Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

“እነርሱ ከደደቢት መጥተው የለ፣ እኛም ሸሚዛችንን እንሸጠለንን” የአንድነት አመራር –ኖአሚን በጋሻው

$
0
0

የምርጫ ቦርድ ታህሳስ 28 ቀን  ባደረገው ስብሰባ፣ የሕወሃት አባል ናቸው የሚባሉት የቦርዱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ከአንድ ቀን በፊት በፋና ራዲዮ የተናገርሩትን በማጽደቅ፣ አንድነት ፓርቲ በምርጫው እንዳይወዳደር የምርጫ ምልክት አልሰጥም የሚል ኢሕገ መንግስታዊ የፖለቲካ ዉሳኔ አስተላልፏል። የአንድነት ፓርቲ በሁለት ወራት ጊዜ ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ አመራሩን ካልመረጠ በምርጫዉ መወዳደር እንደማይችልም ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

የአንድነት ፓርቲ ያለፈው ታህሳስ  ወር 2006 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን መምረጡ፣  ኢንጂነሩም ከዘጠኝ ወር አገልግሎት በኋላ፣  ከአባላትና ከደጋፊዎች በተነሳ ግፊት፣ የመሰረቱትን የሥራ አስፈጻሚ በትነው ፣ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወቃል።

tigstuበድርጅቱ ደንብ መሰረት ብሄራዊ ምክር ቤቱ፣ ከመካከሉ ሶስት አመራር አባላትን አወዳድሮ፣ አቶ በላይ ፍቃደን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ከአቶ በላይ ጋር አሁን የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፣ አቶ ትእግስቱ አወሉ እና አቶ ደረጀ ለእጩነት ራሳቸውን አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ አቶ ነገሰ «እኔን ልትመርጡ ያሰባችሁ፣ አቶ ደረጄን ምረጡ” በሚል ከዉድድሩ ራሳቸዉን በማውጣታቸው ምርጫው በተቀሩት ሶስት እጩዎች መካከል ተከናዉኗል። አቶ በላይ ፍቃደ አብላጫ ድምጽ ሲያገኙ፣ አቶ ደረጄ በሁለተኛ በመሆን ብዙ ድምጽ ያገኛሉ። አቶ ትእግስቱ አወል የርሳቸውን አንድ ድምጽ ብቻ አግኘተው ሶስተኛ ሆኑ። ሁለተኛ የሆኑት አቶ ደረጀ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሰሩ ነው።

አቶ በላይ በደንቡ መሰረት አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አዋቅረዉ፣ በምክር ቤቱ ያጸድቃሉ። የምክር ቤቱ ዉሳኔ፣  ሕጉ እንደሚጠይቀው፣ ለምርጫ ቦርድ ይላካል። ምርጫ ቦርድ ለአዲሱ አመራር እውቅና አልሰጥም የሚል ደብዳቤ ይጽፋል። የደብዳቤ ምልልሶች ይጧጧፋሉ። በዚህ ወቅት ብቻ ቢያንስ ወደ ዘጠኝ ደብዳቤዎችን አንድነት ከምርጫ ቦርድ ጋር ተጻጽፏል። አንድነት ምንም አይነት የደንብም ሆነ የህግ ጥሰት እንዳላደረገ ለማስረዳት ተሞከረ። የአመራር አባላቱ ምርጫ ቦርድ ድረስ በመሄድ ሁኔታዉን ለማስረዳት ሞከሩ።  አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም” እንደሚባል ምርጫ ቦርድ በፍትሃዊነት ሁሉንም ድርጅቶች የሚያገለግል ሳይሆን ከሕወሃት መመሪያ ተሰጥቶች ጠንካራ የተባሉ ድርጅቶች ለመኮርከም የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። የአንድነትን ትእግስት፣ የምርጫ ቦርድን አደርባይነት እንግዲህ ተመልከቱ።

