታዊ መጽሔት ላይ ጽፋ ባወጣችው ጽሁፍ ነበር፡፡

በዚያ ባወጣችወ ጽሁፏ ላይ ርዕዮት አሁን በህይወት የሌለውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እየተባለ ሌት ቀን ስለሚደሰኮርለት የቅንጦት ግድብ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በቁጥር አንድ የሀገሪቱ አምባገነን ላይ ደፍራ ጥያቄ በማቅረቧ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2011 አሁን በህይወት የሌለው መለስ በግል ትዕዛዝ በመስጠት ውብሸት እና ርዕዮት “የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ተሳትፎ በማድረግ ደባ ለመስራት አሲረዋል” የሚል የፈጠራ የክስ ወንጀል ተፈብርኮ ክስ እንዲመሰረትባቸው አደረገ፡፡

በርዕዮት ላይ የቀረበው “ደባ ለመፈጸም እየተባለ በመለስ ዜናዊ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ይጠራ የነበረው ማስረጃ በኢሜል የተጻጻፈቸው እና በባለሽቦ ስልክ ስለሰላማዊ ተቃውሞ እና ለውጥ ስለማምጣት በሚል ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር የተነጋገረችው ተቀድቶ የቀረበ ነበር፡፡

ርዕዮት እና ውብሸት ወደ ችሎት ከመቅረባቸው በፊት በነበሩት ሶስት የእስር ወራት ጊዜ ውስጥ የህግ አማካሪ የማግኘት እድሉ አልነበራቸውም፡፡

ሁሉቱም ጋዜጠኞች የህግ አማካሪ እንዳያቀርቡ ተከልክለዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮው ፍርድ ቤት እስር ቤቱ የማሰቃየት ድርጊት እያስፈጸመብን ስለሆነ፣ ከህግ አግባብ ውጭ የሆነ አያያዝ ያለ በመሆኑ እና ህክምና እንዳናገኝ ክልከላ ተደርጎብናልና ምርመራ ይደረግልን በማለት የቀረበውን ውንጀላ አልቀበልም በማለት ውድቅ አደረገ፡፡

ከእስር ቤት እንድትለቀቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ በቀረበላት ጊዜ ርዕዮት ከህግ አማካሪዎቿ ጋር መገናኘት እንዳትችል ከተፈረደባት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ያህል ተከልክላ የቆየች መሆኑን አረጋግጣለች፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2012 “የኢትዮጵያ ርዕዮት፡ የጥናካሬዬ ዋጋ“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት “ክብር በእሳት ፈተና ላይ” በማለት ትክክለኛ ትርጉሙን ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ የ2012 የደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት/Courage in Journalism Award አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ በእጅ ጽሁፏ አዘጋጅታ በዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውዴሽን/International Women’s Media Foundation (IWMF) ስነስርዓት ላይ ቀርቦ እንዲነበብላት በድብቅ ከማጎሪያው እስር በት እንዲወጣ ባደረገችው ደብዳቤ ላይ “ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ” ከመሆን የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍለኝ ምንም ዓይነት ነገር የለም በማለት ግልጽ አድርጋ ነበር፡፡ ለድፍረቷ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል እና እውነታውን በጽናት መቀበል እንዳለባት አሳምራ ታውቅ ነበር፡፡

ርዕዮት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከመለስ የማጎሪያ እስር ቤት በተለቀቀችበት ዕለት የክርክር አመክንዮዋን እንደገና በድጋሜ አረጋግጣለች፡፡

የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ፍትህ እንዲሰፍኑ በጽናት ለመታገል ቆርጣ የተነሳች መሆኗን አውጃለች፡፡ ትክክለኛ የድፍረት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለእኔ እና ለሁሉም ደጋፊዎቿ አስተምራናለች፡፡

የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን እራሳቸው አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 አሸባሪነት በሚል የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ርዕዮትን በእስርኞች የማማላለሻ አውቶብስ ውስጥ ሆና እጆቿ በካቴና ታስረው ለፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ እንዳለች ያገኟት መሆናቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡

ሽብዬ “ምን እያደረግሽ ነው?” በማለት ጥያቄ አቀረበላት፡፡

ርዕዮት እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጠች፣ “እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ብቻችንን አይደለንም፣ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ነን እዚህ በአሸባሪነት ወንጀል ተከስሰን ያለነው“ በማለት እስር ቤቶቹን አመላከተችው፡፡

ርዕዮት ለሽብዬ እንዲህ በማለት ነገረችው፣ “በምትፈታበት ጊዜ እኔ ምንም ዓይነት አሸባሪ ያለመሆኔን ለእውነት የምሰራ ጋዜጠኛ መሆኔን ለዓለም ህዝብ ሁሉ ንገርልኝ፡፡“

ሽብዬ ትኩር አድርጎ ተመለከተ እና እንዲህ አለ፣ “እነዚህ ሁሉም ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ለአንድ ምርጫ ተዳርገዋል፡፡ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እና የተማሩ ናቸው፣ ቀላል የሆነ ህይወትን መምረጥ ይችሉ ነበር፡፡ ሌሎችን የሙያ ዘርፎች መርጠው መሰማራት ይችሉ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እውነትን፣ ሀገራቸውን እና ወገኖቻቸውን በማፍቀራቸው ጋዜጠኞች የመሆን ምርጫቸውን ይዘዋል፡፡“

ርዕዮት በፍጹም ብቻዋን አልነበረችም፣

ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ዳሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎቹ እንደ እነርሱ ተመሳሳይ የሆኑት በኢትዮጵያ የሚገኙት በርካታዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ብቻቸውን አይደሉም፡፡ በእያንዳንዷ ዕለት እና ሰከንድ በእዕምሮ እና በመንፈስ ከእነርሱ ጋር ነን፡፡

ርዕዮት ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ ጓደኞች ነበሯት፣

የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ)/CPJ የእርሷ ጉዳይ ከሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች ጉዳይም ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ በማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ስላለው ለበርካታ ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ጥረት በማድረግ ሲከታተለው ቆይቷል።

ጋተኮ/CPJ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሽብር ወንጀል እየተባለ በነጻ ዘገባ ላይ የሚደረገውን የጽሑፍ ምርመራ አውግዟል፡፡

ጋተኮ/CPJ እንዲህ በማለት የኢትዮጵያን መንግስት ለማስተማር እና ወደ ህሊናው እንዲመለስ ሲያስተምር ቆይቷ፣ “የኢትዮጵያ ጨካኝ አምባገነኖች መንግስት አሸባሪ ናቸው ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች እና ቡድኖች ጋር ዘጋቢዎች መነጋገር መቻላቸውን አይወድም፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኞች ማድረግ ያለባቸው እንደ እነዚህ ያሉ ተግባራትን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ስራን የሚያከናውኑ ከሆነ ዝም ብሎ ተራ ወሬ የሚያስተላልፍ አፈ ቀላጤ የመሆን ትግባራትን መፈጸም ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ባለስልጣኖቹ እንደዚህ ዓይነቶቹን የሞኝ የውንጀላ ክሶች በአስቸኳይ እርግፍ አድርው በመተው ጓደኞቻችንን መልቀቅ አለባቸው፡፡”

ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW በአጠቃላይ ከርዕዮት ጎን ነበር፣

ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW በርዕዮት እና በውብሸት ላይ ተመስርቶ የነበረውን የድድብና ክስ እንዲህ በማለት አውግዟል፡፡ “እንደ ክሱ ፋይል ከሆነ ማስረጃው በዋናነት በድረ ገጽ መስመሮች በመጠቀም በመንግስት ላይ ሸንቋጭ የሆነ ትችቶችን የሚያቀርቡትን እና በስልክ የተደረጉትን ውይይቶች በተለይም በምንም ዓይነት ሁኔታ ከሽብር ወንጀል ጋር ሊገናኙ የማይችሉትን ስለሰላማዊ ተቃውሞ ድርጊቶች የሚደረጉት ውይይቶች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ በቀረበው የክስ ፋይል ላይ ተከላካዮች ለተከሰሱበት ወንጀል ሌላው ቀርቶ መሰረታዊ የሆኑ የወንጀል ዝርዝሮችን እንኳ ያላሟ ነው…“ በማለት በይፋ ተቃውሞታል፡፡

አምነስቲ ኢነተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትም ከርዕዮት ጎን በመሰለፍ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በእርሷ ላይ እያደረገ ባለው የችሎት ሂደት ላይ ያለውን ቁጣ እንዲህ በማለት ገልጿል፡፡ “ምንም ዓይነት የወንጀል ጥፋት ለማጥፋታቸው ሊያስረዳ የሚችል ማስረጃ የለም፡፡ እነዚህ እስረኞች ህጋዊ በሆነ መልኩ መንግስትን በመተቸታቸው ምክንያት እየተቀጡ ያሉ የህሊና እስረኞች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ መፈታት አለባቸው፡፡“

ፓምባዙካ የዜና ወኪል/Pambazuka News ርዕዮት መፈታት እንድትችል የውትወታ ዘመቻ አደራጅቶ ነበር፡፡ ፓምባዙካ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “የመንግስትን ኢፍትሀዊነት መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ለእውነት እና ለፍትህ በጽናት በመቆሟ ምክንያት ዓለም አቀፍ ዝናን እንድትጎናጸፍ አስችሏታል፡፡“

ደፋር ጋዜጠኞችን እየመረጠ ሽልማት የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን ሽልማት/International Women’s Media Foundation’s Award የሎስአንጀለስ ታይምስ/Los Angeles Times መጽሔት እ.ኤ.አ በ2012 የአሸናፊነት ሽልማቱን በሰጠበት ወቅት ለርዕዮት እንዲህ በማለት ተሟግቶላት ነበር፣ “ርዕዮት ዓለሙ በቬርሊ ሂልስ በተደረገው ጠቃሚ እራት ግብዣ ላይ ሳትገኝ ቀርታለች፡፡ ሆኖም ግን ጥሩ ይቅርታ ይደረግላታል፡፡ የ31 ዓመቷ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው እና በጣም አስከፊ በሆነው አይጦች በሚተራመሱበት እና ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ ታስራ ትገኛለች፡፡ ስለድህነት፣ ስለተቃውሞ ፖለቲካ እና ስለጾታ እኩልነት በድፍረት በመጻፏ ምክንያት ከተበየኑባት አምስት ዓመታት ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በሁለተኛው ዓመት እስር ላይ ትገኛለች፡፡“

ርዕዮት ከጎኗ የቆሙ ወንድሞችም አሏት፣

ኤሊያስ ወንድሙ፣ የጸሐይ አሳታሚዎች አሳታሚ፣ በርዕዮት ስም ሽልማቱ ከሚገኝበት ቦታ በመገኘት IWMF ያዘጋጀላትን እና አሸናፊ የሆነችበትን ሽልማት ተቀብሎላታል፡፡

ኤሊያስ በርዕዮት ስም ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ርዕዮትን ለዚህ ሽልማት ስጠቁም በእርሷ ላይ ያለውን ድፍረት ለማሳየት ነበር የፈለግሁት፣ ስለሆነም በሀገራችን ያሉ ልጃገረዶች ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የለሾች ድምጽ ለመሆን ከመደፋፈር ወደኋላ አይሉም፡፡ የአንድን መንግስት ፖሊሲ በመጻፍ ትችት የሚያደርግን ሰው በአሸባሪነት መክሰስን እንዴት አድርጎ በመሬት ላይ ማነጻጸር ይቻላል?“

ኤሊያስ እንዲህ የሚል ሌላ አማራጭ ሰጥቶ ነበር፣ “ተገቢ በሆነ ስልጠና እጥረት መሰረት ጋዜጠኞቻችን ፍጹም አይደሉም ሊሆኑም አይችሉም፣ ሆኖም ግን ለዚህ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የሚሰሯቸውን ስህተቶች እየተከታተሉ ወንጀለኛ በማድረግ መቅጣት ተገቢ አይደለም፣ ሆኖም ግን ማረም እና ማስተማር ተገቢ ይሆናል፡፡“

የርዕዮት የእጅ ጽሁፍ ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ሾልኮ በመውጣት ለIWMF በመድረስ እውነተኛውን የጋዜጠኝነት ድፍረት በተገባር አሳይቷል፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ በመጠቀም የሚከተሉትን ቃላት አስፍራ ነበር፡

በኢትዮጵያ ወደፊት የተሻለ ነገርን ለማምጣት አንድ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ እምነት አለኝ፡፡ በኢትዮጵያ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎቸ ስላሉ በማወጣቸው ጽሁፎቼ አማካይነት ማጋለጥ እና መቃወም አለብኝ፡፡ ምክንያቱም ጋዜጠኝነት እራሴን በፅናት ላሰማራበት የሚገባ ሙያ በመሆኑ ነው፡፡ ለኢህአዴግ ጋዜጠኝነት ማለት ለፕሮፓጋንዳ ስራ ለገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ ብቻ አድርጎ እንደሚያየው አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለእኔ ጋዜጠኞች ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የለሾች ድምጽ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የተጨቆኑትን የሚያጋልጡ በርካታ ጽሁፎችን የጻፍኩት፡፡

ነጻነትን ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ወደ አደባባይ በመውጣት በመንገዶች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ንጹሀን ዜጎችን በጥይት መደብደብ፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት ማጋዝ…እንዲሁም የመናገር፣ የመደራጀት ነጻነትን መከልከል እና ፕሬስን ማፈን፣ በሙስና መዘፈቅ፣ የአንድ ጎሳ ቡድን በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ መቅረብ የመሳሰሉት ነገሮች የመንግስታችን ጥቂት መጥፎ ስህተቶች ናቸው፡፡ እንደዚህ ያሉ ዘገባዎችን ፈልፍዬ በማውጣት በማሳየው ድፍረት ዋጋ ሊያስከፍለኝ እንደሚችል አስቀድሜ አውቃለሁ፡፡ እናም ያንን ዋጋ ለመቀበል ዝግጁ ነበርኩ፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 ርዕዮት የዩኔስኮን የጉሌርሞ ካኖንን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት/UNESCO Guillemo Cano World Press Freedom Prize አሸናፊ ሆና ተሸልማለች፡፡

ሽልማቱን ከሰጠ በኋላ ዩኔስኮ እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር፣ “ወ/ት ርዕዮት ነጻ በሆነ ዓለም አቀፍ የሜዲያ ባለሙያዎች የዳኞች ቡድን ላሳየችው ልዩ የሆነ ድፍረት፣ እምቢተኝነት እና ሀሳብን በነጻ ለመግለጽ ባላት የዓላማ ጽናት ለእርሷ ዕውቅና በመስጠት ለሽልማቱ እንድትቀርብ ተደርጓል፡፡“

ርዕዮት ዓለሙ እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጋር ያደረገችው ቃለመጠይቅ፣

ርዕዮት ዓለሙ በአሜሪካ ደምጽ የአማርኛው አገልግሎት ጋዜጠኛ በሆነው በሰለሞን አባተ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላታል፡፡ (ከዚህ በታች ያለው በእንግሊዝኛ ከተረጎምኩት በመውሰድ እንደገና ወደ አማርኛ የተተረጎመ የእራሴ ትርጉም ነው፡፡ የርዕዮትን ቃላት በተቻለ መጠን ትክክለኛ ትርጉማቸውን በማዘጋጀት የቃላት ትርጉማቸውን ብቻ ሳይሆን ተመሳስሎዎችን እና የተለመዱ የቋንቋ አባባሎችንም በማከተት ለማቅረብ ሞክሪያለሁ፡፡)

ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ የነበረው ቃለመጠይቅ እንደገና ወደ አማርኛ ተመልሶ ለአንባቢዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡

ሰለሞን፡ ርዕዮት ዓለሙ፣ እንኳን ደስ ያለሽ (ከእስር ቤት በመፈታትሽ ምክንያት) እናም እንኳን በሰላም ወደ ቤትሽ ለመመለስ አበቃሽ፡፡

ርዕዮት፡ እናንተንም እንኳን በሰላም ለማግኘት አበቃኝ፡፡

ሰለሞን፡ ከእስር ቤት በመለቀቅሽ ምክንያት ደስ የተሰኙ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡ ለመሆኑ በስንት ሰዓት ነው ከእስር ቤት የተለቀቅሽው?

ርዕዮት፡ ወደ 4 ሰዓት አካባቢ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሆኖም ግን ሰዓቱን በእርግጠኝነት አላረጋገጥኩም፡፡

ሰለሞን፡ ጧት ነበር የተፈታሽው?

ርዕዮት፡ አዎ፡፡

ሰለሞን፡ የመፈታትሽ ሁኔታ እንዴት ነበር? ከእስር ቤት ሲለቅቁሽ ምንድን ብለው ነገሩሽ? ከእስር ቤት እንደምትለቀቂ ቀደም ሲል የምታውቂው ነገርስ ነበርን?

ርዕዮት፡ የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ወደ እኔ በቀጥታ በመምጣት ሂጂ አሉኝ፡፡ ቀልድ ነው የሚል ሀሳብ ነበረኝ፡፡ ለምን እና በምንድን ምክንያት ነው ከእስር ቤት የምለቀቀው በማለት ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ እንዲህ አሉ፣ “ከዚህ ውጭ!“ ምክንያቱም ከሌሎች እስረኞች ጋር ምን እንደሚያደርጉ ስለምገነዘብ ነው ለምን እና በምንድን ምክንያት ነው ከእስር ቤት የምለቀቀው በማለት ጥያቄ አቅርቤ የነበረው፡፡ ስለእኔ ከእስር ቤት የመለቀቅ ሁኔታ ያልተጣራ እና የተድበሰበሰ ዘገባ ለህዝብ እናቀርባለን የሚል ሀሳብ ካላችሁ እኔ እውነቱን እንደምናገር ታውቁታላችሁ፡፡ ስለሆነም እውነቱን ለህዝብ ከተናገርኩ በኋላ መልሳችሁ ወደዚህ እስር ቤት የምታመጡኝ ከሆነ ከእስር ቤት አለመቀቄን እወዳለሁ፡፡

ከዚያ በኋላ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረብኩላቸው፣ “ምንድን ነው እየተካሄደ ያለው?“ እንዲህ አሉ፣ “ይኸው ነው፡፡“ እኔ ይቅርታ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ቅደመ ሁኔታ አልጠይቅም፡፡ ይቅርታ የመጠየቂያ ጊዜዬ ቀደም ሲል አልፏል እና እርሱንም አልቀበልም በማለት ውድቅ አድርጌዋለሁ ምክንያቱም በመጸጸት ቀርቦልኝ በነበረው ቅጽ ላይ “ወደ ቀድሞው ሁኔታ ተመልሻለሁ የሚል ቋንቋ ነበረበት፡፡” ያጠፋሁት ጥፋት ስላልነበር ያንን ጥፋት ያላጠፋሁ መሆኔን አምኘ ያንን ቅጽ አልሞላም በማለት እንዲመለስ አድርጌ ነበር፡፡

መፈታት የነበረብኝ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 ነበር፡፡ የእኔ በቅድመ ሁኔታ የመፈታት ሁኔታ አልፏል አሉ፡፡ ስለሆነም ከእስር ቤት እንለቅሻለን፡፡ እንግዲህ የሰጡኝ አጭሩ መልስ ይኸ ነበር፡፡ ለእኔ ከእስር ቤት መለቀቅ መሰረቱ ያ ነበር፡፡

ሰለሞን፡ በነገራችን ላይ የጤንነትሽ ሁኔታ እንዴት ነው?

ርዕዮት፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት ከጥቂት ዓመታት በፊት በአንደኛው ጡቴ ላይ የቀዶ ህክምና ተደርጎልኛል፡፡ሌላኛው ጡቴ በአሁኑ ጊዜም እብጠት ይታይበታል፡፡ ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል ብለውኛል፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ቀዶ ህክምና እንዲደረግልኝ አልፈለግሁም ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በአንደኛው ጡቴ ላይ ቀዶ ህክምና ተደርጎልኛል እናም ጥቂት ወሰብሰብ ያሉ ነገሮች ተፈጥረውብኝ ነበር፡፡ ይህንን ነገር አላደረግሁትም፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር የሚፈቅድ ከሆነ አሰራዋለሁ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

ሰለሞን፡ የምርመራ ውጤቶች በሁለቱም ጡቶችሽ ላይ ምን ያመላክታሉ?

ርዕዮት፡ ከሁለቱ አንደኛው የተሻለ ነገር ያሳያል፡፡ ሌላኛው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያመመኝ ነው የመጣው፡፡

ሰለሞን፡ ከነገርሽኝ ሌላ በተጨማሪ መደበኛ የሆነ የህክምና ምክር እና የትኩረት ድጋፍ አላገኘሽም ነበርን? ጥብቅ የሆነ የሕክምና ክትትል ታደርጊ ነበርን?

ርዕዮት፡ በፍጹም እንደዚያ አልነበረም፡፡

ሰለሞን፡ በየዕለቱ እና በየሳምንቱ የሕክምና ምክር ይሰጥሽ ነበርን? የሕክምና ምክር ወይም ደግሞ የሕክምና ምርመራ ይደረግልሽ ነበርን?

ርዕዮት፡ የለም፡፡ በፍጹም እንደዚያ አልነበረም፡፡ ቀደም ሲል እንዳልኩት ቀዶ ሕክምና መደረጉን ከተውኩት በኋላ እንደ ሳይነስ ለመሳሰሉት ነገሮች ካልሆነ በስተቀር ለዚህኛው ጉዳይ የሕክምና ትኩረት አላገኘሁም ነበር፡፡ የሕክምና ክብካቤ አላገኘሁም፡፡ ምንም ዋጋ የሌለው ነገር ቢሆንም እንኳ የቀዶ ሕክምና እንዳደርግ ነግረውኝ በፍጹም አላደርገውም ብያለሁ፡፡ ምንም ዓይነት የቀዶ ሕክምና ላለማድረግ ወስኘ ነበር፡፡ ምክሮች ያስፈልጋሉ የሚል አስተሳሰብ አልነበረኝም፡፡ ቀደም ሲል እንደተናገርሁት ከወር በፊት የሕክምና ትኩረት አግኝቼ ነበር፡፡ ስለእኔ ጡቶች ጉዳይ ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር አላደረግሁም፡፡

ሰለሞን፡ በእስር ቤት ስለቆየሽበት ሁኔታ ጥቂት ልትነግሪኝ ትችያለሽን? ይቅርታ አድርጊልኝ ወደዚያ መልሸ ልወስድሽ አልፈልግም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስለዚያ ጉዳይ ማወቅ የሚፈልጉ በርካታ አድማጮች ስላሉ ነው፡፡

ርዕዮት፡ አዎ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ እንዴት አድርጌ እንደምነግርህ አላውቅም፡፡ እንደ እስረኛው ሁኔታ ይለያያል፡፡ አጠቃላይ በሆነ ለመናገር ስለእስረኞች ያለው አያያዝ ጥሩ ነው የሚባል አይደለም፡፡ ሆኖም ግን የፖለቲካ እስረኞች በተለዬ ሁኔታ ጥሩ በሆነ ሁኔታ የሚያዙ አይደለም፡፡ የእኔን ጉዳይ ብትወስድ ለአንድ ዓመት ከ8 ወራት ያህል ቤተሰቦችን እንዳላይ ተከልክየ ነበር፡፡ እናት እና አባቴን ብቻ እንዳይ ይፈቀድልኝ ነበር፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ነው እህቴ መጥታ እንድትጎበኘኝ የተፈቀደው፡፡

ስለሆነም ከቤተሰቦቼ ጉብኝት ጀምሮ መብቶቼ አይጠበቁም ነበር፡፡ ሕጉ የሚለው ነገር ቢኖር የኃይማኖት አባቴን፣ የሕግ አማካሪ ጠበቃዬን እና ሌሎችንም ሰዎች የማግኘት እና እርዳታ እና ምክር የማግኘት መብት እንዳለኝ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት ብቻ ነበር እህቴ እንኳ መጥታ እንድታየኝ የተፈቀደው፡፡ ለአንድ ዓመት እና ለ8 ወራት ሙሉ እናቴ እና አባቴ ብቻ ናቸው እየመጡ እንዲጎበኙኝ ተፈቅዶላቸው የነበረው፡፡

በእስር ቤት ውስጥ በርካታ ችግሮች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህልም የመጽሐፍት ችግር፡፡ መጽሐፍት በተለይም የፖለቲካ መፅሐፍ ለማግኘት እንዲያውም ፖለቲካ የምትል ቃል ያለበት መጽሐፍ በተለይም በአሁኑ ጊዜ ከታዬ እንኳ ከፍተኛ የሆነ ቸግር ነበር፡፡ እንግዲህ መጽሐፍትን ከውጭ ለማግኘት ነው ይኸ ሁሉ ችግር ያለው፡፡ ሌሎችን በርካታ ነገሮችን መግለጽ እችላለሁ፡፡ በአጠቃላይ በእስር ቤት የነበረው ቆይታዬ ጥሩ አልነበረም፡፡ እስር ቤት በፍጹም ጥሩ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ለእኔ የስቃይ ጊዜ ነበር፡፡

ሰለሞን፡ አባትሽ የአንች የሕግ አማካሪ ጠበቃ ነበሩን?

