Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ስብአዊ መብቶችና ድርጅቶቻቸው፣ ተጠንቀቅ አማራ! ከቦጋለ ካሳዬ

$
0
0

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ስብአዊ መብቶችና ድርጅቶቻቸው

amaraየደላቸው… የሰው ልጅ ይቅር፤ ማንኛውም ህመም ሊሰማው የሚችል ፍጡር አይጠቃ! አይገደል! ብለው እሪ! እሪ! ይላሉ። ያነባሉ። እንቅልፍ አይወስዳቸውም። የሌሎች ስቃዮች እነርሱንም ያስቃያቸዋል።
አንዴ ተማሪ እያለን የደብረ-ብርሃንን የብርድ ልብስ ፋብሪካ ልንጎበኝ ሄድን። አስተማሪያችን ፕሮፌሰር ፓንዲታ የሚባል ህንድ ነበር። ለምሳችን ስጋ ያለበት ሳንዱውች ተዘጋጅቶአል። የደብረብርሃን ብርድ ለጠኔ ዳርጎን ነበርና ሰፍ ብለን ሳንዱቻችንን መግመጥ ጀመርን። አስተማሪያችን ግን ከንፈሩ ደርቆ አይን አይናችንን ያየናል። ለመብላት ፈልጎአል። “ለምን አትበላም?” ብለን ብንጠይቀው፤ “ስጋ አልበላም። እምነቴ ማንኛውንም ፍጡር አትግደል ይላል።” ብሎን እርፍ!
በሆላንድ የእንሳስት መብት ተሙዋጋች የፖለቲካ ፓርቲ አለ። አሁን ዳች ፓርላማ ውስጥ ሁለት መቀመጫ አለው። ፓርቲው መሬት ማንኛውንም የሰው ልጆች ፍላጎቶች ለማሙዋላት ትችላለች። ይሁን እንጂ የሰዎች ስግብግብነትን ለማሙዋላት አትችልም ብሎ ያምናል። እንደ ፓርቲው ከሆነ ለምሳሌ የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ እንዱስትሪ፤ 30% በተፈጥሮ ይገኙ የነበሩ የእንሥሣትና የእጽዋት ዘሮችን በማጥፋት ተጠያቂ ነው። ከብቶችንም ለማደለብም ሆነ የወተት ጎርፍ ለማምረት መኖ በገፍ ስለሚያስፈልገው፤ በዚህም ሳቢያ መሬት ከድሃ ገበሬዎች ስለሚቀማ፤ የአለም ርሃብ እየተባባሰ የመጣበት አንዱ ዋናው ምክንያት ከእንስሳትና እንስሳ ተዋጾእኦ እንዱስትሪ ተግባር ጋር የተያያዘ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም የእርድ እንሳሳት ሲታረዱ ህመም እንዳይሰማቸው ይደረግ ይላል። አንዳንድ እንስሳት በተለይ አሳማዎች ለእርድ ሲቀርቡ ያለቅሳሉ! አንጀት ይበላል ነገሩ።
አሜሪካውያት ሴቶች የምጥን ህመም ስለሚፈሩ ማደንዘዣ ይወጋሉ ይባላል። በአውሮፓ ግን ሴቶቹ ማማጡ በተፈጥሮ ያለ ነገር ስለሆነ፤ እናምጣለን! የምን ማደንዘዣ ነው… እቴ! ብለው የምጡን ህመም ጥርሳቸውን ነክሰው ይጋፈጡታል።
