Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የኦሮሞ ስጋት ግልገል ነፍጠኛ ሳይሆን ግልገል ISOS ነው። –ለ ጀዋር መሓመድ –ከአየለ ገመቹ

$
0
0

በኦሮሞ ስም የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ፖለቲካም ይሁን እምነትም ይሁን ሌላም ቢሆን ግልጽ በሆነና የሌላውን መብት በማይነካ ከሆነ በሰላማዊ የሚደረገውን ማስገደድ በሌለበት የፖለቲካ ሃሳብም ሆነ የእምነት ሰበካ ላይ ተቃውሞ የለኝም።ምክንያቱም ማንኛውም የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት ሊኖረው ይችላል ማነኛውም ሰው የፈለገውን እምነት ሊከተል ይችላል። ማስገደድ የሚባለው እና በአንድ ነገር ለይ ተሸፍኖ የሚደረገውን ድብቅ እንቅስቃሴ ግን እቃወማለው።

The Oromo issue on Al Jazeera. By Yilma Bekeleጀዋር መሐመድ ከትውልዱ ልጀምር አባቱ ኦሮሞ(እስላም) እናቱ አማራ(ክርስቲያን) እንደሆነ ነው የሚናገረው ። ታዲያ  ለምንድነው ምክንያት እየፈለገ ስለኦሮሞ ተቆርቋሪ መስሎ አማራን የሚያጥላላ ንግግር የሚናገረው? እውን ጀዋር መሓመድ የኦሮሞ ህዝብ ተቆርቋሪ ነውን? ስለ ኦሮሞ ህዝብ ተጨንቆ ነውን? በየመድረኩ I am Oromo first  ብሎ ሲናገር የከረመው እንደውም እኮ ለጀዋር መገኘት ትልቁን ድርሻ ያበረከተችለት እናቱ ናት እናቱን የናቀ እና ያንቋሸሸ ሰው ለኦሮሞ ህዝብ ሊጨነቅ ይችላልን? I am Oromo first ማለት ምን ማለት ነው? ቃሉን  ላስተዋለው መልሱን እዚው ላይ ይገኘዋል ።

በነጀዋር እና መሰሎቹ አገላለጽ ኦሮሞ ማለት እስላም አማራ  ማለት ደግሞ ክርስቲያን ማለት ነው። እንግዲህ ልብ በሉ በነጀዋር መሐመድ መስመር የሚሄዱ ሁሉ  የኦሮሞ ግንዱ ወይም መነሻው እስላም ነው ብለው የሚናገሩ  ናቸው ታዲያ የጀዋር ቃል I am Oromo first የሚለው ቃል ሲተረጎም I am Islam first ማለት ነው። በግልጽ ቃንቋ I am Islam first ማለት ይችላል ነበር። ነገር ግን በኦሮሞ ስም ተሸፍኖ ድብቅ አጀንዳውን ማከናወን ግን አይችልም። የአማርኛ ቋንቋንም ለይም ተቃውሞ የሚያሰሙት አማራን ጠልተው ሳይሆን ክርስትናውን ጠልተውት ነው ኦሮሞ ድሮም አሁንም ከሱማሌ ጋር ይጋጫል ከኬኒያ ጋር ይጋጫል ብዙ የኦሮሞ ልጆች በዚህ ግጭት አልቀዋል የሚገርመው እነዚህ ግጭቶች እስካሁንም አሉ አንድም ቀን ግን ሱማሌን የኦሮሞን ህዝብ ጨረሰች ብለው አልያም ኬኒያ የኦሮሞ ህዝብ ገደለች ወይም ጠላቶች ናቸው ብለው በነጀዋር መሐመድ እና በመሰሎቻቸው አፍ ሲነገር ሰምተን አናውቅም። ምክንያቱም ደግሞ ግልጽ ነው። የነሱ ተቃውሞ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ሳይሆን በኦሮሞ ምድር ላይ ISOS መስርቶ ክርስትናን ማጥፋት ስለሆነ ከላይ እንደገለጽኩት አማራ ማለት ክርስቲያን ስለሆነ አማራን እንደጠላት የያዙት እና የኦሮሞ ጠላት አማር ነው ያሉት በግልጽ ቋንቋ የእስላሙ ጠላት ክርስቲያኑ ነው ማለት ነው።

