አክሎግ ቢራራ (ዶር)
እኛ ኢትዮጵያዊያን ከፋሽስቱ የጣሊያን ወረራ ወዲህ እንደዚህ ዓመት ተዋርደን አናውቅም። ውርደቱ ተከታታይና የማያቆም ለመሆኑ ምክንያቶቹ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባርን (ህወሓት) ብሎ ከሚጠራው የጎሳዎች የበላይ ገዢ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር ነን። የሊቢያ ሽብርተኞች የኢትዮጵያን ወጣት ክርስቲያኖች፤ በኃይማኖታቸውና በማንነታቸው ለይተው “የእስልምና ኃይማኖት በእናንተ ኃይማኖት አማካይነት ደም ማፍሰስ ርካሽ አይደለም”(“Muslim blood that was shedunder the hands of your religion is not cheap”) ብለው ወገኖቻችንን ሲያርዷቸውና በጥይት ሲገድሏቸው ያየ ኢትዮጵያዊና ማንም በሰው ህይወት ክቡርነት የሚያምን ግለሰብ ሁሉ ቪዲወውን አይቶ እንቅልፍ ለመተኛትና በሰላም ለመኖር አይችልም። ህሊናውን ለመመራመር ይገደዳል። ይኼ ብሄር፤ ብሄረሰብ ሳይለይ፤ በንፁህ ኢትዮጵያዊያን ላይ —[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—
The post ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ? ለማቆም እንረባረብ። appeared first on Zehabesha Amharic.