Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የህወሃት አፓርታይድ አገዛዝና የተቃዋሚ ኃይሎች !! (በጌታቸው)

$
0
0

በጌታቸው   

«ጅብ እንደ አገሩ ይጮሃል» እንዲሉ ዘፋኝ ስለሀገር ስለራሱ ውስጣዊ ስሜት ስለ ፍቅረኛው ስለቤተሰቡ ስለጓደኞቹና ስለሚታየው ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ይዘፍናል።ፖለቲከኛውም ስለ ወቅቱ ስለአለፈው የፖለቲካ ጉዳይ ስለሥልጣን ማጣትና ስልጣን መያዝ፤ ስለጨካኝ አገዛዝ ስለፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ይተርካል። ሁሉም እንደ ሙያውና አሰላለፉ ያለፈውንና የሚመጣውን ይተነብያል። እኔም ካለፈው የተመለከትኩትንና አሁን እጅ ላይ ያለውን ሁኔታ ስመለከት ወደ ፊት ምን ይመጣ ይሆን በማለት የራሴንና የሀገሬን የኢትዮጵያ ተስፋ  በሚመለከት ሀሳቤን ብሰነዝርስ ብየ አሰብኩ።

በአጭሩ ለማስቀመጥ በዘውዳዊ አገዛዝ የመጨረሻ ዘመን አካባቢ  በነበረው ቀርፋፋ የፖለቲካ አያያዝ ምክንያት ተሸፍነው ሊታለፉ የማይችሉ በርከት ያሉ የሀገር ችግሮች በአደባባይ ላይ መውጣታቸው የግድ ሆነና ንጉሠ ነገሥቱንና ካቢኔያቸውን ከሥልጣን ገበታ ጠራርጎ የሚጥለው ሕዝባዊ ንቅናቄ በ1966ዓ/ም ወርሃ የካቲት ከዳር እስከዳር አስተጋባ። አንዳንድ ድርጅቶች ከዚያ በፊት ተደራጅተን ነበር ይበሉ እንጅ የሕዝቡን ትግል አደራጅቶ የሚመራውና ወደሚፈለገው ግብ እንዲጓዝ ለማድረግ ባለመቻሉ አንዳቸውም የሕዝብ ጥያቄዎች ሳይመለሱ ያልታሰበ ኃይል ወደ ሥልጣን ገበታው ብቅ አለ።ገብቶንም ይሁን ሳይገባን የመጣውን አዲስ ገዥ መደብ ተቃወምን ደገፍን ሥልጣን ያማራቸው ደርግ ብቻውን ጠቅልሎ ይዞ አላካፍልም አለ በለስ ሳይቀናቸው ሲቀር ወደ አመፃዊ ትግል ገቡ አልተሳካም። ቀስ ብለው በጓዳ የገቡትም ወደ ደርጉ አዳራሽ ብቅ ቢሉና ሰነድ መሸጥ ቢጀምሩም ያችን ሥልጣን ደርግ ሊያቀምስ አልቻለም።ደርግ ግራ ተጋብቶ ነበር ቢባል ስህተት እንደማይሆን የሚያሳዩ ሁኔታዎች ነበሩ፦ ደርግን ወደ ሥልጣን ያመጣው የዝቅተኛው የወታደራዊ መኮንኖች ውስጣዊ ትግል ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ የተቀጣጠለው የሕዝብ አሻፈረኝ ባይነት ሆኖ ሳለ እነዚህን ጥያቄዎች ወደጎን በማድረግ ሥልጣኑን የማመቻቸት ትኩሳቱ ላይ ተጠመደ። ሌላው በሁሉም በር መግባት የሚቻልበት ቤት ሲገኝ የተነሳውን የተለያየ ምክንያት ያዘለና ተልዕኮ ያለውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ወይም ራሱን ደርግን ተቃውመው የተደራጁትን ድርጅቶች ጥያቄ በፖለቲካዊ አግባብ ሊፈታ ባለመቻሉ የተቃዋሚው ኃይል እየበረከተ ሄደ። የተቃዋሚ ኃይሎች በሦስት መስመር የተሰለፉ ሆነው አንዳንዴ እርስ በርሳቸው እየተባሉ ደርግ የተወሰነ እፎይታ ያግኝ እንጅ ከአካባቢ አገሮች ወረራ ጋር ተዳምሮ 17ቱ የደርግ የሥልጣን ዘመን ሕዝብን የሀገርን ኢኮኖሚ ያወደመና መጨረሻው የከፋ አወዳደቅ የወደቀ ደርግ ነበር። ሻእቢያ ለመገንጠል እንደ ነዳጅ የሚያገለግለውን ህወሃትን በማጠናከር አሳደገ ፤ ህወሃት ደግሞ በሻእቢያ ሰርጎ ገቦች እየታጀበ ከጌታው ሻእቢያ የሚወርድለትን ትእዛዝ ለማቀላጠፍና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታማኞችን በመመልመል ማደራጀቱን ቀጠለ።እንደሚታወቀው ኢህአፓ በኤርትራ ጉዳይ ግልጽ አቋም ሳይኖረው የዘለቀው በኢሳይያስ አፈወርቂ ማስፈራራት ብቻ አልነበረም።በራሱ በኢህአፓ ውስጥ የፖሊትና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የአመራሩን ሚና ይጫወቱ የነበሩት ኤርትራውያንና ትግራውያን እንደነበሩ ግልጽ ነው።