Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

  ላመስግንህ –ተመስገን። –ከሥርጉተ –ሥላሴ

$
0
0

11.04.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

Temesgen Desalegn behindbar„ደጋግ ፡ ሰዎችስ፡ እግዚአብሄር፡ ከማይወደው፡ ሥራ፡ ሁሉ፡ ይርቃሉ። ይወዳቸዋል፡ ከመከራቸው፡ ሁሉ፡ እንደ፡ አደራ፡ ገንዘብ፡ ይጠብቃቸዋል። ሥርዓቱንና፡ ሕጉን፡ ዬሚወደውን፡ ሁሉ፡ ይጠብቃሉና፡ ኃጢያተኞች፡ ሰዎች፡ ግን፡ ሰይጣን፡ ይገዛቸዋል። (መጸሐፈ መቃብያን ካልዕ ምዕራፍ 9 ቁጥር 25 እስከ ፍፃሜው)“

በቅድሚያ ለክርስትና ዕምነት ወገኖቼ ለማህበረ – ምዕመናን እንኳን ለ2007 የጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ በዕለ – ትንሳኤ አደረሳችሁ – አደረሰን። እንዲሁም አርበኛና መምህር አቶ በቀለ ገርባን እንኳን ከጥብቆ ካቴና ወደ መጠነ ሰፊው ካቴናማ ህይወት አሸጋገረዎት። ቢያንስ ከቤተሰብ ጋር መከራውን በአንድ ጉልቻ መቀበልም አንድ ነገር ስለሆነ። ላደረጉልን መልካም ነገር ሁሉ ዝቅ ብዬ አመስግናለሁ – በአክብሮት። ውለታዎትንም ታሪክ ይክሰወታል ብዬም አስባለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልን።

የዛሬው ባለጉዳዬ – አንድ ፍሬ ልጅ በተግባር የጎለመሰ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደፋር መሆኑ፤ መጪን ጊዜ ቀድሞ የማዬት አቅሙ እንደ ማግኔት ሳቢነቱ፤ የአቅጣጫን ትኩስነት የመለካት ብቃት ብቻ ሳይሆን፤ ስሜቱን ለታዳሚው በመላክ መንፈስን በቋሚነት በመዳፉ የመያዝ ስልቱ፤ ጭንቅ ጊዜን በጭብጥ ትንተና የማብቀል ልዩ ችሎታው፤ የአቀራረብ ይዘቱ ሁለመናነት ወጥ ሆኖ ነገር ግን ጥገኛ ሳይሆን በሃቅ ማሳ መልማቱ፤ ሚዛናዊነቱና – ማዕዘንነቱ፤ የሀቅ ትንፋሽን የማድመጥ ክህሎቱ፤ ለሙያው ያለው ተቆርቋሪነት አክሎ ብቃቱን በሁለገብ ሁኔታ ማዬት እንዲያስችል አበራክቶ የሰጠው ትንታግ የእውነት ዝማሬያችን ነው። ለእኛ የመንፈስ ሃብታችን ነው። ስለዚህም ይህችን ቋጠሮ ከምስጋና ጋር ልኮልምለት – ተሰናዳሁ። ኮቢዬንም ሳማክራት በሐሤት ፈነጠዘች። አዎን! የዛሬ እንግዳችን እሱ ነው እሱ ልጅ ተመሰገን ደሳለኝ …. የብርታት ሰዐቱ። የማግሥት ተስፋ ዋዜማ – የብሩኽ ራዕይ ዜማ።

ላመስግንህ – ተመስገን

      *******

አንተ ዬዕውነት – አርበኛ

የእኛ!

የሃቅ – ሁነኛ – ሥህነኛ

መዋኛ!

የፍቅር – ቤተኛ

ማተበኛ!

የሰው መሆን – ትርጉመኛ

የህሊና – ዳኛ!

የዘር – መገኛ

የዕንባ – ዘበኛ

ወደኛ

ውድዬኛ።

ሎሌነትን – የተጠዬፍክ

ጠፈፍ – ያልክ።

ለዕብለት – ያላደርክ …

ለሃሰት ጉዝጓዝ … ያለተነጠፍክ

ክርክም ያልክ

የልጅ አዋቂ – የአደራ መልክ።

ትግል – ጠርታኽ

አፍልቃኽ።

ነፃነት „ነፃ“ እንድታወጣት – አጭታኽ፤

አንተነትህን – ሰጠሃት

ሆንክላት።

ሰላም – ናፍቃኽ፤  ሽው ስትልህ፣

ከማያልቀው ፏፏቴዋ  – ከመዳህኒቷ ውስጥ ቀድታህ

ቀለጥክላት።

ራዕይ – አምናህ

ተሳካላት።

ላመስግንህ – ተመስገን፤ የማያልቅብህ – ብዕረኛ

ባለማተብ – ዕሴተኛ፣

ጮራ – የእኛ!