የአንድነት ፓርቲ የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ፓርቲ እንደመሆኑ,  የሚሰራዉን ደባ ታግሶ፣ በመንገዱ ላይ የሚቀመጠዉን መሰናክል ድንጋይ እያለፈ ሕዝቡን ማደራጀቱን እየቀጠለ፣ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ ዉስጥ መግባት አያስፈልግም በሚል ምርጫ ቦርድ የጠየቀዉን ለማሟላት ወሰነ። ምርጫ ቦርድ በድርጅቱ ደንብ ላይ የጠቅላላ ጉባኤ የኮረም ቁጥር መጠቀስ አለበት የሚል ጥያቄ በማቅረቡ፣ ምንም እንኳን የኮረም ቁጥር መግባት አለበት የሚል ሕግ ስለሌለ ያንን  የመጠየቅ መብት ምርጫ ቦርድ ባይኖረውም፣ ለአባላቱም ስልጠና ለመስጠት አስቦ ስለነበረ፣ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራል። በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫ ቦርዱ  የጠየቀው የደንብ መሻሻል ያደርጋል። የብሄራዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሲመርጥ አንድ ድምጽ ብቻ ያገኙት አቶ ትእግስቱ አወል፣  በአቶ በላይ ፍቃደ አመራር ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። አቶ በላይ ስልጣኑ የጠቅላላ ጉባኤ እንደመሆኑ፣  የተመረጡት በድርጅቱ ደንብ መሰረት በምክር ቤት እንደሆነ ገልጸው፣ ጠቅላላ ጉባኤው ግን በማናቸውም ጊዜ የምክር ቤቱን ዉሳኔ የመቀልበስ መብት እንዳለው በማስረዳት፣ እንደገና ምርጫ ማድረግ እንደሚቻል ያሳወቃሉ። የድርጅቱ የበላይ አካል የሆነው ከአራት መቶ በላይ ተወካዮች ያሉበት  ጠቅላላ ጉባኤው ፣ የብሄራዊ ምክር ቤቱ በፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው በለቀቁት በኢንጂነር ግዛቸው ምትክ ፣ አዲስ አመራር ማስመረጡ ትክክልና ደንቡን ያልጣሰ መሆኑን ያረጋግጣል። አዲሱን አመራር በድጋሚ ያጸድቃል። አቶ ትእግስቱ አወልን እና አቶ የማነን የተባሉ ግለሰብን ጨምሮ ከአምስት የማይበልጡ ይቃወማሉ። (ቀደምም ብሎ ብዙ ድምጽ ሲያሰሙ የነበሩት አቶ  ዘለቀ ረዲ በጠቅላላ ጉባዔው ወቅትም አልተገኙም ነበር)

አንድ መረሳት የሌለበት፣  የጠቅላላ ጉባኤ በሚደረግበት ጊዜ የምርጫ ቦርድ ተወካይ በስፋራው የተገኙ ሲሆን፣ የጠቅላላ ጉባኤውን ስሜትና የተወካዮችንም አንድነት  በሚገባ ተገንዝበው ሄደዋል።

የጠቅላላ ጉባኤው ቃለ ጉባኤ ፣ የተሻሻለዉን ደንብ በጊዜው ለምርጫ ቦርድ ይላካል። ሆኖም አሁንም ምርጫ ቦርድ አንድነት የምርጫ ዘመቻዉን እንዳያጧጡፍና አባላትን እና ደጋፊዎች ለማዳከምና ለማዘናገት ሲል፣  ሰበብ እየፈጠረ ፣ በኢቲቪም አንድነት ችግር እንዳለበት እየለፈፈ፣ ጸረ-ዴሞክራሲያዊና ጸረ-ሕዝብ ተግባሩን ይቀጥልበታል።

ሕወሃት፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተገኙት አቶ ዘለቀ ረዲ፣ ለሊቀመነበርነት ተወዳድረው አንድ ድምጽ ብቻ (የራሳቸዉን ድምጽ)  ያገኙት አቶ ትእግስቱ አወሉ ( ሁለቱም አንድነትን በዉህደት ከተቀላቀለው ከብርሃን ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመጡ ናቸው)፣ አቶ የማነ የመሳሰሉት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችን በማሰባሰብ፣ ትልቅ የኢቲቪ ሜዲያ ሽፋን በመስጠት፣ የስብሰባ አዳራሾችን በመፍቀድ፣ በገንዘብም በመደገፍ ፣  የአየለ ጫሚሶን አይነት ድራማ ለመስራት መንቀሳቀስ የጀመሩ ይመስላል። እነ ኢንጂነር ዘለቀና ትእግስቱ አወል ከአራት መቶ በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት 10 እንኳን የደገፋቸው ሳይኖር፣ ሕወሃት እነርሱን እያደራጀ ፣ የኢሕአዴግ ካድሬዎችም እንዲቀላቀሏቸው እያደረገ ፣ ስለ እነርሱ እያወራለን ይገኛል።

