Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፫ (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

Temesgen-Desalegn4ተመስገን ደሳለኝ)

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት
የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት
ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም
‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው››
ይለናል፡፡ በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን
በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ ራሷ አሜሪካንን ጨምሮ አብዛኛው
የአውሮፓ አገራት ከሞላ ጎደል በዜጎች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ማሕበረሰብ መገንባት ከቻሉት ውስጥ
ሲመደቡ፤ ብዙሃኑ የአፍሪካ እና የእስያ መንግስታት ደግሞ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል
መንፈስ የተቃኘ አገዛዝ አንብረው፣ የትኛውንም ተግዳሮት በጠብ-መንጃ ዓይን መመልከትን ፈቅደዋል፡፡ ከእነዚህኞቹ መካከል የእኛይቷ
ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት፡፡
ባለፉት ሁለት አስርታት በጠቅላይነት የጨዋታ ሕግ እየተመራ፣ ከሰሜን-ደቡብ የተንሰራፋ መዋቅር መዘርጋቱ የተሳካለት ኢህአዴግ፤
የፖለቲካ ሳይንስን በአብዮታዊነት ለውጦ፣ ሀገሪቱን ለጥቂቶች የፌሽታ፣ ለብዙሃኑ የዋይታ መድረክ ሲያደረጋት አንዳች ኮሽታ
ያለመሰማቱ መነሾም ይኸው ነው፡፡ ለሕግ ከማይገዙ ፖለቲከኞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው አንስቶ፣ በአንድ ጀንበር ሰማይ-ጠቀስ ህንፃን
እንደጓሮ አትክልት የሚያፀድቁ ‹‹አባ-መላዎች›› መበርከታቸው አስማታዊ-ጥበብ ያልሆነብንም ለዚሁ ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርታቸውን እንኳ ያላጠናቀቁ አፍላ-ወጣቶች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ባላቸው መኪኖች መምነሽነሻቸውም ሆነ፣ ለአቅመ
አዳም ሳይደርሱ ግዙፍ የአስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት ሆነው ማየታችን ይህንኑ ያስረግጥልናል፡፡
አብዮታዊ ግንባሩ ከፊተኞቹ ንጉሳዊም ሆነ ወታደራዊው አስተዳደር የሚለይበት ክፉ ገፅታዎች አሉት፡፡ ለአብነትም ከአጀንዳችን ጋር
በሚዛመደው የፍትሕ ሥርዓት ማነፃፀር ይቻላል፡፡ በአፄው ዘመን በአንፃራዊነት የሰፈነው የሕግ የበላይነት በሂደት ተንኮታኩቶ
ቢወድቅም፤ ደርግ በጎዳና ላይ የፈፀመው ዘግናኙ የቀይ ሽብር ጭፍጨፋ ምዕራፍ ከተዘጋ በኋላ ባሉት የሥልጣን ዘመናቱ፣ በእውቀት
የበቁ እና ከአድሏዊነት የራቁ ሊባሉ የሚችሉ ዳኞች እና ዐቃቢያነ-ሕግ በመሾም፣ ዛሬ ካለው የተሻለ ተቋማዊ የፍትሕ ስርዓት ለመገንባት
መሞከሩን የጊዜው መዛግብት ያወሳሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር በሕግ ባለሞያዎች እንደመልካም ነገር የሚጠቀሰው ‹‹ጠቅላይ ዐቃቤ-ሕግ›› ተብሎ
አንድ ሰው ተመርጦ የሚሾምበት አሰራር ነበር፡፡ ምክንያቱም በዚህ ቦታ የሚመደብ ግለሰብ የሀገሪቱን መሪዎችን ጭምር መክሰስ
የሚችልበት ተቋማዊ ሥልጣን ያለው ከመሆኑም በላይ ‹‹አደገኛ ናቸው›› የተባሉ የህትመት ውጤቶችንም ሲያምንበት ሳይሰራጩ ቀድሞ
እስከማገድ የሚያደርስ ሥልጣን ነበረውና፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር በምዕራባዊያን ሀገራት የተለመደ ሲሆን፤ የቀጥታ ሥርዓታዊ
ተጠያቂነትንም ስለሚያስከትል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሕግ ለማስከበር ጠቃሚ መሆኑ በዘርፉ ምሁራንም ዘንድ የታመነበት ነው፡፡
በደርግ ዘመን (ለርዕሰ-ብሔሩ ታማኝ የመሆን ግዴታውን ሳንዘነጋ) ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ ካገኘ፣ በየትኛውም የሥልጣን እርከን ላይ
ያለ ሹመኛን በሙሉ ፍርድ ቤት ከመገተር የማያስመልስ ሥልጣን እንደነበረው ይነገራል፡፡
ይሁንና ይህ ሁናቴ የግርንቢጥ ተመንዝሮ የፍትህ ስርዓቱን ከማፀየፍም ተሻግሮ፣ በሕግ ፊት እኩል ያልሆኑ ወይም በኦርዌላዊያን
ቋንቋ ይበልጥ እኩል የሆኑ ‹‹ዜጐች› ተበራክተው የታዩት በዘመነ-ኢህአዴግ ነው ብል ብዙም ስሁት ድምዳሜ አይሆንም፡፡ ከዓመታት
የጥምዝምዞሽ ጉዞ በኋላም የተቀደሰችዋ የፍትሕ ምኩራብ ረክሳ፣ የዜጎች መብት ተደፍጥጦ፣ ‹‹ሕገ-አራዊት›› ገንግኖ፣ ጠብ-መንጃ
መንገሱ ሊስተባበል የማይችል ሀቅ ሆኗአል፡፡
በርግጥ ከሁሉም አስከፊውና አሳሳቢው ጉዳይ የፍትሕ ሥርዓቱ ለዝግመታዊ ሞት መዳረጉ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ፕሮፍ መስፍን
ወልደማርያም ‹‹አገቱኒ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው የነገሩን ግላዊ ገጠመኝ በሚገባ ከማስረዳቱም ባሻገር፤ ይህን ዘመን ካለፈው ዘመን
እንድናነፃፅረው ዕድል ይሰጠናልና ልጥቀሰው፡-
“ሁለት በጣም የተለያዩ አሰራሮች አጋጥመውኛል፤ መጀመሪያ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ተይዤ ነበር፤ በአንድ መጻሕፍት ቤት ቆሜ
ስመለከት አንድ ሰው መጣና መታወቂያውን ከአሳየኝ በኋላ መጥሪያ ወረቀት አሳየኝ፤ እንሂድ ብሎ ይዞኝ ሄደና በወንጀል ምርመራ
አንድ ክፍል ውስጥ አስገባኝ፤ ሁለተኛው በወያኔ ዘመን በ1992ና በ1998 የተያዝኩበት ነው፤ ሁለቱንም ጊዜ ከአስር እስከ አስራ አምስት
የሚሆኑ የታጠቁ ወታደሮች ነበሩ፤ በ1992 የተያዝኩት አንድ የመጻሕፍት መደብር ውስጥ ቆሜ ነበር፤ ከአስር እስከ አስራ አምስት
የሚሆኑ የታጠቁ ወታደሮች በአካባቢው ተበታትነው ለጦርነት የተዘጋጁ ሆነው ሲጠብቁ ሶስት ያህሉ በመጻሕፍት ቤቱ ገብተው
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>