ርዕዮት፡ አዎ አባቴ የእኔ የሕግ አማካሪ ጠበቃዬ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሌላም ጠበቃ ነበረኝ፡፡

ሰለሞን፡ አባትሽን እንደ እራስሽ የሕግ ጠበቃ እንጅ እንደሌላ የሕግ ጠበቃ አልነበረም የምታያቸው?

ርዕዮት፡ አይደለም፡፡ ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማግኘት አልችልም ነበር፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከማንም ጋር ግንኙነት አልነበረኝም፡፡ አባት እና እናቴ ወደ እስር ቤት በመምጣት ይጎበኙኝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን አባቴ ለሕግ ምክር አገልግሎት አይመጣም ነበር፡፡ ስለአኔ የህግ ጉዳዮች ምንም ነገር መነጋገር አንችልም ነበር፡፡ ወይም ደግሞ ሌላ የሕግ አማካሪም እንዳገኝ እና ምክር እንድቀበል አይደረግም ነበር፡፡

ሰለሞን፡ በእስር ቤቱ ውስጥ የነበረው ንጽህና ስለምግቡ፣ ውኃው እና ስለሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች የነበረው ሁኔታ እንዴት ነበር?

ርዕዮት፡ እኔ በቤተሰቦቼ የሚመጣልኝን ምግብ ነበር የምመገበው፡፡ የእስር ቤቱን ምግብም አይቸዋለሁ፡፡ ጥሩ ብለህ ይመትጠራው ነገር አይደለም፡፡ መጥፎ ነው፡፡ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመዋል ለተባሉ የፖለቲካ አስረኞች የሚቀርበው የተለመደው የኢትዮጵያ እንጀራ እና ወጥ ምግብ በጣም አስቀያሚ ነው፡፡

ሰለሞን፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ስለፖለቲካ እስረኞች ጥያቄ ሲቀርብላቸው የሚሰጡት መልስ “ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኞ የሉም” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ርዕዮት፡ ያ ዓይን ያወጣ ውሸት ነው፡፡ እዚያ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ሌላው ቀርቶ ስለ እራሴ ሁኔታ እንኳ ልነግርህ እችላለሁ፡፡ የእኔ ጉዳይ እራሱ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ እኔን ለእስር የሚያበቃ ምን ወንጀል ሰራሁ? ምናልባትም የእኔን የችሎት ክርክር ሂደት ተከታትለኸው ይሆናል፡፡ ሰለሆነም እነርሱ አሸባሪ የሚል ውንጀላ በመለጠፍ የሀሰት ክስ መስርተውብኝ የችሎት ሂደት ሲካሄድ በነበረው እና ሲቀርብ በነበረው ማስረጃ እንዳያችሁትም ምንም ዓይነት ሽብርተኝነትን ለመፈጸሜ ወይም ደግሞ የሽብር ድርጊት ሙከራ ለመፈጸሙ ሊያቀርቡ የሚችሉት ማስረጃ አልነበራቸውም፡፡

ይልቁንም እውነታው እና ትክክለኛው ነገር በስልጣን ላይ ስላለው ገዥ አካል ትችት በመጻፌ ምክንያት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስለአንዳንድ ነገሮች ትችት በመጻፋቸው ወይም ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀት አባል በመሆናቸው፣ ወይም ሰዎች ስለመብታቸው በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ እያሉ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኞች የሉም የሚል መልስ መስጠታቸው ይቅርታ አድርግልኝ እና የመካድ አካሄድ ነው፡፡ ሆኖም ያንን የመሰለ ምላሽ በመስጠታቸው በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎችን ብቻ ሊያታልሉ ይችላሉ ብዬ ነው የማምነው፡፡

ሰለሞን፡ አብረውሽ የነበሩት ሌሎች እስረኞች ሁኔታስ ምን ይመስል ነበር? አያያዛቸው፣ መንፈሶቻቸው፣ እንዲሁም ሀሰቦቻቸው ምን ይመስል ነበር? በአጠቃላይ እዚያ በነበርሽበት ጊዜ ያለው የእስር ቤት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር?

ርዕዮት፡ ወንጀል ለፈጸመ ሰው እና በእስር ቤት ላለ እንዲሁም ምንም ዓይነት ወንጀል ሳይፈጽም በቁጥጥር ስር ውሎ በእስር ቤት ያለ ሰው ሁሉም እስረኞች ቢሆኑም እንኳ ሰብአዊ መብቶቻቸው ሊጠበቁላቸው ይገባል፡፡ መሆን ያለበት ነገር ይህ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያለው ከምግቡ ሁኔታ ጀምሮ መጥፎ ነገር ነው፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በርካታ እስረኞኝ እየተያዙ እየገቡ እና እስር ቤቱን አጨናንቀውት ባለበት ሁኔታ የሚታየው ነገር ሁሉ አስከፊ ነው፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት እስር ቤት በቆየሁባቸው ጊዚያት ከአጠቃላይ እስረኛ ህዝብ ተነጥለን ከሌሎች አራት እስረኞች ጋር ነበርኩ፡፡ ሆኖም ግን ሌሎች በጣም በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ እየተጠበቁ ያሉበት ሁኔተ ነው የሚታየው፡፡ ስለመድኃኒት፣ ስለህክምና ያለው ሁኔታ በቂ ነው የሚባል አይደለም፡፡

የሕክምና ምርመራ የሚባል ነገር የለም፡፡ የህክምና ምርመራ የምታገኘው በከፍተኛ ሁኔታ በምትታመምበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዚያ ውጭ ለስቃይ ማስታገሻ መድኃኒቶችን ያዝዛሉ፡፡ በአብዛኛው በእስር ቤቱ ያለው ሁኔታ ይህንን ይመስላል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከፖለቲካ እስረኞች ጋር ሰላምታ ለማቅረብ የሚሞክር ሰው ካለ በርካታ የሆኑ ችግሮችን እንዲጋፈጥ ይደረጋል፡፡ ቦታው የጭንቀት ቦታ ነው፡፡ ከውጭው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር እንኳ ፍርሀት ንጉስ የሆነበት ግቢ ነው፡፡ በእስር ቤቱ ግቢ ውስጥ የምናየው ነገር እንግዲህ ይህንን ይመስላል፡፡

ሰለሞን፡ በርካታ ችግሮች በምትይበት ጊዜ ምን ዓይነት ችግሮች አሉ? የአካል ስቃይ የማሰቃየት ድርጊቶች ይፈጸማሉን? ድብደባዎች እና ሌሎች ነገሮችም ይፈጸማሉን?

ርዕዮት፡ እኔ እየነገርኩህ ያለሁት ስለሴት እስረኞች ሁኔታ ነው፡፡

ሰለሞን፡ ስለእዚያ ጉዳይ ዘርዘር ባለ ሁኔታ ብትነግሪኝ፡፡ የሴት እስረኞች አጠቃላይ ሁኔታ እና አያያዝ ምን ይመስላል? ከሕግ አግባብ ውጭ የሆነ አያያዝ ፈጸምባቸዋልን?

ርዕዮት፡ አዎ፡፡ይህንን ነው እየነገርኩህ ያለው፡፡ አንድ ሰው የፖለቲካ እስረኛ ጋር ሰላምታ በመለዋወጡ ምክንያት ችግር ሊደርስበት አይገባም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ለፖለቲከ እስረኛ ሰላምታ ሲሰጥ ከታዬ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፣ ወይም ደግሞ ስለዚያ እስረኛ ጉዳይ የተለየ ትኩረት በመስጠት ይከታተሉታል፡፡ የተለየ ምርመራ ወይም እንደዚህ ያለ ነገር የሚካሄድበት ሆኖ ይቀመጣል፡፡ አየህ ነገሮች በእስር ቤት እንደዚህ ናቸው፡፡

ሰለሞን፡ የወደፊት ዕቅዶችሽ ምንድን ናቸው? በአጭሩ አጠቃላይ ያለሽ ምልከታ ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ምንድን ለማድረግ ታስቢያለሽ?

ርዕዮት፡ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት ይህ ድንገተኛ የመፈታት ነገር ነው፡፡ ስለሆነም የነበረህን ጊዜ አጠናቅቀህ ስትወጣ ወይም በድንገት ስለተፈታህበት ነገር ስታውቅ ነው መናገር የምትችለው፡፡ ስለሆነም በድንገት እስከተፈታህ ድረስ ይህ ጥያቄ ለየት ያለ ሊሆን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ የማስበው ነገር ቀደም ሲል ተቋርጦ የነበረውን ህይወቴን እንደገና መምራት መቀጠል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ምንም ዓይነት ትግል ያካሄድኩ ቢሆንም እንኳ በጽሁፍም ሆነ በማንኛውም በምችለው ነገር ሁሉ ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡

(የቃለ መጠይቁ መጨረሻ)፣

ለርዕዮት እና በእስር ቤት ለቀሩት ለሌሎች ወንድሞቿ እና አህቶቿ ያለኝ የእኔ የግሌ አክብሮት፣

ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ጥቂቶች ታላቅ ሆነው ይወለዳሉ፣ ጥቆቶች በሂደት ስኬትን ይጎናጸፋሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ በእራሳቸው ላይ በመተማመን ታላቅ ይሆናሉ፡፡“

ለጀግኖች እና ጀግኒቶች በተመሳሳይ መልኩ ማለት ይቻላል ብዬ አስባለሁ፡፡

እንደ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ የዞን 9 ጦማሪያን እና ሌሎችም እንደ እነርሱ ያሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኛ ዜጎች ጀግኖች እና ጀግኒቶች ሆነው አልተፈጠሩም፡፡ ጀግንነትንም አልፈለጉም ነበር፡፡ እድሉ የሚሰጣቸው ከሆነ ጀግንነትን ብቻውን ይተውታል፡፡ ጀግንነት እና ጀግኒነት ሲባል ብቻቸውን መተው ማለት አይደለም፡፡ ዕድል እና እጣ ፈንታ በጀግንነት ላይ ይተማመናሉ፡፡

በርዕዮት ዓለሙ እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ መሪ በነበረችው በብርቱካን ሚደቅሳ መካከል በርካታ በትይዩ የተሰመሩ ልዩነቶችን አስተውላለሁ፡፡ ብርቱካን ተመሳሳይ የሆኑ ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ የእስር ቤት አያያዞች ማለትም ለብቻ ነጥሎ ማሰር እና ማዋረድ ተፈጽመውባታል፡፡ ብርቱካን በፖለቲካው ዘርፍ የመጀመሪያዋ መንገድ ፈጣሪ ብቻ አልነበረችም ሆኖም ግን ለኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች ሞዴል እና አርአያ ጭምር የነበረች እንጅ፡፡ በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በጽናት በመቆም መንፈሰ ጠንካራነቷን በተግባር በማሳየት ትምህርት ሰጥታለች፡፡

ብርቱካን በአሁኑ ጊዜ እርሷ ተሸክማው የነበረውን ዓይነት ኃላፊነት ርዕዮት ተሸክማ ስታይ በኩራት በመሞላት በኢትዮጵያ የሩጫ ቅብብሎሽ ዱላውን ለሌላ በማስተላለፍ በማበረታታት ትመለከታለች፡፡ በእሳት የተፈተነ ክብር ምሳሌ የነበረች መሆኗን ወደ ኋላ መለስ ብላ ስትመለከት ትንሽ ፈገግ ትላለች፡፡

ርዕዮትን እና ብርቱካንን በማሰር ብቸኛ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው እና አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊን ታሪክ የሰይጣን መልዕክተኛ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የተረገመ እና መቅኖ ያጣ ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ገሀነም በእራሱ እንዳለ ሆኖ መለስ ዜናዊ ሲጨመርበት ግን የገሀነም ገሀነም ይሆናል!

እነዚህ ደፋር ወጣት ጋዜጠኞች እንደ ሌሎች አብዛኞቻችን ሳይሆን የተወሰነላቸውን የዕድል ዕጣ ፈንታ በሚያገኙበት ጊዜ በአካል ጉዳት ስቃይ ወይም በፍርኃት ተሸብበው ወደኋላ አያፈገፍጉም፡፡

እስክንድር ነጋ በራሱ ድረ ገጽ በመጻፉ ብቻ የ18 ዓመታት እስራት ሲበየንበት በመፍራት አንገቱን አልደፋም፡፡

ርዕዮት ዓለሙ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ14 ዓመታት እስር ሲበይንባት በሎሌነት መልኩ አላጎበደድችም፡፡

ውብሸት ታዬ ነጻነቱን ለመቀዳጀት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን አልለመነም፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ለነጻነቱ ሲል ነብሱን አልሸጠም፡፡

አበርሃ ደስታ ደስታ ከሚያምንበት ነገር በመፍራት አላፈገፈገም፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከመታሰሩ በፊት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2014 በራሱ የግንኙነት ድረ ገጽ አብርሃ ደስታ ህወሀት እራሱ ነጻነት ያለው ድርጅት እንዲሆን አጥብቆ ተከራክሯል፡፡ ከህወሀት አባላት ጋር ጠላትነት የማልሆንበት ምክንያት የህወሀትን ካድሬዎች የምሁርነት እጥረት እና ክስረት ስለማውቅ ነው ብሎ ነበር፡፡

ሁሉም የኢትዮጵያ ደፋር ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ሁሉንም ነገር የላይኛው ከንፈራቸው ሳይንቀጠቀጥ ይቀበላሉ፡፡

በምንም ዓይነት መልኩ ለጭቆና አያጎበድዱም፡፡

መሰረታቸውን በመያዝ በጽናት ይቆማሉ፡፡

በፍርኃት እና በባርነት ተቀፍድደው በዘራፊ ወሮበላ አምባገነኖች መዳፍ ስር ነጻነታቸውን ተነፍገው ከሚኖሩ ይልቅ በእስር ቤት ነጻ ሆነው መኖራቸውን መርጠዋል፡፡

ዌንዲ ሸርማን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢትዮጵያ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲ የምታካሂድ ሀገር ናት፡፡“ በአባባላቸው ትክክል ናቸው ሆኖም ግን ጊዜው ገና ነው፡፡

ርዕዮት እና የእርሷ ትውልድ የሚገባቸውን ቦታ ሲይዙ ኢትዮጵያ ትክክለኛ በመጎልበት ላይ ያለ ዴሞክራሲን እውን ታደርጋለች፡፡ ርዕዮት ላለፉት አራት ዓመታት ከ17 ቀናት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በእስር ስትማቅቅ ባትቆይ ኖሮ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ምን ያህል አስተዋጽኦ ታደርግ እንደነበር የሚያስገርም አይሆንም፡፡

ለእስክንድር ነጋ፣ ለውብሸት ታዬ፣ ለተመስገን ደሳለኝ፣ ለአብርሃ ደስታ እና ለሌሎችም በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን እና የፖለቲካ እስረኞች ታላቅ ክብር አለኝ፡፡

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ጀግኒት እና ለእኔ ኢትዮጵያዊት ጀግና ለርዕዮት ታላቅ ክብር አለኝ!

አምላክ ረዥም እድሜ እንዲያጎናጽፋት እና ትግሏን እንድትቀጥል እመኛለሁ፡፡

“ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ፡፡” ርዕዮት ዓለሙ፣ እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሀምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም

አንቀፅ 39: የራስን ዕድል በራስ መወሰን ሲባል –አስራት አብርሃም

$
0
0

 

Asrat Abrha

አስራት አብርሃም

ውብሸት ሙላት በተባለ የህግ ምሁር ሰሙኑ ገበያ ላይ የዋለው “አንቀፅ 39 የራስን ዕድል በራስ መወሰን” የተሰኘ መፅሐፍ መግቢያ (ፀሐፊው የቃላት ክልሼነት ለማስወገድ ነው መሰል ማስረጊያ የሚል ርዕስ ሰጥቶታል) “የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት አዲስ አይደለም፤ አሮጌ ነው። ብዙ ተፅፎበታል።” በማለት ነው የሚጀምረው፤ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በተቃውሞም፣ በድጋፍም ጭምር በልዩ ልዩ ሚዲያዎችና መንገዶች ሲፃፍበት እንደነበር ይገልፅና ይህን መፅሐፍ ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያት ሲገልፅ ደግሞ “ለአብዛኛው ሰው በሚሆን መልኩ ጠቅለል ብሎና ራሱን ችሎ በመፅሐፍ መልኩ ስለሌለ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በማሰብ” መሆኑን ይገልፃል።

ይህ መፅሐፍ በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 39 ዘጠኝ ላይ ያለው የራስ ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል የሚለውን ሀሳብ ከታሪክ፣ ከፍልስፍና፣ ከህግና ከፖለቲካ አንጻር እያነሳ በጥልቀት የሚተነትን ነው፤ እኔም ሌሎች የሀገራችን ምሁራን በስፋትና በጥልቀት እስኪተነትኑትና እስኪፈትሹት ድረስ እንደመጥምቁ ዮሃንስ መንገድ ልጠርግ በማሰብ ነው በዚህ መፅሐፍ ዙሪያ አንድ ሁለት ለማለት የወደድኩት።

የመፅሐፉ የመጀመሪያው ምዕራፍ ንዑስ ርዕስ “የብሄር ጥያቄ” የሚል ሲሆን ፀሐፊው በኢትዮጵያ ጨቋኝ ከሚባለው ብሄር የተገኘው ነው ያለውን ዋልሊኝ መኮንን “ኢትዮጵያ የአንድ ብሄር ሀገር ሳትሆን የብዙ ብሄረሰቦች ሀገር ናት” ገፅ (3-4) በማለት ድፍሮ ለመጀመሪያ ጊዜ መፃፉን ይነግረናል። የአንድ የሶፊስቶች ተረት በማምጣት፤ የብሄር ጥያቄ የብሄር ጭቆና ውልድ መሆኑን ይገልፅና የጭቆናው ዓይነትና ደረጃው ግን ያን ያህል እንደሚባለው የተጋነነ እንዳልሆነ ነው የሚያትተው፤ ተረቱ የሚለው እንደዚህ ነው፤ አንድ ሰው በደል ይደርስበትና ክስ ለማቅረብ ወደ ፍርድ ቤት ይሄድና ለፍርድ ቤቱ የሚያስገባውን ማመልከቻ ለአንድ ራቦር ፀሐፊ እየነገረ አፃፈ አሉ፤ ፅፎ እንደጨረሰ ለባለጉዳዩ ያነብለታል፤ ሲነበብለት ባለጉዳዩ  ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ይጀምራል፤ የፃፈለት ሰውዬ “ምነው ጌታዬ ማልቀስዎ?” ብሎ ቢጠይቀው “ለካስ ይህን ያክል ተበድዬ ኑሯል? አለ ይባላል” (ገፅ 5) ይልና ፀሐፊው ሲቀጥል በእርግጥ “ሰውዬው ተበድሏል፤ ትንሽ የበደል ጫፍ ያገኘው ራቦር ፀሐፊ እጅግ አጋንኖና አጣፍጦ እንደፃፈው ሁሉ የኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ከራቦር ፀሀፊው አድራጎት ጋር ሲያመሳስሉት ይሰማል” ይለናል። ዋልሊኝ ሲል ሰምተው “ለካ ይህን ያህል ተበድለን ኖረናል” ብለው የብሄር ጥያቄ እንዳጎኑት ዓይነት አድርጎ ነው የሳለው የሚመስለኝ፤ ለማንኛውም ዋልሊኝ መኮንን ደፍሮ ፃፈው እንጂ በያኔዋ ኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄና ጭቆናው ጣሪያ የነካ ጉዳይ የነበረ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ጥያቄው ራሱ አሁን ያፈራው ውጤት በማየትም መረዳት የሚቻል ነገር ነው።

በዚህ የብሄር ጥያቄ ላይ በህግ መንግስቱ የሚታየው ጉድለት አንድ ብሄር ወይም ብሄሮች ስለሚለያዩበት እንጂ አንድ ለመሆን ወይም ለመጠቃለል ቢፈልጉ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ያለማለቱን ልብ ብሎታል፤ ስለዚህ ጉዳይ ሲገልፅ “የእኛ ህገ መንግስት ፈፅሞ የብሄሮችን መዋሃድ ወይንም ወደ አንድ ብሄር የመጠቃለል አዝማሚያን በቃልም በተግባርም አላማው አላደረገም፤ ተቃራኒው የበለጠ እውነት ይመስላል” (ገፅ 9-10) ይላል፤ ይሄ ተገቢ የሆነ ምልከታ ነው። ህገ መንግስቱ ከኢትዮጵያ መገንጠል እንደፈቀደ ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ መጠቃለል የሚፈልጉ ህዝቦች ወይም አንድ ብሄር ከሌላ ብሄር ጋር መዋሃድና መጠቃለል ቢፈልግ ስለሚቻልበት ሁኔታ አለማስቀመጡ የህገ መንግስቱ መሰረታዊ ዓላማ ምን እንደሆነ ግርታን ነው የሚፈጥረው፤ ህገ መንግስቱ ሲረቀቅ እንደዚያ ቢደረግ ኖሮ  አንቀፁ ፍትሃዊነት የሚንፀባረቅበት በሆነ ነበር።

ፀሀፊው በስልሳዎቹ ነበረው ዓለም አቀፍና ሃገራዊ የብሄርተኝነት ትግል እንቅስቀሴ ከዳሰሰ በኋላ በእኛ ሀገርም በዚያ ዘመን የነበሩ ልሂቃን ጥያቄው በማራገብና በማጦዝ እንዚህ ደረጃ ላይ እንዳደረሱት ነው የሚያትተው፤ “የዚያን ዘመን ልሂቃን የብሄርን ጉዳይ በየአገኙት አጋጣሚ እና መድረክ ሰብከዋል። የብሄር ብሄረሰብም ስልጣን ትምጣ ብለው ተመኝተዋል። ከዚያም እነዚህ ልሂቃን ህዝቡ ከማለት ፈንታ ሕዝቤ በማለት ሲጠሩ ተስተውለዋል ከዚያም ያን ህዝብ (የብሀረሰብ አባል) ያኔ የሚለውን ልሂቅ እንደሚከተል ቀድመው ያውቁታልና!

