ከካሳሁን ይልማ (የኢሳት ጋዜጠኛ)
የምትመለከቱት ፎቶ ከ30 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሲያከብሩት የነበረውን ዓመታዊ የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል ለማፍረስ የተመሠረተው የክፋፋዮች ቡድን ነው።
ይህ በጥቂት ገንዘብ አሳዳጅ ወረበሎች የሚመራ ቡድን ዓላማው እና ዒላማው የአላሙዲን ሚሊዮን ብር ስለሆነ የሚፈልገውን ቅርጫ እስካደረገ ድረስ “ሕዝብ እና አንድነቱ ሲዖል ይግባ” የሚል ነው።
ሌላው ተያይዞ ያለው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ ህወሓት ዲያስፖራው ውስጥ ሰረስሮ ገብቶ በሀገር ቤት የፈጠረውን የአፋና ና ቁጥጥር መረብ በውጭ ሀገርም የማንሰራፋት ስሌት ነበር።
ሆኖም ይህ በክፋት እና በሴራ የተመሠረተ ቡድን ከዋናው ፌዴሬሽን ተሰንጥቆ በመውጣት ለመሰንጠቅ ያደረገው ጥረት ግን ሊሳካ አልቻለም። ከዚያ ይልቅ ከፌዴሬሽኑ መርዝ ተነቀለለት ማለት ይቀላል።
ማህበረሰቡም ሴራውን በመገንዘቡ የተነቀለው መርዝ ላለፉት ሦስት ዓመታት ባዘጋጀው ተመሳሳይ ዝግጅት ላይ ለመታደም እግሩን አላነሳም። እባብ መኖሩን አውቆ ወዳለበት የሚሄድ የለምና።
በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተጨዋቾች በብዛት የጊዮርጊስ ተጨዋች የነበሩ፣ በተለይም ከአብነት እና አላሙዲ የክለቡ ባለቤትነት ዘመን ተጫውተው ያሳለፉ ናቸው። በቀጥታ ሲጠየቁ ይሉኝታ ይዟቸው እና ፈርተው ይሄዳሉ። ፈርዶባቸው!
ይሄ ቡድን ከሼኹ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀፍሎ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ለሁለት ዓመታት በግዙፍ ስታዲየም ዝግጅት አዘጋጅቶ ከፋፋዮች እና ጥቂት የህወሓት ደጋፊዎች በተገኙበት ወና ሆኖ በአሳፋሪ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህ ክሽፈቱን በመረዳት ዘንድሮ ወደ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር በመሄድ ከስታዲየም ወረድ ብሎ በትምህርት ቤት ሜዳሌላ ዕድሉን ሞክሯል። ወደ ዴንቨር ሲወሰድ ዋናው ቀመር በከተማዋ በረካታ የትግራይ ብሔር ተወላጆች በመኖራቸው ቢያንስ እነርሱ ገብተው በድኑን ቡድን ነፍስ ይዘሩበታል ተብሎ ነው።
አንድ በዝግጅቱ ላይ ከእንግዲህ በፍጹም እንደማይሄድ በምሬት የነገረኝ ተጨዋች “ዝግጅቱ የህወሓት ፌስቲቫል እንጂ የኢትዮጵያዊያን አልነበረም። እዛ በመሄዴ ለራሴ አፈርኩ” ብሎኛል።
ተሰንጥቀው የተነቀሉት መርዞች ቡድኑን ሲመሠርቱ መፍጠር የፈለጉት ይህንኑ ነበር፣ መከፋፈል። ለሆዳቸው እስካደሩ ድረስ የማህበረሰብ እና የእሴቱን ዋጋ የሚያሰላስል ህሊና የላቸውም። ተመሳሳይ ሴራዎች እና ሸፍጦች በቤተክርስትያን፣ በመስጊድ፣ በጓደኛሞች ማህበራት እና ፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ይፈጸማሉ። ከድርጊቶቹ ጀርባ ያለው አውራ አቀናባሪ ደግሞ ህወሓት ነው።
ስለዚህ ማህበርን፣ ማህበረሰብን፣ ብሔርን፣ ጎረቤትን፣ ቤተሰብን እና የራስን አዕምሮ በጥቃቅን ጥቅማ-ጥቅም የሚሸነሽነው የህወሓት ሥርዓት እንዲወድቅ ሁሉም ተቆርቋሪ ዜጋ የበኩሉን አስትዋጻዖ ማበርከት ግዴታው ነው።