Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ምን;፤ ፤ አለ;; ? ሕዝቡ;; ምን፤ ፤አለ ? (በ ሎሚ ተራ)

$
0
0

(በ ሎሚ ተራ)

“”አግሬን ለሰው ;;—– አግሬን ለሰው;;፦—– አልሰጥም አለ።
ከሻአቢያ ጋር ለሚያብረው ጦር,,—–አልከትም አለ። 
ባገሬ—-መሬት,,—የሰላሙ—-ትግል——ይፋፋም  አለ።!!””

          እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሣችሁ፤! ! ! ! መጪው አመት ወያኔን የምንገላገልበት፤።  ከሻአቢያ ጋር ያበሩትና  ለማበር ያኮበኮቡት ሁሉ ልቦና የሚገዙበት ፤። ከሁሉ በላይ በሀገር ወሰጥ ሀይላችውንና ጉልበታችውን፤  እውቀታችውንና ጥሪታቸውን ሳይቀር በማሰባሰብ ፊት ለፊት ከወያኔ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ላይ ላሉት ታጋይ የፖሎቲካ ድርጅቶች፤ በእሰር ላይ ለሚማቅቁት ቆራጥ ታጋዮች፤ እንዲሁም ለሰፊው የ ኢትዮጲያ ሕዝብ አምላካችን ጉልበትና ብርታት ይሁናችሁ። እሱ  ይታደጋችሁ ። ይከተላችሁም።… ለድልም ያብቃችሁ።

በዬ መጣጥፌን መጀመሩ ሳይበጀኝ አይቀርምና ፤እንዲህ በሚል መዘሙር እየዘምርኩ ወደሚክተለው መልክቴ አልፋለሁ።   እንዲህ-፤ “”  በአዲሰ ዘምን ;;;;;;አዲሰ ነግር፤ ;;;; የ ኢትዮጲያ ;;;; ሕዝብ ;;;;;;፤እንዲከበር””። ይኸንን ከላይ የሞከርኩትን አገራዊ ወኔ ቀሰቃሽ ፉከራና ዝማሬ ለመግብያ ያኸል የተጠቀምኩት ዝም ብዬ አይደለም።  ከዚኸ ቀደም ብዬ ለንባብ ባቀረብኩት ጽሁፍ፤ “በየቀኑ ከመሞት አንዴ መሞት አይሻልም??” በሚል ያለፉትን የትግል ይዘት በተመለክተና በ አሁኑ ወቅት ላገራችን የሚያሰፈልጋት ምን አይነት የትግል አቋም እንደሆነ ለማመላከት በቀጥተኛ ቋንቋ በመጠቀም የግል እይታዬን በ አጭር ቃል አሰቀምጫለሁ።”” ዝርዘር ኪሰ ይቀዳል እንዲሉ፤”።

ታዲያ በርካታዎች የምሰጋና፤ በርካታዎችም በግል ኢሜል መልዕከት በመላክ፤ የተለመደውን የሰድብና የነቀፌታ ውርጀብኛ እንደ ዶፍ አውርደውታል። አኔም አንድቀን ይህንኑ የሰድብ ውርጅብኛ ከነመረጃው ለጽሁፍ እሰካበቃው እንዲታገሱኝ ከመማጽን በሰተቀር እንደ ተሳዳቢዎቹ ወርጄ የሰድብ መልሰ ምት፤ እንደማልሰጥ ቃል ከራሴ ጋር በመግባት፤ ሰለሃገሬ ግን ቢያንሰ የሚገባኝንና በተጨባጭ የተረዳሁትን እውነታ በምችለው ሁሉ ከማቅረብ  እንደማልቦዝን በድጋሚ ቃል እገባለሁ።

እኚህ ኮነሬል መንግሰቱ ሃይለማሪያም እንኳ አቢዮቱን ባፋፋሙበት ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ;እንዲህ፤-

“”ሻአቢያ የሚባል ባልኖረ ወያኔ የሚባል ባልተፈጠረ ነበር ያሉት። “”

