Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የወያኔ  ዜማ በደቡብ አፍሪካ ተሰማ –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaበደል በደልን ይወልዳል እንጂ አያጠፋውም። ችግር ችግርን ይፈጥረዋል እንጂ አያስወግደውም። በደል ፈጣሪ ከላይ ከተቀመጠ… መከራን አምጪ ስልጣን ላይ ካለ… የምንሰማው እና የምናየው ሁሉ ሰቆቃና ዋይታ ነው። ሰቆቃ እና ዋይታ ግዜውን እየጠበቀ የሚፈነዳ የህዝባችን ፍዳ ከሆነ ሰነባብቷል። ሰቆቃ  ፈጻሚዎች እና ናፋቂዎች አናት ላይ ከተቀመጡ ሰቆቃችን ማብቂያ  የለውም። ለኛ የሃዘን እንባችን ለወያኔ ደግሞ  የመዝናኛው ዜማው የሆነ አሳዛኝ ድርጊት ከወደ ደቡብ አፍሪካ እየተሰማ ነው።

የኢትዮጵያ መከራዋ  በይፋ  ከተበሰረበት ግዜ አንስቶ  ከእለት ወደ  እለት ህዝባችን ከሚወዳት አገሩ ሳይወድ በግዱ ተሰዳጅ እየሆነ  ነው። እግዚአብሔር የተፈጥሮ  ጸጋውን አልብሶን እንኳን ለራሳችን ለአለም የሚተርፍ ሃብት በጉያችን ይዘን እንደ  ርሃብተኛ እንሰደዳለን። በልጆቿ የዳበረ እውቀት በልጆቿ የፈረጠመ  ጉልበት በተፈጥሮዎአ ላይ የሚዘምቱ ኃያል ልጆች ኖሮን ሰርተንና በልጽገን አለምን የሚያስደምም እውቀትና ተፈጥሮ ኖሮን ሳለ ገዳይ ነግሶብን አንባ ገነን ተሾሞብን በየአለማቱ ተበተንን። የወገኖቻችንን  ሰቆቃ  በተቃጠለ  ስሜት የደም እንባ እናነባለን። ከአጋም ጋር የተጠጋ  ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል እንደሚባለው ወያኔ ለሆዱ፣ ለስልጣኑ፣ ብሎ ህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍና  በደል ህዝባችንን ተሰዳጅ አደረገው። ዛሬ በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን ለሚደርስባቸው ዘግናኝ ድርጊት ተጠያቂው ወያኔ  ነው።

ከጥቂት ግዜ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ መንግስ ጋር ከአርባ አምስት ሺህ በላይ የሰራተኛ ግብይት ተፈራርሞ ነበረ። ፊርማው ሳይደርቅ የሳውዲ መንግስ በዜጎቻችን ላይ የሰራውን አሳፋሪ እና  ዘግናኝ በደል እርጉዝ ሴት እህቶቻችን ለብዙ በመድፈር ለሞት ሲዳርጉ በአደባባይ በስለት ሲታረዱ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ስናይ በደላችን የተዳፈነ  ፍም ሆኖ በውስጣችን ተቀምጧል። ሌላው ቀርቶ በሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል ለመቃወም በአዲስ አበባ ሳውዲ ኤምባሲ ሰልፍ በመውጣት ብሶቱን ለማሰማት የወጣውን ህዝብ የወያኔ ቅልብ ፌደራል በድፍን አምሮው በያዘው በድፍን ዱላ ህዘባችን እየቀጠቀጠ ሳውዲ የወሰደችው እርምጃ  ትክክል ነው ብሎ ነግረውናል።

በመቀጠል በየመን ከ200 ሺህ ሕዝብ በላይ ኢትዮጵያን ይኖራሉ በየመን በተነሳው ግጭት ሳብያ ኢትዮጵያኑ እንደቅጠል እየረገፉ ነው በዚህ መሃል ቀልደኛው መንግስታችን በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ አልነሳ ካላቹህ መልሳቹህ መልሳቹህ ሞክሩት አልያም መልክት አስቀምጡ የሚል በፌስ ቡክ መስኮት ብቅ ብሎ ነግሮናል። ለየመን ባላሀብት ሲጋራ ሞኖፖልን ከምትሸጡ ይልቅ ለሳዊዲ ባለሃብት፣ ለህንድ እንዲሁም ለገብረመድህን፣ ለኪሮስ፣ ለግደይ፣ ለአላሙዲ፣ የአገሪቱን ለም መሬት ከምትቸበችቡ በችግር ላይ ላለው ዜጋ ለሆኑ አገራቸውን እያለሙ እራሳቸውን እንዲችሉ የአገር ለውጥ በአገር ልጅ የሚለውን   መርሆ  ብትከተሉ  ምን  አለበት? ለነገሩ የሰይጣን መልእክተኛ  አልያም በውስጡ ሰይጣናዊ ሃሳብ ያለበት ይሄን ማድረግ አይቻለውም።

