ፍቱን መጽሔት ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም)
የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል…
ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመንት ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራ ይናቃል…
… ወይም ….
ዘመንህ ሲፈቀድ ካሳ (ዩሐንስ) ትሆናለህ፡፡ ወደ መብት ድንበርህ ትገሰግሳለህ፡፡ አንገትህን ለክብርህ ትሰጣለህ፡፡ ከማንቁርትህ በታች ትመለሳለህ፡፡ ከአገጭህ በላይ ጠላት እጅ ትወድቃለህ …. የራስህ ‹‹መተማ-ዩሐንስ››ትመሰርታለህ… ጠላት የማይሻረው የደም ድንበር ትሆናለህ…
… ወይም …
ዘመንህ ግድ ሲል ካሳ (ቴዎድሮስ) ትሆናለህ፡፡ መቅደላ ላይ ትቆማለህ፡፡ እስህ ትጮሃለህ፣ መድፍህን ታጮሃለህ፣ ጥይትህን ትጠጣለህ፡፡ አሸናፊህን ተሸናፊ ታደርጋለህ፣ አማራኪህን ትማርካለህ…
…የዚህ ዘመን ‹‹ካሳነት›› ምንድን ነው …. ከዲማው ጉዱ ካሳ፣ ከመተማው ዩሐንስ ካሳ፣ ከመቅማላው ቴዎድሮስ ካሳ… የማይገጥመው፣ ዘመን የፈቀደው ካሳነት የቱ ነው ….
… እያልኩ አስባለሁ …
ጉብኝት ጉዞው ወደ ቂሊንጦ ነው፡፡ መኪናዋ ትርገፈገፋለች፡፡ መንገድ ሳይዘጋጋ አዲስ አበባን ለመልቀቅ ትነጫነጫለች፡፡ ጎተራን፣ ንፍስ ስልክን፣ ሳሪስን… እየጠቀለለች ትጎርሳለች፡፡ ቃሊቲ ስትደርስ፣ ሰበታን ወደ ቀኝ ትታ፣ በአሮጌው ድልድይ ስር አፍንጫዋን ወደ ምስራቅ ቀሰረች፡፡ ቃሊቲ ስትደርስ፣ ሰበታን ወደ ቀኝ ትታ፣ በአሮጌው ድልድይ ስር አፍንጫዋን ወደ ምስራቅ ቀሰረች፡፡ እዚያ ቂሊንጦ አለች፡፡ እውስጧ አንድ ‹‹ አዲስ እንግዳ›› ይዛለች….
… የቂሊንጦ አዲሱ እንግዳ ተመስገን ደሳለኝ ነው፡፡ ጥቅምት ሶስት‹‹ ጥፋተኛ›› ተብሏ፣ ጥቅምት አስራ ሰባት ፍርድ ይቀበላል፡፡ እስከዚያ እዚህ ይቆያል፡፡ እሱን ለሚያውቁ ቅር ቢያሰኝም ለእርሱ ግን ለውጥ አያመጣም፡፡ ከእነርሱ በላይ እርሱ ተዘጋጅቷ፡፡ እንግዳው ማነው እነርሱ ወይስ እሱ …. እንድል አድርጓል ተዘጋጅቷል፡፡
ሁለት ልጆች አሉት የሚያሳድጋቸው ከስጋ አብራክ በላይ በተስፋ አብራ ያወዳቸው ብርሃን የሆናቸው ከረሃብ ወደ ጥጋብ ያመጣቸው፡፡ ሚኪ እና ማሪያሟ፡፡
‹‹እንዲያ ብሆን እንዲህ ይደረግላቸው›› የሚልላቸው፡፡ ከእርሱ እንዲያ መሆን በላይ የእነርሱ ‹‹እንዲህ›› መሆን ሐሳብ ላይ ይጥለዋል፡፡ ደጋግሞ አደራ ይላል፡፡ እንዳንድ ጊዜ እንዲህ ነው፤ ፍትህ እየተባለ የሚቆላመጠው ‹‹ፍርድ›› ዱላነቱ ምንም ለማያውቁ ንጹሃን ጭምር ነው፡፡ ስጋ ሳይሆን ፍቅር የተጠለሉት ሚኪ እና ማሪያሟ ‹‹የዱላው›› ተጋሪዎች ናቸው፡፡ ያለጥጥ ተመቺዎች ናቸው፤ ከመጣል ያነሳቸው እጅ ሲታሰር ወደመጣል መመለስ አፋን ከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡ ያሞት የሚያስመርጥ ህይወት …
… የመጀመሪ ቀን ያየኃቸው ፍትህ ጋዜጣ የነበረበት ግቢ ውስጥ ነው፡፡ ሁለት አመት ያልደፈኑ መንታዎች፡፡ ወንዱ በአካል ትልቅ ይመስላል፤ ሴቷ በአስተሳሰብ ብኩርና ይዛለች፡፡ የራስ መኮንን ወንዝ ንጭንጭ ግቢው ላይ የተንጠረበበ ድብርት ፈጥሯል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ አከራይዋ የልጆቹ አባት ላይ ይነጨነጫሉ፡፡ የሚላስ የሚቀመስ ካሳ ሆድ በላይ የግቢዋ ባለቤት ቁርጠት ሆነዋል፡፡
‹‹ምንድነው›› አለ ተሜ፡፡
