የትብብር ምሥረታን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ
እኛ 1ኛ/ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ 2ኛ/ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/መኢዴፓ/ 3ኛ/ የመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅት/መዐህድ/ 4ኛ/ ሰማያዊ ፓርቲ/ሰማያዊ/ 5ኛ/ የሶዶ ጎርደና ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ ሶጎህዲድ/ 6ኛ/ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ/ኢብአፓ/ 7ኛ/ የኦሞ ህዝቦች...
View Articleመልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ለእስር ይወጣል›› ‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ›› ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን...
View Articleየግንቦት 7 ወቅታዊ ጽሑፍ –“ባነሰ ወጪ ድልን መቀዳጃ አመቺ ጊዜ ላይ ነን – እንጠቀምበት”
በአለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንም የማይገናኙ እና የተመሰቃቀሉ የሚመስሉ፤ በጥልቀት ላያቸው ግን የተያያዙና የተደጋገፉ ከመሆናቸው አልፎ እንደከዋክብት ፈለግ አቅጣጫን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶች ተስተውለዋል። የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ሳንጠብቅ አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ። በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘነበው...
View Articleለ‹‹ዜሮ ድምር››ም ያልበቃው የኢትዮጵያ ፖለቲካ
ጌታቸው ሺፈራው በአገራችን ከ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እስከ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ››፣ ከ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› እስከ ‹‹ሽብርተኝነት››፣ ከ‹‹መሃል መንገድ›› እስከ የ‹‹ጽንፍ ፖለቲካ››፣ ከ‹‹ዘረኝነት›› እስከ ‹‹ወያኔነት››፣ ከ‹‹ብሄር›› እስከ ‹‹ጎሳ›› ያልተተረጎሙ ነገር ግን ማንም እያነሳ የሚጥላቸው፣...
View Article[የማለዳ ወግ] –ከሊባኖስ እስከ ሳውዲ፣ ሌላ የደም እንባ እንዳናነባ! * የተዘጋው የአረብ ሀገር ጉዞ ይጀመር ይሆን?
እለተ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2007 ይላል የቀን መቁጠሪያው ። በጠዋቱ ተነስቸ መብተክተክ ይዣለሁ ፣ መነሻየ ከሳምንት በፊት በሃገረ ሊባኖስ መዲና ቤሩት ስሟን ለደህነንነት ስል የማልገልጻት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ ባለችበት ሁኔታ በነፍሰ ገዳይነት ውንጀላ መክሻሸፍ አስመልክቶ አዳዲስ...
View Articleበአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም –ሞረሽ ወገኔ የባህል...
(24/10/2014) ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን...
View Article“አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ (ሥርጉተ ሥላሴ )
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 51 ቁጥር 9) ከሥርጉተ ሥላሴ 24.10.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ) “እርግብ በር” 7ኛው አዲሱ መጸሐፌ ነው። የትውልዱ ነገር ከልጅነቴ ጀምሮ ይጨንቀኛል። በተለይ ወላጆቻቸው ተለያይተው ስለሚያድጉ ልጆች፤ ከጋብቻ ውጪ ስለሚወለዱ ልጆች በእጅጉ አስባለሁ። አንድ ሰው ልጅ መውለድ ያለበት በተለይ...
View Articleበአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም – ሞረሽ ወገኔ የባህል...
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ክህደት...
View Articleዘውደ ወይ ጎፈረ ብሎ መመዳደብም መፍትሄ ነው።
ዳዊት ዳባ Sunday, October 19, 2014 dawitdaba@yahoo.com “ይምርጡን ሳናዳላ፤ ሳንገል፤ ሳናስር፤ሳንዋሽና ሳንሰርቅ ፍፁም በሆነ አገራዊ ፍቅር አክብረንህ እናስተዳድራለን ”። የምርጫ መሪ ቃል ብትሆን ያልኳት። ጎሽ እንዲህ ነው መቅደም። አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዘጠኝ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል...
View Articleበአገር ላይ የሚመጣ አደጋን አቅልሎ የማየት ያልሰለጠነ አስተሳሰብ
(ኤፍሬም እሸቴ) ታዳጊ አገሮችን በሙሉ የሚያመሳስላቸው አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ከገደል አፋፍ ቆሞ ገደሉን መናቅ፣ ከአደጋ ጫፍ ቆሞ አደጋን ማቃለል፤ ከዚያም ከገደሉ ወድቆ መሰበር፣ በአደጋው ተጠራርጎ መወሰድ። ይህ ሐሳብ በርግጥ ፍንትው ብሎ የታየኝ የማሌዢያ አውሮፕላን በዩክሬይን ሰማይ ላይ በሚሳኤል በጋየበት ጊዜ...
View Articleመክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት (በዓለማየሁ ገላጋይ) –ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ፍቱን መጽሔት ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም) የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል… ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመንት ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል...
