Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

  „ከአዞ ዕንባ –ከዝንብ ማር አይጠበቅም“ (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ውዶቼ – የእኔዎቹ አንድ ነገር ከተሳራ በኋላ ተከፍቶ ቢያድር ተወሳክ ይገባበታል። ለጤናም ይበክላል። ጹሑፉ ቅናዊ ቢሆንም ትንሽ ማነፃጸሪያዎችን በማቅረብ ሃስብን መሰብስብ የዘበኝነት ተግባሬ ግድ ስለሚለው ተፃፈ።

de
መቼም ቅጥል – እርር – ካሉ ቅን ወገኔ የተጻፈ „ አሳዛኙ ውርዴታችን“ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37001 በሚል እርስ አንድ አጠር ያለ ጹሁፍ ከዘሃበሻ አሁን አነበብኩኝ። ወንድምዓለም / እህትአለም/ „ከአዞ ዕንባ – ከዝንብ ማር“ እኔ አልጠብቅም። ሃውዚ ላይ ዕልፎች ሲያልቁ ካሜራውን ደቅኖ ለፖለቲካ ትርፍ ወገኑን ከጨረሰ አረመኔ ተስፈኛ እኔይቱ አልሆንም። በራህብ ለሚያልቁት ወገኖቼ ብሎ ላገኘው ገንዘብ ወያኔ፤ ማወራራጃው አሽዋ ነበር። ለደምና ለሥጋዎቹ ብጣቂ ሳይራራላቸው ለእናንተ ነው እያለ፤ እዬማለና እተገዘተ አሸዋ ሰፍሮ ነው ሞታቸውን ያወጀው። በልግ፣ መህር ሲደርስ እልፎች ከቀያቸው ሲነቀሉ – ባለቤት የላቸውም። ከእርሻ ማሳቸው የሚነቀሉት እኮ ህይወታቸው ሞት ነው።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅ ጸሐፊውን … ወያኔ እነዚህ ወጎኖቻችን ማለቃቸውን ምክንያት አድርጎ የሀዘን ቀን ቢያውጅ፤ ጥቁር ለብሶ ቢውል ከቶ ሆድ ይሆነዎት ይሆን?

የሚገርመዎት አደጋውን ያደረሰችው ጀልባ ብቻውን ብትመለስ ሞቱን የሰሙ ወጣቶች እኔ እቀድም እኔ እቀድም ብለው ተሳፍረው ወደ ቀጣይ መዋዕቲነት መሄዳቸው አይቀሬ ነው። ከዚህ ጋርም ሌላ ነገር ማንሳት እሻለሁ። እሰረኞችን ወያኔ ቢፈታ፤ ሌላ ባለተራ ግበቶ ደግሞ ይማቅቃል። የአረብ ሀገሩ ትዕይንት በሚመለከት በቅብ ወያኔ ሲያረገርግ የመሰላቸው ወገኖች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ያን ሁሉ መከራ ተቀብለው ሀገራቸው ገቡ ተብሎ ከተደመጠው ዲስኩር ጀርባ እኛ ያላዬነውና ያልሰማነው፤ ያልደረስንበትም ስንት የበቀል እርምጃ ተወስዶ ይሆን?! ፊት ለፊት በወጡት ላይ …. ሆነ መጠጊያ ባጡት ላይ። ዋናው ልናተኩርበት የሚገባው መሰረታዊ አውራ ተግባር የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆን ከጋራ ስምምነት መድረስን ነው። መርዛማ ምንጭ ከምንጩ ነው ሊደርቅ የሚገባው። በስተቀር ተፋሰሱ ሁሉ ብክል ስለሆነ – አይምሬ ነው። ይህ ማለት የችግሩን ምንጭ ማውቅ እስካልተቻለ ድረስ መፍትሄ ሊገኝ ከቶውንም አይቻልም። እንግሊዘች „የችግሩን ምንጭ ማወቅ ለችግሩ ግማሹ መፍትሄ እንደ ተገኘ ይቆጠራል“ ማለታቸው፤ የችግሩ ጥልቀት – ስፋትና መጠን፤ ልኩን መፍትሄውን ሆነ ጉልበታምና የማያዳግም መፍትሄ አምንጪ ያደርገዋል ለማለት ነው። በእኛም ሀገር „በሽታውን ያልተናገረ መዳህኒት አያገኝም“ ይባል የለ። እንደዛ ነው።

ሌላው የተነሳው „መንግሥት“ በሚመለከት ነው። ጎሳ ላይ የጎሳ አለቃ እንጂ መንግሥት እድገቱ አይፈቅድለትም። ከቤተሰብ ቀጥሎ ባለው ጎሳ ውስጥ መንግሥት አለ ከተባለ፤ ቤተሰብ ላይ የመንግሥት besement አለ ማለት ነው። ስለዚህ ትንሽ ወደ ውስጥ ዘልቀን እንመርምረው። እርግጥ ነው ከቀደሙ ሥርዓቶች የተወረሱት ኢትዮጵያዊ ተቋማትን አፍልሶ ከኢትዮጵያዊነት ጋር አይገናኙም ያላቸው መዋቅሮች ወያኔ አሉት። ቀድመው የተደራጁ ስለነበር። ነገር ግን ባዶ ግድግዳ ጣሬያ የሚሆነውን ቆርቆሮ ወይንም እሳር ካለበሰ – ቤት ሊሆን አይችልም። „ቤት“ የቤትነት መስፈርቱን ካላሟላ ህይወትን ሊያቆይ አይችልም። የወያኔም መዋቅራዊ ቅራቅንቦው ይሄው ነው። ግጭትና ስበቱም እኮ የማይገናኙ ነገሮች በግድ ተሳበቁ ተብለው ነው እኮ?!

