Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የብሄር እኩልነት!

$
0
0

Abrham Destaየብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን’ ማክበር ጥሩ ነው። ምክንያቱም ባህሎቻችን ስናቀርብ እርስበርሳችን በደንብ እንተዋወቃለን፤ ከተዋወቅን እንከባበራለን። ከተከባበርን አንድነታችን ይጠነክራል።

ግን …
ቀን ጠብቆ፣ አብሮ መጨፈር፣ ስለ ብሄር ብሄረሰቦች መዘመር በራሱ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ማረጋገጫና ዋስትና ሊሆን አይችልም። የሁሉም ህዝቦች እኩልነት ለማረጋገጥ አብሮ ከመጨፈር ያለፈ ተግብራዊ ዉሳኔ ይሻል።

‘ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩል ናቸው’ ብለን ከተነሳን ሁሉም ብሄራቸው ግምት ዉስጥ ሳናስገባ (ምክንያቱም ሁሉም እኩል ናቸው ብለናል) በኢትዮጵያውነታቸው እንመዝናቸው። ለማንኛውም ጉዳይ (ለስራ፣ ለስልጣን …) በትምህርት ደረጃቸው ወይ ብቃታቸው ወይ ሌላ ለሁሉም በእኩል ሊያገለግል በሚችል መስፈርት እንመዝናቸው።

ሁላችን እኩል ከሆንን አንድ ሰው ለመመዘን ጉራጌነቱ፣ ኦሮሞነቱ፣ ትግራዋይነቱ፣ አማራነቱ፣ ዓፋርነቱ፣ ሶማሌነቱ፣ ጋምቤላነቱ … ማስታወስ አያስፈልገንም። ማንነቱ የራሱ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ መመዘን መቻል በቂ ነው።

ሰው ለመመዘን ብሄሩ ግምት ዉስጥ ካስገባን ግን ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩል መሆናቸው አናምንም ማለት ነው። ሺ ግዜ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብናከብርም ሰው እንደሰው መመዘን ካልቻልን በቃ የብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩልነት አላረጋገጥንም ማለት ነው።

ይሄ የመለየየት ችግር በብሄር፣ ብሄረሰቦች ብቻ አይደለም የሚስተዋለው፤ በአንድ ብሄር ዉስጥም አለ። ለምሳሌ በትግራይ ክልል አንድ ሰው ለስራ ወይ ለሌላ ሐላፊነት ሲፈለግ የመጣበት አከባቢ ግምት ዉስጥ ይገባል። ስራ ከመሰጠቱ በፊት ከዓድዋ፣ ተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ራያ ወዘተ እየተባለ በትምህርት ደረጃውና ብቃቱ መሰረት ሳይሆን በትውልድ አከባቢው ነው የሚመደበው (የሚመዘነው)።

ሰው በመጣበት አከባቢ መሰረት ከተመዘነ እኩልነት የለም ማለት ነው። ስለዚህ እኩልነት የሚረጋገጠው በጭፈራ ሳይሆን በተግባር ነው። የሰው መብት በሕገመንግስት ስለተፃፈ ብቻ መብቱ ተከበረ፣ ተፈፀመ ማለት አይደለም። በተግባር መታየት አለበት።

አዎ! ሰው በብሄሩ ሳይሆን በተግባሩ መመዘን አለበት።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>