”አንዳንድ ወዳጆቻችን ሄኖክ ሰማእግዜር ላይ በዋይት ሃውስ የደረሰው የቁጣ ተቃውሞ አግባብነት እንደሌለው ተከራክረዋል። በሄኖክ ላይ በአደባባይ ተቃውሞ ሲሰማ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። እንደውም በዲሲ አካባቢ ያሉ አክቲቪስቶስ ዘገባ በተደጋጋሚ ስለሚያዛባ እነሱ በሚያዘጋጁት ስብሰባም ይሁን ሰልፍ ላይ እንዳይገኝ ከዚህ በፊት እንደጠየቁት አውቃለሁ። ማንም ሌላ ሰውን ያለ አግባብ አይቃወምም። በቪዲዮው ላይ እንዳየነውም ተቃዋሚዎቹ በቁጣ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ማንም አልደበደበውም። ሄኖክ የለቀቀው የቪኦኤ ቪዲዮ ዘገባ ግን ተደበደበ ይላል። ህዝብን የሚያስቆጣውም ጉዳይ ይሄ ነው።
በቁጣ ተቃውሞን ማሰማት እንደተባለው አግባብነት የሌለው ጉዳይ ሳይሆን መብት ነው። ዋናው ጉዳይ ሄኖክ ሳይሆን ህዝቡ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት በመገኘት ፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጎዞ ለአንባገኖች ድጋፍ በመግለጽ እንዳይጠናቀቅ ማስገንዘቡ ነው። እነ ሄኖክ ዋናውን ጉዳይ አቅጣጫ ሊያስቀይሩ ቢሞክሩም ተቃውሞው በዋሽንግተን ፖስት ላይ ታትሞ ወጥቷል። ዋሽንግተን ፖስት ላይ የወጣ ዘገባ የኦባማንም ይሁን ይሌሎች ባለስልጣናት ትኩረትን ስለሚስብ የተቃውሞ ሰልፉ በድል ተጠናቋል ማለት ይቻላል። ትንሽ ቅር ያለኝ በተቃውሞው ሰልፉ ላይ መገኘት አለመቻሌ ነበር። ብገኝ ኖሮ እኔም በቁጣ ተቃውሞዬን ከማሰማት አልቆጠብም ነበር። ነጻናት ናፋቂውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በመወከል ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ በወኔ ላሰማችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ምስጋናና ክብር ይገባችሁዋል።
ትግላችን ሁለ ገብ ነው። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!”
Abebe Gellaw
The post በሄኖክ ላይ በአደባባይ ተቃውሞ ሲሰማ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም – አበበ ገላው appeared first on Zehabesha Amharic.