Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

በሚኒሶታው መድኃኔዓለም ቤ/ክ ስም መነገድ ይቁም!!! [አቡነ ማርቆስ ቤ/ክርስቲያኑንን አሳማ ያርቡበት ያሉበት አነጋጋሪ ቪዲዮ]

$
0
0

በቀጣይ ያስተናገድንላችሁ መልዕክት ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙ የሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን የተላለፈውን ጥሪ ነው።

debereselam Minnesota
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
5/3/2014

የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሰላም ለመናድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በታላቁ ደብራችን በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስም የሐሰት ዘመቻ እያደረገ ስለሚገኝ የቤተክርስቲያናችን አባላትና ሌላውም ኃይማኖቱንና አገሩን የሚወድ ሁሉ እየተነዛ ካለው የሐሰት ቅስቀሳና አሉባልታ እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

የቤተክርስቲያናችን የሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የገለልተኝነት አቋም አሁንም ያልተቀየረና የተጠበቀ ሲሆን በቅርቡ የዚሁ የሰላምና አንድነት አፍራሽ ቡድን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ከሆኑት ግለሰቦች መካከል አንዱ ወደ ኢትዮጵያ በመሔድ ሥልጣን ላይ ባለው ኃይል 6ኛ ፓትርያርክ ተብለው ለተቀመጡት አባት ሜኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ባለው ሲኖዶስ ሥር ለመተዳደር ወስኗል በማለት የተሰራጨው የድምጽና የቪድዮ መልእክት ፍጹም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ሁሉም እንዲያውቀው እንወዳለን።

ሰላምና አንድነትን አሻፈረኝ በማለት የቤተክርስቲያኑ አባላት ተሰብስበው የመጨረሻ ውሳኔ እንዳያስተላልፉ መሰናክሎችን ሲፈጥር የነበረው የዚህን ቡድን ሕገወጥ አካሔ በፍርድ ቤት አስገዳጅነት የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ለሜይ 11 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲካሔ ከተወሰነ በኋል የሚያደርጋቸውን ሕገወጥ
አካሒዶች መቀጠል ስላልቻለና በጉባኤውም ተሸናፊነቱን አስቀድሞ በማወቁ ራሱን በእለተ ሆሳዕና ከቤተክርስቲያን ለይቷል። በቅርቡ ተወካዩን ወደኢትዮጵያ በመላክም ሕዝቡ ሳይወስንና ስብሰባም ሳያደርግ ሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በእናንተ አመራር ሥር ለመሆን ወስኗል
በማለት የሐሰት ወሬ ለፓትርያርክ አባ ማቲያስ የተነገረውና እርሳቸውም ያስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ቤተክርስቲያናችንን በማይወክሉ እወደድ ባዮች የተፈጸመ ማወናበድ ስለሆነ ደብራችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አሁንም ሆነ ወደፊት በአባቶች መካከል ያለው መለያየት ተፈትቶ አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትርያርክና አንድ አመራር እስከሚፈጠር ድረስ በገላጋይነት አቋም የሚጸና መሆኑን ለአንድነትና ለሰላም የቆምን ብዙኃን የቤተክርስቲያኑ አባላት ሁሉም እንዲያውቀው በአጽንዖት እናሳስባለን።

ከዚህም በተጨማሪም በበራሪ ወረቀቶችና በራድዮ እንዲሁም በየዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ቤተክርስቲያናችን ሰባኪያንን እና ዘማሪያንን በማስመጣት ጉባኤ ያዘጋጀ እንደሆነ ተደርጎ እየተላለፈ ያለው ቅስቀሳም ሐሰት መሆኑን እንገልጻለን። የተባለው ስብሰባ የተዘጋጀውና የሚመራውም በዚሁ ራሱን ለእምነትና ለእውነት ሳይሆን ለፖለቲካ መሳሪያነት ባዘጋጀው ቡድን ስለሆነ ምእመናን ጥሪው የቤተክርስቲያን እንዳልሆነ እንዲያውቁት እንወዳለን።

በቤተክርስቲያናችን ችግር በመፍጠር ሰላማችንን የረበሹትን የቦርድ አባላት ሽሮ በምትካቸው አዳዲስ የቦርድ አባላትን ለመምረጥ እና በዲሴምበር 15/2013 በከፍተኛ ድምጽ ቤተክርስቲያናችን ባለችበት የገለልተኛ/ገላጋይነት አቋም ትቀጥል ተብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ለማጽደቅ ሜይ 11/2014 በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምጽ መስጠት የምትችሉ የደብራችን አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ ላለፉት ዓመታት ተከብሮ የቆየውን የእግዚአብሔርን ቤት ይኸው የሰላም እና የአንድነት አፍራሽ ቡድን የጋበዛቸው አቡነ ማርቆስ “ህንጻ” እያሉ ሲያቃልሉትና “አሳማ ያርቡበት” ያሉበትን ቪድዮ በድጋሚ ትመለከቱት ዘንድ፤ ላላዩትም ታሳዩ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። አቡነ ማርቆስ ደብረሰላምን አሳማ ማርቢያ አድርጉት ቢሉም የእግዚአብሄር ቤት የአሳማ ማርቢያ አይሆንም።

ወ ስብሐት ለእግዚአብሔር!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>