እውነት ብለዋል። ዛሬ ወያኔን አሽሞንሙኖና በአንቀልባ አዝሎ ኢትዮጲያዊያንን ለሰደትና ለመከራ  ምድሪቷን ለውጭ ዜጎች መፈንጫ የዳረገውን ወያኔን የፈበረከልን ማን እንደሆነ እያወቅንና ታላላቅ የሀገር መከታ የሆኑትን በርካታ የጦር መሪና አዛዦችን ውጦ ከሰቀረው ሻአቢያ ጎን ተሰልፍን ልንታገል ቆርጠናል፤።  ምሁራኖችም ጫካ ገብተዋል። ሌላ በርካታዎችም በተጠንቀቅ ላይናችው። የሚለውን መልዕክት ባደባባይ ማሰተጋባት ግን ምን ያኸል ታማኝነት እና ተቀባይነት እንደሚኖረው ጫካ የገቡት ምሁራኖች አንዴ ገብተዋልና እነሱን ከጫካ የምሁርነት ገለጻ አደርጉልኝ ብዬ አልጠይቅም። ሆኖም ለነሱ እንደሌሎቹ ቀልጠው እንዳይቀሩ ወገኖቼ ናችውና መጸለዬን አላቋርጥም።

እባካችሁ ከሰሜታዊነትና ከድርጅት አፍቃሪነት ወጣ ብለን በጽሞና እና በቅን ኢትዬጲያዊነት መንፈሰ  ጉዳዩን አንመርምረው  ? ?  አሁንም እየከነከነኝ ያለው ነገር ለምን ድርጅቶች ወያኔን ለመጣል ጦር አነሱ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። ነገር ግን ፤እንዴት ሆኖ ነው ? ሻአቢያ ለኢትዮጲያ አንድነት መጠናቀርና ወያኔ እንዲወገድ ትብብር የሚያደረገው? ? እሰቲ  ወደሆላ ተመለሱና፤ ሰንቶቹ የወያኔ መሪዎች የ ኤርትራ ተወላጆች፤ ሰንቶቹ ደግሞ የትግራይ ተወላጅ እንደሆኑ ፋይል አገላብጡ። በተጨማሪም፤—

በ 22 ቱ አምት የመከራ ዘመን ባለ እራዕዩ  መሪ (ድንቄም)  ምን ያኸል ለኤርትራ ተቆርቋሪ እንደነበሩና እንዴትም አይነት ደባ ተሰርቶ ኤርትራ እንደተገነጠለች እንደገና የ ክቡር Colonel Goshu Wolde – Historical Speech –( On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) ይመልከቱ ። የማይዘነጋውን የባድሜ ጦርነትንም በጥንቃቄ መርምሩ፤ የተደረገው ግፍ እኮ እንዲህ በቀላሉና በግርግር መታለፍ ያለበት አይደለም፡።  ይኽንን ሁሉ የፈጠጠ ጉድ እያየን አሜን ብላችሁ ተቀበሉ። ብሎ አቤቱታ ማብዛት ተገቢ ነው ትላላችሁ? እንደ ዜጋሰ እንዲሕ አይነቱን ጉዳይ በጥሞና መመርመርና ማጤን አይገባም ትላላችሁ? መንግሰቱ ሐይለማሪያም ሐይለሰላሴን ከሰልጣን እንዲወረዱ ሲያደርግ የሕዝብ ድጋፍ ነበረው፤። መጨረሻው ባያምርም።

ወያኔ አገር ሲቆጣጠር ግን የሕዘብ ድጋፍ ሳይሆን የሻቢያና የ ዌሰተርን ባንዳዎች ድጋፍ ብቻ ነበር የነበረው፤ አሁንሰ የሕዘብ ድጋፍ አለው እንዴ ? መልሱን መቼ አጣችሁት። የሱ ደጋፊ አሁንም ሆድ አደሮቹና አሰመሳዬቹ ሻአቢያዎች ናቸው። የተከበራችሁ ኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ ሆይ ገና የተደገሰልን ድግሰ እንዲህ በቀላሉ አውረተን የምንዘልቀው እንዳልሆነ     ግን አንድ ነገር እርግጠኛ እንሁን። በጦሩ ውሰጥ የነበሩትን እውነተኛ ላገራችውና ለሕዘባቸው ተቆርቋሪዎቹን ወያኔ በሰመ ባድሜ ጦርነት ብሎ ከሻአቢያ ጋር ተመሳጥሮ በግፍ ከፊት እንዲሰለፉና እንዲማገዱ አደረጋቸው። እረ ሰንቱ።

