Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል1

$
0
0

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል 1
ሰሞኑን የ40ኛውን አመት የህውሃት ምስረታን በማስመልከት ብዙ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል በማምራት የወያኔን የትግል ታሪካዊ ስፍራዎችን ሲጎበኙ ከርመዋል:: ከጉብኝቱም በኋላ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶችንም ሰጥተዋል ተብሎ አንብቤያለሁ:: እስቲ አንዳንዶቹ ያሉትን እንይ
-“የትግራይ ሕዝብ በፍቅር ሊገድለን ነው” ያለው አርቲስት አበበ ባልቻ ነው፡፡
-የደራሲያን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው በለጠ በበኩላቸው “ያየነው ነገር ከነገራችሁንና ከጻፋችሁት በላይ ነው፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊመለከታቸው የሚገቡ ብርቅዬ ፍፃሜ የያዙ ዋሻዎች ናቸው:: ይኼ ታሪክ የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ነው አላችሁት? እንኳን የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ማለትም ያንሰዋል፡፡ የመላ አፍሪካ ታሪክ ነው፡፡ መቀመጥም ያለበት እዚሁ ተወሽቆ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረት በሚገኝበት ሥፍራ ከኔልሰን ማንዴላ ጎን ነው፡፡ ይኼ ታሪክ ከእሱም በላይ ነው” ብለዋል፡፡
– አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ በተሳታፊዎች ከፍተኛ የድጋፍ ጭብጨባ የተደረገለት ይሄን ሲል ነበር “እስካሁን የምንሰማው ትግራይ ለምታለች፣ ተለውጣለች ሲባል ነው፡፡ ስንሰማው የኖርነውና አሁን በዓይናችን ያየነው ግን ለየቅል ነው፡፡ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ያየነው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ሕዝብ የተሠራ ነው፡፡ ተራራ እየፈነቀለ የሚሠራውን ተመልክተናል፡፡ የኑሮው ሁኔታ ግን ድሮ እንደነበረ ነው አልተሻሻለም፡፡ ይህንን በእውነት ልታስቡበት ይገባል፡፡ ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ልጆቹን ለመስዋዕትነት መርቆ የሸኘ ሕዝብ አልተካሰም፡፡ አሁንም እኔ የምለው አስቡበት ነው” በማለት አላበቃም፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የልማት አማራጭ መንገዶች በዚህ ክልል ተግባራዊ የማይሆኑበት ምክንያት “ምንድነው?” ሲል ጠይቋል፡፡ ደጋግሞ ባለሥልጣናቱ እንዲያስቡበትም ተማፅኗል፡፡ የሚወራው ሌላ እየሆነ ያለው ሌላ”
ይህ ሰው ረሳው የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም እንዳላገኘ ረሳው እንዴ?
-በመጨረሻም “የወያኔ ህወሃት ታጋዮች ምርጥ የኢትዮጵያ ጀግኖች መሆናቸውን አይተን አረጋግጠናል” በማለት፣ ሰማዕታቱ ትተውት ያለፉት ንፁህ ታሪክ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለሕዝብ ለማሳወቅ በየሙያቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል::
ይህንን ሲናገሩና ለተከታታይ ቀናት ጉብኝቱን ሲያደርጉ በነባር የሕውሓት መሥራቾችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ታጅበው ነበር:: እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ኑሮ እጅግ በጣም ተወዶ ህይወት አንገብጋቢና ተስፋ አስቆራጭ በሆነበት በዚህ ጊዜ እንዲህ አይነት አድርባይነትን ከየትኛው የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አስተዳደግ እንደተማሩት ማወቅ ተስኖኛል::
እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ዋናዎችን ባለስልጣናትን በመፍራትና በመሽቆጥቆጥ እናንተ ምንም አላጠፋችሁም የበታቾቻችሁ ናቸው ያስቸገሩት “እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል፡፡ ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን” ማለት እንዴት ነው የቻሉት?
የኢትዮጵያ ህዝብ ባሁኑ ሰአት እንኳን የፈለገውን መናገርና መጻፍ ቀርቶ ህወሃት እና ኢህአዴግን ካማና ስለመንግስት ክፉ ከተናገረ ግፍ እንደሚደርስበት ከነሱ በላይ የሚያውቅ ማን አለ? እውነት ግን የኪነ ጥበብ ሰው እንደዚህ ሞራሉን ገድሎ እና ስብእናውን አሳንሶ መኖር ይችላል? ጥበብ በእንደዚህ ያለ ደረጃ ሃገሬ ላይ መውረዷና መዋረዷ በጣም እጅግ በጣም አሳዝኖኛል:: የጥበብ ሰው እንደዚህ ረክሶ የህዝብን ችግር ከመናገር የመንግስትን ባለስልጣናትን መታዘዝንና ጥቂት ፍርፋሪ ለማግኘት እንደ ውሻ መኖርን እንዴት ይመርጣል? (አንዳንድ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች እንዳሉ እንዳንረሳው)
የነበሩት ባለስልጣናት እኮ አቦይ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አዲሱ ለገሠ፣ አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ካሱ ኢላላ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ታጋይ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ናቸው:: እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሰሯቸውን ግፎች እነዚህ አርቲስት ተብዬዎቹ አያውቁት ይሆን? ጋዜጠኞቹስ?
መንገድ ላይ በጥይት ላለቁ ወገኖች፣ በየወህኒው የሚሰቃዩ ኦሮሞ ወገኖች፣ ከየቦታቸው ሚፈናቀሉ አማሮች፣ በግፍ የታሰሩ ሙስሊም ወገኖች፣ የክርስቲያን አባቶች፣ ጋዜጠኞች… ማን የሚሰራው ግፍ ነው?? እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ባለስልጣናት አይደሉም እንዴ?
ድሮም ቢሆን ሰው ለሆዱ መኖር ከጀመረ ምን ሰው ነው? ህሊና የሚባል ነገር የሌለው ሰው ምኑን ሰው ይባላል? በጣም ያሳፈርኝና እጅግ በጣም ከባድ የሞራል ዝቅጠት ነው ብዬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ ደግሞም በጣም ማመን ካለመቻሌ የተነሳ ያሳቀኝ ነገር ሁለት ነው::
– የመጀመሪያው ይህ የሰራዊት ፍቅሬ ፎቶ ነው:: ይህ ሰው የደርግ ወታደር ነበር ብዬ ለማመን ሁላ ከብዶኛል:: የደርግ የሽሬ ሽንፈትን ሲጎበኝ የህወሃት ታንክ ላይ የተነሳው ነው:: የራሱን ሽንፈት ሰላምታ እየሰጠ ያንቆለጳጰሰ ወራዳ ወታደር በአለም ላይ አለ ብዬም አላምንም::

