Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የፓልቶክ ቦለቲከኞችን ማን ሃይ ይበለን (ቶኩማ አሸናፊ)

$
0
0

 

   PALTALK የፓልቶክ ታዳሚ ነኝ ። ሃሳቤን በፓልቶክ ክፈሎቸ ማሰተላለፍ አይከብደጘም። ግፋ ቢል በቀይ መታሰር ሲበዛም ( ባውንስ) ሃሳብን በቁም መግደል  አለበለዚያም  ወያኔ ደርግ ጽንፈኛ አድርባይ ሻቢያ ግነቦት 7 ኦነግ ጎሰኛ ብቻ አንዱን ስም ተለጥፎብኝ እንደምወጣ ሂደት አስተምሮኛል። የፓልቶከ ቦለቲካ ያስተማረኝ አንዱ መጥፎ ገጽታ ነው።በፓልቶከ ክፍሎች አንዳንዴ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሲጠፋ የተለያዩ መጣጥፎቸን ማንበብ የተለመደ በመሆኑ እራሳቸውን አጀንዳ ለማድረግና ምናልባትም ጊዜና ጉልበታቸውን ገንዘባቸውንም ጭምር መሰዋእት በማድረግ ለትግሉ አስተዋጽኦ ለማድረግ ደፋ ቀና ለሚሉ ወገኖቼ እራሳችንን እንድናይና የሳይበሩን አለም በተሻለ መንገድ እንድንጠቀምት ለመገፋፋት በብእሬ ትንሸ ለመኮርኮር ተነሳሳሁ። ማይክ የቸበጠ ሁሉ ወይም በሎቢ ላይ ቃላት የወረወረ ሁሉ ፖለቲክኛ በሚመስልበት  የፓልቶከ መድረክ ቦለቲከኛውን ከፖለቲከኛ መለየት አስፈላጊነቱ ወቅታዊ ነው።  

በመጀመሪያ ፖለቲከኞች የምላቸው በኣንድ ህበረተሰብ ውስጥ የሚታዩትን ፖለቲካዊ አኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የፖለቲካ ስርኣቱን ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉና ኣላማቸውንም ለማስፈጸም በጠራ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ የታነጸ መነሻና መድረሻ ባለው የፖለቲካ ኣጀንዳ ስር የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ነው፤፤ የፖለቲካ ስራ የሚሰራውም የማንኛውም ስርኣት ኣንቀሳቃሽ ህዝብ በመሆኑ ፖለቲከኞች ከህዝብ ጋር ያላቸው ግንኙነት ወሳኝ ነው።

ለዚህ መነሻ ሃሳብ ያነሳሳኝ ከጊዜ ወደጊዜ አየዘቀጠ የመጣው  የዲያስፖራው በተለይም የሳይበሩ ኣለም “ቦለቲከኛ” መብዛት ነው፤ ቦለቲካ የሚለውን ቃል የሰማሁት ድሮ ልጅ ሆኜ በጣም ብዙ የሚያወሩና የሚያወሩት ነገርም እውነትም ዪሁን ውሸት ነገር ግን ሌላውን ለማሳመን የሚጠቀሙበት ቁዋንቁዋ የኣድማጭን ቀልብ የሚስብና ሃሰቱን እውነት እውነቱንም ሃሰት ኣድርጎ የማቅረብ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች” እሱ እኮ ቦለቲከኛ” ነው ሲሉት  ትዝ ይለኛል።

ታዲያ ዛሬ ቴክኒዎሎጂ በፈጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በደምጽ በሚሰሙት ራዲዮ ቴለቭዥን ፓልቶኮች በኣንድ ጊዜ በበዙ ሰዎች ሰለሚደመጥ ቦለቲከኞችን ከፖለቲከኞች ለመለየት የተቸገርንበት ለመሆኑ በእርግጠኝነት ለመናገር  ይቻላል ፡፡ መነሻዬ የዲኣስፖራው ፖለቲከኞች መድረክ የሆነውን ፓልቶክ ክፍሎችና ተዋንያን ቦለቲከኞችን በመሆኑ በዚሀ ጽሁፌ እሱ ላይ አተኩራለሁ።

