ወያኔ ምን ሰራ ብትሉኝ ምንም ነው መልሴ ምክንያቱም እንደ መንግስት ለአንድ አገር መስራት ካለበት ደረጃ 10% እንኳን መስራት ያልቻለ መንግስት ሰለሆነ። በወንጀል የተዘፈቁ ባለስልጣናት፤ በሙስና የተጨማለቁ ካድሬወችን ፈልፍሎ በየክፈለሃገሩ በትኖ ወንጀልኝነታቸው እንዳይታወቅ ሙስናቸው እንዳይጋለጥ የወያኔ መንግስት የልማት የዲሞክራሲ የእድገት በማለት አሰልቺ መፍጨርጨር ውስጥ የገባው ዱኩማኑ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያ ላለችበት ችግር ተጠያቂው በዋንነት እርሱ መሆኑን አስረግጠን መናገር ያለብን ጌዜ ላይ ነን ኢትዮጵያ ዛሬ ትጣራለች የሰላም ያለህ እያለች ህዝቦቿ በወያኔ መፈናፈኛ በማጣቱ ሰላሙን ረግጦ በመያዝ ነጻነቱን በመንፈግ ሰለ ነጻነት የሚናገሩትን እና የሚታገሉትን በሙሉ ከአገር እንዲጠፋ በማድረግ በአገሪቱ ላይ ታላቅ ወንጀልን እየሰራ ያለ መንግስት ነው ።
በሌላ ጎኑ ደግሞ ሰላምን እኩልነትን አምጥቻለው ሁሉም የቤሔር ቤሔረሰብ መብት የተከበረው በኛ አገዛዝ ነው ይሉናል ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ የሆነ ወሬ እንጂ እውነቱ ይህ አይደለም እውነቱ ምንድነው ከተባለ፦
በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያንን ንብረት በሙሉ የሚያንቀሳቅሱት TPLF የሚባል ከአንድ መንደር የተሰባሰቡ አገር በቀል አሸባሪ ቡድኖች ናቸው። ለምን አሸባሪ እንዳልኩት ወደ ታች እዘረዝረዋለው እነዚህ ከአንድ መንደር ከትግራይ የተሰባሰቡ ቡድኖች 90 በመቶ የአገሪቱን ንብረት እየዘረፉ እራሳቸውን እያሳደጉ ሕዝቡን እያደህዩ መኖር የሚፈልጉ የቀን ጅቦች ናቸው። ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አንድም ጊዜ ሰለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተነግሮ የማያውቀው ኤፈረት ተብሎ በሚጠራው የማች ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚስት የሙስና እናት በሆነችው አዜብ መስፍን የበላይ ሃላፊነት የሚተዳደረው ይሄ የማፊያወች ድርጅት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በህገወጥ መንገድ ተቆጣጥሮት ይገኛል።
መሰቦ ሲሚንቶ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል፣ ባባ ዳይሜንሽናል ስቶን፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ኤክስፕረስ ትራንዚት፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ አዲስ ፋርማሲዩቲካል፣ ጉና ትሬዲንግ፣ ሂወት አግሪካልቸር፣ ሼባ ታነሪ፣ ኤክስፔሪየንስ ኢትዮጵያ፣ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ በቴሌ በመራት ሃይል በስኳር ፋብሪካ ወዘት.. ብቻ አጠቃላዩን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው እየዘረፉ ያሉት እነዚህ የወያኔ ጉዶች ናቸው። ይሄንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ ያወቀዋል። እነሱ ግን የዘረፉንን ዝርፊያ ልማት ነው እያለማን ነው ኢትዮጵያ እያደገች ነው ይሉናል ለምሳሌ ያህል በአዲስ አበባ ከተሰሩት ፎቆች ሙሉ ለሙሉ ሊያስብል በሚያስችል መልኩ የአንድ ብሔረሰብ ሰወች የገነቡት የቤተሰብ ፎቅ ነው ይሄ ነው ለነሱ ልማት።
ወያኔወች ከጫካ ይዘውት የመጡት አስተሳሰባቸው በ24 አመት ውስጥ መለወጥ ስላልቻሉ መረዳትም ሆነ ማስረዳትም አይችሉም ሰለ እውነትም አይሰሩም አገሩን ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ መኖር የሚፈልግ በስደት ላይ ሆኖ እንኳን አገሬን የሚል ሆኖ ሳለ በግድ ከሚወዳት አገሩ ግፈኞች ነግሰውበት አሰደዱት በደለኞች እያስተዳደሩት ከፍተኛ በደል አደረሱበት በደሉንም መሸከም ሲከብደው አገሩን ጥሎ መሰደድ ጀመረ እንግዲህ እውነት ያለው እዚህ ጋር ነው የተገፋ ህዝብ የተበደል ህዝብ ከአገሩ ሲወጣ በስደት መልካም ነገር ካልገጠመው ሁለተኛ ሞት ነው። የውርደት ሞት ነው። ስለዚህ ውርደትን ማስቆም አለብን ፦
ውርደት እንዴት ይቆማል ካልን ከላይ ወያኔ አሸባሪ ነው እንዳልኩኝ አሸባሪውን በማስወገድ ነው። ወያኔ ኢትዮጲያውያንን የሚያሸበርበትን ስራውን በዚህ መልኩ ያከናውናል….
