እምብኝ በል-ጎፍንን
እዬገደለ የመጣ ቅጥረኛና ፋሽስት ኃይል የሚኖረውም እየገደለ ነው።
የሰው ልጅ ህይወት እጅግ በጣም ውድ ነው በድሮው ጊዜ የሰው ልጅ ሕይወት ይቅርና ሰው የሚመገባቸው እንሥሣትም ሊታረዱ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቡናው ሲፈላ እጣኑ ሲጨስ ጮፌው ሲነሰነስና ሊታረዱ ሲቀርቡ አራጁ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በአዕምሮው ላይ ሥነ-ልቦናዊ መረበሽ እንደሚፈጥርበት ይታመናል። የለየለት ደም አፍሳሽ ከሆነ ግን ይህ ላይከሰት ይችላል። ታራጆቹ እንሥሣትም በአራጃቸው ወይም በገዳያቸው እጅ ሲገቡና ሲታሰሩ ጭንቀትና መረበሽ ሊኖር እንደሚችል እገመታለሁ። ሕይወት አንዴ ካለፈች አትመለስምና ከባድ ጫና ያሳድራል ነገሮች ሁሉ ይጨልማሉ ይህ ግን የሚሆነው ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡ ላደረበትና አርቆ ለሚያስብ ብቻ ነው። ለአረመኔዎቹና አምባ-ገነኖች ይህ በፍጹም አይገባቸውም።
በሰው ልጅ ላይ የሚፈፀሙ የግድያ ሁኔታዎችን ስንመለከት ዘርፈ ብዙ ሆነው እናገኛቸዋለን።-በሕግ ዓምላክ በሚባልበትና የሕግ የበላይነት ባለበት አገር በሰው ልጅ ላይ ሞት የሚፈረደው ተከሳሹ ወንጀል መፈጸሙ ታምኖበት በፖሊስ ተይዞ በአቃቢ ሕግ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ቀርቦ የፈጸመው ወንጀል በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ የፍርድ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ወንጀሉ በሞት የሚያስቀጣ ከሆነ ዳኛው ወይም ዳኞች የሞት ፍርድ እንዲበየንበት ያደረገውን የወንጀል አፈጻጸም ድርጊትና ምክንያት በዝርዝር ከሕጉ ጋር እያገናዘቡ ካስረዱና ብዙ ተመልካችን እንዳያስደነገጥ ጥንቃቄ በማድረግ ወይም ዝግ በሆነ ችሎት በወንጀለኛው ላይ የሞት ፍርድ ይፈጸምበታል። ይህ እርምጃ የሚወሰደው የአካባቢውን ሕዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ፤ሰላም እንዲሰፍንና የተረጋጋ ለማድረግ ዳግም የዚያ አይነት ወንጀል እንዳይፈጸምና ሕብረተሰቡ በሥነ-ምግባር የታነጸና በሕግ የሚገዛ እንዲሆን ለማድረግ ፤ የወንጀል መፈጸም ተግባርን እንዳይስፋፋ ጤናማ ሕብረተሰብ ለመገንባት የሚወሰድ የመንግሥት እርምጃ ነው። የፖሊስ ፤ አቃቢ-ሕግና የዳኛ ተግባሮች በፍጹም የማይለያዩ ተያያዥነት ያላቸው ሲሆን የአንድን ማሕበረሰብ ደህንነት ፤ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ለማድረግ ደረጃ በደረጃ በየተቋማቸው ማድረግ የሚገባቸውን ፈጽመው መገኘትና አንዱ ሌላውን እያገዘ በጋራ የሚሰሩት የተቀናጀ የሥራ ውጤት ግቡን ይመታል።