‹‹ወር በመጣ ቁጥር በቤት ኪራይ ክፈል አትከፈል ንትርክ፤ ሰለቸኝ ቤቴን ይልቀቅልን፡፡›› አሉ፡፡
ያኔ ፍትህ ጋዜጣ እንኳን ሌላ ዕዳ ልትጨምር እራሷንም አልቻለችም ነበር፡፡ ተሜ ዝም ብሎ የልጆቹን አባት ተመለከተው ፡፡ የልጆቹ አባት የህሊና ጸሎት አድራሻ መስሎ ከመሸማቀቅ ጋር ቆሟል፡፡ ልጆቹ የተነፋፈቀ ፊታቸውን እንደያዙ እግሩ ስር ተኮልኩለዋል፡፡
‹‹ስንት ነው እኔ እከፍላለሁ አለ፡፡ ከዚያች ቀን በኃላ ልጆቹ ‹‹ የፍትህ ጋዜጣ›› ቤተኛ ሆነ፡፡ እነዚህን ልጆች አሁን በቅርብ አይቻቸዋለሁ፡፡ ከትምህርት ቤታቸው አውጥቷው ካፊጤሪያ እያጋበዛቸው ነበር፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ እነሱ አይመስሉም፤፤ የቀረበላቸውን ከ ክ እና ጭማቂ ንቀው ለጨዋታ አድልተደው ነበር፡፡ ተሜ ላይ ነገር ባንዣበበ ቁጥ ነጭናጫው የራስ ሞንን ወንዝና ንዝናዛዋ አከራይ የልጆቹ አዙሪታም ጭጣ ፈንታ ሆነው ይታዩኛል፡፡ ያ ሞት የሚያስመርጥ ህይወት …
… ቂሊቂንጦ ሶስት ሜትር ከፍታ ያለው ግንብ የታጠቀ ጸጥታ ነው፡፡ ከግዝፈቱ ጋር የማይነጻጸር ሽንቁር በር አለው፡ ግንቡን ተገን ያደረገው የጠያቂዎች ማረፊያ የአጠና ድርድር ነው፡፡ በተቀማጮች ሟልጯል፡፡ የአጥሩ አናት ላይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂ ተለጥፏ፡፡ ወደ ማረሚያ ቤቱ የማይገቡ ነገሮ ዝርዝር ነው፡፡ ከሞባይልና ከታሸጉ ምግቦች ጋር ስለት ነገር እንደማይገባ ተገልጻል – ገረመኝ፡፡ ስለት ይዤ ልግባ የሚል ይኖር ይሆን ባህል ካልሆነ በስተቀር፤ መቼም የዘንድሮ ባህል ቅጥ አጥቷል፡፡
… ቂሊንጦ ለጥ ያለ ሜዳ ነው፡፡ ጉትያ የመሳሰሉ ዕጽዋት ሞልተውታል፡፡ በርቀት አዳዲስ ሰፋሪዎች አዳዲስ ሰቀላ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ከመንገድ ወዲያ ማዶ አንድ የኮንዶሚኒየም ሳይት አለ፡፡ ጥቂት ከፍ ብሎ ደግቦ ‹‹ሔኒክን›› ያስገነባው አዲስ ቢራ ፋብሪካ ተገሽሯል፡፡
ለሶስት ሰዓት አስ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ደርበብ ያለች የፌደራ ፖሊስ አባ መዝገብ ይዛ ብቅ አለች፡፡ የፖሊስ ደርባባ ግንጥል ጌጥነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በመደዳ መታወቂያ እያየቸች የተጠያቂውን ስም ትመዘግብ ጀመር፡፡ እኛም ተመዝግበን ለመግባ ስንጠባበቅ ሌላ አጣሪ ፖሊስ መጥቶ ዳግም መታወቂያ ይመረምር ጀምር፡፡ ላለማስገባት ሰበብ ያሚፈልግ ይመስላል፡፡
‹‹ይሄ መታወቂያ አይሆንም››
‹‹ለምን››
‹‹የግል ድርት እዚያው ለድርጅቱ ነው››
‹‹ምን ማለት ይሆን››
‹‹ለምን››
‹‹አልታደም››
ያም ሆነ ይህ አኔ ከማይገቡት ወገን ተመደብኩ፡፡ ይሁን! መጠየቅ የመንፈስ ጉዳይ ነው፡፡ ከግንብ ወዲያ እና ከግብ ወዲህ በሚል ድንበር አያበጅም ስሜ ገብቷል፤ መልጭክት ይደርሰዋል፡፡ እነሆ አለማየሁ የመጠየቅ ተልዖኮውን ዘጠና ከመቶ ተወጥቷል፤ አስር ከመቶ ሲቀረው ተሰረናክሏል ይሉታል፡፡ ተሜን አውቀዋለሁ ፈገግ ይላል፤ ይቀልዳል፡፡ ሊጠይቅ፤ የሄደን ያዝናናል ያጽናናል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ልንዝናና፤ ልንጽናናና ልንጠይቅ የሚገባ እኛ ነን፡፡ እሱማ…፡፡
↧
መክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት (በዓለማየሁ ገላጋይ) –ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
↧