አሁን ባለንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚጠነሰስበት የሚፈጭበት የሚጋገርበት መድረክ ፓልቶክ ሆኖኣል ማለት ይቻላል። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ወያኔ ኢሃደግ ደጋፊዎች ኣባላትም ጭምር  ጀምሮ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅች መሪዎች ተገንጣዩም አስገንጣዩም ኣንድነት ባዩም ጠባቡም ትምክህተኛውም ኣፍቃሪ ሃይለስላሴና ደርግ ስርኣቶችም ጭምር በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የዲያስፖራውም ሆነ የሃገር ቤቱ ፖለቲከኛም ቦለቲከኛም የሚሳተፍበት ዋነኛ መድረክ ሆኖኣል ፥፥ በፓልቶክ ከፍሎች የእምነት የማህበራዊ ጉዳዮች የፖለቲካ ተደማምሮ ከ ሶማሊያ ቀጥለን በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምንገኝ የመሆናችን ምክንያቱ ብዙ ምርምር የሚያስፈልገው ሳዪሆን የብዙ ፈርጅ ችግርተኞች አንደሆንን የሚያረጋግጥ ነው፥፥ የሁዋላ ቀርነት መለኪያም ነው፤፤ የዲሞከራሲ እሴት ደሆች መሆናችንም ነው ፥፥ ዝብርቅርቅ ታሪክ  ኣስተሳሰባችን ላይ የቀረጸው ዝብርቅርቅ ኣመለካከት ነው ፥፥ ይህ ራሱን የቻለ ርዕስ ስለሆነ ወደፊት በሰፊው ለማሳየት እሞክራለሁ፥፥የኣሁኑ ተኩረቴ ግን የፖለቲካ ከፍሎችን ነው፥፥

ለፖለቲካ መወያያ መድረክነት የተፈጠሩ ከፍሎችኣደረጃጀት የተለያየ ነው፥ እንደሃገር ቤቱ በቈዋንቁዋ ላይ የተመሰረቱ ክልሎች በስም ጭምር የኣሮሞ የትግሬ የኣማራ  የሃረሪ   ወዘተ  የክልል ፓልቶኮች

በሃሳብ ከኢትዮጵያ ተገንጥለው ነጻ መንግስት የመሰረቱ ክፍሎች  ሚኒለከ ጅኖሳይድ

የስርኣቱ ዋና ደጋፊ የሚባሉ የሚታወቁ እንደ ገዛ ተጋሩ  Eprdf  ካናዳ ኢትዮ ሲቪሊቲ  በግልጽ የሚታወቁ

በተቃዋሚች በኩል የተወሰኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ኣስተሳሰብ የበላይነትን የያዙባቸውና በርካታ የድርጂት ደጋፊዎችን ያቀፉ ዲሞክራሲ በገደብ የሚሉ

እንደ ኢካዲኤፍ ( ግንቦት ፯ ደጋፊዎች የሚበዙበት)

ቃሌ ( መድረክ መኢኣድ ኢዴፓ ኢህአፓ ደጋፊዎቸ የተደበላለቁበት )

EFND (ኢህአፓ) የመሳሰሉ

በሌላ በኩል የሁሉንም ኣስተሳሰብ እናንሸራሺራለን የሚሉ ነገር ግን ኣብዛኛው ስርአቱን ሂሳዊ ድጋፍ እንሰጣለን በሚል የተዋቀሩ በፖለቲካ የሃይል አስላለፍ መመዘኛ ግን የሰርኣቱ ደጋፊዎች  ጎልተው የሚታዩባቸው እንደ ቅንጂት ስዊዘርላንድ ፡ ኢትዮ ዲኣስፖራ አይነቶችና በመጨረሻም ተጀምሮ አስከሚጨረስ ተቃዋሚንት እነጂ የት ነው ያሉት የሚያስብልና የስድብ ትምህርት ቤት ይመስል የነበረው  ደብተራ ክፍሎች (አሁነ ግን ስድበ ተቅንሶአል)

በየክፍሎቹ ውስጥ የሃገራቸው ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ነገር ግን ሃሳባቸው የበላይነትን ይዞ ያልወጣና ኣሰባሳቢ ኣመለካከት ስር ያልሰደደ በመሆኑ በድምጻውያን ቢዋጡም በርካታ ቅን ዜጎችና በሃሳብ የበሰሉ ዜጎች ለፓልቶኩ ፖለቲካ ዉበት ናቸው ። እጂግ በዝተው የሚታዩት ግን ቦለቲከኞች ናቸው፥፥

