$ 0 0 ከሥርጉተ ሥላሴ 31.10.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ) ነይ እሰኪ ዘንድሮ አለፈልግም ከርሞ የለኝም አርምሞ ሁለመናዬ አሮ በበቀል ተነክሮ ቀለም የለሽ ኑሮ፣ መስቃ ተዘርዝሮ መብቴ ተዘሮ ሁኛለሁ ደንቆሮ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ነጠብጣቤ አሮ ዓይኔም ተማርሮ በበላኃሰቦች እንዲህም ተወሮ ከምሾ ተድሮ ከዋይታ ተዳብሎ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ገሳ ተንተርሶ ሞረሽን ተንፍሶ በደልን ተቋድሶ፣ ዛሬ ተቀልብሶ እህህን ተለብሶ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ ፍሬ ዘሬ ሁሉ … …. በምጣድ ታምሶ አመድ ተነስንሶ ትብያ ተበስብሶ ድንጋዩን ቀልብሶ፣ ተቀበረ ተምሶ ታ ም ሶ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ቢራቢሮ … ተስፋ ቢራ ቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ክርም ተበጥሶ ጅማት ተጠናብሶ ማትብ ቢሆን ጢሶ፣ ፍዳ ተሰልሶ ክብር … ’አሳር ትቢያ ተላብሶ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ሥርዓት ተጥሶ ፍትህ ተገርስሶ ጭንጋፍ ተኮፍሶ ርኩም ተፈውሶ፣ ብዙኀኑ አንሶ መጠጊያ ተውሶ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ስልቻ ቃልቻ ብልቻ ጉልቻ አንተ አለህ መፍቻ፣ መድሕን አንተው ብቻ ሰልችቶናል ግቻ የ እ ን ጉ ቻ ች ር~~~~~ ዛቻ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ጥቅምት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዙሪክ አውሮፕላን ማረፊያ – ሲዊዘርላንድ