ባተሌ – ጋዜጠኛ

ባለቀለም – ዝናርኛ።

ግርማ – የእኛ

ሞገስ – ለእኛ

ማኛ!

ደፋር የኮቢ –  ወታደር

ለህግ ክብር ብር – አንባር።

ግብር የሆንክ ለዘረኛ

ውለኛ!

አንተ ——– የእኛ

የመሆን  —- ሁነኛ

የፋክት! – አርበኛ።

የእኛ እሸት – የእኛ ፍሬ፣

የእኛ ቀንበጥ፣ – የወንዜ ላሂ የሀገሬ

ዬብራና – ሳታና ገበሬ።

ዘንበል ብለህ፤ አዳመጥካት

የልዕልትህ – ድምጽህ ናት፤

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ – ደምህ

አንተን ለእኛ ሰጥታ

የታሪክ ምንጭ – ማሾ አብርታ

የሰጠችን የምልዕት ዕንባ – ጠብታ፤

የፍትህ ዕንብርት – የዕድምታ

የልዕልና አንኳር –  አግታ

ከእውነት ጋር ተጋብታ

ከዘመን ጋር ተጣብታ!

የሃቅ – ለጋ —- ለግላጋ፣

ምዕራፍ አንተን አወጋ፣

ሊያነጋ!

የሥርዓት — ቅጽ

የቅንነት —– አንቀጽ፤

ብላቴና፤

የውስጥነት – ገናና

የርትህ ፍቅር – ዝባድ ገና፤

ዬፎርቹን አራት ዓይናማ

ዛላማ!

የሴንቸሪ – ዘንጣፋ ዞማ።

ላመስግንህ – ወንድምዓለም ታንሽዬ ተመስገን

ደኑ የሆንክ፤ ለፈተና – ለመከራ

ልትደለድል የልዩነትን – ጋራ።

የቁም ነገር ዝና

ዋና!

ዬነፃነት – መምህሩ

ኪዳኑ ነው አዳሩ፤

የተስፋ ብርሃን ምግባሩ

ሰው መሆን ብቻ፣ ብቻ – ጠረኑ።

„እ — ፍ“ ብለው ያላጠፉህ

ቀጥተኛ – ደማምህ

ወጣትነትህን – ገበርክ፤

መንፈስህን – አምነህ ያከበርክ

ልክ!

መማገድህ በባዕትህ – ለባዕትህ

ጥልቀትህ!

የፈቀድከው – ሆነልህ

ከ-ሷው ጋራ ጨለማውን በካቴና፤ ————————-ህመምህ፤

በ-አብነትህ

ከ-ውስጥህ፣

እናት ሆዱ – ደግነትህ

ስስ – አንጀትህ

መሰከረ – ጣትህ

ትክክለኝነትን አበጀኸው – ሠራህ

ስለናትህ!

 

ሥጦታ፤ ዘመን ለሸለመን እጅግ ብርቱ ጋዜጠኛና ጣምራ ብቃት ለሰጠው ለወጣት ተመስገን ደሳለኝ ይሁንልኝ። ታናሼ ወንድምዬ ምህረቱንም አምላኬ ያምጣልህ አይዞህ ዬእኛ ብርቱ። /06.04.2015 ማርያሽታይን ገዳም – ባዝል/ ©ሥርጉተ – ሥላሴ።

 

በመጨረሻ የኔዎቹ ዛሬ ከልቤ ተደላድሎ በተቀመጠው በዚህ ብልህ – ብሂል ልሰናበት „አልቦ ብሄር“ የአንድ መጸሐፍ ያህል ቁምነገር ነው ያስተላለፉት ምርጥ ፍሬ – ውድድድድድ …. ዬእኔ – ጌጥ! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40350 መሸቢያ ሰንበት ማለፊያ ፆመ ሁዳዴ መፍቻ። ኑሩልኝ – የኔዎቹ።

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዜብሄር ይስጥልኝ።

The post   ላመስግንህ – ተመስገን። – ከሥርጉተ – ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>