የቦለቲከኞቹን መገለጫ ከማየቴ በፊት ስለ ክፍሎቹና  የኣንዳንድ ቦለቲከኞች nick name ትንሽ ልበል፥፥ ኣብዛኛዎቹ የፓልቶክ ከፍሎች ስምና ማነነታቸው ኣይጣጣምም ፥፥ ለምሳሌ ኢካዴፍ ቃሌ ቅንጂት ስዊዘርላንድ  ደብተራ ሊክስ  ሞረሽ  ጀኖሳይድ ወዘተ ስማቸውና ውስጣዊ ማንንታቸው የተለያዩ ናቸው።

የፓልቶክ ታዋቂ  ስሞች ለምሳሌ ኣባመላ፡ ሎሬት ጸጋዬ፡ ደብተራው የመሳሰሉ  ስመ ጥር የሃገራችን ታላላቅ ሰዎች ስም ሲሆን ስሙን የያዙት ሰዎችና የፓልቶክ ባህሪያቸው ፈጽሞ  አይገናኝም ፥፥ሎሬት ጸጋዬ  ገብረመድህን በስሙ የሚቀርበውን ፓልቶከኛ  የስድብ ቃላት ከሞት ተነስቶ ቢያዳምጥ ፊታውራሪ አባመላ በዘመናችን የፖለቲካ መለኝነት ምን እንደሚመስል ቢሰሙ ተመልሰው መሞትን ይናፍቁ ነበር፥፥ የፓልቶክ ፖለቲካ የበሺታ ምንጭ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የጎደለው በውጭ እየኖረ ሃገር ቤት ያለው ጥቅም የሚነካበት የሚመስለው በኮምፒውተር ጀርባ ያለ ፈሪ ቦለቲከኛ ነው።

ወደ ዋናው ነጥብ ልመለስና በእኔ እምነት የፓልቶክ ቦለቲከኞች  መገለጫ

፤ እውነትን ሽምጥጦ መካድና ሃሰትን እውነት ኣስመስሎ የማቅረብ ችሎታ

፥ የፖለቲካ ግጭቶችን ልዩነቶችን ፍጹማዊ ማድረግ 100% መደገፍ ወይ መንቀፍ

፤ በመሰረታዊ ጥያቄዎች ፕሪንስፕልስ  ላይ በየጊዜው ተገለባባጭ ኣቍም መያዝ (ኣካሄድ ሊለዋወጥ ይችላል

፤ የውይይት ቁዋንቋቸው (ቶን) የማያደርጉትን የሚያደርጉ መስሎ መቅረብ

፥ ፥የኢትዮጵያ መጻኢ እድል ወሳኝ ሃይሎች ሆኖ መታየት ብቸኛ ኣክቲቪስት ተንታኝ መስሎ መታየት

፤በፓልታልክ ኣበባ የሚፈነድቁ ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት የተቆለለ ቦለቲካ መሆኑ ኣበባ ባዩ ቁጥር ደምጻቸው ከፍ እያለ የሚሄድ የሎቢ ጉበኞች

፤ የኣስተሳሰብ ድሀነትን በስድብ ባለጸግነት ለማካካስ የሚፈለጉ ስድብና ፖለቲካ የተቀላቀለባቸው

፥  ያነበቡትን ሁሉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መደንቀር የሚፈልጉ ከነባራዊ  ሁኔታ የተፋቱ

፥  ሌላው በተናገረው ላይ ብቻ ለመናገር ማይክ ለመያዝ የሚሽቀዳደሙ የራሳቸው ምንም ግባት የሌላቸው

፤ የፖለቲካ መሰረቱ ህዝበ መሆኑን ያልተረዱ በህዝብና በፖለቲካ ድርጅት መካከል ያለውን ኣንድነትና ልዩነት ለመገንዘብ የማይፈልጉ ዘረኛ ሆነው ዘረኝነትን የሚያወግዙ የ ጎሳ ፖለቲካን በኣፍ የሚጠየፉ  ነገር ግን ወሳኝ ነገር ሲመጣ የዘር ጉዋዳ የሚያንጎዳጉዱ።

፤ ስለ ዲሞክራሲ ስለፍትህ ስለ እኩልነት የሚሰብኩ በተግባር ዲሞክራሲን የሚገሉ ፍትሃዊ ወይይትን የሚገድሉ እኩልነትን የሚንዱ

እነዚህ በፓልቶኩ ፖለቲካ በየትኛውም ክፍል የሚታዩ የቦለቲካው መገለጫዎች ናቸው፤፤ ኣንዳንዱ ብዞዎችን ባህሪያት ያሙዋላል አንዳንዱ በተወሰኑት ስር ይወድቃል፥፥ ፖለቲከኛ ሳይሆኑ ቦለቲከኞች ይበዛሉ ያልኩት ከዚህ በመነሳት ነው፥፥ሽፋኑ ደግሞ ሃገር ወዳድነት ነው፤፤ በእርግጥም ብዙው ሃገሩን ይወዳል  ያፈቅራል ። ታዲያ መውደድና ማፍቀር በኣግባቡ ካልተያዘ ኣደጋም እንዳለው መረዳቱ ደግሞ ኣስፈላጊ ነው፥፥ ብዙ ኣፍቃሪዎች ፍቅረኞቻቸውን  ገድለው ለምን አንደገደሉ ሲጠየቁ ስለሚያፈቅራቸው መሆኑን ይናገራሉ ። የነሱ ብቻ እነዲሆኑ ስለሚፈልጉ። የአንዳንዶቻችንም የሃገር ፍቅር እንደዚያ ይመስላል። ሃገርን በግል ኣፍቅረህ በግል ችግርዋን ኣትፈታም፥፥

ዛሬ የደረስንበት የፓልቶክ ፖለቲካ ደግሞ ቅጥ ኣምባሩ የጠፋ ሆኖኣለ ፥፥ በተለይ የሲቪሊቲ ባለቤትና በፓልቶክ የሚታውቀው ቦለቲከኛ ኣባ መላ(ለጊዜው የፓልቶክ ስሙን እጠብቅለታለሁ የፓልቶክ መጠሪያው ነውና ) በ ፓልቶልክ ፖለቲካ ውስጥ እራሱንም እየገነባ የፓልቶክ ታዳሚውም እየገነባው መጥቶ እነሆ በራሱ ቦለቲካ ሆኖኣል፥፥ የግለሰቡን ማነነት ወይም ሰብእና ቁመት ውርደት ሆድ ኣፍንጫ መነጸር ወዘተ ወይም የጥንት ማንነቱን ለመመርመር ከአንድ ወር ቦለቲካ ሆኖኣል፥፥በበኩሌ ፖለቲከኛ ሳይሆን ቦለቲከኛ ለመሆኑ በመመዘኛዎቼ ኣስቀምጬ ኣብዛኛውን መስፈርቶቼን ከሚያሙዋሉት ኣንዱ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል ፥፥ እስቲ እያንዳንዱ እራሱን ይመዝን፥፥ ሰለኣባመላም ወር የፈጀ ውይይት የሚያደርጉ ወገኖቼንም በዚሁ መመዘኛ ኣስቀምጡዋቸው፥፥

የኣባመላ የኣቋም ለውጥ በኣንድ የፖለቲካ ድርጅት ቢሆን የኣቁዋም ለውጡን መመርመር በሱም ላይ ጊዜ ማጥፋት የተገባ ነው፥፥ ምክንያቱም ሃገርን እንመራለን የሚሉ  የፖለቲካ ድርጅቶች ኣቍዋም ለውጥ በሃይል ኣሰላለፍ ላይ ትልቅ ጫና ስለሚያሳርፉ በፕሮግራማቸውም ጭምር ሚዛን ስለሚቀይር ነው፥፥ የሲቪሊትይ ኣቋም ለውጥ ወይም የኣባመላ ኣቋም ለውጥ ከዲያስፖራው ቦለቲካ ኣልፎ በኢትዮጵያ  ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል የሚል ኣመለካከት ካለ ኣሁንም የቦለቲከኞች ችግር ነው የሚሆነው::  እዚህ ላይ ኣባመላን ያነሳሁት የወቅቱ የሳይበሩ ቦለቲካ ሰለሆነ፡ አበመላም ከአርብ እስከእሁድ ታዳሚውን በራሱ ቦለቲካ ዙሪያ ደፋ ቀና እያለ የትላንት ሰዳቢዎቹን የማሰባሰብ ዘመቻ ስለ ያዘ ነው ።