አሁንም ኢህአፓ ነባር አባሎቹን አሰባስቦ የተወሰነ ድንጋይ እንኳን እንዳይወረውር ገትተው የያዙት እነዚሁ የኤርትራና ትግራይ ትውልድ ያላቸው የሻእቢያን ይሁን የህወሃትን ዓላማ ለማሳካት በስመ ታጋይ ኢህአፓ ውስጥ በመግባት ኢህአፓን የበተኑ የኢትዮጵያ አንድነት ሊንኮላሽና የመገንጠሉ ፍላጎት ግቡን ሊመታ የሚችለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖትና አማራው ሲመቱ ነው በሚል ዓላማ ላይ አነጣጥረው የተነሱ እንደነበሩ መረጃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። ክፍሉ ታደሰ «ያትውልድ በሚል የጻፈውን ማንበብ ከቻላችሁ መረጃ አንድ ይኖራችኋል። መረጃ ሁለት የሪጅን ሦስት(የበለሳው ግንባር)ኢህአፓን ከድቶ ትግራይ ገብቶ በህወሃት ስር ሊወድቅና አሁን የደረሰውን «የቢሔራዊ ውርደት» እንዲሁም ጠቅላላ ሀገራዊ ቀውስ የፈጠረው የኢህዴንን ደባ መመልከት በቂ ነው። ኢህዴን ኢህአፓን እንዲበተን አስተዋጽኦ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን 1/የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ኦህዴድን)፤ 2/ድሮ የስምጥ ሸለቆ አሁን የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ደሕዴድ)ና 3/የወታደራዊ መኮንኖች ድርጅት ተብሎ የተደራጀና ቶሎ ብለው ያፈረሱትን የጌታውን የህወሃት ዱላ ፈርቶ እነዚህን ድርጅቶች ለማቋቋም በቤት ሥራ ተጠምዶ ከዚህ ያደረሰ ስንኩልና ቅጥረኛ ድርጅት ሲሆን አሁን ደግሞ (ብአዴን)ብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በማለት ሰፊውን የአማራ ሕዝብ አፍነው የሚገዙ ትውልደ ኤርትራና ትግራይ የሆኑ የአማራውን ሕዝብ ለስደት፤ድህነትና እልቂት ዳርገውት ይገኛሉ።ሰፊው የአማራ ሕዝብ የሌላውን ዛር እየተላበሰ ግንባር ቀደም ለሀገሩ ድንበር መከበር መስዕዋትነት ከመክፈሉ ያለፈ የየትኛውም ሥርዓት ተጠቃሚ እንዳልነበረ በጠላትነት ፈርጀው መጠነ ሰፊ ጥቃት የሰነዘሩበት ድርጅቶች ጠንቅቀው ያውቁታል።ነገር ግን ፀረ ህዝብ ዓላማቸውን ለማሳካት እንዳይችሉ ቀድሞ የሚነሳውና በግንባር ቀደምትነት የሚፋለማቸው ስለሆነ እንፍጀውን አውጀውበታል እየፈጁትም ነው።ለምሳሌ ከአማራው ነገድ ሕዝብ የበቀለው አንዱዓለም አራጌ አንዲት ቅንጣት ታክል ስህተት ፈጽሞ አይደለም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተፈረደበት አንዱዓለም እውነት ነው የተናገረውም እውነትን ነው። እውነትን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ባለመዋሸቱ ታስሯል።ግድ የለም ይታሰር ነገ ይፈታል።ዳሩ ግን በዓለም ከፍ ያለ ዝና ያተረፈችውን ኢትዮጵያ ሀገራችን ለማዋረድ ፤ለመበተን ፤ሀብቷን ለመዝረፍ ትውልዷን ማምከን እንዴት ተወሰነ? በሳውዝ አፍሪካ የተካሄደውን የነጮች በጥቁር ላይ ለዚያውም በራሳቸው ሀገር የአፓርታይድ አገዛዝ «በዓለም ደረጃ ታላቅ ዝና ያተረፉት የነጻነት አርበኛ ኔክሰን ማንዴላን ዜና ረፍት» ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች በምስል እያስደገፉ ያቀረቡትን የክቡሩን ሰው የሕይወት ታሪክ ስመለከት በሀገራችን ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑ መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል የሌላቸው ሀሳበ ኩድኩድና ድኻዎች(ጥቁር ጣሊያኖች )በራሳቸው ሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን ልክ የለሽ ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ከሳውዝ አፍሪካው ጋር እንዳነጻጽረው ገፋፋኝና ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ተመልሸ አሁን የመንግሥታዊ መዋቅሩን የያዘውና በጫካ ሕግ እየገዛ ያለውን ድርጅት ሁለት ካዝና ያለው ተቋም በሚመለከት ጊዜየን ሳላባክን በመደምደም ወደ የተቃዋሚ ኃይሎች በመጠኑ የሚሰማኝን ለማካፈል የሚከተለውን ማስነበብ እወዳለሁ።