እስቲ ላሙን ንዳው አቧራው ይነሳ

ይከተል የለም ወይ ኮርማው እያገሳ

እንደሚባለው መሆኑ ነው፤ ብሄርተኝነት ስትጎንና ስለብሄር ሲወራ የብሄሩ አባል እያገሳ መከተሉ አይቀሬ ነው” በማለት ነው የሚያስቀምጠው።

የዚህ የብሄር ጥያቄ ጉዳይ አላግባብ ሲለጠጥና ሲራገብ የሚኖረው አደገኝነት ሲብራራ ደግሞ አደጋው እንደ ዩጎዝላቪያና እንደ ሩዋንዳ ለጭፍጨፋና ለዘር ማጥፋት ወንጀል ምክንያት እንደሚሆን ነው የሚያትተው። ለዚህ አደገኛ አካሄድ በእኛ ሀገር አልፎ አልፎ የሚታየው ዘርን መሰረት ያደረገ የህዝቦች መፈናቀልና ግጭት እንደማሳያ መቅረብ የሚችል ነው።

በኢትዮጵያ በዘመነ ኢህአዴግ የብሄር ጥያቄ አፈታት በተመለከተ ፀሀፊው ሲያስረዳ ስልጤ፣ መንጃ እና ቅማንት የተባሉ ብሄረሰቦች ጉዳይ ያነሳና በእነዚህ ብሄሮች ጥያቄ ላይ የተጠሰው ምላሽ የሚታየው ተቃርኖና መፋለስ ያስቀምጣል። በሌላ በእኩል ደግሞ በፌደራሉ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ የሚታየው ፍፅም ያልተመጣጠነ ስልጣን በማንሳት በገዥው ፓርቲ የሚሰበከው የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት እውነትነት የሌለው ፕሮፖጋናንዳ መሆኑን በምሳሌ ነው ያስቀመጠው፤ ቁልፍ የሚባሉ መንግስታዊ የስልጣን እርከኖች በእነማን እንደተያዙ በማሳየት።እንደዚሁም በደሬዳዋ አስተዳደርና የሃረሪ ክልል አፈጣጠርን በማምጣት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የብሄር ጥያቄዎችን ለመፍታት የሄደበት መንገድ ከራሱ ከህገ መንግስቱ ሳይቀር ምን ያህል እንደሚቀረን ያሳየናል።

በምዕራፍ ሰባት ላይ ደግሞ የአማራ ጉዳይ ነው የሚያነሳው። አማራ የሚባል ብሄር አለ ወይስ የለም የሚለው የምሁራኑ ክርክር ያነሳና የለም የሚሉትን ትንሽ ጎሸም ያደረጋቸው ይመስለኛል። ይህ ምዕራፍ የሚጀምረው

… እና አማራ ነኝ … መከራ የመከረኝ

መስዋዕትነት ያጠነከረኝ … ፍቅር የተዘከረኝ…

ብፈራንኳ ፍቅርን ነው’ንጂ … በሌላ አልጠረጠርም

ማንም እንዳሻው ለክቶ … እንዳሻው ሊቆርጠኝ ቢያልም…

ከልክ አልፌ አላጥርም

ጉራም ቢሆን ልቀናጣ …

ስሞ ባያሳድገኝ … ነክሶ እሚያነቃኝ አላጣ …

በሚለው የሙሉጌታ ተስፋዬ ግጥም ነው የሚጀምረው። ከዚህ ግጥም ወረድ ብሎ እንዲህ ይለናል “ስለአማራ መፃፌ፣ አማራ ብሄር ስላልሆነ ወይንም የማንነት ጥያቄ ስላነሳ ሳይሆን አንዳንድ ምሁራን ስለአማራ ጉዳይ ሲፅፉ አማራ የሚባል ብሄር የለም በማለት የብሄርነት ህልውናውን ጭምር ከመጠራጠራቸው የተነሳ ነው። … እንደውም አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት እና አልፎ አልፎም ከክርስቲያንነት ጋር አምሳያ በማድረግ ሲያትቱ ይስተዋላል።”

ውብሸት ይህን ዓይነት ዝንባሌ መኖሩን ካወሳ በኋላ ለማጠናከርያነት የፕሮፌሰር መስፍን መከራከሪያ ያነሳል፤ “እሳቸው (ፕሮፌሰር መስፍን) ሊቃውንት አማራ የሚለው ቃል ከስርወ ቃሉ በመነሳት ነፃ፣ የተመረጠ፣ መገዛትን የማይወድ ወዘተ ሕዝብ ነው በማለት የሰጡትን ትርጓሜ መነሻ ያደርጋሉ። አማራ ማለት ነፃ ሕዝብ ማለት ነው ከሚለው አንፃር ብዙም ፍንጭ የማይገኝ ቢሆንም ነፃነትን የሚወድ ለማለት ነው ከተባለም  ነፃነትን የሚጠላ ህዝብ ያለ ስለማይመስለኝ ይህ ዓይነቱ አተረጓጎም ብዙም ስለብሄሩ የሚገልፀው ነገር ያለ አይመስልም”  በማለት ነው የፕሮፌሰር መስፍን  ሀሳብ በምክንያት ውድቅ የሚያደርገው። ገፅ 73 ላይ ደግሞ “ፕሮፌሰር መስፍን ቀጥለውም የተለያዩ ሰዎች “አማራ ነኝ” ሲሉ ክርስቲያን ነኝ ማለታቸውንም እንደሆነ በመግለፅ ክርስቲያን ከሚለው ጋርም ያመሳስሉታል” በማለት አስቀምጦታል፤ በመጨረሻ ይህን ሀሳብ ሲያጠቃልለው “ሊቃውንት ከስርወ ቃሉ በመነሳት ትርጉም የሰጡት አማራ የሚባል ቢያንስ ህዝብ በመኖሩ ነው። የአለቃ ታዬም የአማራን ህዝብ ከየት መጣነት አስረዱ ከማለት ውጪ የለም አላሉም።” በማለት ነው መከራከሪያውን የሚዘጋው። እንግዲህ እኔ የለሁበትም፤ ፕሮፌሰር መስፍን  በህይወት ስላሉ መልስ ይስጡበት። አማራ የለም የሚለው መከራከሪያ የአንድ ህዝብ ህልውና መካድ ብቻ ሳይሆን እንግዲህ ይሄ ጨቋኝ የማሳጣት ሴራ ወይም ወንጀል ተብሎ ያለማስከሰሱም አንድ ነገር ነው።

ይልቅ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ መንጌ ብሶት የወለዳቸው የኢህአዴግ ልጆች ሱሉልታ በደረሱ ጊዜ ዕቃውን ሁሉ ወደ ዝምባዌ ከሸካከፈ በኋላ በቴሌብዥን ቀርቦ በቅጡ የማያውቀውን የኢትዮጵያ ታሪክ ሲደሰኩር የዋለ ዕለት “አማራ ማለት በተራራ ላይ የሚኖር ነፃ ህዝብ ነው፤ ትግሬውም በተራራ ላይ ይኖራል፤ ሌላውም እንደዚሁ በተራራ ላይ ይኖራል እንግዲህ ማነው አማራ?!” ብሎ ነበር ያለው፤ ለካ እንደ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ከፕሮፍ ሸምድዶ ኖሯል፤ በአግባቡ ለመሸምደድም እኮ ልምድና እርጋታ ይጠይቃል፤ ከሄደ በኋላ እንደተሳሳተ ገብቶት ነው መሰል ከቀይ ሽብሩ ለምን ተውኳቸው የሚል ዓይነት የፀፀት ምልክት አሳይተዋል ለገነት አየለ በሰጣት ቃለመጠይቅ ላይ!!

በዚህ መፅሐፍ ላይ ስፊ ትኩረት የተሰጠው ሌላው ጉዳይ የመገንጠል ጉዳይ ነው፤ ይህ አንቀፅ በህገ መንግስቱ እንዲካተት ሆኖ በፀደቀበት እለት የነበሩ ስሜቶች ለማሳየት በወቅቱ እዚያ የነበሩት እና አሁን ሁለቱም በህይወት የሌሉት ነገር ግን ፍፅም ተቃራኒ አቋም የነበራቸው ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ እና ዶ/ር አብዱልመጅድ ሁሴን የተናገሩትን አስቀምጠዋል፤ ሻለቃ አድማሴ “በትናንትናው ዕለት (ህዳር 13/1987 ዓም) ጥቁር ክራቫት አድርጌ ነው የዋልኩት። 90% የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብም በትናንትናው ዕለት በማዘን ወደ እግዚአብሄር ፀልዮአል፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ የከፋ ውሳኔ ተወስኖ፣ ከዚህ የከፋ ህገ መንግስት ወጥቶ አያቅም፤ ጥቁር ቀን ብሎ አውግዞታል” በማለት የአንቀፁን መፅደቅ ሲኮንኑት፤ በተቃራኒው ደግሞ ዶ/ር አብዱልመጅድ “99.9% የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የደስታ ቀን ነው። አንቀፅ 39 ትናንት ባይፀድቅ ኖሮ ግን ለብዙዎች ክፉ ቀን ይባል ነበር፤ ትናንት የፀሀይ ቀን ነው” በማለት ነበር ደስታቸውን የገለፁት።

ፀሀፊው የራስ ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚኖረው ጥቅም እና ጉዳት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በምሁራዊ ትንተና አስደግፎ አቅርቦታል፤ ከአሁን በፊት ከነበረው የእርግማንና የውግዘት አቀራረብ በተለየ ሁኔታ በምሁራዊነት ተጠያቃዊ መንገድ ትርፍ እና ኪሰራው ጉዳትና ጥቅሙ ለማሳየት ጥረት ማድረጉ ነው አንዱ የዚህ መፅሐፍ ጥቅሙ! ይህን መፅሐፍ አንብበን ስንጨርስ በቂ የሆነ እውቀት ስለመገጠል እንደኖረን ያደርገናል፤ መገንጠል ለሚፈልጉ ኃይሎችም ሆነ መገንጠል ለሚቃወሙ ኃይሎች ለሁለቱም እኩል ጠቃሚ የሚሆን ነው፤ ሁለቱም ወገኖች ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው። በሌላ አቅጣጫ ካየነው ደግሞ ጥቅሙናን ጉዳቱን በትክክል ሳይገነዘቡ አንድን ነገር መቋወምም ሆነ መደገፍ ተገቢም አዋጭም ስለማይሆን ነው።

ሌላው በዚህ መፅሐፍ የምናገኘው አዲስ እውቀት የራስን እድል በራስ መወስን እስከመገንጠል መብት በህግ መንግስት ደረጃ ያስቀመጠች ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ያለመሆኗ ነው። ከዚህ በፊት ሶቬየት ህብረት እና ዩጎዝላቢያ በህገ መንግስታቸው ላይ የራስን እድል በራስ መወስን እስከመገንጠል መብት አስቀምጠው እንደነበር ይታወቃል፤ ነገር ግን ሀገራቱ ከሶሻሊዝም መውደቅ ጋር ተያይዞ ሲፈራርሱ ይሄ አንቀፅ እንዲቀር ተደርጓል። በጣም አዲስ የሚሆነው እስካሁን ስሟን በቅቱ ሰምተናት የማናውቅ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የምትባል የሁለት ደሴት ጥምር ሃገርም እንደዚሁ አንዷ ደሴት መገንጠል ከፈለገች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መገንጠል እንደምትችል በህግ መንግስቷ ላይ ማስቀመጧን አስፍሯል። የሚገርመው ደግሞ የአንዷ ደሴት ገዥው ፓርቲና ተቋሚው ፓርቲ ለሴቷን ለመገንጠል በደሴቷ ፓርላማ ላይ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ህዝቡ በተሰጠው ሪፈረንደም ግን በአንድነት ለመኖር ፍላጎት በማሳየቱ የመገንጠሉ ጉዳይ በዚያው ቀርቷል፤ በሌላ ሁኔታ ደግሞ በህገ መንግስታቸው ላይ የመገንጠልን መብት ማያሰፍሩም፤ አንድ ህዝብ ወይም አከባቢ የመገንጠል ሀሳብ ካነሳ እንደ አንድ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ተወስዶ ሪፈረንደም የሚሰጥበት ሁኔታ እንዳለ ከልምድ ወይም ከታሪክ የምናየው ነገር ነው። ኖርዋይ ከስዊዲን የተገነጠለችው በዚሁ ሁኔታ ነው፤ ሌሎችም አሉ። የካናዳዋ ኩቤክ ግዛትና የታላቋ ብሪቴን እስኮትላድ ሪፈረንደምም ማየት ይቻላል፤ በእነዚህ ሁለት ግዛቶች ህዝቡ እንዲገነጠል ወይም አብሮ እንዲኖር ሪፈረንደም ተስጥቶት በሁለቱም ቦታዎች ህዝቡ አብሮ መኖሩ መርጦ መገንለጠሉን ውድቅ አድርጎታል።

ነገር ግን ገለልተኛ የሆኑ መንግስታዊ ተቋማት በሌሉበት፤ ህዝቡም በነፃነት መወሰን በማይችልበት እንደኛው ዓይነት ሀገር ለአንድ ህዝብ ሪፈረንደም ቢሰጥ የፖለቲካ ልሂቃኑ የሚፈልጉት ነገር ይፈፀማል እንጂ የህዝቡን ይሁንታ በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ውብሸት ስለዚህ ጉዳይ ሲያትት “አምባገነኖች ፈላጭ ቆራጮችም ሕዝበ ውሳኔን እንዲከናወን ያደርጋሉ። ሕዝበ ውሳኔን አይፈሩትም፤ ይልቁንም ይደፍሩታል። ህዝብን መድፈር የተለማመደ ህዝብን እንዳሻው በማድረግ የሚገዛ መሪ የሕዝበ ውሳኔን ውጤት ምን ማድረግ እንዳለበትና ምን እንደሚሆን ቀድሞ ይወስንና ሕዝቡ ድምፅ እንዲሰጥ ያደርጋል። የህዝብ ድምፅ የፈጣሪ ድምፅ ነው የሚለውን አባባል ቀይረው የቄሳሩ ድምፅ የህዝቡ ድምፅ ነው ይሉታል። የፕሬዝደንቱ ወይንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይንም የገዥው ፓርቲ ውሳኔ የህዝቡ ውሳኔ ይሆናል።”

የሆኖ ሆኖ ከዚሁ የመገንጠል ሀሳብ ጋር መኖራችን ካልቀረ ስለምንነቱ፣ ስለአተገባበሩና ስለአጠቃላይ ባህርይ በደንብ አውቆ መቆየቱ ጠቃሚ ነው የሚመስለኝ፤ ለመገንጠልም መገንጠል ለማስቀየትም ስለጉዳዩ በቂ እውቀት ይዞ መገኘት አስፈላጊ ነው።ለዚህ ደግሞ ይሄ የውብሸት መፅሐፍ ጠቃሚ ሆኖ አገኝቸዋለሁ።

ሰቆቃ በማዕከላዊ

$
0
0

Nail

‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡››

አበበ ካሴ
እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡

ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡ ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡

በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡
እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡ ‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡

አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ:-

1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው
2. አቶ አብርሃም አይሸሽም
3. ሙሉጌታ ወርቁ
4. አቶ ደረሱ አያናው
5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ
6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው
7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ
8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት
9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ)
10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ)
11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ)
12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ)

ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡

እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡
ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡ ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡

የአንዷለም አራጌ ሁለተኛው መጽሐፍ ‹‹የሀገር ፍቅር ዕዳ›› እተነበበ ነው

$
0
0

Yehager Fikir Idaየቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረውና አገዛዙ ጥርስ ውስጥ በመግባቱ ‹‹ሽብርተኛ›› በመባል የእድሜ ልክ እስራት የተበየነበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ሁለተኛ የሆነውን የፖለቲካ መፅሐፍ ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ አበርክቷል፡፡ ቁርጠኛና የፅናት ተምሳሌት እንደሆነ የሚነገርለት አንዷለም ከዚህ በፊት ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› የሚል መፅሐፍ ከታጨቁባት እንድ ክፍል ውስጥ ሆኖ በማይመች ሁኔታ እስረኞች ሲተኙና በብርድ ልብስ ተሸፍኖ በመፃፍ ለሕትመት አብቅቶ ከፍተኛ አድናቆትን ማትረፉ ይታወሳል፡፡

የፖለቲከኛው ሁለተኛ ስራ የሆነው ‹‹የሀገር ፍቅር ዕዳ – ከቀሳ፣ ጎንደር እስከ ቃሊቲ እስርቤት›› መፅሀፍ ከአያሌ ውጣውረድ በኋላ በትናንትናው እለት ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

መፅሐፉ 400 ገፅ ያለው ሲሆን በ32 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡ ዋጋውም 100 ብር እንደሆ ገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አንዷለም በግፍ የታሰረለት ፓርቲ አንድነት ለተላላኪዎች ተላልፎ ከተሰጠ በኋላም ያለምንም የሞራል መንገራገጭ መፅሀፍ ማበርከቱ ታላቅነቱን በድጋሚ ያስመሰከረ ምርጥ ሰው ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አንዷለም ከመፅሐፉ መግቢያ ላይ ካሰፈረው ተቀንጭቦ የተወሰደውን ቀጥሎ እናቀርባለን፡-

ለምን ይህንን ፃፍኩ?

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት የሚከተለውን ብለው ነበር፡- ‹‹አንድ አቋም ለመያዝ በምንነሳበት ጊዜ፣ ‹ፍርሃት› ይህ አቋም ምን አይነት አደጋ ያስከትልብኝ ይሆን? የሚል ጥያቄን ይመዛል፤ ‹አዋጭነት› በሌላ ወገን ይህን አቋም መያዝ ምን ያህል ብልጠት የተሞላ ነው? ሲል ይጠይቃል፤ ‹ከንቱነት› በበኩሉ ይህን አቋም መያዝ ምን ያህል ዝነኛ ያደርገኛል? ይላል፤ ህሊና ግን ከሁሉም የተለየ ጥያቄን ያነሳል፤ ይህ አቋም ምን ያህል ትክክለኛ አቋም ነው ሲል ይጠይቃል›› እንዲህ ዓይነት ምናባዊ ምልልሶች በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ለውጥ ለማምጣት በሚተጉ ግለሰቦች አይምሮ ውስጥ ተደጋግመው የሚሰሙ ድምፆች ይመስሉኛል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያን በሚመስል የአምባገነንነት መናኸሪያ ሀገር በሰላማዊ ትግል የአገዛዝ ስርዓትን ወደ ዴሞክራሲ ለመለወጥ የሚታገሉ ዜጎች እለት እለት በህይወታቸው የሚያጋጥሟቸው ጥያቄዎች መሆናቸውን በጥሞና እገነዘባለሁ፡፡

የእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች ድምጽ ከመታሰሬ በፊትም ሆነ በኋላ እየተመላለሱ እረፍት ይነሱኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ለመታገል የሚነሳ ዜጋ ሀገር መውደዱ በቀይ መስመሮች መዥጎርጎሩን ለማስተዋል የሚያስፈልገው የቆመበትን መሬት ብቻ ጎንበስ ብሎ ማየት ነው፡፡ በኢትዮጵያችን የሰላማዊ ትግል ቀጠና የፈንጅ ወረዳ ነው፡፡ አገዛዙ ‹‹ህጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ›› የሚል ባነር የሰቀለበት ነገርግን በየእርምጃዎ ርቀት ፈንጅ የሰገሰገበት የፖሊቲካ መልክዓ ምድር ነው፡፡ በዚህ ቀጠና ውስጥ በተለይ ጎላ ያለ እንቅስቃሴ ሲደረግ ዶ/ር ኪንግ ያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ፍጥነት ይጨምራል፡፡

አቋምዎ ከእውነት ጋር በጽናት መቆም ከሆነ ቀጥለው የሚያስቡት፣ በህይወት ከቆዩ በሚያልፉበት የመከራ ሸለቆ ውስጥ ጉልበት የሚሰጥዎትንና ከግራ መጋባር የሚታደግዎትን ሀሳቦች ቀድመው ይዘጋጁባቸዋል፡፡ እኔም በትንሹ ከመታሰሬ ሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ከአገዛዙ ባህሪ አንፃር አሁን እያለፍኩበት ያለው ሁኔታ እንደሚፈጠር ለአፍታ ተጠራጥሬ አላውቅም፡፡ በተያዝኩባት ቅጽበት እንኳን ከጓደኛዬ በላይ ፈቃዱ ጋር እናወራ የነበረው ይኽንኑ ነው፡፡ ልክ በዚህ ጉዳይ ላይ እያወራን የመኪናው መስኮት ተንኳኳና ወደ ውጭ እንድወጣ ጠየቁኝ፡፡ የድንጋጤም ሆነ መገረም ስሜት አልመጣብኝም፡፡ የቀረኝ በማልፍበት የመከራ ሸለቆ ውስጥ ስለማነባቸው መፃህፍት፣ ስለምሰራው ስፖርትና ስለምፀልየው ፀሎት እያሰብኩ ወደ ግዞት ዓለም መነዳት ነበር፡፡

‹‹ምርጫ 97ን›› ተከትሎ ወህኒ ከወረደው የቅንጅት አመራር አንዱ ነበርኩ፡፡ ያን ጊዜ ወደ ወህኒ ስወርድ ትልቁ ህመም የሚሰማኝ ከእጮኛዬ በመለየቴ ነበር፡፡ አሁን ወደ ወህኒ ስወርድ የባለቤቴ ሃዘንና ግራና ቀኛቸውን የማይለዩት ልጆቼ ሁኔታም አብሮኝ ወህኒ ወረደ፡፡ የአምባገነንነት ኢሰብዓዊት ወደር የለውም፤ እነርሱም ኢትዮጵያን በተቀላቀሉ በጣም ጥቂት ጊዜ ውስጥ የአገዛዙ ሰለባ ሆኑ፡፡ በአባታቸው ማደግ የሚችሉ አባታቸው ከአገዛዙ የተለየ አቋም ካልያዘ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከአገዛዙ የተለየ አቋም መያዝ አደጋው ከፍ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ትክክል ነበር፤ ትክክልም ነው፡፡ ይኽን አቋም ስይዝ በተስፋቢስነት ሳይሆን በተስፋ ሙላት ነው፡፡ እኔና ጓደኞቼ ልጆቻችንና ሚስቶቻችን እንዲሁም ሌሎች ዜጎች የሚከፍሉት መስዋዕትነት በከንቱ እንደማይቀር በፅኑ አምናለሁ፡፡ ምንም ያህል የተዋረድን፣ የተናቅንና የተረገጥን ብንሆንም ዓላማችን እውነት፣ ፍቅርና የሁሉም ዜጎች ልዕልና መከበር በመሆኑ አንዳች ምድራዊ ኃይል እውን ከመሆን ሊያስቆመው አይችልም፡፡ ያ ቀን እስኪነጋ ድረስ ግን የሚከፈለውን ዋጋ በፀጋ ከመክፈል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

ከማዕከላዊ የሁለት ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ስገባ አንድም ቀድሞ የማውቀው ፖሊስም ሆነ የፖሊስ ኃላፊ አላጋጠመኝም፤ እግሬ የእስር ቤቱን ቅጥር እንደረገጠ ግን ከሌሎች እስረኞች ነጥለው ወደ ተለየ አቅጣጫ ወሰዱኝ፡፡ ቅጣት ቤት ነው፡፡ ገና ከማዕከላዊ መድረሴ ነው፡፡ ግን ወደ ቅጣት ቤት ተነዳሁ፤ (ስለዚች ቅጣት ቤት የአቶ መለስ ስንብት በምትለው ንዑስ ርዕስ ስር በጥቂቱ ዘርዘር አድርጌ ለአንባቢ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ)፡፡ በዚች የጭንቅ ማማ ውስጥ ሆኜ ማንበብ፣ ስፖርት መስራት፣ መፀለይና መፃፍ በየዕለቱ አቅም በፈቀደ የምሞክራቸው ተግባሮቼ ናቸው፡፡ በጥፍሬ ቆሜም ቢሆን ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› የተሰኘችዋን መጽሐፌን ለማበርከት ሞክሬአለሁ፡፡ ግቢዋ ውስጥ የነበሩት እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ አቶ ቶሎሳ በቾና ኮማንደር ፈቃደ ረጋሳ ከቅጣት ቤቷ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተወሰዱ፡፡ እኔ እና አንድ ሌላ እስረኛ ስንቀር ቅጣት ቤቷ በአዲስ 16 እስረኞች ተጥለቀለቀች፡፡ በተለያየ ወንጀል የተከሰሱና የተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ ያሉ በአመዛኙ ከ18-30 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፡፡

በግቢዋ ውስጥ ያሉት ሶስት ትንንሽ ክፍሎች ሃያ አራት ሰዓት በእስረኛ የተሞሉ ናቸው፡፡ ከቤት ወደ ውጭ ሲወጣም ግቢዋ ስፖርት በሚሰሩ እስረኞች ትጨናነቃለች፡፡ ምኗም ለምንም አይመችም፡፡ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ለማሰብ እንኳን አትመችም፡፡ ቀኑ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ ያልተሄደበት መንገድ ለአንባቢ መድረሷን ሰምቼ ደስ ቢለኝም ቆሞ የሚውለውን የጊዜ ተራራ ለመውጣት ግን አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩ፡፡ የታሰርኩት ባነገብኩት ዓላማ ምክንያት ነው፡፡ የትም ቦታ በምንም ዓይነት ሁኔታም ሆኜ ለዓላማዬ መትጋት አለብኝ፡፡ ያልተፈጸመ ህልም ይዞ መተኛት ቢቻልስ እንዴት ይተኛል? ባልተሄደበት መንገድ አጎላድፌም ቢሆን አንድ የሚረባ መልዕክት እንኳን ለአንባቢ አድርሼ ከሆነ ትልቅ ነገር ነው፡፡ አሁንስ ሌላ አንድ ነገር ማለት ብችልስ? የሚል ጥያቄ ተመላለሰብኝ፡፡ ቀኑና ሃሳቤ አንድ ላይ ተዳምረው አዕምሮዬ ውስጥ ሌላ ተራራ ፈጠሩ፡፡ ቁጭ ብዬ የሀሳብ ውጥረትና የጊዜ መቆም እንዲገሉኝ ልፍቀድላቸው ወይንስ ጊዜንም ሃሳቤንም ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን በስራ ህይወት ልዝራባቸው? ጊዜም እንዲገድለኝ እኔም ጊዜን ልገድለው አያስፈልግም፤ እንደምንም ልጠቀምበት ወሰንኩ፡፡ ሌላ ዙር መጽሐፍ? ምኑን ከምን አድርጌ በምን ላይ እጽፋለሁ? ሌላ ጭንቅ፤ ለማን አማክረዋለሁ?