ግለሰቦች ከሕግ በላይ በሆኑበትና በሕግ ዓምላክ በማይባልባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሚኖረው ግድያን ወስደን ስንመለከት ደግሞ ሁኔታዎች ቦታቸውን ለቀው በግልባጩ እናገኛቸዋለን። ከዚህ በታች ስማቸውን የጠቀስኳቸው አገር መሪዎች በዓለም ላይ እንዲታወቁ ያደረጋቸው ተግባር ምን እንደሆነ አንባቢዎቼ በግልጽ የሚረዱት እንደሚሆን አምናለሁ። «ዘለው ኦፍ ጃንግል» (the law of jangle )«የጫካ ሕግ» በሚል የተፃፈች ትንሽ መጽሐፍ አንድ ወቅት ላይ አንብቤ ነበር። ያች ትንሽ መጽሐፍ ያዘለችው መልዕክት ሕግ ለምን እንደሚወጣና ጠቀሜታው ምን ያህል እንደሆነ ያሳደረብኝ ግንዛቤ እስከ መቼውም አይረሳኝም።መጽሐፏ በጫካ ስለሚኖሩ የዱር አራዊት(እንሥሣት) ህግ አለመኖርና ጉልበታሙ ወይም ጉልበታሞች ተባብረው ጉልበት የሌለውን አስገድደው ገድለው ተመግበው እንደሚያድሩና እንደሚውሉ እንደሚኖሩ ግልጽ አድርጋ ታሳያለች። በሩዋንዳ ፤ካሞቦዲያ እንዲሁም እስከ አሁን ድረስ ትኩሳቱ ባልበረደው ሶሪያ የምንሰማውና የምንመለከተው በዘረዘርኳቸው አገሮች የተካሄደውና እየተከሂያደ ያለውን ስንመረምር በምን አይነት መርህ እየተጓዙ እንደሆነና ጨካኞችና አምባገነኖች የሚፈጽሙትና የፈጸሙት ተግባር ከጫካው ሕግ ያልተለየና አረመኔያዊ ተግባር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
አገርንና ዳር ድንበርን ለማስከበር ይሞታል፤ በሀሰት በፍርደ ገምድል ዳኛ ተፈርዶም ይሞታል፤ ሲሰርቁና ሰው ሊገድሉ ሲሞከርም ይሞታል ፤ በትንታም ይሞታል ፤ሌባ በረት ሲከፍት ፤ ከባለትዳር ሴት ሲልከሰከሱም ይሞታል፤ የሰው ቤት ሲበረብሩም ይሞታል፤ በሕመምና እድሜ ሲደርስም ይሞታል የሰው ልጅ ሕይወት ማለፊያዋ መንገድ ብዙ ነው። የእኔ መነሻ ግን ይህ አይደለም ሥልጣን ለመያዝና ከያዙ በኋላም ጨካኝና ነብሰ ገዳይ ሆነው ለመቀጠል የሚያስቡ አርመኔዎችን አስመልክቶ ትንሽ ለመግለጽ ያህል ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የዘውዳዊ አገዛዝ ዘመን የ1966ቱ የየካቲት የሕዝብ አልገዛም ባይነት ለማንበርከክ የተወሰዱትን እርማጃዎች ፤ቀደም ሲል በአርሲ ፤በጎጃምና በትግራይ የአርሶ አደሮችን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማፈን የተደረግውን እርማጃ ፤በደርግ የወታደራዊ አገዛዝ ዘመን ለመገንጠል በተነሱ ጎጠኞች(ጠባብ ብሔረተኞች) የተወሰደው ፤አዲስ ሥር ዓት እንገነባለን ብለው በሕብረ- ብሔር ድርጅት ተቃውሞ ያነሱትን ትግል ለመበተን የተደረገውን ጥቃት ፤ህወሃት ከኤርትራ ጋር በጫረው ጦርነት የያለቁት የሁለት ወገን ትውልዶችና፤ «ራስ ሳይጠና ጉተና እንዲሉ» ወደ ሶማሊያ ሄደው ያለቁት ኢትዮጵያውያን ፤ ወደ ሩዋንዳ ፤ኮንጎ፤ ኮርያ የሄዱት ኢትዮጵያውያን ፤ ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ በስውር የፈጀው ታጋይ የትግራይ ወጣት ፤ በቀን በአደባባይ መሠረት በሌለው ቂመኝነት የተገድሉት ኢትዮጵያውያን አሁንም በሰበብ አስባቡ እተጨፈጨፉ የሚገኙት ዜጎቻችን ሕይወት ቀጠሮ ተይዞለት በአዲስ ዓመት ይመለሳል የሚባል እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን ። በደርግ ጊዜ ደርግ ሕዝቡን ፈጀው እያሉ ነፍጥ አንስተው የተንቀሳቀሱት የዛሬዎቹ ገዥዎቻችን ለምን ሕዝባችን ይጨፈጭፋሉ?