በበኩሌ ኣባመላ ኣቋም ለውጫለሁ ያለባቸውን ፍሬ ጉዳዮች ትላንትም የምደግፋቸው ዛሬም አንዲራመዱ የምፈልገው ነው።

፩፡  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ያለመደራደር

፪፥ የሻቢያን ቀንደኛ ጠላትነት ማወቅ

፫፥ ለሃገር የሚጠቅም ልማትን የፖለቲካ መጠቀሚያ ኣለማድረግ።መሰረተ ሃሰቡ እሰማማዋለሁ ወያኔ ኢሃዴግ ልማት ልማት ሰልሚል ተቃዋሚ ከሆንኩ የልማት ተቃዋሚ መሆን ኣለብኝ ወይም

ተቃዋሚነት ምንም ዪሁን ምን የምትቃወመውን መቶ በመቶ መቃወም አለብህ የሚል ጨለምተኛ አመለካከት የትም አያደረሰንም።

የሰርአቱ ደጋፊዎችና አባመላም ጭምር አንድ ሰሞን መለስ ማለት አባይ ነው፡ ራእዩ ነው ብለው በአባይ ስም መለስን ከነምናምኑ እንድንደግፈው ሲያደርጉት የነበረው ፕሮፓጋንዳ አልሰምር ሲል አሁን ደግሞ አባይን አለመደገፍ የግብጽ ወዳጅ መሆን ነው በሚል ተራ ፐሮፓጋነዳ ተተክቶአል።

የኣባይ ጥቅም ላይ መዋል ከጥንት ነገስታት ጀመሮ የህዝብ ፍላጎት የነበር በአጼ ሃይለ ስላሴ

በሎኔል መንግስቱም አባይን ለመገደብ ፍላጎቱና ምኞቱ አልነበረም ማለት አይደለም።

በርግጥም ብሄራዊ ጥቅማችንንና ፖለቲካውን እንዴት እንደምናጣጥመው በወያኔ አኢሃዴግ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ተቃዋሚ ሃይሎችም ችግር አለ። የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅምን ጭምር የሚገዳደረው ከሆነ አጥፊ ፖልቲካ ነው። አንዱና ዋነኛው ስርአቱን ምንቃወምበት ለ ፖለቲካ ስልጣን ብሎ የሃገሪቱን ጥቅም አሳልፎ ሰጥቶአል የምንለው። ታዲያ በዚሀ ረገድ ተቃዋሚው የአባይ መገደብ ላይ የሚታዩ ቴክኒካዊ ችግሮችን ከዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ጋር አለ ማጋጨት ተገቢ ይመስለኛል። በሌላ በኩል የአባይን ቦንድ መግዛት ይጠቅመኛል ያለ ሊገዛ ያልጠቀመው ሊተው መብቱን ማክበር ተገቢ ይመስለኛል። ምክንያቱም ከብሄራዊ ጥቅም ባሻገር ከአንቨስትመንት ጋርም የተያያዘ በመሆኑ ነው፥፥ኢንቨስትመንት ደግሞ  በፓልቶክ ወይም  በፖለቲካ ድርጅቶች የሚወሰን ሳይሆን ግለሰቡ ያዋጣኛል ያተርፈኛል በሚለው መስክ ነው ኢንቨስት የሚያደርገው። ኣሜሪካ ውስጥ ቤት ገዝቼ ኢንቨስት ኣደርጋለሁ የሚል ኣሜርካ ኢንቨስት ማድረጉን ለማንም አንደማያማክር ማለቴ ነው፥፥ ጉዳዩን ወያኔ ኢሃዴግ ቦለቲካ ሲያደርገው ፤ እኛም ቦለቲካ ኣናድርገው ነው፥፥ ይህ ማለት የወያኔ አሃዴግን ጩሀት ኣብረን እንጩህ ማለት ኣይደለም ፥፥