አዳምና ሄዋንን ሰይጣን ከገነት ሲያሶጣቸው በእባብ ተሰውሮ ነው። እንጀዋር መሓመድም በኦሮሞ ምድር ላይ የደም ጎርፍ ለማምጣት በኦሮሞ ስም ተሰውረው ለኦሮሞ  ተቆርቋሪ መስለው ነው። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (OLF)ስም በሰፊው በመሰግሰግ ትግሉን እየመሩ ያሉት እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉት እነዚው የነ ጀዋር ስርዓት አራማጆች ናቸው። እንደውም ኦሮሞ እስላማዊ ነጻነት ግንባር (OILF)የሚል የመጨረሻ ራእያቸውን የሚያስፈጽሙበት ግሩፕ እንቅስቃሴ ከጀመረ እና መሳሪያ ካነሳ ቆየት ብሏል። እናም እነ ጀዋር መሓመድ ለኦሮሞ ነጻነት እየታገልኩኝ ነው በሚል ሽፋን ከኦሮሞ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት እና ሃይል ለማሰባሰብ እየጣሩ ነው ።

ISIS(Islamic State of Iraq and Syria) ማለት ሲሆን እነጀዋር መሐመድ ደግሞ ISOS (Islamic State of Oromo and Somalia) ብለው በመነሳት የኦሮሞን ምድር ኢራቅ ለይ እንደምናየው ሶሪያ ለይ እንደምንመለከተው የኦሮሞን ህዝብ እስልምናን በግድ እንዲቀበል አልያም  በሩቅ የምናየውና የምንሰማውን እንደ ኢራቅና ሶሪያው ISIS እንደ ናይጄሪያው ቦኮሃራ እንደ ሱማሌው አልቃይዳ በአገራችን ሊያመጡ የሚንቀሳቀሱ ግሩፕ ናቸው።

እነ ጄዋር የገንዘብ ችግር የለባቸውም ምክንያቱም የሚረዱት በአረብ አገሮች ማለትም ሳውዲ፣ ግብፅ፣ ኳታር፣ ኢራቅ፣ የመን፣ አፍጋኒስታን በመሳሰሉት ስለሆነ የፋይናስ እጥረት የላቸውም።

እንጀዋር መሐመድ ኢትዮጵያን በአንድ ላይ ማሸነፍ ስለማይችሉ ኦሮሞን በመገንጠሉ ስራ ተጠምደዋል። ለዚህም ድጋፍ ማግኛ እና ለኦሮሞ ህዝብ የቆሙ ለማስመሰል በአልጀዚራ ተሌቪዝን ላይ I am Oromo First በማለት የገለጸው አነጋገር I am Islam First ማለቱ እንደሆነ የነጀዋር አራማጆችን ማወቅ በቂ ነው ኦሮሞ ማለት እስላም አማራ ማለት ክርስትያን እንደሆነ የጀዋር የትውልድ ቦታ ያሉትን ሰዎች ሄዶ ማወቅ ይቻላል።|<< እኔ ትውልድ ቦታ 99% እስላም ነው አንድ ክርስትያን ቀና እላለው ቢል በሜንጫ ነው የምንለው>> የጀዋር ንግግር ነው። ያቼ ሜንጫ ለነጀዋር የጽድቅ ሜንጫ ናት በሜንጫ የክርስትያንን አንገት ቆርጠውባት በገነት 7 ሚስት የሚያገኙባት ጽድቅን ሰራን ብለው የሚናገሩበት ነው። ለዚህ ነው እየተዘጋጁ ያሉት ለዚህ ዝግጅታቸው ነው የኦሮሞ ህዝብን መደበቂያ አድርገው ለኦሮሞ ነጻነት እንደሚታገሉ በማስመሰል ለኦሮሞ የሞት ድግስ የሚደግሱለት። በዚህ አጋጣሚም መጥቀስ የምፈልገው ሙስሊም እህቶቻችን የዚህ ጥቃት ተጠቂ መሆናቸው ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም። ማንኛውም ህብረተሰብ የፈለገውን ሃይማኖት የመከተልም ሆነ የማስተማር መብቱን አከብራለው ነገር ግን በግድ ተቀበል የሚል ሊኖር ግን አያስፈልግም።

