እኔ የታሪክም የፖለቲካም ሰው አይደለሁም፡፡ ግን ታሪክ አዋቂ ነን ፖለቲከኛም ነን የሚሉት ሰዎች ለሕዝብ በሚያካፍሏቸው እነሱ ታሪክ ነው ለሚሉት ፅሁፋቸውና አሰትምሮታቸው፣ ምሁራዊ ነው ለሚሉት ትንታኔያቸውና አስተያየታቸው፣ ስኬትን ያመጣል ለሚሉት ንድፈሀሳባቸውና ዕቅዳቸው ለዘመናት የእኔና የመሰሎቼ አእምሮ ለመቀበል እየተቸገረ እራሱ መልሶ እነሱ እኮ ምሁር ናቸው፣ ብዙ ያወቃሉ ስለዚህ ትክክል ናቸው በሚል ሲሸነገልና ሲሸነፍ ኖሯል፡፡ ታሪክም (ፅሑፎቹን ማለቴ ነው)፣ፖለቲካም መነሻቸው ጥላቻ በመረዛቸው ፍራቻ ባሸማቀቃቸው አእምሮዎች ተፈብርኮ ታሪክ ወይም ፖለቲካ ከሆነ ምሁርነትን የሚጠይቅ ሆኖ አላያየውም፡፡ በተሻለ እኔ አና እኔን መሰል አንብበንም (ቢያንስ ማንብ እንችላለን) ይሁን የሰማንውን እውነት ወይም ማጣቀሻ ባለው የሀሳብ መነሻ ታሪካዊም ሆኑ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን ብንሰጥ ተፎካካሪ እንደምንሆን ስለደመደምኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚከተለው ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት ሙከራ አደርጋለሁ (ይህ ሙከራ ነው)፡፡ -..ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