Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ ብሄራዊ ሃዘንን ወደ ብሄራዊ እምቢተኝነት

$
0
0

ሚያዝያ ፲፭,፳፻፯

ብሄራዊ ሃዘንን ወደ ብሄራዊ እምቢተኝነት

በያዝነው ሰሞን የሚሰሙ ዜናዎች፣የሚታዩ ምስሎች፣የሚደመጡ የሲቃ ድምጾች አጥንት ድረስ የሚዘልቁ ብሄራዊ ቁስል ሆነውብናል። ፳፬ ዓመት በኢትዮጵያውያን ጀርባ የተሰበቀውን ፍላጻን በመሸሽ ስደትን እንደ አማራጭ የወሰዱ ወጣቶች የዓሳ ነባሪ የዕለት ከዕለት ቀለብ ሆነዋል፣ የአፍሪካን ጫካዎች ሲያቋርጡ በአውሬ ተቆርጥመዋል፣ከሰባራ ጀልባና ከመንገድ ቀማኛ የተረፉት ባካባቢ አገራት ለመድረስ የቻሉትም በጎማና በቤንዚን ከነህይወታቸው ተቃጥለዋል በማጅራታቸውም ታርደዋል።
የዋሽንግተን እና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ሆይ ፈጣሪ ያጽናሽ፤ ኢትዮጵያ ሆይ የልጆችሽ ደም ለአገር ተንሳዔ ያድርግልሽ ከማለት ሌላ ቋንቋ የለንም። ሐዘናችንን ስንገልጽ ግን ነገ የሚወጣውን የነጻነት ብርሀን ከቅርብ ርቀት በተስፋ እያየነው ነው።

የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ፦

ዘረኝነትን ሸሽተህ ወደ ተሳለው ካራ ወደ እሚንቀለቀለው እሳት፣ እሚሰምጠው ጀልባ ላይ ከመሳፈር ነጻነት ያሳጣህን አረመኔ ዘረኛ ስርዓት እዛው በአገርህ ሜዳ ተናንቀህ ጥለህና ወድቀህ ነጻነትህን ብታውጅ የስደት እና የውርደት ምንጭ የሆነውን ከምንጩ ታደርቀዋለህ። መደራጀትም ምትሐት አይደለምና ከየአካባቢህ የጎበዝ አለቃ መምረጥና መናበብ እንደሚቻል ጠንቅቀህ እወቅ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፦

ኢትዮጵያዊነት ፈተና ላይ ወድቋል ለበርካታ አመታት የዘለቀው መከራችን ዛሬ ላይ ደርሧል፤ ከሰሞኑ አይሲስ በተባለ ሰይጣናዊ ስራ የተቀሉ ወገኖቻችን አይሲስን እንጂ እስልምናን እንደማይወክል ተረድተህ ወያኔ ይህንን ሁናቴ ስልጣን ማራዘሚያ ለመጠቀም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች መካከል ሊያጫጭሰው የሚፈልገውን ሴራ እንደጥንቱ ብልሃት አንድነትህን አጥብቀህ በንቃት፣ በጋራ ትቋቋመዋለህ የሚል የጸና እምነት አለን።

የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል! dcjointtaskforce@gmail.com ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም በነጻነት ትኖራለች !!!
April 27 flyer

The post የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል የተሰጠ መግለጫ ብሄራዊ ሃዘንን ወደ ብሄራዊ እምቢተኝነት appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>