የሰው ልጅ የቆየ እምነትም ይሁን ዛሬ በሰለጠነው አለም እንደምናየው እንስሳትም ይሁን ሰዎች እንዳይሰቃዩ የሚደረጉትን ጥረቶች ጨረፍ ካደረግን ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ።
በኢትዮጵያ መገዳደል አዲስ ነገር አይደለም። በታሪካችን ግዛት በማስፋፋት፣ የተለያዩ ጭቆናዎችን በመቃወም፣ በሃይማኖት ሳቢያ የደረሱ እልቂቶች አሉ። ቀይና ነጭ ሽብር ትልቅ ጠባሳ የጣሉቡን እልቂቶች ናቸው።
አይኖችቻን ይጥፉ! እምቢ አናይም ካላልን፤ በህወሃት አገዛዝ በአማራ ላይ አላባራ ያለው ግድያ ግን ለየት ያለ ነው።
1. በኢትዮጵያ የአማራ(ሸዋ) ገዢ መደብ እየተባለ የሚጠራውን(ክላፋም እንደጻፈው፤ 48% ኦሮሞ ነው፣32% አማራ፣ትግሬዎችና ሌሎች ናቸው) እንደጠላት መፈረጅ የጀመሩት የብሄር-ብሄረሰብ ጥያቄ ያነሱ ሰዎችና ድርጅቶች ናቸው። በወገኖቻችን በኩል የጉዳዩ አነሳስ ለእኩልነት ተብሎ የታሰበና አማራን ለጥቃት ኢላማ ለመዳረግ ሆን ተብሎ የተደረገ አልነበረም ብሎ ማሰብ ይቻላል። በተጨማሪም በአገራችን የመናገር፣ የመጻፉና የመወያየት ነጻነት ስለሌለ እንደዚህ ያለው ፖለቲካ ወደሁዋላ ይዞ የሚመጣውን መዘዝ አስቀድሞ ማየት ዛሬ ላይ ተቀምጦ ያለፈውን እንደመተቸት ቀላል ነገር እንዳልሆነ እንገነዘባለን።
1.2 ይሁን እንጂ ዶ/ር መራር ጉዲናም እንደታዘበው፤ በተለይ ለእኩልነት አማሮች ከማንኛው የበለጠ ትልቅ ዋጋ ቢከፍሉም ዛሬ ግን ተክድዋል። በሁሉም በሚለው ነገር መስማማት ባይቻልም መራራ ህሊና ያለው ሰው ነው። እንደ አፈንዲ ሙተኪ አግላይ፣ ስድና እሥስት አይደለም።
2. እ.አ.አ በ1995 ዴፕሎማሲ በሚል ሄንሬ ኬሲንጀር በጻፉት መጽሃፍ ውስጥ ፤ አሜሪካ የአንደኛው ዓለም ጦርነት እንዳለቀ(1919) ፤ ዳግም በአውሮፓ ጦርነት እንዳይነሳ አውሮፓውያንን አንዱ አገር አንዱን እጠቀልላለሁ በሚል የሚደረግ የሃይል ግንባታ ፍክክር እንዲያቆሙና፤ ከእንግዲህ ብሄሮች የራሳቸውን እድል በራሳቸው መወሰን አለባቸው የሚለውን መርህ እንዲከተሉ ማስጠንቀቁዋን እናነባለን። ይህ የአሜሪካ አለምን በብሄር የማደራጀቱ ፓሊሲ በክሊንተን አስተዳደርም ዮግዝላቪያን በማፍረስ በጉልህ መከሰቱን አይተናል። በኢትዮጵያም ጊዜውን ጠብቆ ይቀር ይሆን?