ብሄራዊ ጥቅምን ወይም ውያኔ ኢሃዴግ የስልጣኑ ዋና ማራዘሚያ የሆነውን የብሄረሰብ ችግር ወደ ጎሳ ፖለቲካ ለጥጦ ጥዋትና ማታ ብሄር ብሄረ ሰብ ስለሚል በመሬት ላይ ያለውን ችግር በመካድ የብሄረ ሰቦችን ችግር ማንሳት አያስፈልግም የሚል ወይም ያነሳን እንደ ዘረኛ መቁጠር አንድነትን ያመጣል ማለትም አይሆንም። የተጠቀሱትን ነጥቦች ያነሳሁት አባ መላን ቦለቲካ ለማድረግ ሳዪሆን አባ መላ በነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ማለትም

የሻቢያን ጠላትነትና ወዳጀነት

የልማትና እድገት ጥያቄ ክዚሁ ጋር የአባይ መገደብ አሰፈላጊነት ክብሄራዊ ጥቅም አንጻር ማየቱንና የብሄራዊ ጥቅም አጀንዳ ደግሞ በየጊዜው ምትቀያይረውና ከፖልተካ ድርጂቶች ጋር በሚኖር ጸብና ኩረፊያ ላይ የተመሰረተ አቅዋም አለመሆኑን ለማሳየት ነው። አባ መላ የሚወቀስበትም የብሄራዊ ጥቅም አጀንዳን አንደፈለገ ማሽከርከሩ  የኣባይ መገደብን እንደ ፈለገ ሲቦተልክበትና የብሄረ ሰብ ጥያቄና ቺግሮቹን የተለያየ ኣቋም መውሰዱ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የተቃዋሚወን ጎራ ኣስተካክለዋለሁ በሚል ኣጉል ጀብደኝነት የተለያዩ የፖለቲካ ኣጀንዳዎች ለምሳሌ የኣማራውንና የኦሮሞውን ኢሊት አስታርቃለሁ; አለም አቀፍ የተቃዋሚ ግራስ ሩት እመሰርታለሁ ;የኣለም ኣቀፍ አርዳታ ቡድን ቃለኣቀባይ ሆኜአለሁ በሚል ተስፈንጣሪ ፖለቲካና የራስ መካብ ቦለቲካ ውስጥ ተዘፍቆ የፓልቶክ ቦለቲከኞቺን እያንጫጫ ያለው ።

ሌላው አባመላ ወስጃለሁ የሚለው አቅዋም ወደመሀል ፖለቲካ መጥቻለሁ

የሚል ነው:: ወደመሀል ፖለቲካ መምጣትና ወደነበሩበት አቁዋም መመለስ ይለያያሉ።  የመሃል ፖለቲካ ለሀገራችን  ይበጃል የሚል እምነት ካላቸው ወገኖች አንዱ ነኝ። አገራችን ካለቺበት ወሰብሰብ ቸግር ልተወጣ የምትችለው ጫፍና ጫፍ የተጣረዘ ፖለቲካ ሳይሆን የብሔራዊ መግባባት ፖለቲካ መስፈን አማራጭ የሌለውና ወደመሀል መምጣት ከሁሉም አቅጣጫ  ሊበረታታ ይገባል የሚል አምነት አለኝ ወደመሀል ሰንተር ፖለቲክስ መምጣት ማለት ግን በነባራዊ አውነታዎች ላይ ተመርኩዞ ያሉትን የተለያዩ ቅራኔዎች ቅደም ተከተል አስቀምጦ በሂደት ሊፈቱ የሚችሉትን ጊዜ ሰጥቶ ከሁሉም  በላይ መፋጠጥን አስቀርቶ የመቻቻልና ተፋላሚ ቡድኖች ሁሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበት መፍትሄ ማቅረብ እንጂ አንዱን ደግፎ ሌላውን በመርገምና በመኮነን ላይ  ያተኮረ ፖለቲካዊ አካሄድ አይደለም :: አባመላ ሲፈልግ ተቃዋሚውን ሃይልና ግለሰቦችን ሲፈልግ መንግስትና ደጋፊዎቹን ሰብእና የጎደለው ተራ ስድብ እያወረደ ለዲያሰፖራው የፓልቶክ ቦለቲከኞችና ፓልቶክን መደበሪያ ላደረጉ ብቸኞች መዝናኛ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም።