ካለሁበት ቅጣት ቤት ውስጥ ከባለቤቴና ከጥቂት የቤተሰብ አባላት ውጭ አብረውኝ ካሉ እስረኞች በተለየ እንዳልጠየቅ ተከልክያለሁ፡፡ ምክንያቱ ተቃዋሚነቴ ነው፡፡ ቅጣት ቤቷ ውስጥ የለመድኳቸው እስረኞች ቢሄዱም ከጥቂቶቹ ጋር መቀራረብ ጀመርኩ፡፡ ከመካከላቸው ፖለቲከኛ እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አንዳንዶቹ በሚያስጨንቅ ሁኔታም ሆነው ስለ እኔ ይጨነቃሉ፤ ይበሳጫሉ፡፡ የመጠየቅ መብቴ በመገፈፉ ያዝናሉ፤ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎችና የሚቸበቸቡ መፃህፍት እንዳይገቡልኝ ስከለከል ድግሞ ስሜታቸው ይገነፍልና ለምን አንድ ነገር አናደርግም ይላሉ፡፡

በእኔ በኩል ቀደም ሲል በቅንጅት ታስሬ በነበርኩበት ወቅት ከፖሊሶችና ከኃላፊዎች ጋር የነበረኝን ኃይል የተሞላበት ግንኙነት ትክክል አልነበረም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፤ በመሆኑም ፖሊሶቹንም ሆነ ልጆቹን በትዕግስት የመገሰጽ ኃላፊነት በራሴ ላይ ጭኛለሁ፡፡ በፖሊሶችና በእስረኞች መካከል የተካረሩ ግጭቶች ሲፈጠሩ ሁሉንም እቆጣለሁ፡፡ በተለይ ልጆቹን በየተራ እመክራሉ፡፡ ችግሩ ሲፀና የበላይ ኃላፊዎች ሁሉ ከተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ጋር ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም ‹‹አንተነህ አይደል እያደራጀህ ይኽን የምትሰራው?›› ይላሉ፡፡ ሁልጊዜም ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ እኔ ነኝ፡፡ ነገም ሌላ ችግር ይፈጠራል፤ መሳሪያ ተቀባብሎ ይነጣጠርብናል፤ በዚያም መሃል ግን ሁለቱንም ለማረጋጋት እሞክራለሁ ነገርግን አሁንም እኔ ላይ ዛቻው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻ ላይ የእኔም ትዕግስት ያልቃል፤ ‹‹ልታስፈራሩኝ ከምትሞክሩ የምታስቡትን ብትፈጽሙ ይቀለኛል!›› እላለሁ፡፡ በኃይል በር በላያችን ላይ ተቆልፎ ስሜታችን እንደደፈረሰ በጉዳዩ ላይ እንወያያለን፡፡ መዳፍ በምታክለው ግቢ ውስጥ በየተራ ልጆቹን አናግራለሁ፡፡ አንዳንዶቹን አመሰግናለሁ፤ አንዳንዶቹን እገስጽና በዚህ ሁኔታም ስለምን ብጽፍ ይሻላል? የሚል ጥያቄ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡………….

በዚህ ዘመንና ትውልድ ፊት ብቻ ሳይሆን ባልተወለዱ ልጆቻቸውና በሚመጣው ዘመን ሚዛን ተመዝኖ የማይወድቅ አቋም እንደያዝኩ የጸና እምነት አለኝ፡፡ የኢህአዴግን አረመኔነት ለመረዳት የሚያስችል መከራ በህይወቴ ያልደረሰ የሚመስለው አንባቢ ሲኖር ይገርማል፡፡ ስቃዩን እኔ ብቻ ሳልሆን ልጆቼም ያውቁታል፡፡ በእያንዳንዷ ቀን ሰዓትና ደቂቃ የማልፍበት የእስር ህይወት የአገዛዙን ባህሪ ከመረዳትም በላይ ብዙ የሚናገረው ነገር አለ፡፡ እኔ የአገዛዙ አፈና ገፈት ቀማሽ የሆንኩት ሰው ቀርቶ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንኳን በሚገባ ኢህአዴግን እንደሚረዳው እንድጠራጠር የሚያደርግ ምክንያት አይታየኝም፡፡ በሌላ በኩል ግን እራሳችን አምላካዊ ሌሎችን ደግሞ ሰይጣናዊ አድርጎ መውሰዱ ተገቢ ሆኖ አላገኘውም፡፡ መጽሐፉ ውስጥ እንደምናየው ይህ ባህሪ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሁነኛ ባህሪ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አቋም የያዙ ሰዎች ሁሉ ግን አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተጠመቁ ናቸው ማለት አይደለም፡፡

ኢህአዴግንም ሆነ ሁላችንንም ያበቀለው የፖለቲካ ባህላችን ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ከኋላ ጀምረን ለማየት ስንሞክር የአገዛዝ ባህላችን አሁንም ለምንገኝበት ዙሪያ መለስ መከራ ትልቅ ድርሻ እንዳለው እንረዳለን፡፡ የኢህአዴግን አይነት አምባገነን አዝሎ የሚንከራተት ነገር ግን ኢህአዴግን ከጫንቃው ለማውረድ እጅ ለእጅ መያያዝን የሞት ያህል የሚፈራ፤ ይልቅስ እርስ በእርሱ መነካከስና መጠላለፍን እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጥር ስንት ዜጋ እንዳለ ማን ማንን ሊያስረዳ ይችላል? ይኽስ ከኋላ ቀሩ የፖለቲካ ባህላችን የሚቀዳ መሆኑን ለመረዳት የሚቸገር ሊኖር ይችል ይሆን? አይመስለኝም፡፡ ሁልጊዜም በጣም ከባዱ ነገር ወደ ውስጥ ማየት እንጂ አሻግሮ ማየት አይደለም፡፡ ስለ ኢህአዴግ ምንነት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አውርተናል፡፡ ነገር ግን ለምንድን ነው እስከአሁን ድረስ እላያችን ላይ እንደሰለጠነብን የቀጠለው? ከእኛ የጎደለውን ነገርም በድፍረት ማየት ተገቢ ነው፡፡

ኢህአዴግ ብሔራዊ እርቅን ተቀብሎ ሁላችንም ወደ አላስፈላጊ አዘቅት ተያይዘን እንዳንወርድ ቢሰራ የተሻለ መንገድ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለገ ግን ለህዝብ ፈቃድ መገዛት ግዴታው የሚሆንበት ሰዓት መድረሱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ጊዜው እንደምናካሂደው ትግል ሊረዝምም ሊያጥርም ይችላል፡፡ በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሰዎች ስኬት የራቃቸው በሰላማዊ ትግል ምክንያት አድርገው ካሰቡ ስህተት ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል የምናምን ሰዎችም በትጥቅ ትግል ምክንያት ሊሳካልን እንዳልቻልን ካሰብን ስህተት ነው፡፡

ለእኔ ከወሬ ባለፈ ሁለቱም ትግሎች ትርጉም ባለው መልኩ እየተካሄዱ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህ ሰላማዊ ትግልን እንዳልባሌ ነገር የሚፈርጁ  ወገኖች መተቸት መብታቸው ቢሆንም ወደ ውስጣቸው ቢመለከቱ የተሻለ የሚያስከብር ተግባር ይመስለኛል፡፡

በግሌ አሁንም ግልጽ ለማድረግ የምወደው ነገር በሰላማዊ ትግል የሃይማት ያህል እንደማምን ነው፡፡ የኢትዮጵያን የመጠፋፋት የፖለቲካ ባህል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለወጥ የሚቻለው የጸና ሰላማዊ ትግል በማድረግ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግልን በሚገባ ጥቅም ላይ ማዋል ስንችል ያጎበጠንን የአገዛዝ ቀንበት ከላያችን ላይ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የአገዛዝ ስርዓቶች መፍለቂያ የሆነውን የፖለቲካ ባህላችንን ማዘመን እንችላለን፡፡

በአጭሩ ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን በቁጥጥር የተለከፈና ሁሉንም ተቃዋሚዎች አጥፍቶና ህዝቡን እረግጦ የመግዛት አባዜ የተጠናወተው ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ የመጠፋፋት ባህልም ወራሽ ነው፡፡ …………………

እንደ ልብ እንዳላነብ መጽሀፍት እንዳይገቡልኝ ይከለከላል፡፡ በማመልከቻ ጽፌ እንዲሁም በአካል ስንገናኝ ‹‹የሮዴዥያ ነጮች ሮበርት ሙጋቤን በአሰሩበት ወቅት እንኳን ትምህትርት አልከለከሏቸውም፤ ከሶስት ያላነሱ ዲግሪዎችን ሰርተው ነው የወጡት፤ እናም እኔም ባልጠቅማችሁ እንኳን በመማሬ አልጎዳችሁምና በተልዕኮ እንድማር ፍቀዱልኝ›› የሚል ጥያቄ ደጋግሜ ባቀርብም ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ የሚፈልጉት የእኔን ባክኖና መክኖ መቅረት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በእኔ በኩል ይኽንን ሁኔታ ለመቋቋም ቀደም ሲል የጠቀስኳቸውን የእስር ቤት መርሃ-ግብሮቼን አጠናክሬ መቀጠል እንደ ሰው ያለመምከን ጥረት ብቻ ሳይሆን በስር ቤት ውስጥ ህልውናዬንም የማስቀጠያ ስልት ነው፡፡ ከእስር ቤት አጥር ውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ለሀገሬ ይበጃል የምለውን ነገር አንስቼ የመወያየት ሰብዓዊ መብቴን ተግባራዊ የማድረግ ህልሜ አውን ሆኖ ለማየት እፈልጋለሁ፡፡ አካሌ ቢገደብም መንፈሴ እንዲገደብ አልፈልግም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሆኜ ነው ይኽንን መፅሐፍ መከተብ የጀመርኩት፡፡

እንደ ሁልጊዜው ሁሉም ነገር የሚከናወነው ፍራሽ ላይ ነው፤ ወንበር አይፈቀድም፤ ለማንበብ፣ ለመመገብም ሆነ ለመፃፍ ያለችኝ ቦታ ዘጠና ሲንቲ ሜትር ፍራሽ ነች፡፡ በእርሷም ላይ የማዘዝ መብት የለኝም፡፡ ድንገት ፀብ ከተነሳ የግብግብ አውድማ ትሆንና ልብሴም ሁሉም ነገሬም ይረጋገጣል፤ ግልብጥብጧ ይወጣል፡፡ ፀቡ ሲበርድ ወደ ቀድሞው ንባብ እመለሳለሁ፡፡ ቴሌቪዥኗን እስከ መጨረሻ ድምፀዋን እንድትሰጥ በማድረግ ከጭንቀታቸው ያረፉ የሚመስላቸው ልጆች ደግሞ ዳንኪራውን ያቀልጡታል፡፡ ከማንበብ ውጭ ግን ሌላ አማራጭ የለኝምና እቀጥላለሁ፡፡ በየጊዜው በሚደረገው ፍተሻ ምክንያት አንዷ ክፍል ውስጥ ያለን እስረኞች ልብስና የተለያዩ ንብረቶችን ሁሉ እየፈተሹ አንድ ላይ ይቆለላሉ፡፡ ትቢያ ይለብሳሉ፣ ይረጋገጣሉ፡፡ ከፍተሻው በኋላ ለረጅም ሰዓት ንብረቶቻችንን የመለየት ስራ እንሰራለን፡፡ በጣም አድካሚ ነው፤ ግን አማራጭ የለንም፡፡ በየፌስታላችን ንብረቶቻችንን ቆጣጥረን እንደ ቀድሞው ወደ ህይወት መመለስ ያስቸግራል፡፡ ሰው መሆናችን ጨርሶ ተዘንግቷል፡፡ ኢሰብዓዊነት  እስር ቤት አውርዶኝም በዚያም ያሳድደኛል፡፡ ኢሰብዓዊነትን የማሸንፈው ግን ሰው በመሆን ነውና ሰብዓዊ ተግባሮቼን የሞት ሞቴን እቀጥላለሁ፡፡

በእንዲህ አይነት ሁኔታ እያለፍኩ አንዳንዴ ኃላፊዎች ይመጡና ‹‹ዋይ! እንዴት ነው ‹አንድ-ዓለም› ታረምክ?›› ይሉኛል፡፡ ነገሩ የሚያበሳጭና የሚያሳዝን ቢሆንም በአንክሮ ‹‹እኔ እኮ በተቀነባበረ ክስ የታሰርኩ የግፍ እስረኛ ነኝ፤ ከየትኛው ጥፋቴ ነው የምታረመው?›› እላቸዋለሁ፡፡ ‹‹ዋይ! አንተ ተው! ስንት ሰው አይዶለም እንዴ መንግስትን ተሳድቦ እቤቱ እያደረ ያለበት ሁኔታ ያለው! አንተን ነጥሎ መንግሥት ለምን ያስርሃል? በልዕ ዕስቲ ተናገራ!›› ይሉና ጥያቄዬን በጥያቄ ይመልሳሉ፡፡

በበኩሌም ‹‹ብዙሃንን ሰብስቦ ማሰር ሳይሆን ጥቂቶችን ነጥሎ በማሰር ህዝቡን ማስደንበርና ተሸማቆ እንዲኖር ማድረግ ነው – የአገዛዙ ስልት›› የሚል ምላሽ እሰጣቸዋለሁ፡፡ ‹‹ታዲያ አንተን ለምን መረጠ?›› የሚል ጥያቄ ያስከትላሉ፡፡ ‹‹ለምን እኔንና ጓደኞቼን እንደመረጠ በውል የሚያውቀው አገዛዙ ነው፡፡ ምናልባት ግን በጊዜው ፊት ለፊት ስለምንታይ የእኛን አንገት በመስበር ሌሎችን ‹እነርሱን የበላ እሳት እንዳይበላችሁ፤ እኔ እንደማዛችሁ ብቻ ተመላለሱ› ለማለት ነው፡፡›› የሚለው ምላሼ አያስደስታቸውም፡፡ ‹‹ዋዕይ! ላንተ ገና አልታረምክም!›› ይላሉ ‹‹ይልቅስ መታረም ያለበት የምታስተዳድሩት ተቋም ነው፤ የሁላችንም ተቋም ነው፤ ነገ የተሻለ ተቋም ሆኖ እንዲወጣ ከተፈለገ አሰራራችሁን አስተካክሉ፡፡ ሰውን እንደ ችቦ አንድ ላይ አስሮ በማንደድ ማጥፋት አይቻልም፡፡ የተለያዩ ስራዎችን በዝርዝር ነድፋችሁ ተግባራዊ ብታድጉ ይሻላችኋል›› የሚል ሃሳብ እሰነዝራለሁ፡፡………………

ከቤቴ ከወጣሁ ጀምሮ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር ያለአንዳች ምክንያት ቅጣት ቤት ውስጥ መሬት ላይ እንደትል ስንከባለል ከቆየሁ በኋላ ድንገት ‹‹ፍራሽህን ይዘህ ውጣ!›› ተባልኩ፡፡ ድንገት ወጥቼ ‹‹ኋይት ሀውስ›› ወይንም ‹‹ዋይታ›› ወደምትባል ጠባብ ቦታ ተወሰድኩ፡፡ ወረቀቶቼ በር ላይ እየተመነጠሩ ሲለቀሙ እስክንድርም መጣ፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ ተገናኘኝ፡፡ በእለቱም ከ50 ገጽ በላይ ወደ መጨረሻ ረቂቅ ለመጻፍ የተዘጋጁ ወረቀቶቼ ተወሰዱብኝ፡፡ እንደገና ማንበብ፣ እንደገና መፃፍ ቀጠልኩ፡፡ የልጆቼ ናፍቆት፣ የሰላማዊ ትግሉ መቀዛቀዝ፣ ወረቀቶቼን የመነጠቅ ስጋትና በዚህ ሁኔታም ሆኜ የጀመርኩት ገደል የመውጣት ትግል በስኬት እንዲጠናቀቅ መትጋት የአዕምሮዬን ጓዳ ከሞሉ ሀሳቦች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የፈጣሪ ፀጋ በዝቶልኝ ከብዙ አድካሚ ውጣ ውረድ በኋላ የሀገር ፍቅር ዕዳን በስኬት ለማጠናቀቅ ችያለሁ፡፡ ትንሽ ቅር ያለኝ ምዕራፍ አምስትን ሳዘጋጅ ጽሁፉ ከወጣ በኋላ የምዕራፉ 167 የግርጌ ማስታወሻ በፍተሻ ወቅት ስለተወሰደብኝ ሁኔታውን መለወጥ የምችልበትን ሁኔታ መፍጠር አልቻልኩም፡፡ ከዚህ ውጭ ያልተሄደበት መንገድ ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በዚህኛው መጽሐፍ ላለመድገም ጥሬአለሁ፡፡ …………….

ትግሉ የዴሞክራሲና የነፃነት ትግል በመሆኑ የዜጎች ልዕልና የሚከበርበት፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በኢትዮጵያ እስኪገነባ ድረስ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳስባል፡፡ ለዘመናት ያልነጋው ረጅሙ የአገዛዝ ሌሊት ሊነጋ የሚችለው የዴሞክራሲ ትግል ውጤት የሆነችው የዴሞክራሲ ጮራ በምድራችን ላይ ስትቀትር ነው፡፡

የዴሞክራሲ ትግሉ በተለይም በዚህ ሰዓት የተለየ ትርጉም ይሰጣል፡፡ አምስት፣ አምስት ዓመታትን እየቆጠረ አገዛዙ የሚተውነው አምስተኛው የምርጫ ተውኔት ተቃርቧል፡፡ የእኔ ፓርቲ አንድነት እንኳን የአገዛዙን አፈና ተቋቁሞ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ በመግባት ህዝብን ነፃ ለመውጣት የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ሲታትር በስርዓቱ መንጋጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ በተቃዋሚው ታግለን ለውጥ ማምጣት አንችልም ብለው የሚያምኑ ግለሰቦች ለውጥ የሚያመጡበትን ወንበር ይዘው መቀጠል ለምን እንደሚፈልጉ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው፡፡ ዘመኑ ከችግሩ በላይ የሚገዝፉ መሪዎችን ይፈልጋል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ያለውን በባዶ ‹‹እኔባይነት›› አባዜ ካልተወገደ ተቃዋሚዎች የዴሞክራሲ ትግሉን ወደ ፊት የሚያራምድ አቋም ሊላበሱ አይችሉም፡፡

በህዝቡ በኩልም ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆሞ የሚያስብበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን ነፃ ለማውጣት ምን እንዳደረገ እራሱን የሚጠይቅበት ወቅት ነው፡፡ ለሁሉም ነገር ምክንያት እየደረደርንና ሌሎችንም እየወቀስን ነገር ግን ከእኛ የሚጠበቅን አንዳች ሳንፈጽም የምንሸኘው ጊዜ ሊኖር አይገባም፡፡ በድፍረት ህዝቡ ሊወቀስ ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ ከዚህ በኋላ ስለእርሱ መጨቆን ማንንም ሊወቅስ አይችልም፡፡ ኢህአዴግን እንኳን ለመውቀስ መጀመሪያ ያመቻቸለትን ጀርባውን መከልከል ይገባዋል፡፡ ይኽንን ለማድረግ ደግሞ ጦር መምዘዝ ወይንም ዝናር ማንገብ አያስፈልገውም፡፡ ፍርሃትን ገድሎ በልበ ሙሉነት የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት ለመሆን መስራትና መታገል ነው፡፡ በፍርሃት መቃብር ላይ የፍትህ፣ የሉዓላዊነት፣ የዴሞክራሲና የወንችማማችነት ችግኞች ይንዘረፈፋሉ፡፡ አገዛዙ ይሄ እንዳይሆን መቁረጥ አለብኝ ያላቸውን እግሮች ሁሉ ቆርጧል፡፡ ቀሪው ትግል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ እኔ ለዚህ ትግል ይረዳል ብዬ ያሰብኩትን ይኽንን መጽሐፍ ቀድሜ ተዘጋጅቼ አበርክቻለሁ፡፡

ፍፁም ለመኖር ሳይሆን ለማሰብ በሚከብድ ሁኔታ በአውራ ጣቴ ወደውቅያኖሱ እንዳልወድቅ በተራራው መሃል ላይ ትልቅ ጥረት በማድረግ ከፈጣሪ ጋር ቀጥ ያለውን ጋራ ተወጥቼዋለሁ፡፡ የታሰርኩለት ሰላማዊ የዴሞክራሲ ትግል ፎቀቅ ባለማለቱ ዘወትር ባዝንም ይህችን ትንሽ ነገር በምጥ ብዛት ሰርቼ በማጠናቀቄ የተወሰነ እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ ለጊዜው የገደሉ ጫፍ ላይ ቆሜ የወጣሁትን ገደል ርቀት እያየሁ ነው፡፡ ነገር ግን ብዕሬ ከጣቶቼ ሳይለይ ሌሎች ሊወጡ የሚገባቸው ገደሎች ተደርድረው ይታዩኛል፡፡ ዴሞክራሲ በሌለበት ሀገር ህይወታችን ሁሉ ጠመዝማዛ መንገድ የበዛበት ገደል ነው፡፡ ሸለቆው እስኪሞላ ገደሉም ሜዳ እስኪሆን ወገባችንንና መንፈሳችንን አጽንተን ለትግል እንነሳ፡፡ የሀገር ፍቅር ዕዳን እነሆ ብያለሁ፡፡

 

ሻእቢያ ለምን ? ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ

$
0
0
ከቀደሙ ልምዶች መማር መጠየቅ ወይም መረዳት ተመሳሳይ ስህተቶች ተደጋግመው እንዳይፈፀሙ ይረዳል በተለያዩአጋጣሚዎች ባለፈው አሰርተ -አመት በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ወደ አስመራ ተጉዘዋል ። ከነዚህም ውስጥ አንዱና ቀዳሚው እኔ ነኝ ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ደጋግሜም ወደ ኤርትራ ተጉዣለሁ ።
ከአርበኞቹ ጋር ሰላምታ ስለዋወጥ ። በተለይ ሰላምታ እየሰጠሁት ያለው አርበኛ ካሳሁን ሁንዴ ኢትዮጵያዊ የግንባሩ አመራር ይጠናከር በማለቱ በሻእቢያ ጉርጓድ ወስጥ ታስሮ ለወራት ሲሰቅይ ከቆየ በኋላ የተረሸነ ።
ወድ አንባቢዬ ሆይ!
 
