ዋሽግቶን ዲ ሲ
ማክሰኞ ፣ ሴፕቴምበር 15 ቀን 2015
ነጎደ እየጠራ ገፋ ትግሉ።ይህ እውነትተኛ አባባል ከቀድሞው የኢህአፓ የትግል መዝሙር ነው።ለአገራቸው ቀድሞ እንደተሰዉት ሁሉ የዛሬዎቹ አርበኞችም ደምሂቶችም ሁላችንም ልንዘምረው የሚገባ ነው።ከታሪክ መማር ማለት በተግባር ይህ ነው ብል ስተት አይሆንም።ከዚህ ወዲያ እየጠራ ይገፋል እንጂ ትግሉ ወደኋላ አይቀለበስም።ጥምረቱን ምንም ሀይል አይገታውም።ህዝባዊ ስለሆነ!የዚህ ጽሁፍም ዓላማ ትግላችን እየጠራ ይገፋል፤የህወሃት ክስረት እየጨረ ይሄዳል ለማለት ነው።
ወያኔ ህወሃት ወሰን የሌለው በጀት መድቦ አቀናበርኩት ብሎ ይፋ ያወጣው “የተቀነባበረ” ሴራ በነሞላ አስገዶም መክዳት ምክንያት መግለጫ ተሰጥቶበታል።ወያኔ ህወሃት “አቀናበርኳቸው” ያላቸው ድርጊቶችን፤በኤርትራ ውስጥ የአቶ አንዳርጋቸውን ግድያ፤በሰንአ የመን የአቶ አንዳርጋቸውን መታገት፤አሁን ደግሞ የነሞላን አንድ ጋንታ ይዞ ወደ ሱዳን ቀጥሎም ኢትዮጵያ መግባት እንቆጥራለን።ይህ ሁሉ የወያኔ ህወሃት መንግስት ጥረት ያላሰለሰ ውጣ ውረድ የትጥቅ ትግል ተጀምሮ፤ጎልብቶ የህወሃት ስንብት እንዳይረጋገጥ ነው።የወደፊቱም መውተርተር ከትጥቅ ትግል መጠናከር ፍራቻ ነው እንጂ ሌላውን ጨብጧል ።ውሉን የሚፈታው ብረት መሆኑን ወያኔ ስቶት አያውቅም።
ሰምኑ በተፈጠረው ሁኔታ ከሁሉም ይልቅ ወያኔ የህወሃትን ስለላ እርባና ቢስ የሚያደርገው ለድርጊቱ ቸኩሎ አላፊነት መውሰዱ ነው።በጣም የረቀቀ ይሆን የነበረው እነሞላ አስገዶም በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ኤርትራ ጋር ጥርስ ተናከሱ ብሎ በስደት ወደ ሱዳን ቢያወጣቸው ኖሮ በሁኔታው ብዙ የፕሮፓጋንዳ ሸመት ይገዛበት ነበር።ስለላ ትልቅ የአእምሮ እሴትን የሚሻ ተግባር ነው። ለወያኔ ህወሃት የሚሆን የስራ ምድብ አይደለም።(ለስለላ የቀጠሯቸው ፈረንጆች ደደቦች ብለዋቸዋል) የወያኔ ህወሃት ስለላ፤ተቧዳኙ የይዘትና የጥራቱ ደረጃው ዝቅ ያለው አይጋ ፎረም፤ ተራ ተላላኪው ኢትዮጵያ ፈርስት፤በዳያስፖራም ወሬ አናፋሽ የሆኑት ኢትዮ ሚዲያ ከነቃጭሉ ደምስ በለጠን ጨምሮ አንዴ ተንጫጩ።እለቱን ጥምረቱን በትነዋል።በኤርትራ ያለ ተዋጊን አተራምሰዋል አሉ በነሱ ቤት። በኢትዮጵያ ውስጥና በዓለም ተሰራጭቶ ያለው ዜጋ ተስፋ ያረገበት፤የለፋበት ሁሉ በወያኔ ህወሃት ቤት የእንቧይ ካብ ነው ማለት ነው። ስለላ የእለት ትንሽ ድል ማግኘት አይደለም።ይህ ሳይገባቸው ከአራት ኪሎ ይባረራሉ ማለት ስለህወሃት ማጋነን አይደለም።በሞላ መክዳትም ወያኔ ተቻኮለ። ይህ ነው የወያኔ ህወሃት ብልሃት።ከንቱ ልፋት! የጅብ ችኩል ይሏል ይህ ነው።የኢትዮጵያ አምላክስ የት ሄዶ?