d2በተያያዥነት የተነሳው ጉዳይ „አሳዛኝ“ መቼ አባርቶ አውቆ። መርዶ ነው ደመር* ነው ዕጣ ፈንታችን።  „ውርደት“ ለሚለው ግን አልተመቸኝም። እኛ ምን ሆነን እንዋረዳለን?! ፈጻሚው አንገቱን ይድፋበት፤ ቀልብ ተሰፋሪው አንገቱን ያቀርቅርበት? ይልቅ እኛ እንዲህ የነገ ተስፋ እዬተዳፋ ባህር ውስጥ የሚደፋበትን ሳቢያውን ሳይሆን፤ የአምክንዮውን ምክንያታዊ መቅኖ በማወቅ …. የዓለም ዕድገት ደረጃና ዘመኑ የፈቀደለት ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲሰፍን መንፈሳችን መሞረድ ነው – መፍትሄው። ሞቱ ይቀጥላል …. ግፉም ይቀጥላል ወያኔ አስካለ ድረስ። ተጠግኖም አይድንም – ነዳላው ብዙ ነውና። ስለዚህ ሊገፋ የሚገባው ነገር፤ የህዝብ ፈቃድ የሚገዛው፤ የሚያስተዳድረው  አዲስ ሥራዓትን ለመፍጠር „በቃንን!“ ወደ አደገ ደረጃ ማድረስ ነው ቁም ነገሩ።

በተጨማሪነት የተነሳው የአሜሪካ አንባሳደር ሃዘናቸው መግለጻቸው ነው። ይህ በሁለት መልክ ሊታይ ይችላል። አንደኛው ከሰብዕዊነት አንፃር ቀኑም የሰብዕዊ መብት ቀን መሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ ባሉበት ሀገር ለሚፈጸመው ግፍ ቸል ቢሉ የዓለም – ዐቀፉን ማህበረሰብ ወቀሳ ሽሽትም ጭምር ነው። ወቀሳውን አይችሉትም። እንዲሁም በቀጣይ ምርጫውም ላይ የሥልጣን ሚዛኑ ላደላው ዲሞክራት ፓርቲ ከፍ ያለ ተጽዕኖም አለው – በስፋት ሲታይ ጉዳዩ። በተረፈ ቅርበታቸውና ሀዘናችን ሃዘናቸው መሆኑ ያስመስግናቸዋል። ነገር ግን  ዬአሜሪካ መንግሥት የነፃነት ቀማኛ ሥርዓትን ከማንቆለባበስ ተቆጥቦ እኛም ሰውነን እና አዲስ ዕይታ እንዲኖረው ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር፤ ይሄ በቅብ የተሽቆጠቆጠው የወያኔ ምስል ቀርቶ ሃዘኑ ሃቁን የመግለጥና የማጋላጥ አቅም አንዲኖረው ከማደረጉ ላይ ነው ብልሃቱ ያለው። ለዚህ ተግተው ከቀጠሉበት – ማለፊያ ነው። በስተቀር ግን …..

ወያኔ እስከ አለ ድረስ የነገ ኢትዮጵያ ተስፋም እንዲህ አመድ ተላብሶ፤ አመድ ቅሞ፤ የተፈጥሮ ገላ ወዙ በጉስቁልና የሚኖሩበት ሥርዓት  ለአፍታ ለድርደር የሚቀርብ ሊሆን አይገባም። እንደ ህዝብ እረኛም ሊታይ አይገባም። ዛሬ እኮ እኛ ትተነዋል። መሰረታዊ የሰው ልጆች አስፈላጊ ጉዳዮችን። መጠለያ፤ ከፈን፤ ምግብ፤ ንጹህ ውሃ ት/ቤት …. እንደ ቅንጦት ከተቆጠሩ ዓመታት ተቆጠሩ። ስለምን? ወገን በባዕቱ ድህነቱን ችሎ መኖር አልቻለም። ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እስረኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የጭንቀት በሽታም ተጠቂም ነው። ከሥጋት፣ ከፍርሃት ቀጥሎ የመንፈስ ጫና ያለው በሽታ በዬጓዳው እንዳሻው እዬተወራኘ ነው። ለመሆኑ ለ90 ሚሊዮን ስንት የሥነ – ልቦና ባለሙያዎች ከቶ ይኖሩን?!

ክውና – የነገ ተስፋ እንዲህ ነው …. አሮ – ጠውልጎ  – አፈር …. ለብሶ፤ አይመስሉ መስሎ፤ አይሆኑቱን ሆኖ – አፈር ቅሞ፤ ትቢያ ተንተርሶ፤ ትቢያን ተማምኖ፤ ትቢያን መጠለያ አድርጎ፤ ትቢያን ጉርሱ አድርጎ፤ ትቢያን ከፈኑ አድርጎ፤ ልጆቻችን በዚህ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት – እ! እም!

  • ደመር … ጠብቆ ነው የሚበበው። ደመረ ከሚለው ቃል የተራባ ነው። ደረበ- ጨመረ – ሰበሰበ ይሆንና በገጠር የጋራ የለቅሶ ቀን ተቀጥሮ በወል ዕንባ የሚፈስበት የዕንባ ምጥ ቀለበት ቀን ማለት ነው።

እልፍ ነን እና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>