ችግር ፈጣሪው እስካለ  ችግሩ አይቀሬ ነው ።  እናም በሱዳን በኬንያ በዛንብያ በግብጽ ችግሮች እንዳሉ ቢታወቅም እንደ  እሳተ ጎመራ የፈነዳው አዲስ ክስተት በደቡብ አፍሪካ ተከሰተ፡ ትናንት በችግራቸው ጊዜ  ችግራቸውን የሸፈንላቸው ሁሉ ዛሬ እነሱ በኛ ላይ ተነሱ። ሳውዲን ብንወስድ ቆሬሾች ሊገሏቸው ሲያሷድዷቸው የነብዪ መሀመድ ወገኖችን  በጉያዋ ያስቀመጠች  በኔ የተከለሉትን በራሳቸው ፍቃድ ካልሆነ ለማንም  አንባገነን አሳልፌ  አልሰጥም ብላ ህይወታቸውን የታደገች አገር….  ለደቡብ አፍሪካም  የነጻነት መሪ የተባለውን ማንዴላን ተቀብላ አሰልጥና የኢትዮጵያን ፓስፖርት ሰጥታ በክብር የሸኝች አገር ዛሬ ያሁሉ ተረሳና የስቃይ ጅራፍ ውለታ ለዋለችላቸው አገር ሲያደርጉ ያሳዝናል። ታሪክ ይውቀሳቸው እውነት ይፋረዳቸው።

ደቡብ አፍሪካዎች ምን ነካቸው? የማንዴላ ህዝቦች ምን አጋጥሟቸው ነው? እንደዚ ወደ አውሬነት የተለወጡት። እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስላቸው በሰይፍ ያጠፋ በሰይፍ ይጠፋል ይላል። ፍርዱን ለፈጣሪ በመተው ከኛ የሚጠበቅብንን ማድረግ ግድ ይለናል።

ነገሮች ሲወጣጠሩ ማስተንፈሻ በመፈለግ ወደ ሰባራ ተግባር የሚሄደው የወያኔ መንግስት ሁሉም ህብረተሰቡ ትኩረት አድርገው ስለ አገራቸው በሚያስቡበት እና በሚሰሩበት ግዜ  በደቡብ አፍሪካ  እንደዚህ አይነቱ ክስተት መከሰቱ ለወያኔ ዜማው ነው። የወያኔ መንግስት ሃሳባቸው ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ስለስልጣናቸው ብቻ የሚያስቡ በመሆኑ የህዝብ በደል ወይም እልቂት ያስደስታቸዋል ምክንያቱም የፖለቲካ አቅጣጫውን ስለሚጠመዝዝላቸው። ለደቡብ አፍሪካ ጭፍጨፋ የአፍሪካ መሪዎች በዜጎቻቸው እየደረሰ ያለውን  ግፍ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ..በጦርነት እየታመሰች ያለችው ሱማሊያ ስለዜጎቿ ስትቆም… ወያኔዎች ግን ምንም ያሉት የለም። በርግጥ ከወያኔ ምንም አንጠብቅም። ምክንያቱም አይተናቸዋልም አውቀናቸዋልም። የሚጠበቀው ከኛው ነው።  እኛው ለኛው።

የህዝባችን እሮሮ ማስቆም የሚቻለው በመጀመሪያ  እሮሮ አምጪውን አናታች ላይ የተቀመጠውን ጨቋኝ አገዛዝ  አውርደን መጣል ስንችል ከዛ በኋላ ዜጋዬ ተበደለ ብለን ስለህዝባችን ፈጥነን መድነስ የምንችለው። ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በህዝባችን ላይ መከራ ቢደርስበት ግድ የለውም። ካሁን በኋላ ወያኔ ህዝባችንን እንዲታደግልን አንጠይቀውም። ለህዝባችን የቆመ መንግስት ነው ብሎም መቀበል አይቻልም። ነገር ግን በህዝባችን ስም በመነገድ ስልጣኑን የሚያራዝመውን ተግባር በማክሸፍ ህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ እናስቁም። ለዚህም ግዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። በሳውዲ በደረሰው የህዝባችን ሰቆቃ  ምንም ያልፈየደው ወያኔ ሙሉውን ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኖ ከሳውዲ እንዲመጡ አድርገናል። ከሳውዲ ለመጡት መቋቋሚያ የሚሆናቸውን ገንዘብ እንረዳለን ብለው በአደባባይ የዋሸን መንግስት….. በየመን በደረሰው የወገናችን መከራ የሁሉም አገር መንግስት አውሮፕላን፣ መርከብ በመላክ ህዝባቸውን ሲታደጉ የኛው መንግስት ተብዬው ግን የስልክ ቁጥር ፌስብክ ላይ በመለጠፍ ህዝባችን ላይ የሚያሾፍ መንግስት ተብዬ…. ዛሬ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ በህዝባችን ላይ በሚደርሰው ግፍ ሊነግሩን የሚፈልጉት ፌዝ እንዳለ  እናውቃለን። የኛ ውሳኔ ግን ፌዘኛን መስማት ሳይሆን ፌዜኞችን በማስወገድ ለህዝብ የቆመ መንግስት እንዲኖረን ማድረግ ተገቢ ነው።

ከተማ ዋቅጅራ

16.04.2015

Emeil- waqjirak@yahoo.com

The post የወያኔ  ዜማ በደቡብ አፍሪካ ተሰማ – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>