ሞላ አስገዶም ወታደራዊ መሪ እንጂ ፖለቲከኛ አይደለም ቢባል እንኳን ሊያስከዳው የቻለውን ምክንያት ቅልብጭ አድርጎ መናገር አለመቻሉ ከነጻ አውጭ መሪ ይልቅ አንዱን የወያኔ ተራ ጄኔራል አስምስሎታል።ፖለቲካው ቀርቶ ስለ አመላለጡ ማቅረብ አለመቻሉ ቢሄድ አያጎዳም የሚለውን አባባል የሚደግፍ ነው።ድርጅቱ ደምሂት ሞላ ሊቋቋመው ያልቻለ የውስጥ እንቅስቃሴ ነበር ላለው ብዙ መረጃ እንድመኝ አድርጎኛል።ሞላ አስገዶም ወያኔ እሱ ለትግል ከተነሳበት ጊዜ በኋላ ምን በጎ አድርጓል?ላነሳውስ የአገራችን አንድነት ምን ፈይዷል? ዳር ድንበሯስ ?እሱ ከሸሸበት ሳይርቅ ለሱዳን በወያኔ የተሰጠውን መሬት ወሬውን አልሰማም ?መሪ መሆኑ ዜና ይከታተላል እንድንል ያስገምታል።ታዲያ ስለረሃብና ስደቱ፤ ሞቱ ውርደቱ አይሰማም ?ስለ ትግራይ ህዝብ የሌላው ይቅር አይሰማም?ይህ ሰው በአስራ አራት ዓመታ አእምሮ አጎልባች ምን ነገሮችን አርጎ ይሆን?ደምሂት ካለው ስልጣንን የማጣት ብሎም የግል ጥቅም በተቀር ሌላ ሞክንያት የሚጥም አይሆንም።ያለውን የጠላት ጦር እንኳን እንዴት “እደጠራረገው” በቂ ወታደራዊ መግለጫ አልሰጠም። በተፈጠረው ሁኔታ ደምሂት አዲስ የተሻለ መሪ የሚያወጣበት እድል ማግኘቱ ለድርጅቱ ብሎም ለጥምረቱ የጠና መሰረት ላይ መቆም ወሳኝ ነው።ሳይደግስ አይጣላም ይሏል ይህ ነው።
በሰጠው መግለጫ ሞላ አስገዶም የሚመስል ነገር እንኳን ሊያቀርብ አልቻለም።የነበረችውን ታሪካዊ እድል አባከናት ለመጨረሻ ጊዜ።”ጥምረቱ ትርጉም የለውም” “ጥምረቱን እኛ ነን ያመጣነው”እነዚህ አባባሎች ስለ ሞላ አስገዶም እና ስለላከው ወያኔ ብዙ ይናገራሉ።ጥምረቱ እንደምናውቀው በአራት ድርጅቶች መላከል የሆነ ነው።መሪዎችን ተከታዮችን ይዞ ማለት ነው።እኒይን ሁሉ ሞላ አስገዶም ሲዘውራቸው ነበር ማለት ነው! ሞላ እንግዲህ በአስራ አራት ዓመታት ያካበተው ምትሃታዊ ሀይል ነበረው? የማይካደው የጦር መሪ መሆኑ የሚሰጠው ያሻውን ሀይል ባሻው ጊዜ ማንቀሳቀስ መቻሉ ነበር።ይህን ተጠቅሞ አምልጦበታል።ሞላ የጥምረቱ አላማ ከደምሂትም ከሱም ከማንም ሌላ ድርጅትና መሪ የገዘፈ መሆኑን ሳይረዳ ይቀራል ማለት አይቻልም።ግን የስልጣንን ማጣት ፍርሃት አየለበት።የደምሂት መግለጫ እንዳቀረበው ሁሉ። የሻቢያ “ኢትዮጵያን መበታተን” ተቃራኒም የመጨረሻው ገቺው ጥምረት\ውህደት ነውና ለክጂው ያቀረበው ምክንያት እንዲያ የወያኔ ስለላ ወደሱ አፍ የዶለውን ነው። “የሻቢያን ጦር መጠራረግ” ብዙ ማለት ያስችል ነበር።እንደ አንድ የጦር መሪ።
