ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
ፓርቲያችን አንድነት አበክሮ በተደጋጋሚ እንደገለፀው ኢህአዴግ ያነበረው አምባገን እና ክፉ ስርዓት ዜጎች በተለያየ ጊዜ የሚያነሱትን የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ የሚቀለብሰው ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም ነው፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ አካሄዱም ስርዓቱን ይቀናቀናሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎችና በግለሰብ ደረጃ ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎችን የተለያየ ስም እየሰጠ ወደ እስር ቤት አውርዷል፡፡ እያወረደም ይገኛል፡፡ በርካታ ዜጎች የአስከፊው ስርዓት ሰለባ ሆነዋል፣ እየሆኑም ነው፡፡ ሀገራችን በመነጋገርና በመደማመጥ ችግራችንን የምንፈታባት እንዳትሆን ሆን ተብሎ ለዘላለም መንገስ በሚፈልጉ ባለጊዜዎች የፊጥኝ ታስራ፤ ዜጎቿ እንደቀደመው ስርኣት ሁሉ በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡
እንደዜጋም በታላቋ ሀገራችን በሰቆቃ እንድንኖር ተፈርዶብናል፡፡ ኢህአዴግ ዛሬም ከመንገድ አፍሶ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ማሰቃየቱንና ማንከራተቱን ገፍቶበታል፡፡ ከጊዜና ሁኔታዎች እንደመማር ዛሬም ለስርዓቱ አደጋ ናቸው የተባሉ ወጣቶች ሰበብ እየተፈጠረ ወደ ማሰቃያ ስፍራ እየተጋዙ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ አፈ-ቀላጤ በሆኑ ሚዲያዎች የታሰሩት ክስና ወደፊት የሚታሰሩት እነማን እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ወጣት አመራሮቻችንና አባላትን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራም ነው-ስራ ከሆነ፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑንም በግል ተነሳሽነታቸው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ ለማድረግ ወስነው በብዕራቸው የሰብኣዊ መብት እንዲከበርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲረጋገጥ በሚወተውቱ የነበሩ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደው የእስር ርምጃ የሚያመለክተው በቀጣዩ አመት የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ የተወሰደ የማሸማቀቅና የወጣቶችን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚፈልገው የአምባገነኑ ስርዓት ተግባር ነው፡፡
ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽላይዞን 9 በተሰኘድረገጽ (ብሎግ) ላይበሳልፖለቲካዊናማህበራዊትችቶችንበማቅረብከሚታወቁትን ወጣት ጋዜጠኞች ማህሌትፋንታሁን፣በፍቃዱሀይሉ፣ናትናኤልፈለቀ፣ዘላለምአጥናፍብርሀን፣አቤልዋበላእንዲሁምጋዜጠኛኤዶምካሳዬ፣ጋዜጠኛአስማመውኃ/ጊዎርጊስእናጋዜጠኛተስፋለምወልደየስበመንግስትየጸጥታሀይሎችበቁጥጥርስርመዋላቸውሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚሸረሽር እንደሆነ እናምናለን፡፡ አፈናው ግን ሌሎችን በሺዎች የሚቆጠሩ ብሎገሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚፈጥር አንጠራጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት የከፈተው የእስር ርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆምና የታሰሩትምታሰሩከተባለበትሰዓትናደቂቃጀምሮየሚገኙበትንአጠቃላይሁኔታእንዲጣራ፤መንግስትያሰረበትንተጨባጭማስረጃካለለህዝብይፋእንዲያደርግ፤ያካልሆነግንእስረኞቹንበአስቸኳይያለምንምቅድመሁኔታእንዲለቅእናሳስባለን፡፡ ፓርቲያችን ዘላቂው መፍትሄ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል አፋፍሞ መቀጠልና በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ ያምናል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ሚያዚያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