Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! –አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ

$
0
0

የዘንድሮ ምርጫ ኣሸንፎ ለመውጣት የህወሓት መንግስት ኣርባው ሲያስወጣ “…ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሬ ድጋፍ ኣገኛለው…” ብሎ ኣስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ በመውለድ ያሁሉ ጥረቱ መና ሁኖ መቅረቱ ህወሓት ተረድተዋል። ድሮም በወከባ የሚገኝ ህዝባዊ ድጋፍ እንደሌለ የሚታወቅ ነው።
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu
ህወሓት ጥረቱ ከንቱ ሲቀር የዘየደው መላ በትግራይና የሚያዋስኑት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኤርትራ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የምርጫው ኣቅጣጫ ለማስቀየስ እየሞከረ ነው። የዚህ ማሳያ “..የኢትዮዽያ ኣየር ሃይል የወርቅ መዓድንና የትጥቅ መጋዘን ደብድበው ጉዳት ኣድርሰዋል..” የሚል በፌስቡክ ካድሬዎቹና በድህንነት ኣካላት በሰፊ እንዲወራ ኣድርገዋል።

የዚህ ምላሽ ተብሎ የተገለፀው ደግሞ “..ሻእብያ ሶሎዳ ተራራን(ኣድዋ ከተማ ኣጠገብ የሚገኝ) በሚሳይል እንደደበደበ..” እነ ዳኒኤል ብርሃነ ኣበሰሩን። ምድረ ካድሬም “..ኣሸው..” እያሉ ለኣየር ሃይላችን ኣንቆለዻዸሱት።

ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለይም ስለ የኣየር ጥቃቱ ሲጠየቁ “..ተደበደብኩ የሚል ኣካል ሲኖር መልስ እንሰጣለን…” የሚል ኣመላካች የእምነት ቃል ገለፁ።

“…በኣንዳንድ የኢትዮ-አርትራ ድንበር የተወሰነ ወተሃደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩና ይህንን ተከትሎ የህብ መፈናቀል እንደተስተዋል..” የፌስቡክና ምንጭቻቸው በግልፅ የማይታወቁ ወሬዎች በትግራይ ክልል እንዲወሩ ተደረገ።

የመቐለ መስተዳደርም የዚህ ወሬ ከሚያራግቡ ኣካላት ኣንዱና ዋነኛው ነበር። በከተማዋ የሚገኙ የባጃጆችና የታክሲ ሹፌሮች በማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ በመሰብሰብ “..ፀጉረ ለወጥ ሰው ስታስተናግዱ መታወቅያ ጠይቁ፣ መኪኖቻቹና ባጃጆቻቹ ፈንጅና ሌላ ተቀጣጣይ ነገር እንዳይጠመድባቸው በንቃት ጠብቁ..” የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጣቸው።

በማስቀጠልም “..በመከላከያችን ጥቃት ደረሰ፣ ይህን ያክል ሰው ሞተ፣ ቆሰለ የሚል ኣሉባልታ እንዳታምኑ፣ እንዳታወሩ..” ወዘተ የሚሉና የውትድርና ምልመላ ማስታወቅያዎች በማስተዋወቅ ህዝቡ የጦርነት ስጋት እንዲያድረው እየተደረገ ነው።

እነዚህ ወሬዎች የትግራይ ክልል ህዝብ ትኩረቱ ከምርጫው ይልቅ በሚናፈሱ ወሬዎች እንዲያደርግና የጦርነት ድባብ እንዲሰማው እየተደረገ ነው።
ይህ ህዝቡ በጦርነት፣ ወተሃደራዊ ጥቃት፣ የሽብር መንፈስ እንዱያድረውና የነዚህ ክፉ ወሬዎች ውጤት የሆኑት መልኣከ ሞት፣ ስደትና ችጋር ወደ ህሊናው እንዲመጡና የምርጫው ትኩረቱ እንዲቀይር እየተደረገ ነው።

በዚህ ኣካሄድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ህዝቡ በተረጋጋ ሁኔታ መብቱን መጠቀም እንዲችል የምርጫው የግዜ ሰሌዳ ለሌላ ግዜ ማራዘም ግድ ይላል።

በተለያዩ ኣካላት እየታነፈሰ ያለው ወሬ ሃቅነት ይኑረው ኣይኑረው ህዝቡን በተረጋጋ ሁኔታ ይበጀኛል የሚለው እጩ ተወዳዳሪና ድርጅት መምረጥ ካልቻለ ለኣገራችን ሰላምና እድገት ኣሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ግድ ይሆናል።

የህወሓት መንግስት ከምርጫ ይልቅ የጦርነት ድባብ ማስፈኑ ምክንያት ከትግራይ ህዝብ ያጣው ድጋፍ ተረድቶ ምርጫው ኣጨናግፎ ለማለፍ ነው።

ምርጫው ሊጨናገፍ ኣይገባም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

IT IS SO..!

The post የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! – አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>