መግቢያ፤
እ.አ.አ. በየካቲት 1896 ባልተጠበቀና እጅግ አስገራሚ በሆነ መንገድ፤ ኢትዮጵያ፤ እስከዚያ ድረስ በየትኛውም ኣሕጉር ተደርጎ የማይታወቀውን፤ አንድ በመልማት ላይ ያለች ሐገር፤ የአንድ ጠንካራ የሆነ የአውሮፓ መንግሥትን፤ የኢጣልያን የጦር ወረራ በድል የተወጣች መሆኑ ለምን ጊዜም ቢሆን በውጭ ጠላት የማትበገር፤ የነጻነት ጮራ ሐገር መሆኗን አረጋግጦላታል። ስለዚህ ታሪካዊ አኩሪ ድል፤ ብዙ ተጽፏል፤ የአድዋ ክብረ-በዓል በሚዘከርበት ጊዜም፤ ዝርዝር ታሪኩና አንድምታው በሰፊው ይነገራል፤ ይጻፋል። የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግን፤ በመጀመሪያ፤ የአድዋው ጦርነት ዋናው መንሰኤ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛቷ ለማድረግ የነበራት አጉል ምኞት ቢሆንም፤ የቀሰቀሰው አንደኛው ምክንያት የትርጉም ጠንቅ የነበረበት የውጫሌው ውል ስለ ነበር፤ ውሉ በአጼ ምኒልክና በኢጣልያኑ ተወካይ በአንቶኒሊ እንደ ተፈረመ፤ ወዲያውኑ በራስ መኮንን የተመራ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ ኢጣልያ ተጉዞ ስለ ፈጸመው ጠቃሚ የዲፕሎማሲ ተግባር፤ ሁለተኛም አድዋ ላይ ለተከናነበችው እጅግ አሳፋሪ ሽንፈት፤ ኢጣልያ 40 ዓመት ሙሉ ጠብቃና ተዘጋጅታ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸመችው አሰቃቂ የበቀል የጦር ወንጀል፤ ዳግመኛ ድል ብትነሳም፤ ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ፍትሕ ስለ አለመገኘቱና በመኪያሔድ ላይ ስላለው ትግል አጭር ዘገባ ይቀርባል።
The post ለአድዋ ድል በቀል ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ -ኪዳኔ ዓለማየሁ appeared first on Zehabesha Amharic.