ህወሃትን ፦ 1/መንግሥት ማለት አልችልም 2/ ወያኔም አልልም(ኢህአዴግም)ማለት አልችልም መሆን የሚችልበት ወይም በዚህ ስም ለመጥራት አንዱንም ነጥብ ወይም መስፈርት አሟልቶ ስለማይገኝ። ወያኔ የሚለው ከግእዙ ትርጓሜ ሲወሰድ አበየ-አመጸ- እምብኝ አለ ስለሚል ማንም የሚጠቀምበት እንጅ በቅጥረኝነት ለተሰለፈ ቡድን መጠሪያ አይሆንም። ምናልባት የአቶ ተክሌ የሻው የትግራይ ወያኔዎች የሚለው ይመቸኛል።መንግሥት ለማለት የሚከብድበት ምክንያት ይህ ቡድን ተግባሩ የማፊያ እንጅ መንግሥታዊ ባህሪ የለውም በዚህ ቡድን ውስጥ የተሰባሰቡትን ስንመለከትም እዚህ ግቡ የባይባሉ ስነምግባር የሌላቸውና በደም የሰከሩ ሰሞነኞች ስለሆኑ በተለመደው ህወሃት እያልኩ እጠራቸዋለሁ።ኢህአዴግ ለማለት ደግሞ አይቻልም ግንባሩ ወይም ስብስቡ ህወሃት ቁጭ ብድግ ሲያስብለው ቁጭ ብድግ የሚልን ስብስብ ግንባር ብሎ ቢጠራውም በዚህ ስሙ መጥራት አግባብ ሊኖረው አይችልም።