እነዚህ ከአሁን ጀምሮ በተከታታይ የማቀርባቸውን የጉዞ ማስታወሻዎቼ እንዲያተኩሩ የምፈልገው በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ላይ ብቻ ነበር ። ሆኖም ግን ስለአርበኞች ግንባር መከታተል ስጀምር ህይወት በራሷ መንገድ ይዛኝ የነጎደችባቸው ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴዎች ነበሯትና እግረ መንገዴን ያየሁቸውና ያስተዋልኳቸው ብዙ ሁኔታዎች አጋጥመውኛል ።
 
 demisይህ ፅሁፌ የማንንም ወገን ወይም ቡድን የመጥቀምም ሆነ የመጉዳት አላማ የለውም ። ምናልባት ባቀራረቤ ከረር ወይም ለስለስ ያደረኩ ከመሰላችሁ ትኩረቴ እውነታው ላይ ብቻ ስለሆነ ፋክት መሆኑን ብቻ ተመልከቱልኝ ። ለወጣቱና በቦታው ላልነበርው የሃገሬ ዜጋ ሁሉ በጉዞዬ ላይ ያየሁትንና የሰማሁትን ማካፈል ግዴታየ ነው ። ሁሉም ሰው የሃገሩ ጉዳይ እኩል ይመለከተዋል ። አንድ ዜጋ ብሄራዊ ጥቅሙን ከማስጠበቅ አልፎ ለወደፊቷ የሃገሪቷ መፃኢ ትውልድ ሰላማዊት  ሃገር ማስተላለፍ ይችል ዘንድ ትክክለኛ መረጃ  ሊኖረው ይገባል ። በሰከነ መንፈስ ተረጋግቶ መርጃን የሚመዝን ሰው ፤ በቀላሉ ስህተት ውስጥ አይዘፈቅም ።
 
ወገኖቻችንና  ዜጎቻችን ከየትኛውም የአገራችን ክፍሎች ይምጡ፤ አምነውብውትም ይሁን ሳያምኑበት እየከፈሉት ያሉት መስዋእትነት አለ ።  መስዋእትነቱን ለመክፈል በፈቃደኝነት የሄዱት የጠበቃቸውና ያገኙት እንዳሰቡት ነበር ወይ ? ያለፈቃዳቸው በምርኮ የሄዱትስ ኑሯቸው እንዴት ነው ? ይህን ማንም ዜጋ ሊያጤነው ይገባል ብየ አስባለሁ ። በኤርትራው ተደጋጋሚ ጉዞዬ መልካምና ቅን የሆኑ ኤርትራውያን ተዋውቄአለሁ ።  በዚያው ልክ ደግሞ የሰው ልጅ ስቃይና መከራ ውስጣቸውን በሃሴት የሚያለመልምላቸው ቂመኛና ጥቅመኛ ኤርትራውያንም አጋጥመውኛል ። በኤርትራው ጉዞየ ላይ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ዘላለማዊ  ወንድሞችም አትርፌአለሁ ። ተኮራርፈን የቀረንም ወገኖች አለን ። ብንኮራረፍም ዛሬ ላይ ሆነን ሁላችንም የነበረውን ሁኔታ ስናጤነው ፤ የችግሮቻችን ምንጮች ምንና እነማን እንደነበሩም የተረዳን ይመስለኛል ። ያም ሆኖ አብዛኛዎቻችሁ  የሃገራችሁ ክብርና ፍቅር ልባችሁ ወስጥ እንደሚነድድ ተረድቻለሁ ። መንገዶቻችን የተለያዩ  ቢሆኑም በቅን ልቦና ለአርበኞቹ ትለፉ እንደነበር ግን ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም ። ስለዚህም በዚህ አጋጣሚ ዘላለማዊ አክብሮቴን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ ።         
 
ለምን ይህን ጊዜ መረጥክ የሚል ጥያቄ ልታነሱ የምትችሉ ወገኖች እንዳላችሁ አውቃለሁ ። እኔም ሆንኩ አብረውኝ የነበሩ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ሳንወተውት ያሳለፍንበት ጊዜ አልነበረም ። አንዳንዴ  ጊዜው ሌሎች ሁኔታዎች ላይ ያተኩርና የህዝቡን የማስተዋል አቅጣጫ ወደ ሌላ መስመር ይዞት ይነጉዳል  ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ጊዜው ያመጣቸው የፖለቲካ ሾፌሮች የግል ፍላጎት ስለአርበኞች ግንባር መነጋገር ፤ የነሱን የፖለቲካ ስራ የሚያደናቅፍባቸው ወይም ጥላ የሚያጠላበት መስሎ ስለሚታያቸው እንዳይነገር እንዳይሰማ መሰናክል ይፈጥሩ ነበር ። ከዚህ ሌላ ደግሞ በነፃነት አስተያየትን መግለፅ ትክክል ነው ብለው የሚያምኑ በጣም ጥቂት ሚዲያዎች  እንዳሉ ሁሉ ፤   አብዛኛዎቹ ድጋፍ እናጣለን ከሚል ስጋት ማንም ሳያስገድዳቸው ራሳቸው ላይ ግለ-ሳንሱር (self censorship) ይጥላሉ  ።  እና መረጃዎች በትክክል እንዳይደርሱ ምክንያት  ይሆናሉ ።
አንድ ፀሃፊ በስሙ እስከፃፈ ድረስ የፅሁፉ ባለቤትነትና ሃላፊነት የራሱ ይሆናል ። የሚዲያዎቹ ሃላፊነት የመነጋገሪያ ፤ የመወያያና የመከራከሪያ መድረኩን ማዘጋጀት ብቻ መሆን ይኖርበታል ።    ስለዚህ በዚህና በመሳሰሉት ጉዳዮች ምክንያቶች  ሳላቀርባቸው ቆይቻለሁ ።ከብዙው በጥቂቱ ምክንያቶቼ እነዚህ ነበሩ ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ዛሬ  አፍጥጦና ገጦ የወጣ ጉዳይ አለ ። የኢትዮጵያ ጉዳይ እየተመራ ያለው በኢትዮጵያውያን አይደለም ብዬ አምናለሁ ። የትእዛዝ ሰጪነትና ተቀባይነት ግንኙነት የሎሌነት ግንኙነት ነው ። ይህ ደግሞ አገራችንንና ህዝባችንን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ። ይህን መስል ግንኙነቶችም ወያኔና ህዝባችንን ያስከፈለው ዋጋ  የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው ። አሁን ግን ጊዜው የደረሰ ስለመሰለኝ ፤ በተከታታይ አቀርበዋለሁ ።
 
  ስለ ኤርትራና  ስለኢትዮጵያ  ህዝቦች ባህላዊ ፤ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግንኙነት እዚህ ላይ መጥቀሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም ። የዛሬው ጎልማሳ ትውልድ የአንድነቱንም ሆነ የልዩነቱን ዘመን በሚገባ ያውቀዋልና ።
 
በረራ ወደ አስመራ!
 
        የአስመራው በረራዬ  ከፍራንክፈርት ጀርመን የተነሳው አመሻሽ ላይ ነበር ። ወደ ደቡብ ምስራቃዊ አቅጣጫ አፍንጫውን የደገነው የተሳፈርኩበት አውሮፕላን የአውሮፓን ሰማይ እየሰነጠቀ ነጎደ ። በአውሮፕላኑ መስኮት አይን አስከሚደርስበት ድረስ የአውሮፓን ምድር ሳይ  አንዳንድ ቦታ ክምችት ክምችት ብለው ሌላ ቦታ ደግሞ ብትንትን ብለው የሚታዩት የኤሌክትሪክ ብርሃኖች ፤ ጥቁር ምንጣፍ ላይ የተበተኑ የአልማዝ ቁርጥራጮች ይመስላሉ ። የአልማዞቹ ምንጣፍ ወደኋላ እየቀረ የሜዲትራኒያን ባህር አየር ላይ መግባቱን የሉፍታንዛው አውሮፕላን የካርታ ማሳያ ጠቆመ ።
 
ሜዲትራኒያን ሲነሳ ሃሳቤ ከመፃህፍቱ አለም ካገኘኋቸው  የታሪክ እውቀቶች ጋር ለምዕተ- አመታት ወደኋላ ይዞኝ ነጎደ ። የዛሬዎቹ የመካከለኛው ምስራቅና የውሮፓው ቋንቋዎች ፊደላት ድምፀት በፊንቃውያን (Phoenicians)  የተጨለፈበት ባህር ነው ሜዲትራኒያን ።  የግርኮች ስልጣኔ ወርሶች የለመለሙትና ፍሬ ያፈሩት የዚህን ባህር ውሃ እየጠጡ ነው ። የካርታጎው አፍሪቃዊ የጦር ሰው ሃኒባል አውሮፓ ላይ በዝሆኖች በመዝመት ሮምን ያስጨነቀው ይህንኑ  ባህር በመሻገር ነበር ። ሮማውያን የሃኒባልን ጦር አሸንፈው ሰሜን አፍሪቃን በመቆጣጠር ቄሳራዊ ግዛታቸውን  የመሰረቱት በዚሁ ባህር ላይ  ።  ክሊዮፓትራና ግብፃዊ ህዝቧ በተለይ የማርክ አንቶኒና የክሊዎፓትራ ፍቅርና ትራጀዲ መድረክም ይኸው ባህር ነው ።  በሃዋርያዊ ጉዞ ለክርስትና መስፋፋት  ታላቁን ሚና በመጫወትም ይታወቃል ሚዲትራንያን ።  አረባውያኑ የነቢዩ ሞሃመድ ተከታዮችም መካከለኛው ምስራቅን አልፈው ሰሜን አፍሪቃን ተቆጣጥረው ስፔንንና ደቡባዊ ፈረንሳይ ድረስ የዘለቁት ይህንኑ ባህር ተሻግረው ነው ። ኦቶማን ቱርኮችም ፤ ተራቸውን እንዲሁ እየጠበቁ በአዕምሮየ ተመላለሱብኝ። በአለማችን ላይ ካሉት ባህሮች ሁሉ እንደሜዲትራንያን ባህር ሰፊ የሰው ልጆች ታሪካዊ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በስተጋብሮችና ግንኙነቶችን ብሎም ጦርነቶች የተካሄዱበት ባህር የለም ማለት እችላለሁ ።  
 
 ምናቤን ከነዚህ የታሪክ ዘመናት አውጥቶ  ወደ ጉዞየ አቅጣጫ የመለሰው የፓይለቱ እወጃ ነበር ። በመጀመሪያ በጀርመንኛ ከዚያም በእንግሊዝኛ በአፍሪካ ሰማይ ላይ መሆናችንን አበሰረ ። ድሮ ድሮ አፍሪካ  “ጨለማው ክፍለ-አለም” ሲባል የትምህርት እጦት ጨለምተኝነት ብቻ ይመስለኝ ነበር ። የአፍሪካ ምድር ምሽት ድቅድቅ ጨለማ ነው ። የአፍሪካ የእውቀት ኋላ ቀርነት የብርሃንም  ጨለማ አድርጓታል ። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወደአስመራ የበረርኩባቸው ከአውሮፓ የተነሱ አውሮፕላኖች ሁሉ ወደ ኤርትራ ከመብረራቸው በፊት በጅዳ ሰማይ ላይ አንዣበው ነው የአስመራን አቅጣጫ የሚይዙት  ። ጅዳም ታዲያ ከአሮፓው ምድር ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ ማለት እችላለሁ ብርሃን ለብሳለች ። የነቢዩ ሞሃመድ አገር መሆኗና የህዝቡ ሃይማኖቱን አክባሪነት ብሎም ፀሎተኝነት ፤ ጭው ባለው በረሃ ፤ ከከርሰ ምድሯ ጥቁር ወርቅ እንዲፈልቅላት እግዚአብሄር ፈቅዶ በብርሃን ተፍለቅልቃለች ።
 
ቀይ ባህርን ተሻገረ አውሮፕላናችን ። ብርሃን ግን የለም ።  አስመራ ስንደርስ ኤሌክትሪኩ ፏ ብሎ እንደሚጠብቀኝ ተስፋ አድረኩ ።  ቀድሞ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውና ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ሁለተኛዋን ከተማ ትባል የነበረችውን አስመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ላያት ነው ። በተለይ ወላጆቻቸው ከኤርትራ የነበሩ አብረውን ያደጉና የተማሩ አምቼዎች ስለአስመራ ሲያሞጋግሱና ትላልቆቹም ትውልደ-ኤርትራውያን እንዲሁ አፍሪቃዊቷ ሮም እያሉ ሲያንቆላጵሷት እየሰማሁ በአይምሮየ የቀረፅኳት አስመራ ለየት ያለች ነበረች ። ልቤ በሃይል መምታት ጀምሯል ። መንፈሴም ተነቃቅቷል ። አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ቆንጆ ነገር ተደረገ ብለህ ስታወራ ፤ የኤርትራ ትውልድ ያላቸው ልጆች አስመራ ጣሊያን የሰራው እንዲህ እንዲህ የሚባል ቦታ ከዚህ የበለጠ አለ ።ድሮ ድሮ  ነው የተሰራው ብለው በደቦ እየተቀባበሉ የሚነግሩን ሁሉ ታወሰኝ ። “አደየ አስመራ ! አደየ ኤርትራ”
 
 አስመራንም አይቼ የአርበኞቹንም እንቅስቃሴ ተመልክቼ የምሰራው  ጋዜጣዊ ሪፖርት እየታየኝም ወስጤ በደስታ ሞልቷል ።በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች መምታት ይቻላል የሚባለው ለዚህ ይሆን?  አውሮፕላኑ ለመውረድ ማኮብኮብ ጀመረና ዝቅ እያልን ስንሄድ የመንደርደሪያው ማሳያ ሰልፈኛ ብርሃኖች ታዩኝ ። ከአገሬ ከወጣሁ ረዘም ያለ ጊዜ ስላለፈና የአገሬ አካል የነበረችውን የአስመራን መሬት የአውሮፕላኑ ጎማ ሲነካ የተደበላለቀ ስሜት ነበር የተሰማኝ ። ደስታ ይሁን ሃዘን ፤ ፍርሃት ይሁን ስጋት ወይም ጥንቃቄ ሁሉም በአንድነት ይተረማመሱብኛል፤ ምን ነካኝ? ስል ራሴን ጠየቅሁ ። ቀደም አድርጌ ደጋግሜ ያሰብኩበት ቢሆንም ፤ ያደረከው ውሳኔ ትክክል ነው ወይ ሲል ህሊናዬ እንደገና ራሴን ጠየቀኝ ። ትክክለኛም ሆነ አልሆነ አንዴ መጥተሃል  የመጥህበትን ጉዳዮች ፈፅም ሲልም መከረኝ ።
 
“…..አንታ ሃላፋይ መንገዲ እንተረኪብካያ ንመለይ፤
 ሰላም በልለይ።…..”
 
 ትርጉም                                  
“…..አንተ በመንገድ አላፊው ቆንጂትን ካገኘህልኝ ፡
 ሰላም በልልኝ።…… “ 
 
እያልኩ የአስመራን መሬት ረገጥኩ ።
 
   ከአውሮፕላን እንደወረድኩ እኔን ሊቀበሉ የመጡጥ ሰዎች አውሮፕላኑ ድረስ መጥተው ተቀበሉኝ ። ሁለት ነበሩ ። ሃላፊነታቸውንና የየትኛውመስሪያ ቤት ተወካይ እንደሆኑ ሳይነግሩኝ ስማቸውን  ብቻ በመግለፅ ተዋወቁኝ ። ሻእቢያዎች ናቸው በሚል ግምት እኔም ተዋወቅኳቸው ። ኤርፖርቱን በአይኔ ለመቃኘት ሞከርኩ ። ተርሚናሉ እዚህ አሜሪካን አገር አንድ መካከለኛ ገቢ ያለው ሰው ሊሰራው ከሚችለው ቤት አይበልጥም ። ከተርሚናሉ ትይዩ  በቆርቆሮ የተሰራ መኪና ቤት ውስጥ አንድ  የእሳት አደጋ መኪና ቆሟል ። ሊቀበሉኝ የመጡት ሰዎች ከሌሎቹ ተሳፋሪዎች ነጥለው ወደሌላ አቅጣጫ ወሰዱኝ ። በኔና በሌሎቹ ተሳፋሪዎች መካከልም የባላ ቅርፅ ያለው መንገድ ተፈጠረና እኔ ሌላ በር ሌሎቹን ተሳፋሪዎች ደግሞ ሌላ በር ዋጠን ። እኔ የገባሁበት በር ትላልቅ እንግዶች የሚገቡበት VIP በር ነበርና የክፍሉ ወለል ከዳር እስከዳር በቀይ ምንጣፍ ተሸፍኗል ። ሶፋዎቹም እንደዚሁ ቀያዮች ናቸው ። ይሁንና የወለሉ ምንጣፎች በጣም ያረጁ ናቸው ። ሶፋዎቹም እንደዚሁ ያረጁ ስለሆኑ  መዳፍ ፤ ክንድና ጭንቅላት የሚያርፍባቸው ቦታዎች  በሳሙናና በቡርሽ ከመታጠብ ብዛት የሶፋዎቹ ፀጉሮች አልቀው ድርና ማጋቸው ተጋልጦ ቀለማቸውን ለውጠዋል ። ከድዩቲ ፍሪ (Duty free) መግዛት የምትፈልገው እንዳለ ጠይቀውኝ ፤ ማየቱ አይከፋም በሚል በኮሪደሮች ውስጥ እያቆራረጥን ወደሱቁ ገባን ።  ኮሪደሮቹ  ወስጥ ከሶስት ኢንች ያልበለጠ ውፍረት ያላቸው የስፖንጅ ፍራሾች መሸፈኛ ጨርቆቻቸው የተቀዳደዱ ፤  በየቦታው ተበታትነው እንሱን እየዘለልንና እየተራመድን ነው ወደሱቁ የገባነው ። እነዚህን ፍራሾች ማንኛውም ወደ ኤርትራ ለስራም ሆነ ለጉብኝት ከሚመጣ ቱሪስት አይን የተሰወሩ አይደሉም ። እንግዶች እየጋበዝክ መግቢያህ ላይ ያለውን ቆሻሻ እንዳለማፅዳት ይቆጠራል ።  ከኤርፖርቱ  በአንዲት አሮጌ ቶዮታ ኮሮላ መኪና ከሁለቱ ተቀባዮቼ ጋር ወጣን ።  ከተማይቱ ምንም አይነት የመንገድ መብራትም ሆነ የቤቶች መብራቶች አይታዩባትም ፤ ጨለማ ውጧታል ። የኤርፖርቱ ኤሌክትሪክም በጀኔረተር እንደሚሰራ ተረዳሁ ።  ከኋላ ተቀምጬ የሚታየኝ የመኪናዋ መብራት  ማሳየት የሚችለውን ብቻ ነበር ። አቆራርጠን ተጣጥፈን  ከተማው መሃል ገባን  ። በኋላ ላይ እንዳረጋገጥኩት ከተማዋ መሃል ላይ በምትገኝ አንድ ተራ ካርቱም ሆቴል የምትባል  ውስጥ ነው መኝታው  የተያዘልኝ ። ወደክፍሌ ስገባ ኮሞው ላይ( White Horse) ውስኪ ተቀምጣል ። አማራ ውስኪና ጥሬ ስጋ ላይ ሲንደፋደፍ ፤ እኛ ኤርትራውያን ጥሬ ቆሎ እየበላን አሸንፈነው ነፃነታችንን ተቀዳጀን እያሉ ይፎክሩ የነበርው አባባላቸው ውስኪዋን ዘወር ብዬም እንዳያት አላደረገኝም  ። ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሮቾች ግን ሰላም አልሰጡኝም ። ሲተረማመሱ  ስላይኋቸው እየቀፈፈኝም ቢሆን ተኛሁ ። ንጋት ላይ ከእንቅልፌ ተነስቼ መስኮቱን ከፈትኩ ። የውጪውን ቀዝቃዛ አየር ሳምባዬ እስከሚችለው ድረስ ሳብኩት ። ያደኩባት አገሬ አየር ሰውነቴን እስኪወጣጠር  ድረስ የሞላው መሰለኝ ።  ፀሃይ ገና አልወጣች ነበርና ደስታየን የተሟላ ያደርገው ዘንድ የወፎቹን የጠዋት ዝማሬ ማዳመጥ ተመኘሁ ። ምንም አይነት ዝማሬ የለም ። በቀጣዮቹ ማለዳዎችም የወፍ ዝማሬ የለም ። ወፎች አስመራ ውስጥ ለምን እንደሌሉ እስካሁን ሊገለፅልኝ  አልቻለም ። የወቅት ነው እንዳይባል በተለያዩ ወቅቶች ደጋግሜ ሄጃለሁ ፤ ወፎች የሉም ። አሽሟጠጠ አትበሉኝና  ለኤርትራ ወጣቶች የስደት መንገዱን (ስግረዶም) ያሳዩአቸው ወፎቹ ሳይሆኑ አይቀሩም ።  ዛሬ ወፎቹም የሉም ፤ ወጣቶችም የሉም ኦሮማይ! ። ስደቱ  ወደ ታዳጊዎችም እየተዛመተ ነው ። ሱዳን ሸገራብ ፤ ኢትዮጵያ እንዳባጉና የስደተኞች መቀበያ ማእከላትን በመመልከት የታዳጊዎቹን እድሜ ማወቅ ይቻላል ።  ሰሃራ ሳይናይና ሊቢያም ምስክሮች ናቸው ።
  
 ከተማዋን ለማየት ከሆቴሉ ወጣሁ ።  ሆቴሌ የሚገኝበትን መንገድ ላይ ወደ ግራ ታጠፍኩና መቶ ሜትር ያህል እንደሄድኩ  ኮምፔሽታቶ ላይ “ሲኒማ ኢምፔሮ” ከሮማዊ ፅሁፉ ጋር ፊትለፊቴ አገኘሁት ይህ ሲኒማ ቤት በጣሊያኖቹ ዘመን  ለነጮቹ መዝናኛ ከተከፈቱት ሲኒማ ቤቶች አንዱ ነው ። ከሲኒማ ቤቱ በስተቀኝ የአስመራ ከተማ ምልክት የሆነችውን የሮማ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ካቴድራልን ታገኛላችሁ ። ይህቺ ቤተ-ክርስቲያን በጣሊያኖች ቅኝ ግዛት ዘመን የኤርትራን የዘመኑ  ጌቶች ነጮችን  ከክርስቶስ ጋር የምታገናኝ ብቸኛ መንገድ ነበረች ። ስጋ-ወደሙም የሚቀበሉት የታላቂቱ ሮማ ዜጎች ብቻ ነበሩ ።  የአስመራ ከተማ መስራች የገበሬው የእንግዳ ቁቢ ልጅ አሉላ አባ ነጋ ይህን ሳያይ ቀድሞ መሞቱ ጠቀመው ። (ይህን የአስመራ ከተማ አመሰራረት ታሪክ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ) ።
  
  ከዚያ በተረፈ የከተማዋ ቤቶቹ የስሚንቶ ምርጎች በየቦታው ተቦዳድሰው  የቆመ የገበጣ  ገበታ ይመስላሉ ።  ቀለም የሚባል ነገር ካረፈባቸው ዘመናት ስለተቆጠሩ  የቀድሞ ቀለማቸውን አንኳ ማወቅ አይቻልም ። የአስፋልቶቹ እድሳቶች ያለእውቀት ወይም ለግብር ይውጣ አለያም በችኮላ የተሰሩ ሆነው ፤ አሮጌው ወይም ያረጀው ሬንጅ ሳይነሳ በላዩ ላይ አዲሱ ተመርጎበታል ።  በዚህም ምክንያት ሬንጁ እየቀለጠ ቀስ እያለ በመውረድ የውሃ መፋሰሻውን ደፍኖታል ። ጠዋት ነውና አስመራ እንደተኛች ነበረች ። በኋላ ላይ ስትነቃ ግን የሰዉ እንቅስቃሴ ይህን ሁሉ ትዕይንት ይጋርደዋል ።  
 
ከዚህ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ ሳገኘው ወደ አስመራ ወጣ ገባ እያልኩ የማጫውታችሁ ይኖረኛል ።
 
