ያልከውን አላልኩም..ሰማህ ወይ ወዳጄ?
እንዴት እበላለሁ?..እጄን በገዛ እጄ::
ክብሬን አላቀልም..እንደምን አድርጌ?
እንደሌለ አውቃለሁ..
የቁሳቁስ እንጂ..የጀግና አሮጌ::
መቼም..መቼም..መቼም አልዘነጋ
የናቤን..የማሞን..ክብርና ዋጋ::
እንዳልከው በእግራቸው..በዓለም የነገሱ
ሁሌም የሚኖሩ..በታሪክ ሲወሱ
ሕያው ጀግኖቻችን..መቼም አይረሱ!!!
ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ፈለግ ተከትለው..ዛሬ በእግር ኩዋሱ
በፈጸሙት ገድል..ቢንቆለዻዸሱ
በእግራቸው በሠሩት..
ባስመዘገቡት ድል..አገር ስላኮሩ
በክብር ቢነሱ..በክብር ቢጠሩ
ፈጽሞ አልገባኝም..ምንድ ነው ነውሩ?!?
ሰማህ ወይ ወዳጄ?
ስቼ ያሳሳትኩት..
…አልታይህ አለኝ
ስለእግራቸው ውጤት..
እንኩዋንም ደስ አለህ!..
…እንኩዋንም ደስ አለኝ!
* * *
___ ፋሲል ተካልኝ አደሬ ___ —