ህወሃት ዘራፊ ድርጅት ነው። በተለያዩ ስሞች እየተጠራ ከዚህ የደረሰው ህወሃት ኢትዮጵያንና አማራን ማጥፋት ብሎ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ የግል፤ የድርጅትና የመንግሥት ተቋሞችን በመዝረፍ የተሰማራ ለመሆኑ አሁንም በዚሁ መንገድ መቀጠሉን ራሱ ተቋሙ ሳያፍር የሚገልፀው ጉዳይ ስለሆነ በዚህ እንተማመንና የሀገር የሆኑ ታላላቅ ተቋሞችን ለትውልድ እንዳይተላለፉ ማውደም ድልድዮችን ግንቦችን ታሪካዊ ቅርሶችን ማፈራረስ ለምሳሌ የዋልድባ ገዳም የመሰሉትን በዶዘር ገብቶ ማረስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማይጠበቅ ምግባረ ብልሹ የሆነ ተግባር ነው። የመንግሥት መዋቅርን የተቆጣጠረ ድርጅት አሁንም በዚያ መጥፎና የትግራይን ሕዝብ አልፎ ለሌላውም እልቂት ምክንያት የሆነውን የደደቢቱን ስሙ አለመቀየሩ፤ የገብረሕዮት አክሲዮን ወጋገን ባንክ፤ ጉና የንግድ ድርጅት፤ኤፈርት፤የምናምንቴ ትራንስፖርት …ወዘተ ብሎ የሚጠራቸው ተቋማቅት  የመዝረፊያ ተቋሞች ናቸው።በነዚህ ተቋሞች አማካኝነት የሚዘረፈው የሀገር ሀብት ለሀገር እድገት የሚውል አይደለም።አንድ ምሳሌ እንውሰድና እንመልከት የህወሃቱ ጉና የንግድ ድርጅት ማሽላ ፤ሰሊጥና ጥጥ ይገዛል እንበል የሀገር ባለሀብቶችም እንዲሁ ማሽላ ፤ ሰሊጥና ጥጥ ይገዛሉ።ነገር ግን ይህ የግዥ ወቅት ከመድረሱ በፊት ከላይ እስከ ታች ባለው የህወሃት መዋቅር መመሪያ ተላልፎ ካድሬው የግል ባለሀብቶችን በትዕዛዝ በማገድ ጉና የንግድ ድርጅት ያለ ተወዳዳሪ በሚፈልገው ዋጋ ምርቱን የሚገዛበት ሁኔታ ይመቻቻል።በሥራው የሚሳተፉትም የድርጅቱ አባላት ብቻ ናቸው።ይህ አይነቱ የንግድ ድርጅት በተመሳሳይ በአማራ ክልል አምባሰል ሲኖር በደቡብና በኦሮሞ ክልልም ለጊዜው ስማቸውን ባልይዘውም በዚህ መንገድ በንግድ ሥራ የተደራጁ ተቋሞች አሉ።የሕዝብና የጭነት ማመላለሻ አገልግሎ፤ባንኮች፤በመካናይዝድ የሚያርሱ የእርሻ ድርጅቶች፤በሕዝብ ስም ለድርጅቱ ከውጭና ከሀገር ውስጥ እርዳታ የሚሰበስቡ እንደ ጥረትና ኤፈርት እንደ አልማ የመሰሉ የልማት ማህበር የሚባሉ ሕዝብን ያደኸዩ የመዝረፊያ ተቋሞች ሀገሪቱን ከጫፍ እስከ ጫፍ ጥፍረው ይዘው የሀገር ሀብት ይዘርፋሉ።የሚገርመው ነገር እነዚህ ተቋሞች ከፍተኛ ካፒታል ያላቸው ሲሆን ለሀገር እድገትና ግንባታ የሚውል «የገቢ ግብርና ታክስ የማይከፍሉ »መሆኑና ተዘርፎም ይሁን ተነግዶ የተገኘው ገንዘብ ጥቂቶች ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት መሆኑ ነው።»

ህወሃት፦መሞት የሚፈልግ ነገር ግን የሚገድለው ያጣ ድርጅት ነው።ይህ ድርጅት ሥልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ በኃይል የሚተማመንና ጦር በማደራጀት ሕዝቡን አስገድዶ ለመግዛት ወይም በብጥብጥ ሀገር እያመሰ ለመኖር ያሰበ መሪዎቹ በደም የሰከሩና በውስጣቸው ሰላምን ያጡ ሲባንኑ የሚኖሩ ለመሆናቸው እያንዳንዷን የወንጀል ድርጊት አፈጻጸም ወስደን ብንመለከት ያን ተግባር ለመፈጸም የሚያስገድደው ምክንያት ከሕዝብ የተነጠለ ተስፋ ያጣ በውስጡ መተማመን የሌለውና ለመስንበት ሲባል ተመሳሳይ በወንጀል ተግባር የተጨማለቁ ኃላፊዎች ያሉበት ሲሆን ለጥቅሙ ሲል የታጠቀውን የመከላከያ ኃይል ተማምነው የሚኖሩ ናቸው።ለዚህም ነው በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ በየጊዜው የመቀያየር በጡረታና በመሳሰሉት ምክንያቶች ማግለል ኦሮሞውንና አማራውንም በጥርጣሬ ማየት ማሰርና ማባረር የሚስተዋለው