ሕወሃት “አንድነት እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሩን ማስመረጥ አለበት። አለበለዚያ በምርጫው አይወዳደርም” የሚል ዉሳኔ ነው በመጨረሻ ሲሰጥ አላማ ምን እንደሆነ በግልጽ አሳይቷል። አንደኛ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲደናገጡን ተስፋ እንዲቆርጡ ነው። ሁለተኛ አንድነት እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ጊዜዉን እንዲያጠፋ ነው። ሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤው ወጭ የሚጠይቅ እንደመሆኑ አንድነትን በገንዘብ ማዳከም ነው። ቢቻላቸውም ደግሞ አራተኛ በአቶ ዘለቀረ ረዲ ወይም ትእግስቱ አወል የሚመራ የአየለ ጫሚሶ አይነት “አንድነት” ተመስርቶ የአንድነትን ሕጋዊ ሰርተፊኬት ለነርሱ በመስጠት አንድነት ከምርጫው ዉጭ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ቅንጅትን  ለአየለ ጫሚሶ ሲሰጡ፣ ያኔ የቅንጅት መሪዎች ከእስር ቤት መዉጣታቸው ነበር። በመካከላቸውም ብዙ አለመስማማቶች ነበር። አሁን ያሉት የአንድነት አመራር አባላት በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ሆነ በምክር ቤቱ፣  የጠነከረ አንድነት ያላቸው ናቸው። ይሄንንም በስራቸው እያሳዩ ነው። በአንድነት ታሪክ አሁን ያለበት አይነት ጥንካሬ አንድነት ኖሮት አያውቅም።

አባላትና እና ደጋፊዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ከሆነ ደግሞ፣ ከምርጫ ቦርድ በሚሰዘነዘረው ዱላ እንደዉም አባላት የበለጠ ይጠናከራሉ እንጂ አይዳከሙም። አቶ አዲሱ፣  በፋና ራዲዮ የተናገሩት እንደተሰማ፣ በአገሪቷ ሁሉ ያሉ አባላት ፣ “ይሄ ያህል በራዲዮ ኛ ላይ ዘመቻ ከተጀመረ ጥሩ ሰርተናል ማለት ነው” እያሉ የበለጠ ለመስራት መሯሯጥ ጀምረዋል። አላወቁትም እንጂ ሕወሃት ለአንድነት ትልቅ ማስታወቂያ እየሰራለት ነው። እንኳን የነ አቶ አዲሱና አቶ መርጋ ተራ ደብዳቤ ይቀርና፣  ሞት  ወይም እሥር የማይፈሩ ጀግኖች የበዙበት ፓርቲ ነው የአንድነት ፓርቲ።

አንድነትን በገንዘብ ለማዳከም የታሰበዉን ካየን ደግሞ፣ አንድ የአንድነት አመራር አባል እንደተናገሩት  “እነርሱ ከደደቢት መጥተው የለም እንዴ። ሸሚዛችንን ሽጠን የሚያስፈልገውን እንሸፍናለን” እንዳሉት ፣ ለትግሉ የሚያስፈለገው ወጭ ይሸፈናል። አንድ ጊዜ ሕዝቡ ከጎኑ የሆነ ድርጅት አይወድቅም። የጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ እንደገና አቶ በላይ ሆነ ሌላ ጠንካራ አመራር የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይመርጣል። ሕወህትቶች ደስ ካልተተሰኙ ጸጉራቸውን ይንጩ እንጂ፣ መሪያችንን  እኛ እንጂ  እነርሱ አይመርጡልንም።

እንግዲህ ዉድ ኢትዮጵያዉያን ይሄ ሁሉ ትግል ነው። ሕወሃት የሚፈልገው ምርጫዉን ከትርኪምርኪ ድርጅቶች ጋር አድርጎ አሸነፍኩ ብሎ ማወጅ ነው። አላማቸው አንድነት ምርጫዉን ቦይኮት እንዲያደረግ ነበር። አንድነት ቦይኮት ማድረጉ ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደሌለው በመግልጽ በዉጭም ሆነ በአገር ዉስጥ ያሉት በማሳመን የምርጫ ዘመቻዉን ሲያጋግለው፣ ኦፌሴላዊ የምርጫ ዘመቻ ገና  ሳይጀመር፣ ገና ከወዲሁ ለክልልና ሆነ ለፌደራል ተወዳዳሪዎች አዘጋጅቶ እንደጨረሰ ሲገልጽ፣ በየከተሞችን በሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትሃዊ ምርጫ በሚል ሰልፎችን እና ሕዝባዊ ሰብሰባዎች ሲጠራ፣ ሕውሃት ደነገጠ። ያንን ለማስቆም ብሎ ከህዝብ ካዝና የተገኝ ገንዘብን እየበተነ ነው።

እንግዲህ የአገራችን ፖለቲካ ግለቱ ጨምሯል።  ከዳር የቆምን፣ ተስፋ ቆርጠን የተቀመጥን ትግሉን እንቀላቀል። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን። አንድነትን እንደገፍ። የለዉጥና የነጻንትን ችቦ እናቀጣጥል። እኛ ከተባበረን የሃባትሙ አያሌውን አባባል ልዋስን እመኑኝ ደርግም ወድቋል፤ ወያኔም ትወድቃለች።

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>