3. የተቀረው የአፍሪካም ፍዳ ይኼው ነው። ምንም እንኩዋን አህጉሩ (ከኢትዮጵያ በስተቀር) በአውሮፓውያን ተቀራጭቶ የዛሬዎቹ አገሮች ቢፈጠሩም፤ ሰላም እንዲሰፍን በሚል ሽፋን የአፍሪካን ሃብት ለማራቆት በጎሳ ላይ የተመሰረቱ አገሮች እንዲመሰርቱ የሚያቀነቅኑ አሉ። አንዱ አቀንቃኝ የመለስ ዜናዊ አማካሪ የነበረ “ተራማጅ” የሚባል ሶሻል ዴሞክራት ነው። ቻይና ሳይታሰብ መጣና ጫወታውን ለውጠው እንጂ።
4. ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ፤ ጨቁዋኙ አማራ፤ ተጨቁዋኝ ሊሎቹ ተብሎ ህወሃትን፣ ኦነግንና ኦብነግን በሚደግፉ የውጭ ኃይሎች ሆን ተብሎ ድርሰት ተደርሶአል። በጉዳይ ላይ ብዙ መጻህፍት ተጽፈዋል። ብዙ ፒ.ኢች.ዲዎች ተመርቀውበታል። ይህቺን ማስታወሻ ዛሬ ቅዳሜ በምጽፍበት ሰዓት እንኩዋን የኢትዮጵያ ማህበር በሆላንድ ሁለት በዚሁ ድርሰት ዶ/ር የተባሉ ቀንደኛ የአማራ ጠላቶች ጠርቶ ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት ፖለቲካ አቅጣጫ እንድንወያይ ጋብዞናል። እኔ ጠላቶቼን ቀደም ብዬ ስላማውቃቸው ከእነርሱ ጋር ስለ አገሬ አቅጣጫ መፍትሄ ለመፈለግ አልሂድም። የውይይት መብታቸውን ግን አከብራለሁ።
5. የውጭ ኃይሎች እነዚህ ብሄረተኛ ድርጅቶችን የሚደግፉበት ምክንያት ምንድን ነው? ህወሃትን የሚደግፉበት ምክንያቶች ግልጽ ናቸው። መሬት አግኝተዋል። ሽብርን ለመዋጋት በሚል ሰበብ ለሞት የሚማገድ የሰው ሃይል በቀላሉ ያገኛሉ። የህወሃት የጎሳ ፖለቲካም የኢትዮጵያን አገራዊ ስሜት ለማደብዘዝ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ከመሬቱም፣ከወታደር መማገዱም ሆነ እርስ በእርስ ከማናከሱ ፖለቲካ ህወሃት ተጠቃሚ ነው። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ በሚገባ እንዳስቀመጡት፤ ህወሃት በምጽዋት የሚኖር የለማኞች አገዛዝ ነው።
6. ኦብነግን በመደገፍ የሚገኝም ነገር አለ። ጋዝ ወይም ነዳጅ ነው። እ.አ.አ በ2009 በጄኔቫ አንድን የእንግሊዝ ኢምባሲ ሹመኛ ከሰዎች ጋር ሆነን አንገጋግረን ነበር። ኤርትራም ተሹሞ የሰራ ሰውና ስለ አካባቢው እውቀት ያለው ነው። ስለ ስብአዊ መብቶች ጉዳይ በኢትዮጵያ ገለጻ አደረግንለት። አላማችን በየአራት አመቱ አባል አገሮችን ስለ ስብአዊ መብቶች መሻሻልና ችግሮች በሚገመግመው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ላይ (ዩኒቨርሳል ፕሮዴክ ሪቪው) የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ ነበር። በጉባኤው ላይ አስተያየት ሰጭ አገሮች ከ5 ደቂቃ በላይ አይሰጣቸውም። ታዲያ እንግሊዙ የትኛውን የሰብአዊ ጥሰት አነሳ? በኦጋዴን ብቻ የተከሰተውን። በቃ። ሌላ ጥሰት ለወሬ ነጋሪም አልተሰማ። ቅዱስ ቫቲካን፣ሲዊዘርላንድ፣ሲውዴን፣ አውስትራሊያና ብራዚል በሚገባ በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለጉባኤው አስረድተዋል። የአሜሪካው ግን በጣም የተለየ ነበር። ኦባማ ገና በስልጣን የመጣበት ወቅት ስለነበር ለዴሞክራሲ መስፋፋት ተስፋ አልጨለመም ነበር። የአሜሪካው አምባሳደር የህወሃትን የጎሳ የበላይነት በጉባኤው ላይ ፍርጥ በማድረጉ፤ ሆዳሙ ፍሰሃ ገዳ ውሸት ነው ብሎ ቡራ ከረዩ ያለበት ትያትር ነበር ያየነው። ትእቢተኛው መለስ ዜናዊም ቀብጦ አምባሳደሩን ባለጌ ማለቱን አስታውሳለሁ።
7. ኦነግን በመደገፍና ኦሮሚያን በማስገንጠል ኦሮሞም ሆነ የውጭ ኃይሎች ምንም! ወላ ሃንቲ! የኢኮኖሚ ጥቅም አያገኙም። ባእዳን ዛሬ ካጋበሱት መሬት የበለጠ ኦነግ ኦሮሚያን መስርቶ ቢኮፈስ የበለጠ ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ? አይችሉም። ኦሮሞም እንደ አማራ አብሮ በደሙና በአጥንቱ በገነባት ኢትዮጵያ ሁሉ መብቱ ተከብሮ ነው መኖር የሚፈልገውም፤ የሚሻለውም።
7.1 ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እየለዩ፤ ኦሮሞዎች ትናትም ሆነ ዛሬ ተጨቁኑዋል እየተባለ ጎልቶ በስብአዊ ድርጅቶች ሆነ በአለም አቀፍ ድርጅቶች የሚነገረው፤ የኦሮሞ ተቆርቁዋሪነቱ(ብሄረተኝነቱ) ገኖ ኢትዮጵያዊነቱ ተሙዋጥጦ ይጠፋል ከሚል ምኞት ነው። አቤ ቶኪቻው ይኼን ወዲያው ተገንዝቦ ማለፊያ አስተያየቱን እንዲህ ሲል ስንዝሮአል፤..”ስንቅ ያቀበሉ ኦሮሞ ያልሆኑም ታስረው እየማቀቁ ይገኛሉ።” የኦሮሞ ጥያቄ የሚባለው በተጨማሪም እንዲገን የሚደረገው አማራና ኦሮሞ እንዳይቀራረቡ ለማድረግና የወያኔን የግዛት ዘመን አደጋ እንዳይገጥመው ለመከላከል ነው። አማራና ኦሮሞ ተቀራርበው እንደ አምስቱ የአርበኞች ትግል(ጉራጌዎችም አሉበት) መዋጋት ከጀመሩ ህወሃት በግድ ይጠፋል። ይኼን እየተገነዘቡ፤ ብዙዎቹ የኦነግ ብሄረተኞች በአማራ ጥላቻ ስላበዱ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለአድነታችን ጠላቶች መሳሪያ ሁነዋል። እነ ተስፋዬ ገ/አብና አንድናቂዎቻቸው አፈንዲ ሙተኪም የሚሰሩት ይኽንኑ ስራ መሆኑን አንብበናል። በጆራችን ስምተናል፡፡
7.2 ኢሳያስም ቢሆን እንዲህ እየባለገ በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈለገው፤ ኢትዮጵያን በማፍረሰ ቀመር ውስጥ ሊጠቅም ስለሚችል ነው። ዴምሄት 45 ሺህ የታጠቀ የትግሬ ጦር ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ በትግርኛ ቁውንቁዋ ከተገኙ ምንጮች ሰሞኑን እንዳስነበበን፤ ትግርኝ ትግሪኝን ለመሰረት ኢሳያስ ያዋቀረው ጦር ነው። ሴቪ አድና ግን ከመሃከላችን ሆኖ ዴምሂት ወያኔን ለመጣል የሚታገል ጦር ነው ይለናል። የሚገርመው ሴቪ አድና አስብ የትግራይ ነው ሲል ጽፎኣል። ለነገሩ አስብ የአፋር ነው፡፡ የሚቀርበውም ለወሎ ነው። ትግራይ ትግርኝ ግን ግን አማራጩ ፕላን ወይም ፕላን ቢ ነው። ይቅናችሁ።
