Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ጀዋር እና ኢስላማዊት ኦሮሚያ (ለያሬድ አይቼህ መልስ)

$
0
0

jawar
ከብሩክ ደሳለኝ
በህይወቴ ከመጠላው ነገር ቢኖር ከንቅልፌ ሚቀሰቅሰኝና በባዶ ሜዳ ሚንጅሰኝ ሰው ነው። አንድ አማራ ሲያልፈ የሰማውን ስም ወስዶ በብእር ስም የሚያደርቀን ያሬድ አይቼህ ሚባሉ ግለሰብ እንደ ትሪፓ ማይታኝክ ሃሳባቸውን እየነሰነሱብን ይገኛሉ። በየጠላቤቱ የተወራ ሁሉ ፖለቲካ ሚመስለው በዛብን። በተለይ እኛ ወጣቶች አበሳችንን ሚያበዛብን ብሽ ሆነብን። አማሪኛው ልክ ኦነጎች እንድሚጽፉት እንግሊዝኛ የሰዋሰው ውርጅብኝ ይበዛበታል። ማለትም ሁለት ነጥብ እና አራት ነጥብ በተነፈሰ ቁጥር ያስገባል። እነዛ ኢንግሊዝኛ ሲጽፉ ኮማና ኤክስክላሜሽን ያበዛሉ። ወደ መጣሁበት ሃሳቤ ስመጣ ፥ አዲስ የፖለቲካ አመለካከት ያምጡልን መስልዋቸው አቶ ያሬድ ድህረግጽን ጠጅ ቤት አድርገውብናል። 
አቶ ጀዋር አልጀዚራላይ የፖለቲካ መከረባበት ላደረጉት አስተያየት በሰጡበት “ጀዋር መሃመድ እና የአማራ ልሂቃን” በሚል ርእስ በጻፉት መጣጥፍ ላይ ፈላስፋው እንደነገሩን ከሆነ አማራ ምትባል ብሄር ብታርፍ ይሻላታል ብለውናል። ያ ሲገርመን ያማራ ቅቦች ለካስ ንቀው ሲተው የተፈሩ መስልዋችው አብዋራ ያስነሳሉ። ለንደዚ አይነቱ መልስ መስጠት መውረድ ነው ብዬ ባስብም ሊያርፍ ስላልቻለ ትንሽ የሃሳብ ኩርኩም የሚያስፈልገው ይመስላል። አስርደቂቃ እሱላይ ማትፋቴ ቢያበሳጨኝም የሚላቸው ነገሮች መርዝ ስለሆኑ ትንሽ ወደሱ ደረጃ መውረድ ያስፈልጋል። ምንን ምን ካላሉት ምን ላይ ይቀርባል ይላለ የሸገር ልጅ። እናም ከጽሁፋቸው ቆንጠብ አድርገን “….ዐማራዎች ሆይ! የድሮዋ እትዮዽያ ተመልሳ አትመጣም። አማርኛ ቇንቇ ሁሉም የሚናገርባት ….ወዘተ ይሉናል። እያንዳንዱን ብንነጋገርበት አመት ይፈጃል።
ግን ኢትዮዽያውስጥ ሌላ ብሄር አማሪኛ ባወራ ቁጥር በፊደል ለጎጃም ገበሬ ሚከፈለው መስሎት ይሆን? አላዋቂ ሳሚ አለ። ብቻ ሰብዬው በሞቅታ የጻፉትን አንቡትና ተገረሙ። ካመለካከቱና ጽሁፉላይ እንደሚያራምደው ስነልቦና ነኝ የሚለውን ብሄረሰብ ሳይሆን ምን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ያሳያል።  ደሞ ያ ሳያንሰን አንድ ጭስ ጭስ የሚል “ጃዋር እና ኢስላማዊት ኦሮሚያ” በሚል ርእስ ሌላ ጽሁፍ ድህረገጽ ላይ ደፉብን። አቶ ጀዋር በቃዡ ቁጥር የህልማቸው አስተርጉዋሚ ሆነው አቶ ያሬድ ከች ይላሉ። የባለፈው ጽሁፉ ላይ ከታች ብዙ አስተያየትና ምክር ቢለገስም ሰውየው ሊማሩ አልቻሉም። አዙረሽ ለበሽ ሲልዋት ገልብጣ ለበሰችው ይላል ያገሬ ሰው። እናም ባጭሩ እዚች ላይ ላብቃ። ትንሽ ከቆየሁ የኔንም ስም ይወስድና ስሙን ይቀይራል። ደሞም እንደ አቶ ያሬድ የማይታኝክ ስጋ ሳልሆንባቹ በዚቹ ላጥ ብል ይሻላል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>