አንድነት ለዴሞከራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ2007 ምርጫ ከሁሉም ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ በጣም ግልፅና የማያሻማ የምርጫ እስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው። በዚህ ስሌትም የተዘጋውን የፖለቲካ ምህደር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ማስከፈት እንደሚችል አምኖ በምርጫው በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗል። በዚህ ምክንያትም የያዘውን የምርጫና የሰላማዊ ትግል መስመር አስቀድሞ በይፋ በማወጅ የመርህ ፓርቲ መሆኑ አስመስክሯል። ይሄ አቋሙ በምርጫው እንደሚሳተፉ እርግጠኛ ሳይሆኑ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ ፓርቲዎችና በሂደቱ ዝም ብለው በደመነፍስ ከገቡ ፓርቲዎች በእርግጠኝነት የተሻለ አቅጣጫ ያስቀመጠ ፓርቲ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ሊሆን የቻለው አንድነት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዴት እንደሚሰፋ፤ ገዥውን ፓርቲ በምን ሁኔታ አስገድዶ ወደ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ መምጣት እንደሚችልና እንዴት አምባገነናዊ በሆነ ስርዓት ውስጥ በምርጫ አሸናፊ ሆኖ መውጣት እንደሚቻል ተረድቶ የመታጊያ እስትራቴጂውን በአግባቡ የነደፈ ፓርቲ በመሆኑ ነው። -—[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——-