አሁን ወደ አርበኞች ግንባር ።                
     
ኮለኔል ፍፁም ይስሃቅ በቅፅል ስሙ “ሌኒን’ የአርበኞች ግንባር ፤ የድምሕትና ፤ የግንቦት 7 ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳይዋና አዛዥ ። በወታደራዊ ሰንሰለቱ “በስሪት አሃደ” በጀነራል ተክሌ ማንጁስ ስር መተዳደር የሚገባው ። ግን ከወታደራዊ ሰንሰለት ውጪ በቀጥታ ከፕሬዚደንቱ ፅ/ቤት ዋና ሹም ከኮለኔል ተስፋ ልደት ተ/ስላሴ ጋር የመገናኘት ስልጣን ያለው ።
ሻለቃ ሓድጎ የአርበኛችና የግንቦት ሰባት ተዋጊዎች ጋር አብሮ የሚኖር የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውን ተቆጣጣሪና በአርበኞቹ ላይ ያለገደብ ሙሉ ስልጣን የነበርው ።( ከኮለኔል ፍፁም ይስሃቅ ጋር ባለመግባባት ከስልጣኑ የተነሳ) ።
ሻለቃ ዳዊት የዲምህት TPDM ተዋጊዎች ጋር አብሮ የሚኖር የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውን ተቆጣጣሪና በተዋጊዎቹ ላይ ያለገደብ ሙሉ ስልጣን ያለው ። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ከሻለቃ ሓድጎ መባረር በኋላ የአርበኞች ግንቦት 7ና የድምህት ተዋጊዎች ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው ።
ኮለኔል ተስፋ ልደት የፕሬዚደንቱ ፅ/ቤት ዋና ሹም ።
( እኔ በነበርኩበት ጊዜ) ኮለኔል ጣእመ አብርሃ ጎይቶም በቅፅል ስሙ “መቀለ” የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ወታደራዊናፖለቲካዊ ጉዳይ ዋና አዛዥ የነበረይህ ሰው ኮለኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን ለመግደል በሻእቢያ ወደዚምባቡዌ ተልኮ ተነቅቶበት ተይዞ የተመለሰ ነው ።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው የሻእቢያ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ፤ቀጥታ ግንኙነት ከሌለው ከኮለኔል ተስፋልደት ተ/ስላሴ በስተቀር ሁሉም ፈላጭ ቆራጭ አዛዦች ናቸው ። በህይወት ላሉትም ሆነ ህይወታቸው ላለፈው ሰዎች ቀጥታ ተጠያቂዎች ናቸው
ከነዚህ ከላይ ከጠቀስኳቸው ሌላ የየድርጅቱን ሰራዊት ለውጊያ ወደ አገር ውስጥ ይዘው የሚገቡ መስመራዊ አዝማች የበታች ሹማምንት አሉ ።
በምንም መልኩ ጦርነት ከተነሳ አገራችን የምትወረረው በሻእቢያ ነው ። አዝማቾቹ ደግሞ እነዚሁ ከላይ የጠቀስኳቸው ወታደራዊ ሹማምንቶች ናቸው ። በሻእቢያ ቅኝት የሚራመዱት ደግሞ እንደ ባንዳ ወይም የሻእቢያ አጋሚዶ ሊቆጠሩ ይገባል ። እኔ እስከማውቀው ድረስ በሻእቢያ አመራር የሚዋጉ ፤ በራሳቸው ጦርነት የማንሳትም ሆነ የመዋጋት ወታደራዊ ብቃትም ችሎታም እንዲኖራቸው አይደረግም ፤ አይፈቀድምም ።
ይህ እየተሰማ ያለው  የጦርነት ነጋሪት ተጋግሎ ጦርንርት በሁለቱ አገሮች መካከል ቢነሳ አሁን ሻእቢያን አመራር የሚከተለው ሁሉ ሻእቢያን ደግፎ ሊሰለፍ ነው ማለት ነው? ተጨባጭ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ባላገኝም ፤ በታሪካችን በሶማሊያ ጦርነት ጊዜ ሶማሊያን ደገፉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ያንን እድፍ እስከዛሬ ድረስ አጥቦ ማፅዳት አልተሳካላችውም ። ዛሬም ሻእቢያን የሚደግፉ ወገኖች ቆም ብለው ሊያጤኑ ይገባቸዋል እላለሁ ።
አርበኞች ግንባር ቀድሞ ከነበረው ሃይል ሆን ተብሎ በየጊዜው እንዲመናመን ተደርጓል ። ምክንያቱም በውስጡ ያሉት ሰዎች በአብዛኛው አማሮች ናቸውና ። በሻእቢያ ህሳቤ አማራ ማለት የኢትዮጵያዊነት ቫይረስ ተሸካሚ ማለት ነው ። ሻእቢያ ደግሞ ኢትዮጵያ እስካልፈራረሰች ድረስ ኤርትራ ሙሉ ነፃነቷን ገና አላገኘችም ብሎ የሚያስብ ድርጅት ነው ። ስለዚህ የአማሮች መጠናከር አደጋ ያመጣል ብሎ ያስባል ። አማራ ያልሆኑ ሰዎችን ግን እንደፈለኩ አሽከረክራቸዋለሁ ብሎ ያምናል ።
ግንቦት 7 በሰው ሃይል አኳያ ከአንድ ሰው የእጅ ጣት በማይበልጥ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ነው መሰብሰብ ችሎ የነበረው ። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ያለፍላጎታቸው ወደአውሮፓ ትሄዳላችሁ ። እዚያም የግንቦት ሰባትን አላማ ታስተምራላችሁ ። በመጀመሪያ ግን ኤርትራ ስልጠና ትወስዳላችሁ ተብለው ባዶ የውሸት ተስፋ ተሰጥቷቸው ከመጡ በኋላ እዚያው ሓሬና ማሰልጠኛ ጣቢያ ለሻእቢያ ባሪያ አስዳሪዎች መጫወቻ ሆነው የቀሩ ሰዎች ናቸው ። ስለዚህ አርበኞች ግንቦት 7 የተባለው ውህደት ትልቁን ቁጥር ልስጠውና ቢበዛ ከመቶ ሃምሳ  በላይ ተዋጊ የለውም ።። በነገራችን ላይ የግንቦት ሰባት ተዋጊዎች ናቸው ተብለው ፤ አይደለም ከፊት ለፊት ፤ ከኋላ እንኳን የተነሱትን ፎቶ ድርጅታቸው እስከዛሬ አሳይቶን አያውቅም ። የሌሎችን ድርጅቶች ፎቶዎችና ፊልሞች በገደምዳሜ የራሱ ለማድረግ ሲሞክርና ሲያሳይ ግን አውቃለሁ።
 ኦብነግ ( የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር) ከሌሎች የኢትዮጵያ ተዋጊ ሃይሎችና ድርጅቶች ለምሳሌ ከአርበኛችግንባር ድምሕት ወይም ከኦሮሞ ነፃ-አውጭ ርድጅት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖረው ተደርጎ ተነጥሎ ለብቻው ቀይ ባህር ላይ የተቀመጠና ልዩ ቁጥጥር የሚደረግበት ድርጅት ነው ።
 ያም ሆነ ይህ ኤርትራ ውስጥ ተዋሃደ የሚባለው አርበኞች ግንቦት 7 ፤ ብቻውን በራሱ ለውጊያ ብቃት አለው አልልም ።
የጦርነቱን ዜና እኛ አደረግነው እያለ አርበኞች ግንቦት 7 በራሱ ሚዲያ ቢወተውትም ፤ እየተዋጉ ነው ተብለው የምናያቸውና የምንሰማው ግን ድምህትቶ ናቸው ። የትግራዩ ድርጅትም ተዋህዷል እንዴ?

ተግባር አሸናፊ ነው! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2015 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ግን ዓይኔ የኔ ነበርክን? መንፈሴስ? በእርግጥም ከእኔ ጋር ነበራችሁን? „ የአንቺ – ነበርን“ – መልሱ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አይደለም ዛሬ ቀድሞም ቢሆን ትግራይ – የበላይ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለድል ያበቃው ጥንካሬው – አልነበረም። ጦርነትን ለማሸነፍ ሚስጢር በመዳፍ መሆንን – ይጠይቃል። አቅም ያለው፤ ቀልፉን የያዘ ሥጋና ደም ነበረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነበር ማለት – ይቻላል። ተገለን ተጨቁነን ነበር የሚለውን ቅጥፈት አመድ የሚያአደርገውም ይህ ቆሞ የሚሄድ – የታሪክ ሃቅ ነው። እነዛ የዘር ልክፍተኞች እንደ የተሰጣቸውን ሃላፊነት፤ የገቡትን ቃል ተላልፈው ታማኝነታቸውን አፈር አስግጠው ሚስጥርን እንደ ቄጠማ ባይነሰንሱት ኖሮ፤ በሁለት ቢላዋ ባይበሉ ኖሮ .. ኖሮ ኖሮ ወያኔና ኑሮው በጫካው የዕድሜ ልክ በሆነ ነበር። ክህደቱ ሀገርን እንዲህ አፈረሰ – ትውልድንም ቀጣ። ያን የመሰለ በ200 ዓመት ሊገነባ የማይችል ተቋማት፤ የመንፈስ ሃብታት ሁሉ – ፈራረሰ። በውስጥ አርበኛ – ባንዶች። ዛሬም የነፃነት ትግሉን ካባ ደርበው ውስጣችን እያረዱ የእኛ የሚመስሉ ግን የእኛ ያልሆኑ አሉ። ስለዚህ ቅኖች በቅንነት የሚያስተላልፉትን መልዕክት እንዳሻቸው በማደረግ፤ በመደለዝ ምኞታችን ህልማችን እንዲጎዳ ጥፈረ መጥምጦች አሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፤ ጋርድ ተቁሞ ተውሎ የሚታደረውም – ለዚኽው ነው። የሳይበሩ ጦርነት ቅራኔው እዬከረረ በመጣ ቁጥር እጅግ የከፋ በመሆኑ ብዕሮች ትጥቃቸውን ጠበቅ አድርገው ሊጠብቁት ይገባል ነው – ዕድምታው። ህልም እንደፈቺው እንዳይሆንም፤ ብልህነት መልካም ስለሆነ ነበር የጻፍኩት። እንጂ ትራሴን ከፍ አድርጌ መተኛት – ይቻለኛል።

ጤና ይስጥልኝ የተከበሩ አቶ ይገረም አለሙ እንዴት ሰነበቱልኝ – በአያሌው። እጅግ አድርጌ – አመሰግነወታለሁ። ከሁሉም በላይ እንዲህ ቅርብ ያደረጉኝ መሆኑን በአሁኑ ጹሑፉዎት – ተገነዘብኩ። እንኳንም – ፃፍኩት። በውስጠዎት ሥርጉተ ያላትን የእህትነት ልዩ ቦታ መረዳት – ቻለች። እናም ሐሤትን አፈሰች – ቸረፈሰች። ከልቤ ነው ተረብ – እንዳይመስለዎት። እሺ!

ውድ ወንድሜ – ዛሬ የኔው ይባሉ፤ ወያኔ መጥላቱ ብቻ በቂ – አይደለም። ይህን ተግባር ላይ ስላሉ የሚውቁት – ይመስለኛል። ወያኔን ሃርነት ትግራይን የጠላንበትን መሠረታዊ ምክንያት ሥሙንም  ግብሩን ተንተርሶ ያወጣው ማንፌስቶውን ነው። ማንፌስቶ የተመሰረተበት ዓላማና ተልዕኮ – አለው። ተልዕኮውና ዓላማውን በመፈጸመና በማስፈጸም እረገድ ግዳጁን የተወጣ የጎጥ ድርጀት ነው። የቀረውም ቦታም ካለ እስከ ተኛን ድረስ – ይቀጥላል። ስለዚህ ዘንበል ወይንም ዘመም ብለው የሚቀርቡ ሃሳቦች ወደ ዬትኛው መንገድ ወይንም አቅጣጫ ወይንም ተፋሰስ እንደሚነጉዱ ወይንም ለዬትኛው ፍላጎት አቅም ሊሆኑ እንደሚችሉ ቆም ብለን በማስተዋል ሊቃኝ ይገባዋል ነበር የጹሑፌ – ዕድምታ። ያነበብኩት ከልብ ነበር ውስጤን ሰጥቼ –  ቢያቅለሸልሸኝም – ስለማከብረዎት። ፁሑፎዎት ዘሃበሻ ብቻም አይደለም ፖስት ያደረገው፤ ሌላ ቦታ ላይ – ተገናኝተናል። በጎሪጥ ሳላዬው ተዚኽም አለህ ለካ? ብዬ ከአቦል አስከ በራካው ቤት ያፈራውን የቡና ቁርሳችን እዬከሰከን – በቤተ – ኢትዮጵያ – ተንበሽብሸንበታል።

ወንድሜ – እኔ አይጋ ፎረም ገብቼ – አላውቅም። ምን እንደሚመስል መልኩንም ገፁንም – አላውቀውም። ወይንም በስልትና በጥበብ፣ በሚያምር የድምጽ ቅላጼ የመርዝ ሰለባ ለመሆን – አልፈቅድም። „ሲወዱም ሲጠሉም እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ ይላሉ ጎንደሬዎች። ማለት የሸገር ራዲዮ ታዳሚ – አይደለሁም። ከሰማዬ ሰማይት በላይ ቅዝፈት በሚያሰኘው ጹዑም ድምጽ ዲዲት እሰኪበቃው ድረስ – ይረጫል፤ ዬኢትዮጵያዊነት ተቋማት ሁሉ – ያለርህራሄ ይደረመሳል – ዝግጅቱ። የተረሱ የቂም ኩትኩቶችን እዬቀራረፈ – ግመጡት ይላል – መሰናዶው፤ በፍቅር እብድ የሚሉ የተሰለቡ አሉ ማር ወላላ በሃሞት ጠቅልሎ  – ስለሚያዘንብላቸው፤ እኔ እህተዎ የተመሠረተበትን መሰረታዊ ፍላጎት ጠረኑን ከሩቁ – አውቀዋለሁ። „አማራጭ ራድዮ¡“ እንዴት ተቀለደ?!  ህም – ምን ልልዎት ነበር ለማለተርፍበት ጊዜ – አልከስርም። እምታደምባቸው ድህረ ገፆችም ቢሆኑ እጅግ ውስን – ናቸው። እኔን የሚመስሉኝን  – ብቻ። ውስጤን የሚፈውሱትን – ብቻ። ወይንም ዕንባን ሳይረገጡ ግን የተለዬ ሃሳብን የሚያስተናግዱትን – ብቻ፤ ወይንም ማጣቀሻ – ሲያስፈልገኝ፤ ወይንም ትንተናቸው ት/ቤቴ የሆኑትን ብቻ። ነገረ ጥፋትን ወያኔዊ ተፋሰሱንማ –  አድገን አረጀንበት እኮ፤ ጥዋት ማታ የሚፈሰው ዕንባ ይበቃል …. ዜናው እሱ ነው መሽቶ እስኪ ሲነጋ …. እሱም ይሰንብትልንም እዬተባለ ነው¡ – እያደመጥን፤ አይገርመዎትም መከራ ይቀጥል … ህም!

ሌላው ሃሳበዎትን በሃሳብ ሙግት እንዳልተመቸኝ የጻፍኩትም – ስላከበርኩዎት ነው። እርስዎ ሳላነብ እንደጻፍኩት አድርገው ነው – የገለጹት። አልከፋኝም። ሁሉንም ለማስመቸት ነው አደባባይ – የወጣሁት። ከዚህ በበለጠም ፈጨትም – ደቆስም ቢያደርጉኝም በመከራ የሰለጠነ ሰብዕና ስላለኝ አቀባበል ይደረግለታል –  ደስ ብሎኝ። ተደብቄ – አላውቅም።

አማርኛ ቋንቋ የፍልፍስና – ቋንቋ ነው። አማርኛ ቋንቋ የምርምር – ቋንቋ ነው። አንዱ ቃል፣ አንዱ ስንኝ፣ አንዱ ፊደል በዬሥርአቱ ሚስጢርን – ይቃኛል። ድምጽ ምቱ እራሱ ነጮች የቀረብን – ይሉታል። ቲያትርም – እጫወታለሁ። የቲያትር ቲሙ እኔን ከሚፈልግበት ዋንኛው አማርኛ ትረካዎቼንና ግጥሞቼን እጅግ ስለሚያፈቅሩት – ነው። ሙዚቃዊ ቃናው በነፋሻማ ምት እያዝናና፣ እዬጠገነ በልስሉስ መዳፉ – ይፈውሳል – ድህነትም ነው። አማርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ነው። የጻፉት አሳምሮ – ገብቶኛል። እርግጥ – እርእሱ አልሰረሰረኝም። ወይንም እኔን ለመዝረፍ አቅም – አልነበረውም።

የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ይገርም እኔ የፖለቲካ መሪ – አይደለሁም። ወይም የፓርቲ አባል – አይደለሁም። ስለዚህ ውስጤን ግልጥልጥ አድርጌ ለማሳይበት የታሰርኩበት ፕሮግራምና የፓርቲ ደንብ – ገመድ የለም። ገፊ ኃይል የለኝም – ከዕንባ በስተቀር። ፖለቲካ መሪዎች ሆዳቸው የሚውቀውን ሃቅ ለበስ አድርገው በቅኔ – ይቃኙታል። ፖለቲካ ሥነ ጥበብ ነውና። ሥርጉቴ ግን ክንብንቡን ገለጥ አድርጋ ተክለ ቁመናውን ከውስጧ ጋር በሃዲድ – ታገናኘዋለች። የሆነ ሆኖ ህዝብ መስታውት ነው ዳኝነቱን ለብዙኃኑ ህሊና – አስጠዋለሁ። አንድ መስመርም ላይ ካለንም ደስታውን አልችለውም – ችርስ! በዚህ ባንመቻች በሌላው ይደምር ነው አይደል? በነገራችን ላይ የጹሑፎዎት ሊንክ በሙሉ – እይዛቸዋለሁ ዝምድና ስላላቸው – ከስሜቴ ጋር። ሳይመቸኝ ደግሞ እንዲህ ቅርቤ ስለሆኑ ወጥቼ አልተመቹኝም – እላለሁ። ሸጋ ነው አይደል?! እንደወደዱት መግቢያወት ፏ ብሎ አቀባበል – አድርጎልኛል። ለማንኛውም የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማጣጣል ከፈለጉ ሥርዓተና ህግን በተሟላ ሁኔታ ያለው እጬጌው – ቅኔኛው አማርኛ ቋንቋ ህገ = ነጥብ አለው ስላቅ የሚባል ¡ እርስዎም ያውቁታል በዚህ ቢጠቀሙ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መግባባት እንችል – ነበር። ሌላው ስድስት ገፅ እንደሆነም – ነገርውኛል። የተሸከመው ዬዘሃበሻ ብራና ነው። ዘሃበሻ ስብሰባውን የሚመራበት ህገ ደንብ ሲኖረው በፍትሃብሄሩ ህግና ሥርዓት ክሱ – ይቀጣኛል ወይንም በወንጀለኛ መቅጫውና ሥርዓት። የተዳፈነ ወይንም የተከረቸመ ሙግት የለም። ያ ሙግት አይደለም። ተጠዬቅ ለማለት አቃቢ ህጉን፣ ዳኛውን፣ ጠበቃውን፣ ችሎቱን ሊይ የታደመውን ግራቀኙን መርታት መሠረት ያደረገውን መነሻውን ሳያስታምሙ ወይንም ሳያቆላምጡ መፋለም የተገባ ነበር።ከአያያዝ ይቀዳል ከአነጋገር ይፈረዳል“ እንዲሉ።  አማርኛ ቋንቋ እንደ ወድአራባ – ወዳከር ወይንም ደበር እንጀራ ሊጥ ሊሸበልል – አይችልምቦንዳም ወይንም ጣቃም – አይደለም። እራሱን መግለጽ እንዲችል ሆኖ የተፈጠረ ፀዲቅ ነው። እንደ ተፈለገ በክትና በዘወትር ቃናዎች ማዘናጠፍ – ይቻላል። ስለዚህ ሙግቴ ብትን ብሎ መብራራት – ስለነበረበት በፈቀድኩት መልክ – ተከውኗል። አንድ ተናጋሪ ለንግግር ከመሳናዳቱ በፊት ንግግሩን ሊያግዘው ፤ ለንግግሩ አጥንትና ሥጋ ሆኖ እንዲያቆመው መረጃዎችን በእውነት ላይ ተንተርሶ በአግባቡ እንደ ዕርዕሱ ፍላጎትና ዝንባሌ አቀናብሮ በዘርፍ ዘርፎ አደራጅቶ ማቅረብ – አለበት። በሚገባ ተሰናድቶ። ጸሐፊም እንደ ተናጋሪ ማለት ነው። ልዩነትም አንድነትም እንዳላቸው ለማጠዬቅ ነው „እንደን“ የተጠቀምኩት።

ሌላው አጫጭር ጹሑፎች ለራዲዮ፤ ለዜና፣ ለማስታወቂያ፤ ለባራሪ ጹሑፍና ለርዕሰ አንቀጽ የሚያገልግሉ ናቸው። ይህን በሚመለከት ከ5 ዓመት በፊት ድህረ ገጼ ላይ ያልሰረዝነው አለ። እንዲያውም የዛን ጊዜው እና የዛሬውን አቋሜንም ያሳዬወታል። በድምጽ ነው የተሠራ …. ለናሙና እንጂ ከጹሑፉ ጎል ጋር አደራጅቶ መምራቱም ቢሆን – ተኑሮበታል።

http://www.tsegaye.ethio.info/kana.html (www.tsegaye.ethio.info)

  • እስከ መቼ?
  • ክብር ከሚሸጥ …
  • ምን ምን ይሸትሃል?
  • ሞትና ሞት ሲፋጠጡ …
  • የራህቡ ነጋሪት ከአምስት ደቂቃ በላይ አልሄዱም ከሙዚቃ ጋር —-

ወንድሜ ሆይ! እርቅና ሰላም የሚወርደው በጥት ፍልስፍና – አይደለም፤ ነገን ለማሳደር ሃቅ ዓይነ እርግብ ተዘጋጅቶለትም – የማይሆን ነው። ቀጥ ባለ ግልጽነትና – ቀጥተኝነት እንጂ። ምንም እንኳን እርስዎን ባይመለከትም ጦር የተመዘዘበት የጋራ ሃብታችን አማርኛ ቋንቋ ከመሰረቱ ጠፍቶ በትግረኛ ቋንቋ እንዲተካ ተግቶ በታታሪነት እዬማሰነ ያለው የትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዴት ድቅቅ እንዳለ አንድ ጨዋታ – ላወጋዎት – ፈልግኩኝ። ያው ቋንቋውም የጥቃቱ ሰለባ – ስለሆነ። ዝምድናችንም – እንዲጠብቅልን በማሰብ፤ ቀኑን አላስታውስውም ሚዚያ ላይ በያዝነው ዓመት „አርተ“ የሚባል የኦስትሪያ የጀርመንና የሲዊዝ የጋራ የቴቪዥን ፕሮግራም አለ። „የትምህርት ሂደትና የትውልዱ እንክብካቤ“ የሚል በታላቋ ብርታንያ እና ኢትዮጵያ ያሉ ሁለት የ13 ዓመት ታዳጊዎችን በንጽጽር አቅርቦ ነበር። በዛ ፕሮግራም አፋር ነበር – የተመረጠው። የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣቱ ሃመድ ት/ቤቱ ለመድረስ የሦስት ሰዓት የእግር ጉዞ – ያደርጋል። ደርሶ መልስ ስድስት ሰዓት፤ ቃጠሎ ነው ቋያ ነው። መንገዱ አሽዋ ነው። ውሃ ጥሙ ይህ ነው አይባልም ለዛ ለጋ – ቀንበጥ። ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ ላይ ካለው ምንጭ መቅጃ ሳያስፈልገው አንገቱን ከጉድጓዱ ውስጥ እንዳለ አስገብቶ ተጎንብሶ – ይጠጣል። አይጠቅመውም – ተቃጥሏላ! ሃመድ ጎበዝ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። በሂሳብ አጅግ ጎበዝ ነው። ጋዜጠኛው „የትኛውን ትምህርት ትወዳለህ ብሎ ሲጠይቀው“ „አማርኛ ቋንቋን“ አለው። „ለምን?“ ሲለው „ስለምወደውና ከወገኖቼ ጋር መግባባት እንድችል“ አለው። በቃ የ40 ዓመት የተጋዳላይ ተልዕኮ አሽዋ ውስጥ ሲቀበር ቁጭ ብዬ – ተመለከትኩት። ተነስቼም ሻማ – አበራሁኝ። እንዲህ ነው ፈጣሪ ካሳ – የሚያዘጋጀው፤  ስለዚህ አማርኛ ለእኔ – ፀሐዬ ነው። በስስት ነው – እምወደው። አይቼም – አልጠግበውም። ማለት የፃፉት በመደዴ አልተሄደበትም – ገብቶኛል ለማለት ነው። ስለሆነም ለጻፍኩት መልስ ይቅርታ – አልጠይቅበትም። ትውልዱ አበጥሮና አንተርትሮ እንዲያውቅ በምፈልገው መልክ ተዛማጅ በደሎችን አክዬ – ኮልሜዋለሁ። ግቡን እንደሚመታም ተስፋዬ ዝልቅ ነው። „በቃኝን – እንዲያነጥር“ ሆኖ ተላከ። እርግጥ ነው ዕራእሱ ብቻውን ወንዳታ የሚሉለት  – ይኖራሉ። የእርስዎ ትንተና የሚመቻቸውም – ይኖራሉ። ክር ላይ የተንጠለጠሉ ዕሳቤዎች ጥገታቸው ስለሆነ። ኤንም ቢንም ሲንም ዲንም እንዳይከፋው መንደር ፍለጋ ሲማስኑ ውለው ለሚያድሩት ሊመች ይችል – ይሆናል። ለእኔ ግን ከእርእሱ ጀምሮ  – አልተመቸኝም ነበር። የአንድ ጹሑፍ እርእስ አኮ ጎል – ነው። ውስጥ ሳይገባ እርእሱ ራሱ በቂ  – ነበር።