View Article‹‹የነ እንትና ታቦት›› :ዳንኤል ክብረት
ዳንኤል ክብረት ዓርብ ዕለት የተከበረውን የአቡነ አረጋዊ በዓል ለማክበር አውስትራልያ አደላይድ ነበርኩ፡፡ እዚያ ከተማ የሚገኝ አንድ የድሮ ወዳጄ በፌስ ቡክ አገኘኝና አደላይድ መሆኔን ነገርኩት፡፡ ‹‹የት እንገናኝ›› ሲለኝ ‹‹ነገ (ቅዳሜ) የአቡነ አረጋዊን በዓል ለማክበር ስለምሄድ እዚያ እንገናኝ›› አልኩት፡፡...
View Articleየ “ካዛንችሱ መንግስት በአዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት” –ከግርማ ሰይፉ ማሩ
ዛሬ ጥቅምት 17/ 2007 እግር ጥሎኝ አዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት ጎራ ብዬ ነበር፡፡ የታዘብኩት ነገር ያስታወኝ ኤርሚያስ ለገስ “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ባወጣው መፅሃፍ ውስጥ “የካዛንችስ መንግሰት” ብሎ ያስነበበንን በገሃድ ከካዛንችስ ቦታ ቀይሮ አዲስ አበባ መስተዳደር ግቢ ውስጥ መኖሩን ነው፡፡ የካዛንችሱ መንግሰት...
View Articleየማለዳ ወግ…. የተመስገን ደሳለኝ እናት…
የማለዳ ወግ … ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ ! ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና...
View Articleልማት ካለ ነፃነትና ፍትሕ ፋይዳ የለውም –ክፍል ሁለት
ከ ይኩኖ መስፍን ቦስተን ሰሜን አሜሪካ መልካም አስተዳደርና የፓለቲካ ምሕዳር የሞያ ነፃነት በተገደበባት” ነፃ የፍትሕ” የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት በሌሉበት! የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት በጠፋበት” በጋብቻና በዝምድና የተሳሰረ አንድ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ የሀገሪትዋን ሁለንትናዊ ሰብኣዊ ማተሪያላዊና አእምራዊ ሀብት...
View Articleዕንባና ጸሎት ያሳደጉት ልጅ (ልቦለድ) – (ከኤፍሬም እሸቴ)
(ደራሲው ኤፍሬም እሸቴ) ይህንን አጭር ልቦለድ ከማንበባችሁ በፊት በቪዲዮ የተቀናበረውን የተመስገን ደሳለኝን ወንድም የታሪኩ ደሳለኝን ጽሑፍ እንታዳምጡ ልጋብዛችሁ። በቪዲዮው ላይ የቀረበው የታሪኩ ጽሑፍ እውነተኛ ታሪክ ሲሆን የእኔይቱ መጣጥፍ ግን ልቦለድ መሆኗን እንድትረዱ በማስጠንቀቅ ወደ ንባቡ ልምራችሁ። (ቪዲዮው...
View Articleጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የእስር ቅጣቱን በመቃወም ይግባኝ ሊጠየቅ ነው
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳትና ሀሰተኛ መረጃን በመስጠት በሚል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት የ3 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ጠበቃው አቶ አመሀ መኮንን አስታወቁ። ጠበቃው አክለውም፤ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ሕጉ እስከፈቀደው...
View Articleአይቴ ብሔሩ ለኦሮሞ፤ የኦሮሞ አገሩ እንግዲህስ የት ነው?
(ከኤፍሬም እሸቴ) ገና ሃይ ስኩል ተማሪ ነኝ። የትምህርት ጥማቴ ገና ያልወጣልኝ። ተስፋዬን በደብተሬ ቅጠሎች መካከል አቅፌ የምዞር። ሰው ለመሆን የምማር። ተስፋዬን ከመናገሻ ተራራ ጀርባ የተሰቀሉ ይመስለኝ ነበር። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ፣ ከተራራው ገመገም ጀርባ የምትወጣው ፀሐይ ተስፋዬ በካዝና ከተቀመጠበት አገር...
View Articleቢራቢሮ … (ከሥርጉተ ሥላሴ)
ከሥርጉተ ሥላሴ 31.10.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ) ነይ እሰኪ ዘንድሮ አለፈልግም ከርሞ የለኝም አርምሞ ሁለመናዬ አሮ በበቀል ተነክሮ ቀለም የለሽ ኑሮ፣ መስቃ ተዘርዝሮ መብቴ ተዘሮ...
View Articleየህገ ወጡ መጅሊስ አባላት እና ሲቪል ፖሊሶች ባዩሽ መስጂድን ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው ታወቀ!
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፦ የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት እና ሲቪል ፖሊሶች ባዩሽ መስጊድን ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው ታወቀ:: ዛሬ ረፋዱ ላይ የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት፣ ሲቪልና ፌደራል ፖሊሶች፣ እንዲሁም ወደሃያ የሚጠጉ በእድሜ የገፉ ሴቶች አንድ ላይ በመሆን የሴቶችን መስጂድም ጭምር በማስከፈት ወደመስጂዱ...
View Article