ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ
አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያኖች በሙሉ ያነበቡት መጻሕፍ ነው። ልብ ወለድ ሳይሆን እውነተኛ መጽሐፍ ነው። ሰው ያሰበውን ይጽፋል ሰው የተመኘውን ይናገራል ሰው እርሱ እራሱ ደስ ያሰኝውን ይከትባል። አንዳርጋቸው ግን ሂይወቱን፤ ሙያውን፤ እውቀቱን፤ ሃብቱን፤ ለኢትዮጵያን በማይጠፋ መልኩ አስነብቦ አሳውቆናል። የአንዳርጋቸው የሂይወት መፅሐፍ ሚሊዮኖች አንብበው በስራው ተደንቀው ሚሊዮኖች የተከተሉት እውነተኛ ደራሲ እውነተኛ የሂይወት ተጓዥ ቆራጥ፤ የእውነት አርበኛ መሆኑን ተረድተው ሚሊዮኖች የሱን ፈለግ ተከትለው የሃሰት ሃይልን ፤የሃሰት ደራሲን ፤የሀሰት ተጓዥን፤ ለመደምሰስ እንደተሰለፉ አልተረዱትም ይሆን?
ኮፒ ራይት ወንጀል ነው ተብሎ እንዲቆም ትግል እየተደረገ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ከአእምሮ አፍልቆ ተጨንቆ ጊዜውን ገንዘቡን አፍስሶ የሰራውን ስራ ምንም ሳይደክም ባቋራጭ የሰውን ስራ ሰርቆ የራስ አድርጎ በማቅረብ የሚደረግ የፈጠራ ዘርፍ ወንጀል በመሆኑ። ወያኔ ደሞ የማያሳየን የወንጀል አይነት የለም፦ የማያመጣብን የክፋት ሃሳብ የለም ፤ የማይነግረን የመጠፋፋት ወሬ የለም፤ ሰሚ አጣ እንጂ እናም አርበኞች ግንቦት ሰባት በይፋ ጦርነቱን አውጆ ሲንቀሳቀስ ወያኔን በአጭር ጊዜ ጉሮሮው ላይ እንደሚቆም ስለሚያውቁት በተቻላቸው መጠን አርበኞች ግንቦት ሰባትን የሚያጥላላ ስራ ለመስራት ዝግጅታቸውን በበረከት በፈጠራ ድርሰት እየተሰናዱ ይገኛሉ። የጉጅሌው መንግስት አርበኞች ግንቦት ሰባትን አሸባሪ፧ አሸባሪ ቢለውም የኢትዮጵያ ህዝብ መንገዶችን እየፈለጉ ወደ አርበኞች ግንባር ሲቀላቀሉ ሲያዩ በመደናገጥ ሌላ ደግሞ የመብት ጥሰት ለመፈጸም የክህደት ስራወችን በመስራት ላይ ናቸው ።
ቴድሮስ አድሃኖም ለአንዳርጋቸው ላፕቶፕ ሰጥተው መፅሐፍ እየጻፈ ነው ብሎ መናገር በተበላ ቁማር ማንም የሚደናገጥ ወይም የሚረበሽ የለም ቤተሰቡን እንዳያገኝ የተከለከለው አንድ አርጋቸው ፤ በአለም ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዲፕሎማቶች፤ እናዳይጎበኙት የታገደው አንድአርጋቸው ከማንም ህብረተሰብ ጋር እንዳይገኛኝ አድርገውት ጭለማ ቤት ውስጥ አስቀምጠውት ላፕቶፕ ሰጥተነው መጽሐፍ እየጻፈ ነው ማለት በበደል ላይ በደል በጥፋት ላይ ጥፋት እየተሰራ መሆኑን እናውቃለን። በደልንም ጥፋትንም የሚቆመው ወያኔን በማስወገድ ብቻ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ ተረድቶታል።የየሕዝቡን ጥያቄን፦ በቤተሰቡ ይጎብኝ የውጪ ዲፕሎማት እና ጋዜጠኞች ይጎብኙት የሚለውን ሳትመልሱ ላፕቶፕ ሰጥተነው መጽሃፍ እየጻፈ ነው የሚለውን የደደቢቶች ንግግር ወደበለጠ እልህና ትግል ውስጥ የሚያስገባን እንደሆነ እንድታውቁት ለመናገር እወዳለው ።
በረከት ስሞኦን አንተ በሞት መንገድ ላይ ያለህ የሞት ተጓዥ ነህና ባለችህ በጥቂት ዘመንህ ለህዝብህና ለአገርህ መልካም ሰርተህ ማለፍ ብተመኝ ምን ነበረበት አሁን የምትሰራው የክፋት እና የጥፋት ስራህ ረዘም ላለ ጊዜ እንኖራለን ብለው ለሚያስቡት ለልጆችህ ነውና አስብበት ወንጀልን በመስራት ስልጣንን ማቆየት የአንባገነን መንግስት መገለጫው ቢሆንም ስው ያልሰራውን ስራ እንደሰራ አድርጎ ማቅረብ ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ዋጋውም ወደግላዊ ሂይወትህ ውስጥ የሚያስገባ አደገኛ ነውና ይታሰብበት
አንተ ዛሬ አንድ የውሸት ፈጠራ መፅሐፍ በአንድአርጋቸው ጽጌ ስም ስልጣንህን ተጠቅመህ ልታወጣ ትችላለህ ነገር ግን መቶ እጥፍ ሰለአንዳርጋቸው እውነተኛ ስራ ሰለ አንተ ደግሞ የክህደት ስራ እንደሚወጣ አትዘንጋ። በአንድ የውሸት የፕሮፖጋንዳ መጽሐፍ የአንዳርጋቸው ጽጌን ስም በማጠልሸት የትግል ሂደቱን አበላሸዋለው ብለህ ያሰብክ ከሆነ ዛሬም እዛው ጫካ ውስጥ እንዳለህ የሚያሳይ ነው። አንዳርጋቸው በማሰራቹ ትግሉ አበቃለት ምስጥሩንም ዘረዘረው ብላቹሁ ጭቃ ወሬአቹሁን ስታወሩ አርበኞች ግንቦት ሰባት የትጥቅ ትግሉን በግሃድ ጀመርኩ ብሎ አወጀ የዚህን ጊዜ መያዥያና መጨበጭያው ሲጠፋቹ የውሸት ድርሰት ለማጻፍ ተነሳቹ መጻሃፉን አንዳርጋቸው እንደ ጻፈው አድርጋቹህ የራሳቸውን የከሰረ ፖለቲካ መቀስቀሺያ ልታደርጉ ተነሳቹሁ እንግዲህ ይህን የክፋት ሃሳባቹሁን ሕዝቡ ቀደሞ ተረድቷል። ከወያኔ እውነትን መጠበቅ ወይም ሰላምን ማሰብ አይቻልም ወያኔወች ባለቻቹህ ጥቂት ግዜ ወርያቹሁን ቃርሙ አርበኞች ግንቦት ሰባት የዘመናቹሁን ፍጻሜ እስከሚሰጣቹህ ድረስ እንደ አበደ ውሻ ይሄንንም ያንንም ንከሱ ወያኔን ማስወገድ በሃይል ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት ሰባት የተነሳው ለዚህ ነው።
ድል ለአርበኞቻችን
ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ
- 08. 2015
Email samilost89@yahoo.com