8. እንደመደምደሚያ፤ የሰው ልጅ የሚያመዛዝን አእምሮ ስላለው፤ እንኩዋን ለራሱ ለሰው ለእንሳስት ነፍስ ሲሳሳ አይተናል። ህወሃት ሰው በነገዱ አማራ ነህ እያለ መገደል የጀመረው በወልቃይት ጸገዴ ነው። እኛ ግን በስፋት የሰማነው መጀመሪያ በአርባጉጉ ነው። በአርባጉጉ አራጆቹ እርጉዝ ሴቶችን በሳንጃ ከመግደላቸው በፊት በጽንሱ ጾታ ፤ አማራ ወንድ? ወይስ ሴት? በማለት ይወራረዱ እንደነበርና ጡት ቆርጠው እስከማስበላት እንደደረሱ ራሳቸው ኦሮሞዎቹ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጽፈው ከሰጡት ደብዳቤ መረዳት ይቻላል።
8.1 አማራ ተገደለ! ራስህን ተከላከል እያልን የምንጮኸው በዘር ቆጠራ ተለክፈን አይደለም። እጅግ ስብአዊነት ስለሚሰማን እንጂ። እንሆ 23 አመታት ተቆጠሩ፤ ፕሮፌሰር ዓስራት ወልደየስ እንዳሉት ጠላቶቹ አማራ የሚሉትን ፈልገው ሲያጡት አናይም። ስንት አማራ እየጠፋ አምነስቲ ምን አለ? ምንም። የፕሮፈሰር መስፍን አማራ የለም ነገር፤ አማራን ከጥቃት ለመከላከል አላስቻለም።
8.2 ስብአዊ መብቶች ብዙ ናቸው። ዓማራ ተብሎ በተለያዩ መንገዶች ሲጠፋ፤ ጠፋ! ተፍናቀለ! ተገደለ ብለን ስንጮኽ የጎሳን ፖለቲካ ማራመድ ነው የሚሉን ስለሰብአዊነት የጠለቀ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው። ለነገሩ እውቀት እንደ አባት ስም አይወረሰም። ጥናትና ጥረት ያስፈልግዋል። አንዳንዶቹ ከተለያዩ ጎሳዎች በመወለዳቸው አማራ አምሮ ከተነሳ የትኛውን እንመርጣለን ብለውም የሚጨነቁ ቅይጥ-ጎሰኞች አሉ። እነዚህ ሰዎች ስብአዊነትን ከሁሉም በላይ መሆኑን የዘነጉ ናቸው። ለነገሩ በኢትዮጵያ ዳርቻ ካሉ ጎሳዎች በስተቀር ያልተቀላቀለ የለም። ስለዚህ በኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ አገርን ለመበዝበዝና ካልሆነም ለመበተን የሚካሄድ ስልታዊ ሃሳብ/አይዶሎጂ እንጂ በትውልድ ሃረግ የሚመዘን ጉዳይ አይደለም። እኛ አማራ ንጽህ ዘር ነው፤ የራሱን መንግስት ያቁም አላልንም። በአማራነቱ የሚደርሰበት ጥቃት በአገዛዙ እቅድ የሚደረግ ስለሆነ ራሱን ከጥፋት ያድን ነው የምንለው። ምንም እንኩዋን በቅርቡ ባሳተመው መጽሃፉ ስለ አማራ እልቂት አንድም ነገር ያልተነፈሰው ብርሃኑ እንክዋን በደረሰበት ትችትና፤ ይኼንኑ ጉዳይ በመገንዘብ ባለፈው መስከረም የኢትዮጵያ አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ በአደረገው ንግግር አማራው በተለይ የጥቃት ኢላማ መደረጉን አምኖአል። ከአክሱም የተገኘው ጌታቸው ረዳ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>