ሳሙኤል አሊ ከኖርዌይ
የወያኔወች የውስጥ ጅማታቸው መፈታት ከጀመረ ሰነባብቷል። የሚይዙትና የሚጨብጡትን ካጡ ትንሽ ቆየት ብለዋል በወያኔ ሃሳብ በዘር ፖለቲካ እየጠላለፈ ምስራቁን ከምዕራብ፤ ደቡብን ከሰሜን፤ እያነሳሱ የራሳቸውን ወታደሮች አጠናክረው ሰለ አገሩ ቀና አሳቢውን ወይም መብቴን እጠይቃለው የሚለውን እየገደሉ አገሩን በሙሉ በራሳቸው ቁጥጥር ስር አድርገው መቶ አመት እንገዛለን በሚል እቅድ ተነሳስተው ኢትዮጵያዊኑ እርስ በእርስ እንዲጠላላና እንደጠላት እንዲተያዩ እያደረጉት ነው ። በከፍተኛነት የባንዳነትን ስራ እየሰሩ እራሳቸውን በሁሉም እረገድ የበላይ አድርገው ሌላውን ዜጋ እንደሁለተኛ ወይም እንደ ባርያ ለመግዛት ቀን ከለሊት እየሰሩ ያሉት የወያኔ ቡድን የደም ዝውውራቸው የሚቋረጥበት የልቦና ተንኮላቸው የሚኮላሽበት የዘር መረባቸው የሚበጣጠስበት ትግል ተጀምራል። ያርበኞች ግንቦት ሰባት የነጻነት ጥሪ ወደ ትጥቅ ትግል መግባት ሲያስጨንቀው ከርሞ ዛሬ ጭቆናው ይብቃ ያለው ሕዝቤ የባርነት ኑሮን አልቀበልም ያለው ኢትዮጵያዊ በግፈኛው ወያኔ ላይ መሳርያውን አንስቶ ወደ ግንባር በመትመም ጀግንነቱን እያሳየ ይገኛል። አርበኞች ግንቦት ሰባት በይፋ ጦርነቱን መጀመሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በጉጉት የሚጠብቀው የነበረ ቢሆንም ወያኔወች ደግሞ በጽኑ የሚፈሩት ጉዳይ ነበር። እንግዲህ የማይቀርላቸውን የጥፋት ዘመናቸውን ማቅረቢያውም በአርበኞች ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ የነጻነት ጥሪ በይፋ ተነግሮ ወያኔወችን በቆፈሩት ጉድጋድ በያሉበት ሊቀብር ተነስታል።
የግቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በሕዝብ ለማስጠላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልማሱትም ጉድጓድ የለም። ስሚ አጡ እንጂ በአንዳንድ በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያን ላይ ትንሽ ጉንጉምታ የሚፈጥር አዝማምያ የነበረ ቢመስልም ዛሬ ግን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ያንን ጉምጉምታ አጥፍተውታል። በርገር እየበሉ ጦርነት የለም፧ አሜሪካና አውሮፓ ቁጭ በለው አገር ቤት ያለውን ሕዝብ ማስጨረስ የለም ፧ የሚለውን የወያኔ የማደናገርያ የሃሰት ቅስቀሳ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደበርሃ በመውረድ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ጦር መቀላቀላቸው ለሁሉም ግልጽ ያደረገና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወያኔ የተባለውን ጭራቅ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ያስገነዝበናል። በኢትዮጵያ አገራችን ሊደራደሩ ፍቃደኛ የማይሆኑ አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ዶክተር ብርሃኑ ወደ ወረደው በርሃ ወርዶ ወያኔን ዶግ አመድ አድርጎ ነጻነቱን እንደሚያውጅ የታወቀ ነው። ለዚህም ነው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ነጻነት በመታገል መስዋትነትን የከፈሉት። ዛሬ እነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ በርሃ ገብተው መሰራት ያለበትን ስራ እየሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ የብርሃኑን ጮራ የሚያይበትን ለወያኔ ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር የሚጠፋበትን መንገድ ቀይሰው በርሃ በመውረድ ታላቋን አገር ከጥፋት ለመታደግ መሰዋትነት እየከፈሉ ያሉት።
ዛሬ ወያኔና የወያኔ አጫፋሪ ሁሉ ዶክተር ብርሃኑ ኤርትራ በርሃ ገባ ብለው ሲያሽማጥጡ የነበሩ ሁሉ ነገ አዲስ አበባ ቤተመንግስት ገብቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ሲያደርግ ታዪታላቹ ፧ የነጻነት መዝሙር የሰላም ባንዲራውን ይዞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በህብረት ሲያዘምር ታዪታላቹ። እመኑኝ ደርግ እንደወደቀው ወያኔም ይወድቃል፦ እንዳለው ሃብታሙ አያሌው; ዛሬም እመኑኝ ነገ ወያኔወች የዘረፋትን ሳይበሏት ጎሮሮአቸው ላይ እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮአቸው ላይ ይቆማል፧ እመኑኝ ኢትዮጵያን አጠፋለው ብሎ የተነሳው ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጠፋዋል፧ እመኑኝ ነጻነቱን ነፍገን፤ ጨቁነንና፤ እረግጠን፤ የበላይ ሆነን እኖራለን የሚለውን ወያኔ በሕዝባችን የጠነከረ ብትር ቀምሶ ከኢትዮጵያ ምድር ይጠፋል፧ ይህ ቀን እሩቅ አይደለም ሁላችንም አርበኞች ግንቦት ሰባትን በመቀላቀል በመደገፍ ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር መውጫና መግቢያ አሳጥተን የምናጠፋበት ጊዜ ቅርብ ነው።
ወያኔወች የማወናበጂያ ዘዲያቸው በሙሉ ከሽፎባቸዋል የወያኔን ክፋት ሁሉም ኢትዮጵያዊ አውቆታል አሁን ወያኔ የማጥፋቱን ስራ ብቻ ሳይሆን አገርንም የማዳኑ ስራ እየተሰራ ነውና፦ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሩን ከጥፋት ለመታደግ ባአገር በነጻነት ለመኖር ለኢትዮጵያ አገርህ ስትል ተነሳ ድላችን በአገራችን ፤ መኖርያችን በአገራችን፤ መደሰታችን በአገራችን፤ ሆኖ ስደትና ችግር እንዲቆም ዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች የወያኔ የክፋት መረብ ከአርበኞች ጎን በመሰለፍ የድላችንን ዜና አብረን እናብስር።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ሳሙኤል አሊ ከኖርዌይ
Email samilost89@yahoo.com
20.7.2015