hg

– ሌላው ደግሞ ነዋይ ደበበ አገሬን አልረሳም እያለ ከሳሞራ የኑስ እና ከ አባ ዱላ ገመዳ ጋር እየተቃቀፈ የሚዘፍነውን ሳይ ነው:: የዛሬ አስር አመት 1997 ላይ ይህ ድምጻዊ ከአሜሪካን አገር አንድ ፎቶ ልኮ ነበር በዛ ፎቶ ላይ ጣቶቹን የ‘V’ ቅርጽ ሰርቶ የቅንጅት ደጋፊ መሆኑን እና ወያኔ ነብሰ ገዳይ ነው ብሎ ስንት ሰው እንዳነሳሳ ትዝ ይለኛል:: እሱን ተከትሎ የሞተውን ወጣት እንዲረሸን ካደረገው ከሳሞራ ጋር እየተቃቀፉ መደነሱን ሳይ በጣም ልቤ ተረበሸ:: ንዋይ ደበበ ምንም ቢሆን ይህን ያረጋል ብዬ ስላላሰብኩ
እንግዲህ ይህን ካልኩ በኋላ ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎች ደግሞ አላማቸው እና ህልማቸው እስኪሳካ በቻሉት አቅም ትክክለኛ ስነምግባር ለማነጽ ጥበብን ይጠቀሙበታል:: አሸርግዶና ተሞዳምዶ ተዋርዶና ክብርን ሸጦ መኖርን እጅግ ይጠየፉታል ሁልጊዜም ጥበብን እንደ ታላቅ ጸጋ ተቀብለው ከህዝባቸው ጎን እንደተሰለፉ በድህነትና በስደት ይኖራሉ እንጂ ክብራቸውንና ህሊናቸውን ሸጠው መኖር ስለማይመርጡም እንኮራባቸዋለን:: ለዛሬው በዚህ ላብቃና ለመሰነባበቻ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>