ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ ፈልጎ መጻሕፍት የሚያገላብጥ ባይተዋር መጀመሪያ የሚታየው የሀገሪቷ ጥንታዊነትና ውበቷ፥ የነዋሪዎቿ መልከ መልካምነትና በብዙ ጎሳዎችና ነገዶች መኖሪያነቷ ሲሆን፥ እነዚህ መልካካም ኢትዮጵያውያን በፖለቲካው ረገድ ዕድለ ቢሶች መሆናቸው ነው። የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት፥ በተለይ በኛ ዘመን፥ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ ተካሂዷል፤ ብዙ ሕይወትም አልፏል። ግን እንቅስቃሴውን መርተው መንግሥት ለመገልበጥ የቻሉ ሁሉ፥ “ካስወገድነው አገዛዝ የኛ አገዛዝ ይሻልሃል፤ እነ እገሌን አደኽይተን አነ እገሌን አናበለጽጋለን፤ በረዢም ዘመን ትግል ካስወገድነው እስር-ቤት መሰል አገዛዝ የኛ እስር-ቤት መሰል አገዛዝ ይሻላል” የሚሉ እንጂ ሕዝቡን ከአገዛዝ ነፃ የሚያወጡ አልሆኑም። እንዲያውም ያቋቋሙት አገዛዝ “ከድጡ ወደ ማጡ”” የሚባል አገዛዝ ነው። አይፈረድባቸውም፤ እነሱ የሚያውቁት ምን እንደሚፈልጉ እንጂ ሕዝቡ ምን እንደሚፈልጉ አያውቁም። ከየት አግኝተው ይወቁት? የሚያውቁት አያገባቸው ገብተው መፈትፈትና መጕረስ ነው። “ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ነፃ አውጥቶ ዴሞክራሲን አጎናጸፋት” የሚል የታሪክ ክብር የሚቀዳጅ ጀግና ማን ይሆን? ለጊዜው የሚታየኝ እንከን የለሽ ንጹሕ ምርጫ የሚፈቅድ ባለሥልጣን ወይም የምርጫውን ሕግ የሚያስከብር የፖሊስ አዛዥ ነው። -—-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——-
↧