Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

በሬ ሆይ ሳሩን አገኘሁ ብለህ ገደሉን ሳታይ… የግል አጭር አስተያየት

$
0
0

ከአበባዉ ላቀው (labebaw@gmail.com)

ሰሞኑን የኤርትራዉ “ፕሬዘዳንት” ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢሳት ቴሊቪን ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም እርሱ የተናገረዉን  ትርጉም ስሰማና አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ልባቸዉ ሲማልል ስሰማ በጣሙን አዘንሁ። ምክንያቱም እያንዳዱ ኢትዮጵያዊ  ይህን እብድ ጠንቅቆ ያውቀዋል የሚል ግምት ነበረኝ። ሆኖም ግን ግምቴ ትክክል አለመሆኑን የሰሞኑንን ግርግር በደንብ አሰረዳኝ።

ይህን ኢሳያስ የሚባል isayaበደ ዉሻ ኢትዮያን ነክሶ ዜጎቿን ለእብደት የዳረገ የሰይጣን ፍጡር አምነን ልባችን በተደጋጋሚ አይነሸዋረር! ብርሀኑ ነጋያራሱ ተልኮ ያለዉ ጸረ-ኢትዮጵያ ነዉ። 97ቱን የምርጫ ድል ከሕዝብ እጂ ተነጥቆ ለወያኔ ጀባ እንዲባል በጓሮ በር ከበረከት ጋር ስምምንነትያደረገ እኮ እርሱ ነዎ! ከምርጫ ሳምንት ቢኋላ ማክሰኞ ሊደረግ የነበረውን የሙት ከተማ አድማ ከበረከት ጋር ተስማምቶ እንዳይደረግ ያደረገእኮ እርሱ ነው! ያልሞተቸዉ ብርቱካን ሚዴቅሳ ትመሰክራለች። የብርሀኑን ከሀዲነት 16 የልደት ዘመኑ ጀምሮ በበረሃ ያደረገዉን የክህደትወንጀሎች ለማወቅ አሲምባ የነበሩ ሰዎችን ጠይቃችሁ ተረዱ።

ሕዝብ ሆይ ዝምብለህ ማንም አጭበርባሪ የነገረህን እያመንህ የመሪዉን ማንነትሳታጣራ እንደከበት አትነዳ! ጉዞው ወደገደል ነዉና! ይህ ሳያስ የሚባል እብድ እንኳን ለሚጠላት ኢትዮጵያና ሕዝቧ መልካም ሊያስብ ቀርቶየራሱንምሕዝቤየሚለወን የኤርትራ / ህዝብ መውጫና መገቢያ አሳጥቶታል። ሰሞኑን የአሜሪካው PBS African Programስለኤርትራ ህዝብ ስደትና መከራ የሚያስተላልፈው ዶክሜንታሪ በቂ ማስረጃ ነው። አባቶቻችንን፣ወንድሞቻችንን እና ዘመዶቻችንን እንክትአድርጎ የበላ ማነው? ባንዳ የባንዳ ልጅ ኢሳያስ አይደለምን?  በቀድሞ አለቆቹ (ጣልያንና እንግሊዝ እንዲሁም ተባባሪዎቻው) መሪነትኢትጵያን ሲደማ እና ሲያጠፋት የኖረ፣

ወያኔንን ከዉልደት ጀምሮ የፈጠረ፣ ከሃዲ ድርጅቶችን እንደነ ኦነግና አብኦነግ ያሉትን የፈጠረና ከወያኔ ጋር ባደረገዉ የዉሸት ጦርነት ከ70ሺ በላይ ወንድሞቻችንን የጨረሰ፤ ኢሳያስ አይደለምን?  አሁን ኢሳት ይህን ሰይጣን ቅዱስ አድርጎሊቃርብልን እና ልባችን ኢሳያስን ማመን ሲጀምር የእራሳችንን ጤንነት መመርመር ያስፈልጋል።  በተለይ በምዕራቡ አለም ውስጥ ያለን ዜጎች ዝምብሎ የተነገርንን ብቻ ሰምተን አሜን ብሎ መቀበሉ ያሳፍራል። ያለን እይታ ከሚኖረን ልምድ አንጻር ሰፋ ያለ ሊሆን ይገባዋል።

በየቀኑ የምናነባቸው እና የምንሰማቸዉ የአለም ዜናዎች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች ወዘተ የዕዉቀት አድማሳችንን ያሰፈላናል ብየ እገምታለሁ። ይህም እንደ ሰሞኑ ያለዉን የኢሳያስን ቀልድ አዘል ሌላ የ100 ዓመት የቤት ስራ ከልብ ሊገባን እና ልንቃወመው በተገባን ነበር። ዝምብሎ ማንም በሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን የቀረበን ቃለመጠይቅም ሆነ ትንታኔ (ለዚያዉም የኢሳያስን)  የምናምን ከሆነ የበሬው እጣ እንዳይገጥመን እፈራለሁና  እንድናስተዉል እመክራለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ የጠለቀ ትንታኔ ለሚሰጡ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ጉድዩን በዚሁ ልተወው።

አክባሪያችሁ

አበባዉ

The post በሬ ሆይ ሳሩን አገኘሁ ብለህ ገደሉን ሳታይ… የግል አጭር አስተያየት appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>