ይድረስ ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፡
ጤና ይስጥልን አቶ አንዳርጋቸው እንደምን አሉ ፤ በኢሳት መስኮት እንዳየሁዎ ጤናዎ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል ብየ እገምታለሁ ። እንደባህላችን ከብቶቹስ እንዴት ናቸው እንዳልልዎ ኤርትራ ከብት ለማርባት እንዳልሄዱ አውቃለሁና ምንም እንዲሉኝ አልጠብቅም ። ልጆቹስ እንዳልል መንታዎቹ ልጆችዎ በ single mother ለንደን በእንክብካቤ እያደጉ መሆኑን ስለሰማሁ በጥያቄ አላስቸግርዎትም ። ትግሉ ብል ይሻላል እንዴት ነው እየሰመረ ነው ? በረሃውን እየለመዱት ነው ? በቃ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ህይል በየጦር ሜዳው ወያኔን እያርበደበደው ነው አይደል ? እንግዲህ አራት አመት ሞላዎ እኮ ! ዘመኑ እንዴት ይሮጣል ጃል ። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