ይህ ያነሱት ነጥብ በ90ዎቹ አጋማሽ እንደ ኢሮፓ አቆጣጠር አሽኮኮ የተበላለት ሃሳብ – ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከራሱ በበቀሉ ይጠፋል የሚል ዕድምታ የነበራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ ብዙ – ደክመውበታል። እነዛ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው የተከበከቡት ወገኖቻችን ግን ለቀለም ትምህርት ቅድሚያ በመስጠት ያን ተስፋ ጣል ጣል አድርገው እንጀራቸው ላይ በማተኮር ዛሬ እናቴ ቢጠሯቸውም – አይሰሙም። በቀለሙ ከመጨረሻው ደረጃ – ደርሰዋል። ያን ጊዜም ቢሆን „ትግራይ የሞተለትን ያህል አልተጠቀመም“ ነበር – ሙግታቸው፤ ወይ መዳህኒተአለም አባቴ እል ነበር ያን ጊዜ? ይገረም አሉ ሥመዎትን ይገረም ነው ነገርዬው፤ ዛሬም ቢሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሥሩ ይነቀል ቢባሉ የሚስማሙ – አይመስለኝም። ክርና መርፌ የሚያደርጋቸው ማጣበቂያ መስመር አለና። የተከደነች ኪዳን አለች። ስለዚህ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ተደክሞበታል እነ አጅሬ ግን ወይ – ንቅንቅ!  እርግጥ ለዬት አድርገን ልናያቸው የሚገቡ ምርጥ ወገኖቼ እንዳሉ – አውቃለሁ። ዘውድ – የተከበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ አይነት፤ በፐርሰንት ሲታይ ግን እጅግ ዝቅተኛ – ነው ዳታው።

ሌላው የተጎዳው አይደለም ቀልብ – የሚሰጠው። የአያያዝ ጥበቡም ቢሆን ተጠቃሚው ሲቆላመጥ ተዘውትሮ – ይታያል። ኑልን ተብሎ ሲለመን። ለእኔ ይህ የተንጋለለ – ነው። የተጎዳው ደግሞ እኩልነት ቀርቶበት ለሥነ – ልቦናው ራፊ ሲደረብለት – አይታይም። ብልጫው ቀርቶበት ማለቴ ነው። ማስታመሙ ይበቃ ነው – ጹሑፌ ያለው። ጊዜ ከመብላት አቅምን እንደ ዘር ከመበትን በስተቀር ትርፉ – ምንም ነው። አልጨመርነም። በ24 ዓመት ስንት አሉን?! ስንቶቹ ናቸው የእኛ – የሆኑት። እንዲያውም ከእኛ የተዘረፍነው የሚያል ይመስለኛል። አሁን እራሱ  ዬአርበኛውን እንቅስቃሴ በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። ለዚህም ነው „ኤርትራ“  እነማን? ከእነሱ በላይ ላሳር – ያልንላቸው። ለዚህም ነው „ኤርትራ“ አጀንዳ የሆነችው። እናም ሁል ጊዜ ፍላጎታችን ቁልቅል ….

እንዲሁም – በፖለቲካ አስተሳሰብ ወተት ያደገውን እና ህሊናው ሊለማ የሚገባው ዕንቡጥ መንፈስ እኩል አይተረጉሙትምት – ጹሑፉዎትን። ለዚህ ነው በፈቃደኝነት በዘበኝነት የነፃነት ትግሉን እያገለገልኩ – ያለሁት። በትርጉም የሚቃናውን – በትርጉም፤ በሥርዓት መታረቅ ያለበትንም – በህግና በጭብጥ – እምፋለመው፤ የእኔ መርኽ ተከስክሰው ወይንም ተልከስክሰው ሊቀሩ የማይገባቸው የሃቅ ወርቆች በአታቸው መንበራቸው ላይ መሆን ይገባቸዋል ባይ – ነኝ። በመርህ ደራጃ በችግራችን አመንጪ ላይ መስማማት ካልተቻለ መፍትሄ አምንጭነቱም የጫጫ ነው የሚሆነው። ፍላጎታችን – ንፋስ በነፈሰ ቁጥር ሲፍረከረክ እንቦጭ ብሎ ሲወድቅ የሚታዬውም ለዚህ ነው።

የትም ቦታ ተሰክስከው ቀን አብረው ይተክላሉ፤ ሌት ሲነቅሉ – ያድራሉ። አቅም የማያድግበትም፤ አቅም የሚሳደድበትም ምክንያት ይሄው ነው። ቆዳ ለእኛ፤ ሥጋ – ለሥጋ። ይህን – አይተናል። ትናንት ኢትዮ ኤርትራዊውን የአጥፊው ማንፌስቱ መሥራች አዛውነቱን አቶ ሰዬ አብርሃምን ካልተቀበላችሁ፣ ዘውድ ካላደፋችሁ ይምራን ይግዛን ይንዳን ብለው ተራማጅነትን – አወጁ። ወይንም እስከ መገንጠል ብለው፤ አሻም ያልነውን ደግሞ በአጥር ጣሾች በተራማጅ ሃሳብ ሥር ይሾጎጡና እዬተገላበጡ እያደኑ አቅምን እንዴት እንዳወደሙት – ታዝበናል። ይገርመወታል ለጎሰኝነት ጥብቅና ቆመው አውራ የነበሩት ዛሬ ደግሞ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ሆነው – እያዬን ነው። ጃንጥላውን ሸንቁረውም ሸንጉረውም – ፈረሰ። ያ ጃንጥላ ግርዶሽ – ነበር። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች ድሎታቸው ነው።  አብዝተው ያደባሉ አቅም ብቅ ሲል ከተቀበሩበት ይወጡና ጦርነት – ያውጃሉ። ግን ምንግዜም አዝማቹ – ተግባር ነው። ተግባር – ያሸንፋል። አሸናፊው ተግባር ያስቀደመው ሃሳብ ደግሞ የብዙኃን ነው። አሁን አውላላ ሜዳ ላይ ያሉ – ይመስሉኛል። ትግሉ ዓላማን ማሳካት ሆኖ ሳለ ህዝበ ጠቀም በሆነ ፍላጎት ላይ ስንጥር ማባዛት። በቃ! ለነገሩ በሚመጥን ተግባር የሚመጥን ፍቅር ይዛቅበታል። በስተቀረ አይደለም መጠለያ – መቆናጠጫም አይኖርም። ስለዚህ ቀዳዳ የሚከፍቱ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ሊሰጣቸው ይገባል። አብሶ እርእስ በሚገባ በተደሞ ሊታይ ይገባዋል።

አዩ ወንድምአለም — ይህን የማነሳለዎት በምክንያት ነው። ተጠቃሚው በሥነ ልቦናው ላይ የደረሰበት ጉዳት – የለውም። ሥነ ልቦናው የበላይ ነው። በግራ በቀኝ ነው የሚደገፈው። የተጎዳው ግን ሥነ ልቦናው በግፍ – ተደርምሷል። መንፈሱ በልዟል – ወይቧል። ማዲያታማ ሆኗል። በተቀጠቀጠ ሥነ ልቦና አቅም መገንባት ፈፅሞ –  አይቻልም። ከምንግዜውም በላይ አቅምን ለማምጣት የተጎዳውን ሥነ ልቦና በጥሩ አቀራረብና አያዬአዝ የኃይል ምንጭ ማደረግን – አሁን ይጠይቃል። እሱዎ ያሉት ሃሳብ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩለዎት በ90ዎቹ አጋማሽ ብዙ – ተደክሞበታል፤ ግን – አልሠራም። እንዲህ በቀላሉ ለቅለቅ ተደርጎ ማጥራት – አይቻልም። የተጎዳና ያልተጎዳን፤ ተጠቃሚና – ተገፊን በእኩል አያያዝ በአንድ ማስኬድ በፍፁም – አይቻልም። እውነቱ ይሄ ነው። ከንፍሮ ጥሬ ካወጣቸው እጅግ እጅግ ጥቂቶች በስተቀር ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ – የለም። ኑሮም – አያውቅም። በዬፌርማታው ነው – የሚንጠባጠበው። ንክኪ ያለው ሁሉ። ጥርት ላለ ድል ጥርት ያለ አቋም ወሳኝ ነው። በጥገና  – አይሆነም። በውሽልሽል ዕሳቢም ቀዳዳ በቀዳዳ ነው – የሚሆነው። የማይጠገነው – አይጠገነም። ሁለት ውሃ ዬያዘን ብርጭቆ አንድ ብርጭቆ አድርጎ ማዋህድ – አይቻልም። ቢሞከር ብርጭቆው ይሠበራል ውሃውም – ይፈሳል። ሃቁ ያለው ከበይ ተመልካቹ ሳይሆን – ከተጠቃሚው ነው። ተጠቃሚው አልተጠቀመም እዬተባለ አቅም መፍጠር – ፈጽሞ አይቻልም። በእኛ ውስጥ ለመኖር ጥቅምን በርግጫ ማለት – ያስፈልጋል። ስለማያውል – ስላማያሳድር። ስለማያሰነብትም። በመርኽ ድርድር – የለም። no አልተግባብቶም – yes ተግባብቶ። ይሄው ነው። ጨረስኩኝ። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ይህ የመጨረሻዬ ነው። ሌላ ከኮለሙ ደግሞ ካልተመቸኝ መስመር ላይ እንገናኛለን .. ወይ ፌርማታው ላይ እንጠባበቃለን … ደህና ይሰንብቱልኝ። የእኔ ድንግልም – ትጠብቅልኝ።

የኔዎቹ እኔ ሰንበትን ተንተርሼ – አሰብኩኝ። ለዛውም አሁን ጥብብ ያለ ጊዜ ላይ – ነበርኩኝ። ታዲይንላችሁ በድንገት አቶ ይገርም ወደ ቤተ ሥርጉተ ጎራ አሉና ቡናና ሻይ፤ ሽሮዋንም ተከተክ አድርጌ በዘንጣፌ ቤት ለእንግዳ ስልላችሁ እግረ መንገዴን ናፍቆቴቼን ግኝት። መሸቢያ ሰሞናት! ዘሃበሻ ኑሩልኝ – ለምልሙልኝ።

„እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!

አርበኞቻችን መርሆቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

ለሰላም ጥረት ሳይፈተሽ ጉልበት  –  ይገረም አለሙ

$
0
0

“ሰማይ ሲደማምን ይወረዛል ገደል ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል፣” የሀገሬ ሰው ብሶቱን በቀረርቶ የሚገልጽበት  ስንኝ ነው፡፡

peace-dove1አርበኞች ግንቦት 7 ፊሽካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል ብሎ ባወጀ ማግሥት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ድምጻቸው የተሰማው የግንባሩ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጦርነት  ያወጁት ኃይሎች  ወደውና ፈቅደው  ሳይሆን በወያኔ እብሪትና እምቢተኝት የገቡበት ጦርነት መሆኑን ገልጹ፡፡ከሁለቱም ወገን የሚጠፋው የወንድማማቾች ህይወት በመሆኑ ወደዚህ መንገድ በመግባታችን እናዝናለን፤ ገደልን ብለን የምንፎክርበት ሳይሆን በሚከተለው ጥፋት የምናዝንበት ነው ጦርነት ነው አሉ፡፡ አክለውም  ወደማንፈልገው ጦርነት የገፋን ወያኔ  ከእብሪቱ ወጥቶ ፈቃደኛ ከሆነ ጦርነቱን የጀመሩት ወገኖች አሁንም ቢሆን ኢትጵያን ለዴሞክራሲዊ ሥርዓት ለሚያበቃ ውይይትና ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ጦርነት መጀመሩን ካወጀ ግንባር መሪ አንዲህ አይነት ቅዱስ የሆነ አነጋገር መስማት ያስደስታል፡ የወያኔ ተቀዋሚ የሆን ሁሉ እንደህ ብናስብ መልካም ይመስለኛል፡፡ አባረህ በለው እያሉ መፎከሩም ሆነ ኮረኔል ማራኪ እያሉ ስክስታ መውረዱ ሲበጅ አላየንም፡፡

በወያኔ በኩል የተደመጠው ግን ጥቂት ሻዕቢያ የላካቸው በሚል ንቀት ደምስሰናቸዋል የሚል ጉልበተኝነት ነው፡፡ ከህሊና የሚመነጭ ሳይሆን ከጡንጫ የሚወጣ ባሩድ ባሩድ የሚሸት አስተውሎት የጎደለው ከትናንት አለመማርን የሚያሳብቅ ቃል ነው የሰማነው፡፡

ደርግ ወያኔዎችን ተራ የመንደር ሽፍቶች እያለ ማናናቁም ሆነ ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ  ለማጥፋት  የመረጠው ወታደራዊ ዘመቻ  ውጤት እንዳላስገኘ፣ መድፍ መትረየሱም ሆነታንክ አውሮፕላኑ በስልጣን እንዳላዘለቀው አይተናል፡፡እፍኝ የማይሞሉ ከሚል ማጥላላትና አወደምናቸው ደመሰስናቸው ከሚል ፕሮፓጋንዳ ወጥቶ፡ ጥያቄያቸው ምንድን ነው? ጠመንጃ አንስቶ ዱር ቤቴ ለማለት ያበቃቸው ብሶት ምንድን ነው? ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅመው መንገድ የቱ ነው ወዘተ ለማለት  ፈቃደኝነትም አስተውሎትም ያልነበራቸው ሰዎች በመጨረሻ ሰአት ጉልበት ሲከዳቸው ለድርድር እጃቸውን ቢሰጡም የሚፈይድ አልሆነምና በእብሪታቸው ራሳቸውን ለስደት ለእስራትና ለሞት ሀገሪቱን ለውድቀት ዳረጓት፡፡

ጠመንጃ አንግበው ዱር ቤቴ ያሉ ወገኖቸን አላማ በወታደራዊ ኃይል ማጥፋት እንደማይቻል ወያኔዎች ከራሳቸው በተማሩ ነበር፡፡ ነገር ግን  በሥልጣን ጥማት ታውረው እንኳን ከትናንት ከዛሬም የማይማሩ በመሆናቸው ዱር ቤት ከማለት አልፈው ፊሽካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል ላሉ ወጎኖች የተለያየ ስም መስጠትና ጥቂቶች ናቸው ብሎ ማናንቅ፤ ደመስሰናቸዋል እያሉ መፎከር ገጠር ከተማ ሳይሉ ወጣቶችን የተለያየ ስም እየሰጡ ማሰርን ነው የተያያዙት፡፡

አሜሪካዊው ኤድመንድ በርክ የተናገሩት ተብሎ አንደሚጠቀሰሰው «መላው የሰው ልጅ ጥቅምና ደስታ ሁሉም መልካም ተግባር የተመሰረተው በፖለቲካ መቻቻልና አቅምን በማሸጋሸግ ድርጊት ነው»፡፡ስለሆነም  ዜጎችን ዱር ቤት ለማለት የሚያበቁ ምክንያቶችን በፖለቲካ መቻቻልና በብሄራዊ መግባባት ለማስቀረት መጣር ለራስም ለሀገርና ለህዝብም የሚጠቅም ውጤት ያስገኛል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ እኛም ዱር ውሎ ማደሩን፣ዝናር መታጠቅ ጠብ መንጃ ማንገብና ቃታ መሳቡን  እናውቅበታለን የሚል ደረጃ ከተደረሰ ደግሞ እያናናቁ፣ የተለያየ ስም እየሰጡና እየወነጀሉ ፕሮፓጋንዳ መስራት፣ወይም እንጨፍልቃቸዋልን እያሉ ጦር ማዝመት በሥልጣን ሊያሰነብት አለመቻሉን  ወያኔ ራሱ ከመጣበት ሂደት መረዳት በቻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ሲረገጡና ሲረግጡ አእምሮ እኩል ስለማያስብ ወያኔ ከደረግ ሽንፈት መማር አልቻለም፡፡

ወያኔን በፋኖነቱም ሆነ በመንግስትነቱ እንዳወቅነው ለሥልጣኑ ሲል ሀገር ቢፈርስ ሕዝብ ቢጨራረስ  ደንታ የሌለው መሆኑ እንጂ  ለሀገርና ለሕዝብ  የሚያሰብ ቢሆን  ጦርነቱ ከመባባሱ በፊት የሰላም በሮችን በመክፈት ነገሮች ሁሉ በውይይት በፖለቲካ መቻቻልና አቋምን በማሸጋሸግ ዴሞክራሲያዊ አግባብ መስመር እንዲይዙ ቢያደርግ ለራሱም ይበጀው ነበር፡፡

ጦርነት ከተባባሰና የሰው እልቂትና የሀገር ሀብት ውድመት ከነገሰ በኋላ ለማደራደርም ሆነ እጅ ለመጠምዘዝ ላይ ታች የሚሉ መንግሥታትና ተቋማትም የተጀመረው ጦርነት  የሁለቱንም ወገን አቅም ወደሚፈትሽበት  ደረጃ ከመደረሱ በፊት ዛሬ አሁን  ቢያስቡበት ነው የተሻለ የሚሆነው፡፡ ነገሮች በገፉና በተካረሩ ቁጥር ዱር ቤቴ ያለው ወገን አቅሙን እየፈተሸ ጉልበቱን እያጠነከረ በራስ መተማመኑን እያዳበረ ስለሚመጣ በአንጻሩ ስልጣን ላይ ያለው ሀይል የሚወስዳው የጥፋት ርምጃዎች ይቅር ወደማይባል ደረጃ ስለሚደርስ ለድርድር መቀመጥ ቢቻል አንኳን ተዋጊው ኃይል የሚያቀርባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የደደሩ ይሆናሉ፡፡

ጦርነት ሰው አይመርጥም የፖለተካ አሰላለፍ የብሄረሰብ ማንነት የሀይማኖት ምንነት ሳይለይ ሁሉንም ነው ተጠቂ የሚያደርገው፡፡ ጦርነቱ በሚካሄድበት አካባቢ እየኖሩ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ በመሆን መዳን ተቀዋሚ በመሆን ማመለጥ የዳር ተመልካች በመሆን መትረፍ አይኖርም፡ስለሆነም በተለይ የጦርነቱ መቀጠል ወይንም መቆም መፍትሄ በእጁ የሆነው ወያኔ አባላት  የደርግና ወያኔን ጦርነት አጀማመርና እድገት ሂደትና ውጤት ቆም ብላችሁ አስቡና ለራሳችሁ ስትሉ መሪዎቻችሁ ከእብሪት መንገድ ወጥተው ወደ ሰላም መንገድ እንዲያመሩ  ጠይቁ፡፡

እዚህ በሀገር ቤት በሞቀ ጎጆአችሁ እየኖራችሁ ሌሎችም አውሮፓና አሜሪካ እየተንደላቀቃችሁ፤እስረው ግደለው ደምስሰው ወዘተ የምትሉ የወያኔ ደጋፊ ነን ባዮችም ለሀገርና ለሕዝብ ደንታ ባይኖራችሁም አድራጎታችሁ እንደግፈዋለን ለምትሉት ወያኔ እንደማይጠቅም በግዜ ብትገነዘቡ መልካም ነው፡፡

ዛሬ ትናንት አይደለም፤ በሕዝብ ላይ እልቂት በሀገር ላይ ውድመት አድርሶ ተደብቆ መኖር ከህግ አምልጦ ማደር አይቻልም፡፡ ነገር ግን ወያኔ እስከ ዛሬ ያደረሰው ጥፋት ከበቂ በላይ ቢሆንም፤ጥፋቱ እያባነነው የሕዝብ ደም እያቃዠው ዛሬም በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመረ ነው፡፡ አስተሳሰባቸው እንደ ጋሪ ፈረስ የተቀየደ ደጋፊዎቹም ሆታና ጫጫታ የቁልቁለቱን መንገድ እያፈጠነለት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ ጠፍቶ እንዳያጠፋን ያሰጋል፡፡

ኢትዮጵያ በመላው አለም ተበትነው ለየሚኖሩበት ሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ እውቀትም ልምድም እድሜም የጠገቡ በረካታ አንቱ የተባሉ ልጆች አሏት፤እነዚህም ወገኖች በዚህ ወቅት የዳር ተመልካች ሊሆኑ አይገባም፡፡ ውድ ህይወታቸውን መስዋእት ለማድረግ በጦር ግንባር የተሰለፉ ልጆቿ ከሚያደርጉት የነጻነት ትል ጎን ለጎን ጥፋቱ ሳይበረታ ወያኔ ለድርድር አንዲንበረከክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት በግል፤ በጋራና በተደራጀ ሁኔታ የሚችለውን ቢያደርግ ነው መልካም የሚሆነው፡፡ ዛሬ ምንም አንዳልያዩና እንዳልሰሙ ሆነው አድፍጠው የሚያዩትንና ኋላ እልቂት ሲባባስ ተደራደሩ ማእቀብ እንጥላለን፤አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እናቀርባለን ወዘተ ለማለት የማይመለሱትን መንግሥታትና አለም አቀፍ ድርጅቶችም ማንቃት ማሳስብ ያስፈልጋል፡፡የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችም ከጭፍን ሆይ ሆያታ ወጥታችሁ የድርጅታችሁ መሪዎች  ለድርድር ፈቃደኛ እንዲሆኑ ማሳሰብ መጠየቅ ብሎም ማስገደድ ብትችሉ ለድርጅታችሁም ለመሪዎቻችሁም ለእናንተም ይጠቅማል፡፡ ለሰላም የሚደረግ ጥረት ውጤት የሚያስገኘው አቅም ከመፈተሹ በፊት ሲሆን ነው፡፡ለማይቀር ውድቀት አወዳደቅን ማሳመር ብልሀትም እውቀትም ነው፡፡


አርበኞች ግንቦት 7 በወልቃይትና አርማጭሆ መሬቶች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት በህዝቡና በህወሓት መካከል ሆኗል አለ

$
0
0

arebegnoch
የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንደዘገበው:

* ‪‎የተጀመረው‬ የነፃነት ትግል በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
* የህወሓት‬ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲፈፅመው የቆየው እስር፣ አፈና፣ ግድያ፣ ማንገላታት፣ ማሸበርና ማፈናቀል በነፍጥ የሚደረገው ትግል ከተጀመረ ወዲህ በእጅጉ ከፍቷል፡፡

ሁለገብ የትግል ስልት የሚከተለው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በጠብመንጃ ስልጣን ጨብጦ በመንግስትነት ስም የኢትዮጵያን ህዝብ አፍኖ እየገዛ እና አንጡራ ሀብቱን ከገደብ በላይ እየመዘበረ የሚገኘውን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለ ዘረኛ ቡድን ከመመካትም አልፎ በሚያመልከው ጠብመንጃ ደምስሶ በምትኩ ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረት ለማድረግ በበረሃ የጀመረው የትጥቅ ትግል በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል አንድ እግሩን በአስተማማኝ ሁኔታ ተክሏል፡፡
መላ ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በሸፈነ መልኩ በቅርቡ ለሚደረገው የህወሓትን ጎጠኛ ቡድን በኃይል ጠራርጎ ከአገራችን ምድር የማስወገድ ጦርነት የነፃነት ትሉ ብቸኛ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፍ እና በበላይነት እንዲመራው የሚያስችሉ ህወሃትን ህልውና በማሳጣት ግብአተ መሬቱን የሚያፋጥኑ ሰፊና ጥልቅ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