ወይስ ከጌታ ትእዛዝ ወርዶ ተፈቅዶላቸው ነው?ደርግ በሕዝብና በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ባለሥልጣናት ላይ ኢ-ፍትሃዊ እርማጃ ወሰደ ያ አስፈሪ ሞት በራሱ ላይ መጣ። ህወሃት ከዚያ አስፈሪ ሞት የሚያመልጥበት ምን ብልሃት አገኘና ነው እንዲህ በእብሪት ተወጥሮ ሕዝብን በጅምላ የመጨፍጨፍ ተግባሩን እንደ ሰደድ እሳት እያቀጣጠለ ያለው? ግራኝ መሐመድ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነበር በውጭ ድጋፍና እርዳታ በክርስቲያን ሕዝባችን ላይ ጨካኝ ጭፍጭፋ እንዳደረገ ታሪክ ዘግቦት አልፏል ። ቶርኮች ፤ ግብጾች እንዲሁም በዓረቦች ድጋፍ በሱዳን መሐዲስቶች(ድርቡሽ) እየተባለ የሚታወቀው በተመሳሳይና በተደጋጋሚ በክርስትና እምነት(በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ሃይማኖት) ላይ ዘምተው አልተሳካላቸውም።ኢትዮጵያዊ የእስልምና እምነት ተከታዮችን እስላማዊ መንግሥት ሊያመጡብህ ነው ብሎ ሕዝብን ማስፈራራትና የማከፋፈል ዘመቻ ማካሄድ የት ሊያደርስ ነው? ለመሆኑ ህወሃት ምንስ እምነት ኖረውና ነው እስላማዊ መንግሥት ክርስቲያናዊ መንግሥት እያለ ሊሰብከን የከጀለው ? ይህ ከንቱ ውዳሴ ነው። ስለዚህ ሕዝቡ ጀሮውን ሊሰጥ አይገባውም ባይ ነኝ። መጀመሪያ የዜጎችን መብት ማክበር ይቅደም።የቻይና ባለሀብቶች ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ተወልደው በአደጉበት እትብታቸው በተቀበረበት በአጥቢያቸው በአገራቸው ምን እየሆኑ እንደሆነ የሚያውቀው ህወሃት ዜጎቼ ተደፈሩ ብሎ ለምንስ እርምጃ አልወሰደም ? ከዚህ በላይ መርከስና መውረድ የበለጠ ምን ሊመጣ ይችላል? አቶ በረከት እናቱ ሲቀበሩ መድፍ እንዲተኮስላቸው አስደርጓል እናቱ ቢሞቱ እህት እንኳ የለውም የሚያዝን ልብ? እግዚአብሔር ያሳያችሁ!! እውን እኒህ ጠይም ደማማ እናት እንዲህ ተፈንክተው ደማቸውን እያዘሩ እንዲሄዱ ማድረግ ይገባል ? ምን አይነት ሥልጣኔስ ሊባል ነው? አሁን እኒህ እናት ጠቅላይ ሚንስቴር ለመሆን መንግሥትን ለመፈንቀል እያሸበሩ ነው? እንዲህ የተቀጠቀጡት? ኢትዮጵያ አገራቸው አይደለችም ? ወይስ ኢትዮጵያዊ መሆን የግድ ካልተቀጠቀጡና ደማቸውን እያዘሩ ካላሳዩ (ካልታዩ) ኢትዮጵያዊ ዜግነት አይገባቸውም ?ኢትዮጵያ እኮ የሁላችን አገር ናት። እንዴት ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያዊ እናቱን ደም እያዘሩ እንዲሄዱ ያደረጋል? ምን አይነት ሰው በላ ሥርዓት ነው የተፈጠረብን? ለመሆኑ ይህ በህወሃት ዘመን ተወልዶ በህወሃት የታጠቀ የአጋዚ ነብሰ በላ ጠመንጃ አንጋች ኃይል እናት እህት ሚስት ይኖረው ይሆን ? ሴቶችን እንደ ፊውዳሉ ሥርዓት ማናናቄ አይደለም እኒህ እናታችን ሴትና በእድሜ ጠና ያሉ ናቸው በምን ሂሳብ ነው የተደበደቡት በምን ምክንያት ነው ደማቸው እንዲፈስ የተፈረደባቸው? ይህ የህወሃት አጋዚ ሠራዊት አደብ የሚገዛውና ለሕግ የሚገዛው መቼ ነው ?