ከዚሁ ጋር ሌሎች ቦለቲከኞቻችን  ወደመሀል መምጣትን ከግራ ዘመሙ የፖለቲካ አስተሳሰብ በተቀዳው አድርባየነት ስፈርጁት ይታያሉ :: ዓለም በተለያዩ ቅራኔዎች በተወጠረችበት በዚህ ዘመን ፖለቲካዊ  ቅራኔዎችን ለማርገብና በተለያየ መልኩ ሴንተር አቅዋም አንደመሳሪያ ሆኖ ያገለግላል :: በፖለቲካ የተነሳ የብዙ ሕዝብ ህይወት የሚቀጥፉ ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍቻ

አንዱ ዘዴ ነው ።ይህም አቅምን ለመገንባትና የሃሳብ የበላይነትን ለመያዝ የሚያስችል አትሞስፈር መፍጠር ማለት ነው ። ወደ መሃል መምጣት” ምን ተቃዋሚ አለና” እየተባለ አይደለም። ቀስ በሎ ወደ ነበሩበት ለመመለስም መሸጋገርያ መንገድ ሊሆን አይችልም።

ሰለዚህም አባ መላ የስርአቱ ደጋፊ ነኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ ሲሆን የፖለቲካ

ተርሚኒዎሎጂዎችን ይዘታቸውን  ለራስ እነዲጠቅሙ በመመጠን ግራ የተጋባወን የድአስፖራ የፓልቶክ ቦለቲከኛ ማስጨብጨብ ከተራ ፕሮፓጋንዳ ውጭ ሊሆን አይችልም ።

ከላይ የውቅቱ የፓልቶክ  ቦለቲካ ምን አንደሚመስል አንዱን ክስተት ብቻ  በመሰረታዊ ጥያቄዎች ዙርያ ለማሳየት ያህል አንጂ ሰለአባመላ ብዙ ለመጻፍ ፈልጌ አይደለም :: የችግሩን ተጠያቂነትም ለአባመላ ለመስጠት አይደለም።የሚወራው ሰለአባመላ ሆድና ቁመና ሰለ ቀድሞ ማንነቱ ከመሆኑም በላይ ፓልቶከኛ ተቃዋሚው ትግሉን ወዴት እየወሰደው ነው ? የሚለው የዝቅጠት ፖለቲካ እነዲያቆም ለመገፋፋት ነው። ከሁሉም በላይ የስርአቱ ደጋፊዎች ምን ያህል እንደወረዱ የሚያሳየው ተመለሰልን ብለው የተፉትን ምራቅ ለመላስ አንድ ሳምንት ጊዜ እነኩዋን ለአባመላ የማሰቢያ ጊዜ አለመስጠታቸው ነው፡፡ ቦለቲካ ማለት ይህ ነው።

የፓልቶክ ቦለቲከኞች  አስደናቂ ባህርይ  አባመላን በሀሳብ ዙሪያ ሳይሆን ልክ የአባ መላ የአቀራረብ ባህሪይ ያለው የአራዳ ልጅ ተፈልጎም ይሁን ራሱ ፈልጎ ስለ አባመላ ህይወተ ፖለቲካ በአራዳ ቁዋንቁዋ  ከ800 በላይ ቦለቲከኞች ቁጭብለን ሰናዳመጥ አጃኢብ ያሰኛል :: በርግጥ በተነሱት የአቅዋም ጥያቄዎች ላይ አጀንዳ ይዘው የተወያዩ ከፍሎች የሉም ማለት አይደለም : በእንዲህ አይነቱ ውይይት ላይ የሚሳተፉት እድምተኞች  ግን  ቁጠራቸው በጣም ትንሽ ነው :: ይሄም የሚያሳየን ዲያሰፖራው ፓልቶክን የመማሪያና የሃሳብ መለዋወጫ  ለትግሉና ለሀገርም የሚበጁ የሃሳብ መፍለቂያዎች ከመሆን ይልቅ የቦለቲካ ኮሜዲያን ማፍለቂያ መድረክ እንዳይሆን ከልባቺሁ ለለውጥ መሳሪያነት ለመጠቀም የምትፈልጉ ወገኖች በያላችሁበት እራሳችሁን ፈትሹ። እንፈትሽ።

በመጨረሻም ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አባባል ልዋስና ” ኑ እንዋቀስና ኢሃዴግን እናፍርሰው”

 

ቶኩማ አሸናፊ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>