ወገኖቼ ፤ መርሳት የሌለብን በተለያዩ አገሮች በተደረጉ ትግሎች በአገር እውሰጥ እየሞቱና እየታሰሩ በዙ መከራና ሰቃይም ደርሦባቸው እኔ መሰዋእት ሆኜ ቀሪው ትውልድ ነጻነቱን ያግኝ በሚል ንጽሁ የዜግነት መንፈሰ መሰዋት ሆነው ነው በመጨረሻ ነጻነት ያገኙት። ለምሳሌ የ ሳውዝ አፍሪካን  አፓርታይዱን ሥርአት ለ ናሙና ማንሳት እንችላለን የማነዴላን እና በርካታ አገር ወዳድ ዜጎች መሰዋትንት። ሌላኛው ደግሞ በቅርቡ 50 አመቱን ያከበረው አሜሪካዊው ማርቲን ሉተር ኪነግ ነው።

እኔ በበኩሌ ወያኔ ፈራርሦ ያበቃለት ሥርአት ነው። የሚወድቀውም እሰካሁንም ባገር ውሰጥ በቆራጥነት በመታገል እንደነ ማንዴላና ማርቲን ሉተር ኪንግ በሰላሙ ትግል ፍዳውን ያሰቆጠሩት ቆራጥ ኢትዬጲያዊያን ማንዴላዎችና ማርቲን ሉተር ኪንጎች ናቸው። ይልቁኑ ይኸንኑ ያገር ውሰጥን ትግል በሙሉ ሃይላችን በመደገፍና በማበረታታት የወያኔን ክርሰ መቃብር ማቅረብ እንጂ እንደገና ወያኔ እንዲንሰራራ ከሻአቢያ ጋራ መወገን መፍትሄ ነው ብዬ አላምንምና መላው አንባቢያንን አንዲሁም በሻቢያ ደጋፊነት ወያኔን እንጥላለን ብለው ለሚያምኑ ድርጅቶችም ጭምር የምማጸነው ቆም ብለው እርምጃቸውን እንዲመረምሩ ብቻ ነው።

 

እውንቱ እኮ የኢትዮጲያዊያን አንድነትጠንክሮ ወያኔ ከተወገደ ወዲያ ኢትዮጲያዊነት ለምልሞ ዲሞክራሲ ሰፍኖ እትዮጲያ ያለባሕር በር ትቀመጥ የሚል እትዮጲያዊ ይኖራል ትላላችሁ? ? አይመሰለኝም። ታዲያ በዚህ መንገድ ዳር ድንበራችን ቀይባሕር አይመሰላችሁም ? ? ይህንን ደገሞ ወያኔም ሻአቢያም ጠንቅቆ ያውቀዋል ። ታዲያ በዚህ ሂሳብ እንዴት ሆኖ ነው ወያኔ ደጋፊና ተባባሪ የሚሆነው ተላላችሁ ? ወይሰ የኔ ሂሣብ የተሳሳተ ነው ? ? መልሱን እናንተው መልሱ። እግዚ አብሔርም ማሰተዋልን ይሰጠን እያልኩ ያዲሰ አምት ምኞት መግለጫዬን በዚሁ እደመድማለሁ። በቸር ይግጠመን ቸር ወሬም ያሰማን። !!

 

ኢትዮጲያና ኢትዬጲያዊነት ለዘላለም ይኖራል። ወያኔ ግን በተባበረ የ ኢትዮጲያዊያን ጠንካራ ክንድ ይወገዳል!!

 2005-kinijit-demonstration-picture

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>