ሀወሃት፦አንድነትን አጥብቆ የሚጠላ በዘረኝነት የተበከለ ድርጅት ነው።አንድ ለአምስት አደረጃጀትን መነሻ አድርገን ብንወስድና 99.6 ድምጽ አግኝቼ ተመርጫለሁ የሚለው ኃይል ውሸቱን እንዴት እንደሚፈበርከው በግልጽ ያሳያል።99.6 ድምጽ ያገኘ ድርጅት በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያገኘ ማለት ነው።አንድ ለአምስት ማለት ደግሞ ከሕዝብ የተነጠለና ሕዝቡን የማያምን የሕዝቡን የየእለት ከእለት እንቅስቃሴን ለመከታተል አንድ ሰው አራቱን በመከታተል ሪፖርት የሚያደርግበት መንገድ ነው ሁለት በጣም የማይቀራረቡና የሚጋጩ ሁኔታዎች። ስለዚህ ድርጅቱ የሕዝብ ድምጽ ሌባ መሆኑን ራሱ የተቀበለ ለመሆኑ ይሰመርበታል።በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ህወሃት በርከት ያለ ገንዘብ በመመደብ እንደ ሽመልስ ከማል የመሰሉ አፈጮሌዎችንና ጮማ ምላስሞችን በማሰማራት የእቁብ ፤ የእድር ፤የሰንበቴ፤የሚካኤል የጊዮርጊስ ወዘተ… እና የመረዳጃ ፤የልማት ማህበራትን ፤ድርጅቶችን፤በቤተክርስቲያትን  በተቃዋሚ ኃይሎች ውስጥ፤በእስልምና ሃይማኖትና በማንኛውም የሕዝብ ስብስብ ውስጥ በመግባት የተጋቡ የአማራ ወንድና የትግሬ ሴትን እስከ ማፋታት የሚሄድ የስለላ መዋቅር ያለው ፀረ-ሕዝብ ድርጅት ሲሆን ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ የሚቀላብደው በችግር ውስጥ የሚገኝ ጸረ-ሰላም በመሆኑ ነው።

