ኢትዮጵያ ላይ መጭው ትውልድ ይቅር የማይለው የታሪክ ሰህተት እየስራ ያለው የትግራይ ነጻ አውጭ ነኝ ብሎ በኢትዮጵያ ምድር ስልጣን ላይ ያለው የወነበዴ ግሩፕ እንደሆነ የታወቀ ነው።እዚህ ጋር በትንሹ እንደ ጠቋሚነት መጥቀስ የምፈልገው እና አንባበውም ሊያሳድገው የምፈልገው ነጥብን ነው።
ኢትዮጵያ ረጅም እድሜ ያላት የታሪክ አገር፣ የፍቅር አገር፣ አብሮ ተቻችሎ የሚኖርባት አገር፣ናት። ወያኔ ግን ይህቺን ባለብዙ ታሪካዊ አገርን ሙሉ በሙሉ አፍርሶታል። ያለውን እውነት ትንሽ ወደሃላ ሄደን እንመልከት
ኢትዮጵያ ታረክ ያላት አገር ናት። ይንን ስንል የሰው መገኛ እንደሆነች ታሪክ የሚነግርላት የነድንቅነ ሽ(ሉሲ) መገኛ፣ የጥንት አብያተ ክርስትያናትና ጥንታዊ መስጊዶች ያሉባት አገር፣ ክርስትና እና እስልምናው ተፋቅረው ተጋብተው ተዋልደው የሚኖሩባት ታሪካዊ ፊቅራዊም አገር ነች። ለአለም በሙሉ ምሳሌ መሆን የምትችል የፍቅር ተምሳሌት የውቦች አገር እንደሆነች ታሪክን ወደሃላ አገላብጦ ማየት እና የስውን አኗኗር መቃኝት በቂ ነው። ለዚህም ታሪክነን ስንቃኝ ኢትዮጵያዊ ንጉስ አርማህ በአረቦች አገላለጽ ንጉስ ነጃሺ የሚባሉት በዛ ዘመን ንጉስ አርማህ ሙስሊም ስደተኞችን ተቀብሎ አገራቸው ሰላም እስኪሆን ድረስ ያለምንም ችግር እንዲኖሩ አድርጎ መጠለያ የሰጠ የአለማችን ቀዳሚ መንግስት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ንጉስ አርማህ የክርስትና እምነት ተከታይ ቢሆንም ከሳውዲ የመጡትን የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን ያለምንም ችግር በእምነታቸው ሳያገላቸው በዚህም በንኖርባት አለማችን ላይ ስደተኞችን በመቀበል የመጀመርያ አገር ያደርጋታል። ይህ የሆነው በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ነው። ሌላው ደሞ አብሮ ተቻችሎ እና ተዋደው የሚኖሩባት አገር ነች።82 የተለያዩ ብሔር ያለባት አገር ብትሆንም የዘር ልዩነት ሳይኖር በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ዘር ሳይጠይቅ ተጋብተው በፍቅር የሚኖሩባት አገር የነበረች ነች ሌላው ቀርቶ ሃይማኖትም ሳይለያችው ተዋልደው ተፋቅረው የሚኖሩባት አገር ኢትዮጵያ መሆኗን ታሪክ የዘገበው አሁንም ያለ እውነታ ነው። ለዚህም እረጅም ግዜዎችን በፍቅር አሳልፋለች ኢትዮጵያን የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት የምትደረገው ያለ ምክንይት አይደለም። ዛሬ ዛሬ የምናየው ግን በጣም የሚገርምና የሚደንቅ የሚያሳዝንም ነው። የምን ጉድም እንደመጣብን አናውቅም የኢትዮጵያ ታሪክ ጀማሪ ወያኔ እስክመስለው ድረስ ኢትዮጵያዊነትን እንዲረሳ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጣም የሚደንቅ ነው።
ቅዱስ ያሬድ የበቀለባት ምድር ፈላስፋው ዘረያቆብ የተገኘባት ምድር ዛሬ እነዚህን ወያኔ የሚባል ጉዶችን ታውጣ። በለስ ኩርንችትን ሲያፈራ አላየንም ነበር… አሁን ግን በለስ ኩርንችትን አፍርቶ አየነው። እነዚህን ኩርንችቶች ደግሞ የራሳቸውን ባንዲራ እየለበሱ በተለያየ መድረኩ ላይ ለብሰውት ሲጨፍሩ ይታያሉ። የኢትዮጵያ ባንዲራ ጥለው ቢጫና ቀይን ባለኮኮቧን መልበስና ማውለብለብ እየፈለጉ እንደመጡ የሚያሳዩ ነገሮች እየታዪ ነው። ቢጫውም ፍጥነትህን ቀንስ ቀዩ ደሞ ቁም የሚል መልዕክት እንዳለው አልተገነዘቡ ይሆን? ዝም ብለው ቀይና ቢጫ ባለኮኮቧን የወያኔ ባንዲራ ለብስው የሚዘሉብን። ሰው ልቦናው ካልመለስው እና ካላስቆመው በሌላ ሃይል መቆም እንደሚቻል አልተረዱ ከሆነ የግድ ቀን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይል ሲያስቆማቸው ያኔ ትረዱታላቹሁ።
ወያኔወች ለኢትዮጵያን ነጻነት እንዳመጡልን በተደጋጋሚ እየነገሩን ነው። ኢትዮጵያኑ ደግሞ በወያኔ በሚባል አገር በቀል ቅኝ ገዥ ስር ወደቀች እንጂ ነጻነታን አላገኘችም እያሉ ነው። በዚህ ዙርያ ግን ትግሬዎች በዚህ ተሳትፎ ውስጥ እንዳሉ እሙን ነው ምክንያቱም ቋንቋው ማስፈራሪያ እስከመሆ ን የደረሰበት ግዜ ላይ ደርስናል።ትግሪኛ ተናጋሪ ከሆነ የፈለገውን ነገር ማደረግ የሚችል ከመሰላቸው ሁሉ ነገር ከፊታቸው ያዩታል። ግዜው ደርሷል።
ድልና ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
ከ-ሳሙኤል አሊ 26.02.2015 Email-samilost89@yahoo.com
The post ወያኔ ታሪክ ሰሪ ነው ወይስ ታሪክ አጥፊ? – ከ-ሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.