ከሳሿ…. በጣም ትገርማለች…. ክስ ስታቀርብ ልክ እንደ አደቬነቸር ነዉ የምታወራዉ…. በሆነዉ ነገር የማፈርና የመፀፀት ስሜት አይታይባትም… እንደዉም ዘና ብላ ‘ከሴሌበሪቲ’ ጋር መማገጧን እንደ ዝና የምታወራ ነዉ የምትመስለዉ…. ‘ሴቶች ሆይ ፓስተር ተከስተን አወጣሁት …እንቁልልጭ!’ የሚል አይነት ድምፀት አላት… እንደዉም…እንደዉም ዝነኛ ለመሆን ያደረገችዉ ነዉ የሚመስለዉ….ፍራጅ አትበሉኝ እና! ቀሚሳን ግለባ ሙታንታዋን አዉልቃ ከአንዴም ሁለቴ የልባን ካደረሰች በኋላ ተደፈረኩኝ ብላ ለክስ መነሳቷ ማፈርያ ከመባል ሌላ ምን ያስብላታል?!! የሚገርመዉ ሂደቱ ነዉ ….. ስልክ ስትደዋወል… ቴክስት ስትላላክ…. “የኔ ቆንጆ” ስትባል “ኪኪኪኪ….” እያለች ስታስካካ ከርማ…. ምሳ ጋብዛ… እራት ከነ ቮደካና ሻንፓኝ ጋር ስትጋት…. ሆቴል ክፍሉ ድረስ ስትገባ… ጡቷን ገልጣ እያስጎበኘች…ጭራሽ ከሌላኛዉ ፓስተር ጋር ለ “ተሪ ሰም 3-sum” እራሏን እከማመቻቸት ደርሳ…. እንኳን እንትን ጥፊም ይደጋማል ስትባል ደግማ… አስደግማ…እምምም…! መቼም….
አንተ ፓስተር ሆነህ እኔ ዳዊትህ…
መቼ ተመችቶህ ትደገማኛለህ ….
ሳይሰብላት ሁለተኛዉ ቀን እንካ በሞቴ አላለችዉም…ፓስተር ተከስተን!
ያሳዘነኝ ምስኪኑ ባል ነዉ… ጋሽ ማላኩ የሺ ዳኛ…. እሱን ቤት አስቀምጣ ሚስት ሆዬ እንደ መላክ የምታየዉ ተከስተን ነበር…. ደግሞ “he was like an angle for me”… ምናምን ትላለች ወይ ፈጣጣነት…! ሰዉየዉ ሜስቴ ተደፈረች ይላል … እሷ ግን እሮማንቲክ ታሪክ ትነገረኛለች… ሳቁም ሳይቀራት….መደፈርና መማገጥ ሜኖሶታ አይለይ ይሆን እንዴ? ይባስ በሎ ቅሌቱ አይጋለጥ ብለዉ የተከላሉት አሸማጋዮች ያሰፍራሉ … እዉነትን በአደባባይ ለመግለጥ የሚፈሩ የሃሴትና የክፋት ከባ የደረቡ አሰመሳይ አላጋጮች ማለት እነሱን ነዉ!
ጭፍን ፍርድ አይሁንብኝ አንጂ ፓስተሮቹና ዘማሪ ነን ባዮቹማ ወጥ ከረገጡ… መንፈሳዊ እሴታቸዉን አተዉ ማጋጣ ከሆኑ ሰንብተዋል…! በክርስትና እና በእምነት ሽፋን አለማዉያን የማይደፍሩትን ወራዳ ነገር ነዉ የሚፈፅሙት….! እያየን እንዳላየ የምናልፋቸዉ ስንቶቹን ነዉ…? የአንዳዶቹ አልተገለጠም እነጂ ከዚህ የበለጡ በርካታ ታሪኮችን ገና እነሰማለን! አብዛኞቹ ፓስተሮች ሀኬተኛ ናቸዉ… መንፈሳዊነት ባለፈበት አለለፉም…. ለእነሱ ትልቁ ቁምነገር… ህዝብን ሰብስቦ እያንቻጩ ማጃጃል ብቻ ነዉ… በየመነደሩ ቸርች እየከፈቱ ገንዘብ ማጋበስ ነዉ ተቀዳሚ አላማቸዉ…! ስለሃገር… ስለወገን… ስለፍትህ… ስለነፃነት… ስለአንድነት… ስለሰባዊነት….ተሳስተዉ በአደባባይ አያወሩም….እነደዉም አያገበኝም ባዮች ናቸዉ! ይልቅ ስለሚነዱት መኪና… ስለሚለብሱት ሸሚዝ…
ስለሚበሉበትና ስለሚጠጡበት ሬስቶራነት ማዉራቱ ነዉ ለነሱ ክብር መስሎ የሚታያቸዉ….ሆዳቸዉ አምካቸዉ የሆኑ ሆናዋልና! ‘ፓስተረዬ…!’ እየተባባሉ መሸናገል ለእነሱ ከምንም በላይ ነዉ…፡፡ በአንዳቸዉም ላይ ቅንጣት ታህል የኢትዮጵያዊነት መንፈስም ሆነ ስሜት የላቸዉም… ከአሚሪካና ከናይጄሪያ ፓስተሮች የቀዱትን አክቲንግ መድረክ ላይ ወተዉ ለመተዉን ሙከራ ያደርጋሉ እንጂ አንዳችም እራሳቸዉን ለመሆን ጥረት አያደርጉም…፡፡ እና እደምን የህዝብ ሞራል በነዚህ ይቀኛል… እንደምንስ የህዘብ መንፈሳዊ ህይወት በነኝህ ይታነፃል? እነኝህ ሰዎች ኢትዮጵያዊ ማንነትን ለማክሰም ዋጋ ተከፍሏቸዉ የሚያገለግሉ ሁሉ ነዉ የሚመስሉት…! ደግሞ እኮ ጉራቸዉ… አይጣል ነዉ!….ከነሱም ብሰዉ አሻግረዉ ሌሎችን ለመተቸት ጣት ይጠቁማሉ! እርግጥ ነዉ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ እያጡት ከመጡት ነገር አንዱ እዉነተኛ መንፈሳዊ አባቶችን ነዉ… በየትኛዉም የእመነት መስመር ቢኬድ ሃይማኖት መሪዎችና አስመላኪዎች ሃኬተኛና አባያ ሆነዋል የሃኬትን እነጀራ ይበላሉና!
አዳሜ ይሆይ ነቄ መሆን ያለብ ይሄኔ ነዉ … ፓስትርን ማመን…. እምምም…!ክብር ማሳጣት ብቻ ሳይሆን ትዳር ማፍረስ ቤተሰብ መበተንም እያስከተለ ነዉ… ህዝበ ክርስትያ ሆይ ጠንቀቅ ይሄኔ ነዉ!!!!!
We will not approve any comment on this page for the safety of the family and ongoing legal cases
Thank you
Zehabesha Editorial Board
The post በፓስተር ተከስተ ላይ የወሲባዊ ቅሌት አቤቱታ ስላቀረበችው ወይዘሮ ጉዳይ የኔ አስተያየት appeared first on Zehabesha Amharic.