ህወሃት፦ህወሃት መንፈሳዊ ሞራል  ብሔራዊ ወኔ የሌለው ቅጥረኛ ድርጅት ነው።በኢትዮጵያ የተለያየ እምነት የሚከትሉ እስልምና እና ክርስትና እምነታቸው የሆኑ ለረጅም ጊዜ በመከባበርና በመተባበር ሲኖሩ ይህ ድርጅት ደርግን ከተካበት ቀን ጀምሮ ሌት ከቀን አንዱን በአንዱ ላይ ለማናከስ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም።ሊሳካለት ግን አልቻለም።የቻለው ወይም የተሳካለት ቢኖር የእስልምና ሃይማኖት መሪዎቹን ማሰር ካድሬ እስላሞችን በመሪነት መሾምና የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ደግሞ ህወሃታዊ ሲኖዶስ እንዲሆን ማድረግ ነው።ዛሬ በውጭ ቀላልና ዋና የገቢ ምንጭ ሆኖ የሚገኘው ህወሃት በቀጥታ ወደ ውጭ የሚልካቸውን የሰንበት ተማሪዎችን ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የለቀቁና ካድሬዎቹን ካባ እያለበሰ ቄስ ናቸው በማለት የአማራ ፤የኦሮሞ፤የትግሬ የሌላም የሌላም ቤተክርስቲያን በየመንደሩ በመክፈት ሕዝቡን ማራራቅና ቅሬኔ ውስጥ ማስገባትን ዋና ተግባሩ አድርጎ ይዞታል፤በወርሃዊ መዋጮና በሙዳይ ገንዘብ ሀብታም የቤተክርስቲያን መሪ መፍጠርና የማይሰሩ የሰበካ ጉባኤዎችን በማስመረጥ የህወሃትን መዋቅር ማጠናከር አንዱ ስልት ሆኗል።የሚገርመው ግን ጽላቱ የት እንደሚገኝ ነው።አንዳንዱ ከግሪክ ነው ይላል ሌላው ከኢትዮጵያ ነው ይላል።ሞቀም ፈላም ተጠያቂው ግን አስፈጻሚው ህወሃት ይሆናል ማለት ነው።በሌላው መልኩ ህወሃትን ስንመለከት ትግራይን ገንጥሎ ከኤርትራ ከአፋር ከአማራ ሰሜን ወሎና ሰሜን ጎንደርን ቆርሶ በመውሰድ ታላቋን የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረት እንደነበርና አሁንም ሕዝባዊ ኃይሉ እየገፋ ከሄደ የኢሳይያስን ቡድን ገፍቶ የሚጥል ሴራ በመሸረብ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚኖሩ ኤርትራውያን በበላይነት የሚመሩት መንግሥት ለመመሥረት የማይቦዝን ሲሆን የአሰብን ወደብ አልቀበልም ያለበት ምክንያትም በኤርትራ እጅ እንዲቆይ ማድረግ ከዚህ አንፃር ሊታይ የሚችል መሆኑ፤ ኤርትራን ያስገነጠለበት አጀንዳም ባካፕ ወይም የኋላ ደጀን በማድረግ ኢትዮጵያን እስከሚያፈራርሱ ጊዜ ለመግዛት ሊጠቀሙ የሄዱበት መንገድ መሆኑን እኛ ኢትዮጵያ ሀገራችን የምንል ጉዳዩን ከተለያየ አንግል ለጥጠን ልናይ ይገባናል፤ የኢትዮጵያን ለም መሬት ኢትዮጵያውያንን በማፈናቀል ለውጭ ከበርቴዎች በነፃ የቸረ፤ ሰፊና ለም መሬት ከኢትዮጵያ ሳልፎ ለሱዳን የሰጠ የኢትዮጵያን ዳርድንበርና ሉዓላዊነት ያስደፈረ ከሃዲ ድርጅት ነው።በነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች ህወሃት አንድም ቀን ቢሆን ማደር የማይገባው በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ኑና ግጠሙኝ በማለት ጉድጓዱን ቆፍሮ ቀባሪ እየጠበቀ አጥፍቶ ሊጠፋ የተዘጋጀና እንደ እንሰሳ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለ ጀግና በሀገር ጠፍቶ 22ኛውን ዓመት አሳልፎ 23ኛውን አመት እየተሻገረ ያለ ሀገርን ያጠፋ የዐረብና የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።

በመጨረሻም ህወሃት መሬት ለሱዳን መስጠት ለምን ተገደደ የሚለውን ስንመለከት 1ኛ/ ሱዳን ለህወሃት ሆነ ለሻእብያ ትልቅ ባለውለታ ነች ወይም አሁንም ሆነ በደርግ ወቅት ከደደቢት የበለጠ ምሽግ ሆና ማገልገሏ ግልጽ ነው።2ኛ/ ህወሃትን የሚቃወሙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን በሱዳን አማካኝነት ከሱዳን ምድር ጽ/ቤታቸው እንዲዘጋ ንብረታቸው እንዲበረበር፤ከሱዳን እንዲወጡ በማድረግ የሱዳን መንግሥት ከፍተኛውን ድርሻ ተወጥቷል።ለዚህም ነው የመሬት ጉርሻ ለሱዳን እንዲሰጡ የተገደዱበት ይኸም ቀደም ሲል ቃል የተገባበት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው። የሚገርመው ግን ከኔ ከራሴ ጀምሮ የሱዳንና የኢትዮጵያን ድንበር አበጥሮ የማያውቅ ይኖራል ብየ አላስብም ራሱ ህወሃት ያውቀዋል።የህወሃት ዓላማ ግን ሱዳን ከኢትዮጵያ የወሰደችውን መሬት ልትጠቀምበት ትችላለች ብለው አምነውበት ሳይሆን በሁለቱ አገር ሕዝቦች መካከል የሚኖረውን የወንድማማችነትና የወዳጅነት ግንኙነት ለማደፍረስ የታሰበ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እንዲሻክርና እንዳይኖር በብጥብጥ ለማኖር የተጠመደ ፈንጅ ነው።