1፦ዘርን ከዘር በማጋጨት የእከሌ ዘር በዳይ የእከሌ ዘር ተበዳይ አንዱ አጥፊ አንዱ ተጠፊ በማስመሰል የዘረኝነት መርዝን በኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል በመርጨት በጥላቻ እንዲተያዩ በማድረግ እርስ በእርስ እንዲጫረሱ ሌት ተቀን የሚሰራ አሸባሪ ቡድን ነው።
2፦ እውነትን የሚጠላው ወያኔ የሽብር ቡድን ከምስረታው ጀምሮ በደም የተጨማለቁ የወንጀለኞች ስብስብ ስለሆኑ እውነትን ይጠላሉ ለኢትዮጵያን መፃኢ ተስፋ ቅን የሚያስቡትን የነፃነት አርበኞችን እውነትኞችንና እውነትን ተናጋሪወችን እያደኑ ያጠፋሉ።
3፦ የተማረን ይጠላሉ የወያኔ ባለስልጣኖች 98% ከትምርት ነጻ ናቸው ባላቸው እውቀት የበታችነት ሰለሚሰማቸው የተማሩ ኢትዮጵያዊያንን በማሰር፤ በመግደል፤ በማሳደድ እንደተጠመዱ ነው፡፡ ዛሬ መንግስት ማለት ከተወሰነ አካባቢ የተውጣጣ የደንቆሮ ስብስብ የሆነ ይመስላል።
ብዙ ሰለወያኔ ክፋት እና ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሰራውን ስራ ብንዘረዝረው አያልቅም ወደ ስራ የምንገባበት ወደ ተግባር የምንለውጥበት ጊዜው አሁን ነው ።ገዳያችንን መግደል አለብን፡ አሳዳጃችንን ማሳደድ አለብን ፡በዘረኛው የወያኔ አምባገነናዊና ግፈኛ አገዛዝ እየተማረሩ ሃገራቸውን ጥለው የሚኮበልሉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እጂግ በርካታ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በወገኖቻችን ላይ በሳውዲ፤ በየመን ፤በደቡብ አፍሪካን ፤በሊብያ፦ የደረሰባቸው ግድያ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መቀጠሉ ስለማይቀር የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አንተ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ሱማሌ ፤ ጉራጌ ፤ ሃድያ፤ ሐረሪ፤ ከንባታ ፤አፋር ፤ትግሬ፤ አንባባል ጠላት ከፊታችን ነግሶ አሸባሪ በላያችን ተሹሞ።ወገኖቻችንን በአገራቸው ላይ እየተገደሉ በስደትም እየሞቱ ሰለሆነ ሞትንን ማሸነፍ ያለብን ገዳዩን ስንገድል ነውና በአገር ተደስቶ ለመኖር ሰርቶ ለማደግ ፍቅር አንድነት ለማምጣት ቆርጠን ከዳር እስከዳር ሁሉም በአንድነት በመነሳት ወደየትም እንዳይፈናፈኑ አድርገን አሸባሪውን ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ እናጥፋ።
እምዬ ኢትዮጵያ የሚያስለቅሰሽ ያልቅስ ደምሽንም የሚያፈሱት ደማቸው ይፍሰስ የሚያስጨነቁሽም ይጨነቁ የሚረብሹሽም ይረበሹ ደስታሽን የሚናፍቁ ሁሉ ደስታሽን በአንድነት ይዩ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!
ሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ) 08.05.2015
Email samilost89@yahoo.com
The post ከአገራችን ያሰደደንን ወያኔን አሳደን አገር ነፃ ሆና የምንኖርበትን ዘመን እናምጣ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.