ከሞላ አስገዶም የሁለት ቀናት ወሬ በኋላ ወያኔ ህወሃት ምን ይዞልን ይመጣል ?ከኤርትራ እስከ ዋሽንቶን ዲሲ በረቀቀው ስለላ ስራው፤ጥምረቱን አመከንኩት።አለቀ።ደቀቀ።እያለ ሊያዝናናን መሞከሩ ይጠበቃል።መጽሀፍም ታተመ መባል ፤ቃለ መጠይቆች፤ይቀጥላሉ። ለውጊያ እንዘጋጅ፤ኤርትራ ዘመቻ ብዙ ድግሶች ይኖራሉ። ከልማት ወሬ በራብ መምጣት እፎይ ስንል ስለ ኤርትራ ደግሞ የምንታክትበት ሁሉ ከፊታችን ነው። ወያኔ መከራውን እያየ ነው።ሙስና ስቅ ስቅ ያሰኘዋል።ኢኮኖሚው ውሉ ጠፍቷል።አሻንጉሊት ድርጅቶቹ ተዳፍረውታል።ተጠልቷል።ከሁሉም ይበልጥ ሰሜን ኢትዮጵያን ጎንደር፤ትግራይ፤ወሎን ብቻ ከላይ የሚመጣን ይበልጥ ይሰጋል። ይህና ይህ ብቻ ነው የህወሃት እንቅል ነሺ ቅዥት።
የትግሉን ሂደት ስናስተውል ዋናው በዚህ አጋጣሚ ጎልቶ እየሄደ የሚወጣው የጎሳና የክልል ድርጅት አመለካከት መክሰሚያው መዳረሳችን፤ ከወያኔም እንገላገል ካልን በጠባቡ ከማሰብና ከማየት ለዓላማም የጎሳና የክልል መሰረት ከመስጠት ርቆ ጥምረት ውህደት አስቦ “አገራችንን ማዳን” በትልቁ የተጻፈበት ባቡር ሳያመልጥ ቶሎ መሳፈር ነው። ይህ ባቡር ከአስራ አራት አመታት በኋላ እድሉን ያባከነውን ሞላን ጥሎት ገስግሷል።ሌሎች ድርጅቶችን ይህ ፈጣን ባቡር ማምለጥ የለበትም።ከዚህ ወዲያ ጥምረት ወይም የሞላ መንገድ ነው።ካልሆነ የጎሳና የክልል ድርጅት በቃኝ። ተውኩትም ማለት የኮራ አማራጭ ነው።በግሌ ወደፊት በታሪክ ያስመሰግናል ባይ ነኝ።
የጥምረቱ ፍሬ እና ገለባ በቶሎ ለየ።እየጠራ፤ ገፋ ትግሉ።ፈጠነም እላለሁ።ኢትዮጵያን አምላክዋ እንደታረቃት ትልቁ ምልክት የጥምረቱ እንቅፋት ብዙ ዋጋ ሳያስከፍል ራሱ በገዛ እግሩ ሹልቅ ማለቱ ነው።ሹልክ እንደ ሞላ አስገዶም።ወገኔ የትግራይ ሰው የሚገጥምበትን ለማሰማት ያብቃን።አሁን የጥምረቱን የስራ ውጤት እንስማ።ስለ ሞላ በዚህ ይቁም ከናካቴው::እየጠራ ገፋ ትግሉ።ፋሽስቱን ባንዳውን እያስወገደ። ነጎደ ጠራ ትግሉ!
አነድነት ሀይል ነው!
ድል ለመብቱ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ!
ኢትዮጵያ በህዝቦችዋ አንድነትና ፍቅር ለዘለዓለም በነጻነት ትኑር!