እኛ ኢትዮጵያውያንስ መቼ ነው እንደበግ እየተጎተትን ከመታረድ የምንድነው? ድምፃችን ይሰማ በማለት ሁለት ዓመት አንዲት ጠጠር ሳይወረውሩ፤አንዲት ቅጠል ሳይበጥሱ የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው ጥያቄ ስለአቀረቡ ችግሩ ምኑ ላይ ነው? መልሱን መስጠት ወይስ እያፈሱ ማጎርና መደብደብ በጥይት መቁላት? ኧረ እናስተውል ጎበዝ እስከ መቼ ነው ቀን እንዲህ ሊገፋ የሚችለው ?አሸባሪውስ ማን ሆነና ነው? አሸባሪ የሚሉት ለእምነታቸው ነፃነት የሚታገሉትን ነው ወይስ ከነዚህ ለእምነት ነጻነት ከሚታገሉት ኢትዮጵያዊ እስላሞች ውስጥ ሰርጎ የገባ አለ በሚል ነው ? ሰርጎ የገባ ካለ ለይቶ ማውጣትና በሕግ እንዲቀጣ ማድረግ የማን ተግባር እንደሆነ ከጠፋቸው እውነትም ጠፍተዋል ማለት ነው ቢጠፉም ይሻላቸዋል።
እየገደለ የመጣ ፋሽስታዊ ኃይል የሚኖረውም እየገደለ ነው። ያልኩበት አብይ ምክንያት ህወሃት በወርሃ የካቲት 1967 ዓመተምህረት እንደ ድርጅት ከመቆሙ በፊት የተለያዩ መጠሪያዎችን ይዞ ይንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን በመጨረሻ ህወሃት በሚለው ስም ጸንቶ ሲቀጥል ከቀን አንድ ቀን ጀምሮ በሰው ግድያ የተጀመረ የራሱን አባላት ሳይቀር እየበላ ያደገ ድርጅት ሲሆን 17 ዓመት ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት 22ዓመት መላ አገሪቱን ከወረረ በኋላ ጊዜውን ያሳለፈው ሰው በመግደል ነው። ሰው መግደልና በደም መጠማት ደግሞ በሕክምና ሊድን የማይችል በሽታ መድኃኒቱ በመሰል እርምጃ(አክሽን )ሊወገድ የሚችል ከቫይረስ የከፋ በሽታ ነው። ህወሃቶች የፈለገው ብዛት ያለው ሰው ይሙት አንድ ሰው ይሙት ቅንጣት ታህል አይሰማቸውም የሚሰማቸው የሰው በላው ሥርዓት አስከባሪ ወይም እንደ አበደ ውሻ የሚክለፈለፈው አንጋች ሲሞት ብቻ ነው። ሰው የገደለ እኮ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ራሱን ለመሸሸግ መታገል አለበት።እንዴት ሰው ገድሎ ታማኝነቱን ማስመስከር እንደ ዝና ተቆጥሮ ይሳለቁብናል? ቤተመንግሥታችንስ እንዴት የነብሰ ገዳዮች መናኻሪያ ይሆናል?እየገደሉን መጥተው እንዴት እየገደሉን እንዲኖሩ እድሉን እንሰጣቸዋለን? ስማቸው ተቆጥሮ የማያልቅ ወንዝ የማያሻግሩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወይም ከአውሮፓና አሜሪካ ሄዶ ኢትዮጵያውያንን ከህወሃት የአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ሊያወጣ የሚችል እንደሌለ እንቅጩን እንነጋገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወጣት ኢትዮጵያውያን የሚመራው ሰማያዊ ፓርቲና አሁን ከእንቅልፉ የባነነው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን እንደ አንድ ግኝት እንደ አንድ ርምጃ እንውሰድና ትግሉን አጋግሎ መቀጠል ያለበት ሲሆን ከዚያ ባሻገር ያለው ግን መድሕሃኒቱ ያለው ከየሁላችን እጅ ነው ። እምብኝ አልገዛም