ዛሬ (እሁድ) ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ መጀመሪያ የደረኩት ነገር ቢኖሮ የመሶኮቱን መጋረጃ ከፈት Aድርጌ ውጪውን ማይት ነበር። በረዶው እንደጉድ ተከምሮዋል። የታየኝ ገና መኪና አሙቄ፣ በረዶ ጠርጌ፣ መጥረግማ ቢሆን በማን እድል ፈቅፍቄ ጉዞዬን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማቅናት ነበር። መንገዱም ከሞላ ጎደል ቢጠረግም ፍጥነትን በተመለከተ እንኳን ለመብረር በተፈቀደው ፍጥነትም ለመሄድ የደፈረ የለም። ሁሌ መኪና የሚያሽከረክሩ ጸባያቸው እንደዚህ ቢያምር እንዴት ጥሩ ነበር። ሁሉም በጥናቃቄ መሪውን እንደ ህጻን ልጅ ታቅፎ የሚነዳው ነው የሚመስለው። በእርግጥ አናዳንዶቹ በራሳቸውም ይሁን ከቁጥጥር በላይ በሆነ ምክንያት እዚያም እዚህም በረዶው ውስጥ ውትፍ ብለው የሚታዩ አሉ።
↧