Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የማለዳ ወግ…. የተመስገን ደሳለኝ እናት…

$
0
0

የማለዳ ወግ … ይድረስ ለወዳጀ ወንድም ለወዳጀ ታሪኩ ደሳለኝ !

ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ ፣ ተናደድኩ …በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!
yetemesgen enat
ምን እንደምል አላውቅም … ለተጎዱት እናታችን አዝናለሁ ፣ ብቻ ሳይሆን ለመስዋዕትነት ለቀረቡት ለዚህች ቁርጥ ቀን ግንባራቸውን እንደ ተሜ ለሰጡት ብርቱ የሃገሬ ልጆች እናቶች በሙሉ አዝናለሁ “..ልጅሽ ወንድሜ ታስሯል! ” ለምትለው የመርዶ ነጋሪው ያንተ ጭንቀት ቢገባኝም ወጣት ነህና እንባህን ጠራርገህ ወንድምህ የሰጠንን ቃል አክብር ፣ ተከተልም! የጀግና ዘር አያለቅስም ! ተሜ አልነገረህም ? ወንድ ልጅ አደኮ አያነባም … በቃ እንዲያ ነው !!!!

አንድ ወዳጀ ማምሻው ላይ ጋዜጠኛ ተመስገንን ታውቀዋለህ? አለኝ … እንዲህ መለስኩለት ወዳጀ Abdu ጋዜጠኛ ተመስገንን በአካል አውቀዋለሁ፣ ከሳውዲ ለእረፍት ሄጀ በአንድ መአድ ቁጭ ብለን ክፉ ደጉን አውርተናል። ከርሴን ልሞላ የተሰደድኩትና “በካሳደገኝ ላስተማረኝ ወገኔ አልለይም ፣ ከምወዳት ኢትዮጵያ ፣ አልሰደድም እንቢ ” ካለው ጋዜጠኛ ጋር የነበረን ቆይታችን ያማረ ነበር። ተሜ ከሃገር ውስጥ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ ኑሮውና ከዚያም አልፎ በሳውዲ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ወንድም መሆኑን ባውቅም ያኔ ደግሜ አረጋግጫለሁ። በኢትዮጵያ ላይ የመጣው አበሳ እያዘነ እየተቆረቆረ እንደ ዜጋና እንደ ባለሙያ ራዕዩን ሲያንሸራሽር የደረሰበት እንግልት ግድ የማይሰጠው ጀግና ወጣት ጋዜጠኛ ነው። እንዲያው በአጠቃላይ እኔ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ ማለት ይቀል ይሆናል ፣ ኢትዮጵያን እንደ ተሜ እወዳታለሁ ማለት አይቻልም። እሱን መሆን የእሳይ ወላፈኑን ፣ ረመጥ እሳቱን ጭምር እየተለበለቡ ኢትዮጵያን መውደድ ከቶ ማንስ ይቻለዋል። ለብዙዎቻችን በጣም በጣም ከባድ ነው ! በቆይታችንና ከተሜ ጋር ባለን ቀረቤታ የተረዳሁት ይህን እውነታ ነው! ስለ ኢትዮጵያና ስለህዝቧ ራዕዮን ስድብ ፣ግልምጫ ማግለሉ፣ ከመቶ ያለፈ ክሱ ፣ እስራት ፣ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻው ምኑ ቅጡ ይህን ሁሉ ተጋፍጦ ጋዜጣ መጽሔቱን ሲዘጉበት እየከፈተ ” ትግሌ እስከቀራንዮ ነው ፣ አልሰደድም” ያለ እንደ ተሜ ብርቱ ጋዜጠኛ መች አለ ? ይህን ተሜ አውቀዋለሁ! የጀግና ቤቱ ወህኒ ነው እንዲሉ ፣ ተሜ ወደ ቤቱ ገብቷል ! በቃ ተሜ “ስለተገፋሁበት ምክንያት ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ትጉ እንጅ ስለእኔ እንዳታለቀረሱ ” ብሎኛል ተሜ …የማውቀው ብርቱው ወዳጀ ጋዜጠኛ ተመስገን …ብየ መለስኩ !

እናም እውነቴን ነው የምልህ ፣ በተሜ ኩራት የደም ስጋ ፣ የአንድ ማህጸን የእማማ ልጅ ስለሆንክ ክብር ይሰማህ እንጅ ተሜ ” አታልቅሱ ” ብሏልና አታልቅስ …ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ ቀራንዮ በግርማ በክብር እየሄደ ነው ፣ ሆዳችን አታባባው … ዳሩ ግና ምን የሚባባ ሆድ አለን ? …
ብቻ ይሁን :(

ነቢዩ ሲራክ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>