ማለት ፤ ፍርሃትን ማስወገድ ፤ ራስን ነፃ ለማውጣት መታገል ፤መደራጀት ፤ አንድነት መፍጠር የህወሃትን ሰርጎ ገቦችና ሰላዮችን ማዋከብና ማጋለጥ ፤የሚሠሩት ጸረ-ሕዝብ ተግባር ህወሃት በአማራ እናትና እህቶቻችን ላይ የሚያመክንና የአማራውን ሕዝብ ቁጥር ዝቅ እያደረጉ ከሁሉም አካባቢ እያፈናቀሉ እየገደሉ ዘሩን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ድርጊት በቀጣይነት ማጋለጥ በርን ከፍቶ አለማስገባት…ወዘተ እንጅ እንደ ብሉይ ኪዳን ቀኙን ሲመታህ ግራውንም ስጠው ወይም በየተራ እንደ ዓመት በዓል በግ እየተጎተቱ መታረድና በየከርሸሌው እየገቡ በፈላና በቀዝቃዛ ውሃ መቀቀል በሌባ ጎማ ተዘቅዝቆ መገረፍ፤ በኤሌክትሪክ ሽቦ መጠበስ ፤በሴትና በወንድ ብልት ወስጥ አሰቃቂ ተግባር በመፈጸም የገደሉትን ሰው ዘቅዝቆ ማንጠልጠልን በመኪና መጎተት በደርግ ጊዜ ከነበረው በሚበልጥ ሁኔታ መዋረድ እንዴት እንዲቀጥል እድሉን እንሰጣቸዋለን? እኛም ቤት እሳት አለ መባል አለበት። ነፍጥ ወይም ጠመንጃ አንግቶ የሚንቀሳቀስ ኃይል ካለም የህወሃትን የመከላከያ ሠራዊት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማዋከብና ቢያንስ ወደ ሕዝብ ያዞረውን መሣሪያ እንዲያነሳ ማድረግ፤ በህወሃት ፖሊስ ፤ ደህንነትና የመከላከያ ሠራዊት፤በካድሬው ላይ የመበተን ወይም በውስጡ ያለው ቅራኔ እንዲባባስ የፕሮፓጋንዳ ሥራ አዘውትሮ መሰራት አለበት ወደዚህ ለመግባት የሚያስችሉ ብዙ ክፍተቶች አሉ በፖሊስና በመከላከያ በደህንነት ውስጥ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር የተያዘው ከአንድ ጎሳ በመጡ ስለሆነ ሌላውን ለማነሳሳት ለም ሆኖ ያለ ነጥብ ነው። በግንባሩ በውስጡ የተፈጠረውን የእኔ እቀደም እኔ ሽኩቻም እንዲባባስ መገፋፋት ይገባል በተጨባጭ ያየነው የግንባሩ አባላት ባኮረፉ ቁጥር እንዳያፈነግጡ ተሰርቶ የማያውቅና ራሱ ባወጣው ሕግ ላይ እንኳን ያልሰፈረ 3 ጠቅላይ ሚንስቴር ወዘተ…የፖለቲካ ሥልጣን ከችሎታና ከአቅም ብቃት የተመዘነ ሳይሆን ላለመቀያየም የሚደረገው ጥረት ውስጡ ምን ያህል የነኮረና የበሰበሰ እንደሆነ ስለሚያሳይ ይህን መጠቀም ያሻል። በግብር የሚሰበሰበው ገንዘብ ገቢ እንዳይሆን ማድረግ ፤ ከውጭ የሚገኘውን እርዳታ እንዳይሰጥ ማድረግ በማንኛውም አይነት መንገድ የሚገኘው ገቢ ለአገር እድገትና ልማት ሳይሆን የሚውለው የህዳጣኖችን ከርስ መሙያና ፍላጎት ማስተናገጃ እንጅ ለሕዝብ ብሶትና ችግር ስለማይውል ይህን በጡንቻው የሚያምን ኃይል ለማሽመድመድ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንዲወርድ ማድረግ ማዳከም ገበሬው ፤ነጋዴው ፤ ሌላው ግብር ከፋይ አልከፍልም እንዲል ማድረግ ያስፈልጋል። ተተኪ ትውልድ እንዳይኖር የተስማሙ ጭፍኖችን በማሳከም በሕብረት ለአንዲት ኢትዮጵያና ለአንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም አይነት ዘርፎች መስዕዋትነት መክፈል ይገባናል። ኢትዮጵያ ተተኪ ትውልድ እንዳይኖራት የማድረጉ ዓላማ የማን እንደሆነ አስፈፃሚው ማን እንደሆነ እንተዋወቃለን። ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆንን የጠሉና ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ላለመጋፈጥ ታሪክን ሸምጥጠው የካዱ ሁሉ ፈጥነው ችግራቸውን ቢያስተካክሉ ይበጃቸዋል። አዎ ኢትዮጵያ አሁን ከራስዋ በበቀሉ የአገር ውስጥ ጣሊያኖችና ከውጭ እንግሊዝና ጣሊያን አጥልተውብን በሄዱት የመከፋፈልና የእርስ በርስ አለመተማመን ምክንያት ችግር ገጥሟታል ።ነገር ግን በቅርቡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ትሆናለች። ያኔ ታዲያ እነዚህ የእናት ጡት ነካሾችና የበሉበትን መሶብ የደፉ የአገር ውስጥ ጣሊያኖች ጀንበር ትጠልቅባቸዋለች፤አንገታቸውን እንዲደፉ የግድ ይሆንባቸዋል።ለሆዱ ያደረው የሚበዛ ቢሆንም እውነቱ የት ላይ እንዳለ መርምረው ያወቁ ወይም የሚያውቁ በዚህ ሥርዓት ውስጥ ስለሚገኙ ምርቱን ከገለባው የመለየት እንቅስቃሴም ሊሰራ ይገባል።የራስን ደጋፊ ኃይል በየተቋሙ መፍጠር ካልተቻለ መሣሪያ አምላኪ የሆነው ቡድን የውስጡን ቅራኔ ጋብ በማድረግ ነገሮችን በመለጠጥ የተለከፈበትን ወረርሽኝ ወደ ሌላው እያላከከ እድሜ ለመግዛት ስለሚችል የዚህ ዓይነቱን እድል አለመስጠትና በሩን መዝጋት አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን በጣም ጠቃሚ ነው። ሥርዓቱ መበስበሱን ለማየት ሩቅ መሄድ አያስፈልግም የአማራው ነገደ ብሔር ዘሩ እንዳይራባና ቁጥሩ እንዲቀንስ የተደረገው ፀረ-ሕዝብ ተግባር ቀላል አይደለም ነገር ግን ምሥጢሩን ደብቆ ለመያዝ አለመቻል ዋና ምልክት ነው። አሁንም ይህን ትኩረት ሰጥቶ ቢቀሰቀስበትና ለዓለም ሕብረተሰብ እንዲደርስ ቢደረግ አንዳንድ ጤናማ የሆኑ አገሮች ድጋፋቸውንና ግንኙነታቸውን ስለሚያቋርጡ ሥርዓቱ ብጥስጥሱ የሚወጣበት ጊዜ እየፈጠነ እንዲሄድ ያደርጋል። የታሰሩ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ድርጅት አባላት እነአንዱ ዓለም አራጌ (የሕሊና እስረኞች) የታሰሩበትን መርምሮና ግልጽ አድርጎ ማቅረብ አንዱ የማጋለጥ ሥራ ተሰራ ማለት ነው። ክቡር አምባሳደር እምሩ ዘለቀ እንደጻፉት ሳይቦዝኑና ሳይሰላቹ በተቻለው መንገድ ሁሉ ሥርዓቱን ማዋከብ ያስፈልጋል።
(Adolf Hitler German-Rodolfo Graziani Italy– Joseph Stalin Soviet Union -Omar Hassan al-basher Sudan–Mengistu Haile Mariam- and Meles Zenawi in Ethiopia)
ራዶልፍ ሂትለር በጀርመን አገር የሚኖሩ ይሁዳዎችን ጨረሰ ፤ አዶልፎ ግራዚያኒ አውሮፓን አቋርጦ ባሕር ተሻግሮ በአፍሪካ ምድር የቅኝ ተገዥ አገሮችን ለማስፋፋትና ሀብታቸውን ለመዝረፍ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ ሕዝባችን ጨረሰ ፤ጆሴፍ ስታሊን የብላድ ሚር ኢሊችን ሥልጣን ከተረከበ በኋላ እንደ ሬድ ተረርና የስታሊን ዱላ በሚል የራሱን ሕዝብ ጨፈጨፈ ፤ የሱዳኑ ኦማር ሀሰን