እነጀዋር መሐመድ ከአረብ አገር በሚያገኟቸው የገንዘብ እርዳታ በመታገዝ ኦሮሞን እስላም ሊግ (አረብ ሊግ) ውስጥ ለማስገባት እና የኦሮሞ ህብረተሰብንም በግድ ለማስለም የሚንቀሳቀሱ የሰላም ጠሮች እንደሆኑ ሊታወቁ ይገባል። ኦሮሞን መነጠል የፈለጉትም ትልቁ አጀንዳቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነች መቼም ቢሆን ሊያሰልሟት እና ሃሳባቸው ሊተገበር እንደማይችል ስለሚያውቁ ለድብቅ አላማቸው ኦሮሞን ገንጥለው ለመምታት እንዲያመቻቸው Oromoia free, I am Oromo first እያሉ ፖለቲከኛ መስለው በኦሮሞ  ህዝብ ላይ የISOS (Islamic State of Oromo and Somalia) ለማድረግ ጦርነት አውጀውበት በድብቅ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ኦሮሞን ከሌላው ህብረተሰብ ለመለየት ከሚጠቀሙበት አነጋገር ብንመለከተ 1. መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ,2. ኦሮሚያ ነጻ, 3. ኦሮሞ ከአበሻ ጋር መጋባት ይቁም 4. ኦሮሞ ለኦሮሞ የሚሉ ሲሆኑ ኦሮም ከሱማሌ ጋር ወይንም ከሱዳን ጋር ቢጋቡ ምንም ግድ የላቸውም። ምክንያቱም የነጀዋር ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ ስለሆነ። እዚህ ጋር በኔ አመለካከት ማንም ኢትዮጵያዊ ከሱማሌም ጋር ከሱዳኑም ጋር ወደው ከተጋቡ ተቃውሞ የለብኝም ለመጥቀስ የፈለኩት የነጀዋር አካሄድ የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ ለይ የሞት አዋጅ አውጀው እንደሚንቀሳቀሱ ለማሳየት ነው።

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ኦሮሞ ከኢትዮጵያ  ተገነጠለች ማለት በነጀዋር መሐመድ እና መሰሎቻቸው የISOS  የግዳጁ  አዋጅ በኦሮሞ ህዝብ ላይ አውጀውባት  ዛሬ እንደምናየው የኢራቁ እና የሶሪያው ISIS የራሳቸውን ዜጋ እንደበግ እንደሚያርዱት የናይጄሪያው ቦኮሃራ በናይጀሪያው ላይ እልቂት እንደሚፈጽመው የሱማሌው  አልቃይዳ በሱማሌው ላይ ጭፍጨፋ እንደሚያደርገው OLF (Oromo Liberation Front) የነበረ ወደ OILF (Oromo Islamic Liberation Front) ተቀይሮ በሩቅ የምናየውን ወገን ወገኑን ሲያርደው እነጀዋር መሐመድ ወደ አገራችን ሊያመጡት ሳይታክቱ እየሰሩ እንደሆነ ልናውቅባቸው ይገባል።

ለጀዋር መናገር የምፈልገው በኦሮሞ ህዝብ ላይ በአንድም በሌላም መልኩ ያንተ ድብቅ እንቅስቃሴ እንዳለ  ስለሚታወቅ ከተጠያቂነት እንደማታመልጥ ላስገነዝብህ እወዳለው። እናም እኛን የሚያስፈራን ግልገል ነፍጠኛ ሳይሆን ግልገል ISOS ነውና አረፍ ብትሉ ጥሩ ነው። ኦሮሞን ነጥሎ  መምታት አይቻልም የኦሮሞ ህዝብ ያለምንም ጭቆና እንዲኖር እንፈልጋለን።

ጀዋርና መሰሎቹ እንድታውቁ የምንፈልገው እኛ ኢትዮጵያዊ ነን። በኦሮሞነቴ የምኮራ ኦሮሞኔቴን ማንም ሊነጥቀኝ የማይችል ኢትዮጵያዊ ነኝ። የትውልድ መንደሬ አንቦ የኦሮሞ ምድር አገሬ ግን ኢትዮጵያዊ ነው። እኔ ደግሞ እላለው I am Ethiopia first ስለዚህ በኦሮሞ ስም እየቀለዳችሁ የአረቡን አለም የደም ጎርፍ ለማምጣት የምትጥሩ በሙሉ በኢትዮጵያ ምድር ላይ አትችሉም። የትኛውም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ አይፈቅድላችሁም ስለዚህ ግልገል ISOS ተርምሳችሁን አቁሙ።

የኦሮሞ ሊህቃን(ሙሁራን) እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም ያገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የኦሮሞ ህዝቦች ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ነጥሎ ለመምታት የሚጥሩትን እና በኦሮሞ ለትፋት ያሚያዘጋጁትን በነቃ ልቦና የሚሰሩትን ስራ ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብ እና የኦሮሞን ህዝብ ከተጋረጠበት ጥፋት ትጠብቁት ዘንድ አላፊነቱ የሁሉም ስለሆነ ኦሮሞን ለማጥፋት የተሰማራውን ሃይል በህብረት ማሳፈር አለብን ። በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱትን የጥፋት ሃይሎች ክትትል እንድታደርጉባቸው ጥሪዬን አስተላልፋለው።

ከ-አየለ ገመቹ

The post የኦሮሞ ስጋት ግልገል ነፍጠኛ ሳይሆን ግልገል ISOS ነው። – ለ ጀዋር መሓመድ – ከአየለ ገመቹ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>