ወደ የተቃዋሚ ኃይሎች ስመጣ የተቃዋሚ ኃይሎችን በሁለት ከፍየ አያቸዋለሁ፦

1ኛ/ ሥርዓቱን በሰላማዊ መንገድ በመታገል በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈን የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት፤ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች በእኩልነት ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሥርዓት ለመገንባት የተነሱ ናቸው። መነሻቸው ወይም ዓላማቸው በጣም የሚደገፍና ቅን አስተሳሰብ ነው። ችግሮች ድርጅቶች ህወሃትን በሚገባ አውቀው እንደ ባህሪው ክፋት ተንኮሎችን በጣጥሶ መሄድ የሚያስችለውን መንገድ አልተጠቀሙበትም። ይኸውም መጀመሪያ አንድ ጠንካራ ሕብረ ብሔራዊ ድርጅት መገንባት አለመቻላቸው ሲሆን ሁለተኛ የተንበሸበሸ ብዛት ሳይሆን ጥራት ያላቸው ጥቂት ድርጅቶች ቢኖሩ መልካም ነበር።ይህም አልሆነም ባሉበት ደረጃም ሆነው ገና ከመጀመሪያው መደራጀትን ሲመርጡ ህወሃት ሰርጎ እንዳይገባ የተጠነቀቁ አይደሉም።ይህ በሀገር ቤት ይሁን በውጭ አገር ያሉትን የሚያጠቃልል ነው።ይህን ለማለት ያስገደደኝ የህወሃትን ጠብ አጫሪነትና ሰርጎ ገብነት በተለያዩ ደረጃዎች በመመልከቴ በድርጅቶች ውስጥ የሚፈጠሩትን የመከፋፈልና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊውን መፍትሄ መስጠት ባለመቻላቸው የህውሃት እጅ ገብቶበታል እንድል ያስገድደኛል። በሕቡ አደረጃጀት ምን ያህል ርቀው እንደሄዱ ባላውቅም አንድ ለአምስት የተደራጀ የስለላ መዋቅር ዘርግቶ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የልብ ትርታ አዳምጣለሁ ብሎ የሀገር ሀብት ዘርፎ የተደራጀን ቡድን መሰናክል ለመበጠስ ሕቡ አደረጃጀት አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሁሉም ድርጅቶች ፕሮግራማቸውን ለህዝብ ለማስተዋወቅ ፤ አባልና ደጋፊ ለማፍራት ያጋጠማቸውን የካድሬ ፤ የደህንነት፤ የመከላከያና የፖሊስ ወከባ ሁላችንም ሳንገነዘበው አልቀረንም ለዚህ ችግር ሕቡ አደረጃጀት አስፈላጊ ነው ብየ አስባለሁ። በተረፈ አንድነት ሊፈጥሩ አለመቻላቸውና በተናጠል ትግሉን ለመቀጠል የሚሄዱበትን መንገድ እርስ በራሳቸው የሚያደርጉትን መጠላለፍ ሳልደግፍ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግድያ፤ እስራትና አፈና ፤ ድብደባ ፤የንብረት ዘረፋ፤ማፈናቀል…ወዘተ ለህዝብ ጀሮ እንዲደርስ በማድረግ የሚሄዱበት መንገድ ጎሽ የሚያስብል ሆኖ አግኝቼዋለሁ ቀጥሉበት ።