አልበሽር ከዐረብ ጋር ያልተዳቀሉትን የደቡብ ሱዳንን ሕዝብ ፈጀ ፤ ዝሃና ግራውን መለየት የተሳነው መንግሥቱ ኃይለማሪያም በቀይ ሽብር ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር እያለ ተኪ የማይገኝለትን ወጣት ምሁር ሠራተኛ ፤ አርሶ አደር ፤ የከተማ ነዋሪ ፤ ነጋዴ አዛውንት ጨረሰ የኤርትራን ተቃዋሚዎች በኃይል ለማንበርከክ ሞክሮ የመገንጠል እድል እንዲታደሉ አደረገ ። ሌላው የአገር ጉድና አረም የምዕራባውያንና የዐረቦች አሽከር አያት ቅድመ አያቶቹ የጣሊያን አባሽ አጎንባሽ ሹምባሽና ለባሽ የነበሩት ልጅ በነ-ስብሃት ነጋና አባይ ፀሐየ አጆሃ! እየተባለ የሻእቢያን የመገንጠል ዓላማ ነዳጅ ሆኖ አገለገለ ኢትዮጵያን ወደብ የሌላት አገር አደረገ ፤ አብዛኛውን ከውጭ አገር የሚያዋስነውን የአገሪቱን ለም መሬት ለባዕዳን በረከት ሰጠ ፤ ሊበርድ የማይችል የጎሳና የሃይማኖት ግጭትና ጦስ አቀጣጥሎ በአበበ ገላው (አንድ ጋዜጠኛ ወቀሳ) ምክንያት በ30 ሰከንድ ውስጥ በድንጋጤ ርዶ ያለቀኑ የተቆረጠ ቅጠል መስሎ እኛን ረመጥ ውስጥ ከቶ ከማይጠየቅበት ዓለም ተጓዘ ያ ሚፈራውን ሞት ሞተ። መለስ ዜናዊና ድርጅቱ ህወሃት ነፍጥ ያነሱት የትግራይ ሕዝብ በሁሉም አይነት መንገድ ተበደለ ብለው እንደሆነ አድርገን የምንረዳ ልንኖር እንችላለን። የዛሬውን አላውቅም እንጅ ህወሃት የትግራይ ወላጆችን ጨርሷል።የተረፉትን ጧሪ አልባ አስቀርቷል፤ተኪ የማይገኝለት ወጣት ትውልድ በልቶ ያደገ ድርጅት ነው።በርግጥ በሥርዓቱ ዙሪያ ያሉት ሚሊየነር ሆነዋልከሚገባው ብላይ ከበርዋል ። የትግራይ ሕዝብ ግን በሳውዝ አፍሪካ እንግሊዞች ካራመዱት የአፓርታይድ አገዛዝ ሊመሳሰል የሚችል ሲኦል ውስጥ ገብቶ ነው የሚገኘው።በቅርቡ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የሚሊዮኖችን ድምጽ ለማሰባሰብ በጀመረው ዘመቻ መቀሌ ላይ በክልሉ ገዥዎች የተደረገውን ሰምተናል።ትግራይ ውስጥ ወይን ከሚለው የህወሃት ጋዜጣና ከህወሃት ራዲዮ አልፎ ዜና ማድመጥና ማንበብ ወይም በሌላ አነጋገር ሌሎችን ጋዜጦችና መጽሔቶች አይገቡም የመገናኛ ብዙሃንን መስማት የሚያስቀጣ እንደሆነ ይታወቃል።የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ይህን እሥራት ሰብሮ መውጣትና መብቱን ማስከበር ይገባዋል።
በመጨረሻም በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት አስተዳደር ክፍል አዘጋጅነት በ18/08/2013 ዋሽንግተን አርሊንግተን የሚካሄደው የታዋቂ ግለሰቦች ፤ የፖለቲካ አክቲቪስቶች ፤ የሃይማኖት መሪዎችና የተቃዋሚ ድርጅቶች ፤ የስቪክ ማህበራትና ሌላውንም ያካተተው ስብሰባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ የምሥራች ይዞ ብቅ እንደሚል ተስፋ አደርጋለሁ። ለሁሉም ግን የማሳስበው ቢኖር ሰጥቶ መቀበል ፤ መናበብ ፤ መደማመጥ ፤ መከባበርና ፍቅርን መተሳሰብን የሚያጎናጽፍ እንዲሆን መልካም አርአያ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!