ሰኔ 25 2007 ዓ.ም በወልቃይት የተጀመረው ህወሓትን የማድማትና ከስሩ የመገዝገዙ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወደ አርማጭሆ ተስፋፍቶ ህዝባዊነትን በተላበሰ ሁኔታ የማውደም ስልቱን እየቀያየረ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን የሚታገልለት የኢትዮጵያ ህዝብም የትግሉ ባለቤትና መሪ ሊሆን የሚችልበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥራል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በወልቃይትና አርማጭሆ መሬቶች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት በህዝቡና በህወሓት መካከል ሆኗል፡፡ በአካባቢው ህወሓት ሲያደርሰው በቆየው ግፍና በደል ተማረው ከፋኝ ብለው ነፍጥ በማንሳት ጫካ ገብተው የሸፈቱት ገበሬዎች በአርበኞች ግንቦት 7 ጥላ ስር በአንድነት እየተሰባሰቡና በአንድ ዓላማ ተሳስረው የነፃነት ፍልሚያውን አጋግለውት ይገኛሉ፡፡ ህወሃት መራሹ የመከላከያ ሰራዊት በያቅጣጫው በሚደርስበት የደፈጣ እና ድንገተኛ ጥቃት መድረሻው ጠፍቶበት እየታመሰ ይገኛል፡፡ በሰራዊቱ መካከል እርስበርስ አለመተማመን እያየለ ከመምጣቱ በተጨማሪ ሽሽትና መክዳት የዕለት ከዕለት ተግባሩ ሆኗል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ ብልጭ ድርግም ሲል የቆየው የፀረ ህወሓት ትግል ንቅናቄ ችቦ ተለኩሶ መንቀልቀል በመጀመሩ ህዝቡ በየአካባቢው ያለማንም አነሳሽ በራሱ ውስጥ ለውስጥ እየተደራጀ ለአይቀሬውና የመጨረሻው ፍልሚያ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 በህወሓት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወዲህ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡ ከአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የእንቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጅጉ በመጨመሩ አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን የመቀበሉ ተግባር ከአቅሙ በላይ እየሆነበት መጥቷል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ መካከል እያደረገ ከሚገኘው ጦርነት ጎን ለጎን ከመተማ እስከ ጎጃም እንዲሁም አርባ ምንጭ ድረስ የድርጅቱን ህዝባዊ ዓላማና የትግል ጥሪ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን አሰራጭቷል፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለ24 ዓመታት ሲፈፅመው የቆየውን መጠነ ሰፊ ሽብር አሁንም በተለይም ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ በከፋ ሁኔታ አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ህወሓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ታማኝ የሚላቸውን ደህንነቶቹንና የታጠቁ ቡድኖቹን አሰማርቶ ህዝቡን በተለይም ደግሞ ወጣቶችን እያፈነ ወደ ስውር ማጎሪያው በመውሰድና ሰቆቃ በመፈፀም ተግባር ከመጠመዱ አልፎ ሌላ ጭምብል በማጥለቅ ህዝብ ጨፍጭፎ የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ስውር ሴራ መጠንሰሱን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ አጋልጧል፡፡

ከህወሓት የደህንነት ቢሮ ታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያረጋግጠው ህወሓት በጎንደርና አካባቢው በጦር አውሮፕላን ህዝብ በመጨፍጨፍ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በኤርትራ መንግስት የማላከክ ስውር ዕቅድ ነድፎ አሳቻ ሰዓት እስኪያገኝ እየተጠባበቀ አድብቶ ይገኛል፡፡

“ዝግጅቱ የህወሓት ፌስቲቫል እንጂ የኢትዮጵያዊያን አልነበረም”

$
0
0

AESAONE

ከካሳሁን ይልማ (የኢሳት ጋዜጠኛ)

የምትመለከቱት ፎቶ ከ30 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሲያከብሩት የነበረውን ዓመታዊ የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል ለማፍረስ የተመሠረተው የክፋፋዮች ቡድን ነው።
ይህ በጥቂት ገንዘብ አሳዳጅ ወረበሎች የሚመራ ቡድን ዓላማው እና ዒላማው የአላሙዲን ሚሊዮን ብር ስለሆነ የሚፈልገውን ቅርጫ እስካደረገ ድረስ “ሕዝብ እና አንድነቱ ሲዖል ይግባ” የሚል ነው።

ሌላው ተያይዞ ያለው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ ህወሓት ዲያስፖራው ውስጥ ሰረስሮ ገብቶ በሀገር ቤት የፈጠረውን የአፋና ና ቁጥጥር መረብ በውጭ ሀገርም የማንሰራፋት ስሌት ነበር።
ሆኖም ይህ በክፋት እና በሴራ የተመሠረተ ቡድን ከዋናው ፌዴሬሽን ተሰንጥቆ በመውጣት ለመሰንጠቅ ያደረገው ጥረት ግን ሊሳካ አልቻለም። ከዚያ ይልቅ ከፌዴሬሽኑ መርዝ ተነቀለለት ማለት ይቀላል።

ማህበረሰቡም ሴራውን በመገንዘቡ የተነቀለው መርዝ ላለፉት ሦስት ዓመታት ባዘጋጀው ተመሳሳይ ዝግጅት ላይ ለመታደም እግሩን አላነሳም። እባብ መኖሩን አውቆ ወዳለበት የሚሄድ የለምና።

በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተጨዋቾች በብዛት የጊዮርጊስ ተጨዋች የነበሩ፣ በተለይም ከአብነት እና አላሙዲ የክለቡ ባለቤትነት ዘመን ተጫውተው ያሳለፉ ናቸው። በቀጥታ ሲጠየቁ ይሉኝታ ይዟቸው እና ፈርተው ይሄዳሉ። ፈርዶባቸው!

ይሄ ቡድን ከሼኹ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀፍሎ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሁለት ዓመታት በግዙፍ ስታዲየም ዝግጅት አዘጋጅቶ ከፋፋዮች እና ጥቂት የህወሓት ደጋፊዎች በተገኙበት ወና ሆኖ በአሳፋሪ ሁኔታ ተጠናቋል።

ይህ ክሽፈቱን በመረዳት ዘንድሮ ወደ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር በመሄድ ከስታዲየም ወረድ ብሎ በትምህርት ቤት ሜዳሌላ ዕድሉን ሞክሯል። ወደ ዴንቨር ሲወሰድ ዋናው ቀመር በከተማዋ በረካታ የትግራይ ብሔር ተወላጆች በመኖራቸው ቢያንስ እነርሱ ገብተው በድኑን ቡድን ነፍስ ይዘሩበታል ተብሎ ነው።
አንድ በዝግጅቱ ላይ ከእንግዲህ በፍጹም እንደማይሄድ በምሬት የነገረኝ ተጨዋች “ዝግጅቱ የህወሓት ፌስቲቫል እንጂ የኢትዮጵያዊያን አልነበረም። እዛ በመሄዴ ለራሴ አፈርኩ” ብሎኛል።

ተሰንጥቀው የተነቀሉት መርዞች ቡድኑን ሲመሠርቱ መፍጠር የፈለጉት ይህንኑ ነበር፣ መከፋፈል። ለሆዳቸው እስካደሩ ድረስ የማህበረሰብ እና የእሴቱን ዋጋ የሚያሰላስል ህሊና የላቸውም። ተመሳሳይ ሴራዎች እና ሸፍጦች በቤተክርስትያን፣ በመስጊድ፣ በጓደኛሞች ማህበራት እና ፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ይፈጸማሉ። ከድርጊቶቹ ጀርባ ያለው አውራ አቀናባሪ ደግሞ ህወሓት ነው።

ስለዚህ ማህበርን፣ ማህበረሰብን፣ ብሔርን፣ ጎረቤትን፣ ቤተሰብን እና የራስን አዕምሮ በጥቃቅን ጥቅማ-ጥቅም የሚሸነሽነው የህወሓት ሥርዓት እንዲወድቅ ሁሉም ተቆርቋሪ ዜጋ የበኩሉን አስትዋጻዖ ማበርከት ግዴታው ነው።

ተግባር ትጥቁ ተግባር –ተግባር ስንቁ ተግባር –ተግባር ትንፋሹ –ተግባር ነው! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 19.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ / ምሳሌ 16 ቁጥር 9/

Birhanu nega photoየተግባር ግብ ተግባር ነው! ተግባር ስርክራኪ የለውም። የተግባር አሰር የለውም። ተግባር አቮል ነው። ተግባር በኽር ነው። ተግባር ዓይነታ ነው። ተግባር የነጠረ ንጡህና ፃድቅና ፀዲቅም ነው። ንጡህና ጻድቅ ደግሞ ልክስክስ የሆኑ ጉድፎች ክፍሉ አይደሉም – አይሆንም። ስለሆነም ተግባር፣ ተግባርን ጸንሶ ተግባርን ይገላገላል እንጂ ተግባር ክፋትን – ቂም በቀልን ጸንሶ ዬእንግዲህ ልጅን – አይገላገልም።

የተግባር ሩኹ ብሩኽ – ራዕይ ነው። ብሩኽ ራዕዩን ለማግኘት በሠርግና ምላሽ አለመሆኑን ጠንቅቆ – ይገነዘባል። ተግባር መከራን ለመቀበል፤ ፍዳን – ለመሸከም፤ አሳርን ለማስተናገድ የተዘጋጀን ጀግና – ይደግፋል፤ ይመራል – ያስተዳድራል። የተግባር ድፍረቱ የሚመነጨው ከተነሳበት እውነተኛ ህዝባዊ ዓላማና ካስገኘው ውጤት – ይነሳል። አመሻሽ ላይ ተነስቶ እንቅልፍ እንቅልፍ ይለው የነበረውን እንጉልች አውሎ ቁጭ በል ያሰኘው እርምጃ እንሆ — ተግባርን ስንቅና ትጥቅ ያደረገው ትንፋሽ አስቀድሞ፤ በተግባር አዝማችነት ተስፋን ለማማፋፋት ከተግባር ተነስቶ – ተግባር ላይ ሰከነ። ተመስገን!

አዎን! የተግባር መነሻው ተግባር ነው። የተግባር መድረሻው ተግባር ነው። ተግባር ሁልጊዜም አሸናፊ ነው። ተግባር ሁልጊዜም ድል ላይ ነው። ተግባር እንኳንስ እሱ ሊሸነፍ ተሸናፊዎችን ሳይቀር በነጠረ ጭብጥ በመሆኑ – ነፃ ያወጣቸዋል። የተግባር መሳሪያው ተግባር ብቻ ነው። የተግባር ጠበቃው ተግባር ብቻ ነው። የተግባር መከላከያው ተግባር ብቻ ነው። ዳኛው ተግባር መከረኛውን አሁንም በተግባሩ – ይክሰዋል። በጥርስ የተያዘው ሌት ተቀን የሚከተከተውን፣ ደመ -መራሩን – መከራውን እንደ ጌጥ ቆጥሮ ቀልጦ ሻማ እንዲሆን – ይረዳዋል። የተግባር ታቦቱ  -ድርጊተኛው ነው። የተግባር ሽልማቱ የተሰጠው መክሊቱ ነው።

አሁንስ? እኮ አሁንስ? ምን ይባል ይሆን። ክርችም ዝግት ይሆን – ይሆን? ፀጥ ረጭ ይሆን? ወና ይሆን ዕጣ ፈንታው የአታሞው፤ ወይንስ ደግሞ ያው እንደተለመደው የለወጥ ንፋስን እንዘውር ተብሎ አካኪ ዘራፍ ይባል ይሆን?  ዬዕንባ ወታደር አይተኛም – አያንቀላፋም። ይልቁንም ዕንባን የረገጠውን በተግባር አብነት በማስተማር፤ በማደራጀት ቀንዲልነቱን በተግባሩ  – ያረጋግጣል።

ተስፋ ተግባር ነው ወታደሩ፤ ለተስፋ ድርጊት ነው – መጽናኛው፤ ለተስፋ መሆን – ሁነኛው። እነሆ ሁነ። እነሆ ተስፋ አዎ ሆነተስፋ ነው ሆነ። ተስፋ በድርና ማግ ራዕይን ዕውን ለማድረግ የበዛውን መከራ ለመቀበል  – እውነትን ፈቀደ። ተመስገን!

ይህ ታሪካዊ ጉዞ ይህ አደራን የተቀበለ ጉዞ ዛሬን ለማሳደር ነገን አብቅሎ ያሰብል ዘንድ ትውልዳዊ ኃላፊነትን ወዶ በመቀበል የግዙፉ ትውፊት ተልዕኮ አስኳል ነው። ሞትን ፈቅዶ – ለተቀበለ፤ ሞትን ወዶ –  ላከበረ፤ ሞትን ናልኝ ብሎ ለመገናኘት ለገሰሰ ወገን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን፤ እንዲሁም መስኪዶቻችን ማናቸውም ቤተ አምልኮች ሁሉ በዚህ ነፍሰጡር ሴቶች ተረግጠው ጽንስ ሞት በተፈረደበት ዘመን ያሉ ሁሉ ይህን ጊዜ የሱባኤ ወቅት በማድረግ ማህበረ ምዕመኑን ወደ አንድ የጸሎት አቅጣጫ በመምራት ሰፊ የሆነ የተደራጀ የጸሎት ተግባር በግልና በጋራ እንዲከወንብት በማደረጉ በኩል ሰፊውን ድርሻ በመውሰድ በይፋ ዕወጃ ከጎን መሰለፍ ያለባቸው – ይመስለኛል። አባቶቻችን ለድል የበቁት ባለ ሀገር፣ ባለ ሰንድቅ ዓላማ፣ ባለ ማንነት፤ በለ ዕምነት እንድንሆን ያደረጉን በዚህ መንገድ – ነው።

„በቃኝ“ እንዲህ ነው። „በቃኝ“ ለቁርጥ ቀን „የቁርጥ ልጅ ነው“ የአሻም ምላሹ „የአሻም ጉልላት“ ነው። የቁጭ በሉ ዳንኪራ አሁን አድራሻውን መፈለግ አለበት። የሚያዘናጉ ሆነ ትጥቅን የሚያስፈቱ ዘመቻዎች ሁሉ እዩኝ እዩኝ እንዳሉ ሁሉ ደብቁኝ ደብቁኝ ማለት – አለባቸው። አጀንዳቸው እነሆ እንዲህ – አከተም። ሊቀጠል፣ ሊሰፋ ወይንም ሊጣፍ የማይችል አጀንዳ ግብዕቱን የሚፈጸመው እንዲህ በተግባር አሸናፊነት ነው። አዎን ተግባር ሻንፕዮን ነው። የተግባር መዳሊያው መሆን ብቻ ነው። ሆኖ መገኘት!

ያመነ – የተቀበለ – የቆረጠ – ለድል ይበቃል። ድሉ የዕንባ ነው። ድሉ የህዝብ ነው፤ ድሉ የነገ ነው። ድሉ የትውልድ ነው። ድሉ የተስፋ ነው። ድሉ – ለተገፉት ነው። ድሉ ለመከረኞች ነው። ድሉ የኢትዮጵያ ነው። እርግጥ ነው ድሉ ለቀለጤዎችና ለድሎተኞች ግን አይሆንም፤ እንዲያውም ዛሬ ትቅማጥ በትቅማጥ እንደሚሆኑ – አስባለሁ።

ቅድስት እናቴ እመቤቴ፤  የሰማይና የምድር ንግሥት፤ የሰማይና የምድር እምቤት፤ የሰማይና የምድር ልዕለት እናት ናትና፤ ሩህሩህ ናትና፤ ስደቱንም ታውቀዋለችና መክሊትን ጠብቂ። ጥላ ከላላ ትሁናችሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የዕለቱ ዕርእሰ አንቀጽ ምንጭ – http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45166

 

አርበኞቻችን መርሆቻችን – አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

ቅዱስ ጊዮርጊስ አደራህን – ተጋድሎውን ባርክ!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ እንደገባው ሁሉ በቅርቡ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ይገባል!!!

$
0
0

ሳሙኤል አሊ ከኖርዌይ

የወያኔወች የውስጥ ጅማታቸው መፈታት ከጀመረ ሰነባብቷል። የሚይዙትና የሚጨብጡትን ካጡ ትንሽ ቆየት ብለዋል በወያኔ ሃሳብ በዘር ፖለቲካ እየጠላለፈ ምስራቁን ከምዕራብ፤ ደቡብን ከሰሜን፤ እያነሳሱ  የራሳቸውን ወታደሮች አጠናክረው ሰለ አገሩ ቀና አሳቢውን ወይም መብቴን እጠይቃለው የሚለውን እየገደሉ አገሩን በሙሉ በራሳቸው ቁጥጥር ስር አድርገው መቶ አመት እንገዛለን በሚል እቅድ ተነሳስተው ኢትዮጵያዊኑ እርስ በእርስ እንዲጠላላና እንደጠላት እንዲተያዩ እያደረጉት ነው ።  በከፍተኛነት የባንዳነትን ስራ እየሰሩ እራሳቸውን በሁሉም እረገድ የበላይ አድርገው ሌላውን ዜጋ እንደሁለተኛ  ወይም እንደ ባርያ ለመግዛት ቀን ከለሊት እየሰሩ ያሉት የወያኔ  ቡድን የደም ዝውውራቸው የሚቋረጥበት የልቦና ተንኮላቸው የሚኮላሽበት የዘር መረባቸው የሚበጣጠስበት ትግል ተጀምራል። ያርበኞች ግንቦት ሰባት የነጻነት ጥሪ ወደ ትጥቅ ትግል መግባት ሲያስጨንቀው ከርሞ  ዛሬ ጭቆናው ይብቃ ያለው  ሕዝቤ  የባርነት ኑሮን  አልቀበልም ያለው ኢትዮጵያዊ በግፈኛው ወያኔ ላይ መሳርያውን አንስቶ ወደ ግንባር በመትመም  ጀግንነቱን እያሳየ ይገኛል። አርበኞች ግንቦት ሰባት በይፋ ጦርነቱን መጀመሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በጉጉት የሚጠብቀው የነበረ ቢሆንም ወያኔወች ደግሞ  በጽኑ የሚፈሩት ጉዳይ ነበር። እንግዲህ የማይቀርላቸውን የጥፋት ዘመናቸውን ማቅረቢያውም በአርበኞች ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ የነጻነት ጥሪ በይፋ ተነግሮ ወያኔወችን በቆፈሩት ጉድጋድ በያሉበት ሊቀብር ተነስታል።

Birhanu Nega Bonger G7የግቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በሕዝብ ለማስጠላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ  ያልማሱትም ጉድጓድ የለም። ስሚ አጡ እንጂ በአንዳንድ በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያን ላይ ትንሽ ጉንጉምታ የሚፈጥር አዝማምያ  የነበረ ቢመስልም ዛሬ ግን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ያንን ጉምጉምታ አጥፍተውታል። በርገር እየበሉ ጦርነት የለም፧ አሜሪካና አውሮፓ ቁጭ በለው አገር ቤት ያለውን ሕዝብ  ማስጨረስ የለም ፧ የሚለውን የወያኔ የማደናገርያ  የሃሰት ቅስቀሳ  የአርበኞች ግንቦት ሰባት  ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከአውሮፓና ከአሜሪካ  ወደበርሃ  በመውረድ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ጦር መቀላቀላቸው ለሁሉም  ግልጽ ያደረገና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወያኔ የተባለውን ጭራቅ ለማጥፋት ቆርጦ  የተነሳ መሆኑን ያስገነዝበናል።  በኢትዮጵያ  አገራችን ሊደራደሩ ፍቃደኛ የማይሆኑ አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ዶክተር ብርሃኑ ወደ ወረደው በርሃ  ወርዶ ወያኔን ዶግ አመድ  አድርጎ  ነጻነቱን እንደሚያውጅ የታወቀ ነው። ለዚህም ነው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ  አመራሮች  እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ነጻነት በመታገል መስዋትነትን የከፈሉት።  ዛሬ እነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ በርሃ  ገብተው መሰራት ያለበትን ስራ  እየሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ የብርሃኑን ጮራ የሚያይበትን ለወያኔ ደግሞ  ከኢትዮጵያ ምድር የሚጠፋበትን መንገድ ቀይሰው  በርሃ በመውረድ ታላቋን አገር ከጥፋት ለመታደግ መሰዋትነት እየከፈሉ ያሉት።

ዛሬ ወያኔና የወያኔ አጫፋሪ ሁሉ ዶክተር ብርሃኑ ኤርትራ በርሃ ገባ ብለው ሲያሽማጥጡ የነበሩ ሁሉ ነገ አዲስ አበባ  ቤተመንግስት ገብቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ሲያደርግ ታዪታላቹ ፧ የነጻነት መዝሙር የሰላም ባንዲራውን ይዞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በህብረት ሲያዘምር ታዪታላቹ። እመኑኝ ደርግ እንደወደቀው ወያኔም ይወድቃል፦ እንዳለው ሃብታሙ አያሌው; ዛሬም እመኑኝ ነገ ወያኔወች የዘረፋትን ሳይበሏት  ጎሮሮአቸው ላይ እንዳደረጉት  የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮአቸው ላይ ይቆማል፧ እመኑኝ ኢትዮጵያን አጠፋለው ብሎ  የተነሳው ወያኔ  የኢትዮጵያ ሕዝብ  ያጠፋዋል፧ እመኑኝ ነጻነቱን ነፍገን፤ ጨቁነንና፤ እረግጠን፤ የበላይ ሆነን እኖራለን የሚለውን ወያኔ በሕዝባችን የጠነከረ ብትር ቀምሶ ከኢትዮጵያ  ምድር ይጠፋል፧  ይህ ቀን እሩቅ አይደለም ሁላችንም አርበኞች ግንቦት ሰባትን በመቀላቀል በመደገፍ ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር መውጫና  መግቢያ  አሳጥተን የምናጠፋበት ጊዜ  ቅርብ ነው።

ወያኔወች የማወናበጂያ  ዘዲያቸው በሙሉ ከሽፎባቸዋል  የወያኔን ክፋት ሁሉም ኢትዮጵያዊ አውቆታል አሁን ወያኔ የማጥፋቱን ስራ ብቻ ሳይሆን አገርንም የማዳኑ ስራ እየተሰራ ነውና፦  ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩን ከጥፋት ለመታደግ ባአገር በነጻነት ለመኖር ለኢትዮጵያ አገርህ ስትል ተነሳ ድላችን በአገራችን ፤ መኖርያችን በአገራችን፤ መደሰታችን በአገራችን፤ ሆኖ ስደትና ችግር እንዲቆም ዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች የወያኔ  የክፋት መረብ ከአርበኞች ጎን በመሰለፍ የድላችንን ዜና አብረን እናብስር።

ድል ለኢትዮጵያ  ሕዝብ

ሳሙኤል አሊ ከኖርዌይ

Email samilost89@yahoo.com

20.7.2015

የእርዳታ ጥሪ…!

$
0
0

unnamedኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የዓረና-መድርክ ኣባል ምርጫ 2007 ዓ/ም ተከትሎ በ 3 ሰዎች በሑመራ ማይካድራ ቀበሌ መገደላቸው ይታወቃል።

ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የሁለት ህፃናት ኣባት ሲሆኑ የ70 ዓመት ሽማግሌ ወላጅ እናታቸውም ጡዋሪ ነበሩ።

ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ሲገደሉ ወይዘሮ ኣኸዛ ፃዲቅ የ70 ሽማግሌ፣ ህፃን ሚኪኤለ ኣብራሃ የ 15 ዓመት ልጅና ሚልዮን ታደሰ የ 7 ዓመት ህፃን ያለ ጧሪና ያለ ኣሳዳጊ ቀርተዋል።

ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በኣገራቸው በሰለማዊ መንገድ ሲታገሉ የተሰዉ ጀግና ከመሆናቸውና እነዚህ ህፃናት ልጆቻቸው ወደ ጎዳና ተበትነው ለኣደጋ ሳይጋለጡ ሁላችን ኢትዮዽያውያን የተቻላችን ድጋፍ እንድናደርግላቸው ዜግነታዊ ሃላፍነታችን እንድንወጣ ግድ ይለናል።

ስለዚህ የምንችለው ድጋፍ በኣያታቸውና ሞግዚታቸው ወይዘሮ ኣኸዛ ፃድቅ ገብረሚካኤል የተከፈተላቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥር Z57508001815 የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ሒዋነ ቅርንጫፍ እንድታስገቡላቸው በት ህትና እንጠየቃለን።

ሃምሳ ሎሚ ለኣንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጣእሙ ነውና እጃችን እንዘርጋላቸው።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>