2ኛ/ ህወሃትን በቋንቋው እናናግረዋለን እንጅ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን ሊያስረክብ አይችልም ብለው በትጥቅ ህወሃትን ለማንበርከክ የተሰለፉ የተቃዋሚ ኃይሎችን ሞራል በእጅጉ እያደነቅሁ ነገር ግን እነዚህ ኃይሎችም ቢሆን ከፍ ብየ እንደገለጽኩት ከህወሃት ሰርጎ ገብነት ነፃ ለመሆናቸው፤ እርስ በርስ ከመጠላለፍ የወጡ ለመሆናቸውና በጋራ አንድ ግንባር ፈጥረው ለመታገል ያላቸውን እምነትና ቁርጠኝነት ለማመን እርግጠኛ አይደለሁም። አንዳንዶቹ ከተመሠረቱ ህወሃት በጥቂት ዓመታት የሚበልጣቸው ሲሆን ቀደም ብለው የትጥቅ ትግሉን የጀመሩ ሲሆን በነዚህ ኃይሎች ነፃ የወጣ ምድር አለ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። ምናልባት ለድርጅታዊ ጠቀሜታና ደህንነት ተብሎ ከሆነ መልካም ነው። አንዳንዶቹ ማፈግፈጊያ ያደረጉት የኤርትራን ምድር ሲሆን በበኩሌ ይህ የግሌ አስተያየት ነው የኢሳይያስን መንግሥት በማመንና ከሱ ድጋፍ በማግኘት ህወሃትን ታግየ እጥላለሁ ብሎ ማሰብ« ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል »ብሎ እንደማሰብ ነው ብየ አስባለሁ። ለምን ቢባል ወደ ኋላ እንመለስና ኢሳይያስ አፈርቂ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አመለካከት ከዚያ በፊት በታጋይ ድርጅቶች ላይ ከህወሃት ጎን በመሆን ያደረገው ጭፍጨፋና የነበረው አቋም ሲታይ ጊዜን ማባከን ወይም በህወሃት መንገድ እየሄዱ ነው የሚመስለው። ሻእብያ ህወሃትን ቃል አስገብቶ እንደፈረስ ይጋልበው እንደነበር መዘንጋት የለብንም። ለምሳሌ ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆነ ሙሴን ባላምነውም ሰበር ዜና በማለት ያቀረበውን ስንመለከት የኤርትራና ህወሃት ጀኔራሎችና ባለሥልጣናት በሳውዲዓረቢያ ስብሰባ ማካሄዳቸው ተግልጿል። በዚህ ከተግባቡ ምናልባት ኢሳይያስን በማስወገድ አፍቃሪ ህወሃት ኃይል በኤርታራ አደራጅቶ ትግራይና ኤርትራን በጋራ በማድረግ እንዲሁም ከአፋርና አማራ ክልል በእቅድ የተቀመጠውን መሬት አካሎ የመለስ ዜናዊ «ራእይ»ን ተግባራዊ ለማድረግ ከመሆን ሊያልፍ ይችላል ወይ? ይህ ከሆነስ የኤርትራን ምድር ደጀን ያደረጉ በትጥቅ ትግል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? በበኩሌ ነፍጥ ያነሱ ኃይሎች መጀመሪያ ሳይረፍድ ግንባር መፍጠር አለባቸው።ሁለተኛ የተከፈለው ይከፈል የኤርትራን ምድር ለቀው ኢትዮጵያ   ውስጥ ነጻ መሬት መያዝ ወይም የጎሬላ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ግድ ይላቸዋል። ከዚህ ባለፈ ግን አማራጩ የራሳቸው ቢሆንም በአፈና ላይ ለሚገኘው ሕዝብ ደርሶ ከአፈና ለማውጣት ጊዜ የሚገድል ሆኖ ነው የሚታየኝ። ከፍ ብየ እንደገለጽኩት ህወሃት ጥጋቡ መረን በመዝለሉ ሞትን እየናፈቀ ያለ የሰላማዊ ትግልን በር እንዳይከፈት አጥብቆ የዘጋ ተቃዋሚዎችን ትንሽም ቅንጣት ያህል ሊያከብርና በሀገር ጉዳይ በጋራ ሊመክር የማይችል እብሪተኛ ድርጅት በመሆኑ በትጥቅ ትግል ማስተንፈስ ከተቻለ ልክ የማይገባበት ምክንያት አይኖርምና ለሀገርና ለህዝብ ብላችሁ ትግስት አስጨራሹን የትግል ጎዳና ከጀመራችሁ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ሕዝቡንና ሀገሩን ስለሚወድ የተቻለውን ሁሉ ድጋፉን እንደማይነፍጋችሁ እርግጠኛ ሆኘ ልነግራችሁ  እወዳለሁ። የተቻለውም በድጋፍ ብቻ ሳይገታ ትግሉንም ሊቀላቀል እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ።

ለዛሬ ያለኝን በዚህ ጨርሻለሁ በቼር ይግጠመን።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላአለም ትኑር!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ሞት ለህወሃት!!!

 

ጌታቸው   Pen

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>