ከዛሬ ጀመሮ የዞን ዘጠኝ ኩሩ አባል መሆኔን አረጋግጣለሁ –ግርማ ካሳ
ርዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ …….እያልን ስሞችን መዘርዘር እንችላለን። በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕገ ወጥና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ የታሰሩ ወገኖቻችን፣ ከእሥር እንዲፈቱ ስንጠብቅ ፣ ሌሎች እየተጨመሩ ነው። ከቃሊት ዉጭ ሆነው እነ ርዪትን ሲጎበኙ የነበሩ አሁን እነ ርዮት አለሙን እየተቀላቀሉ...
View Articleበሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እና ልጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በአጽንኦት እናወግዛለን!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመሬት ስሪት ላይ ግልፅ አቋም እና ፖሊሲ ያለው ፓርቲ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በዚህም መሰረት መሬት በሦስት መሰረታዊ አውድ ላይ እንዲመሰረት ይህም ማለት በወል፣ በመንግስትና በግል ይዞታነት እንዲከበር...
View Articleበቅሎን አባትህ ማን ነው? ቢሉት “አጎቴ ፈረስ ነው አለ”አሉ፤ ምንነትና ማንነት፡ የዘመኑ አንገብጋቢ ጥያቄ
ከፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም ሚያዝያ 2006 ምጽዓት የቀረበ ይመስላል፤ ብዙ ሰዎች ሳይጠየቁ በቁሎው የተጠየቀውን ጥያቄ ራሳቸውን ጠይቀው አጎቴ ፈረስ ነው የሚለውን መልስ እየመለሱ ናቸው፤ ስለምንነታቸውና ስለማንነታቸው በውስጣቸው አንድ አስጨናቂ ነገር እንዳለባቸው ግልጽ ነው፤ የጎዶሎነት ስሜት ስለሚሰማቸው የድረሱልኝ...
View Articleሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮና ጩኸት እስከመቼ? (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል...
View Articleአንድነት ሕዝቡን ለመድረስ የዘዉግ ድርጅቶች የግድ አያስፈልጉትም (አሰፋ ቤርሳሞ)
አሰፋ ቤርሳሞ (abersamo@gmail.com) በመድረክ እና በአንድነት መካከል ስላለው ግንኙነት ሁለት ኢትዮጵያዊያን የጻፉትን አነበብኩ። ዶር መሳይ ከበደ፣ መድረክ ዉስጥ ባሉ የዘዉግ ደርጅቶች እና በአንድነት ፓርቲ መካከል ያሉት የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች የማይታረቁ መሆናቸውን በመገልጽ፣ አንድነት ጊዜዉን እና...
View Articleጃዋር ነበር የሚለው፣ አሁን ግን የኦሮሞ ተማሪዎችም ደገሙት –ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት (ናኦሚን በጋሻዉ)
ናኦሚን በጋሻዉ naomibegashaw@gmail.com በዉጭ አገር የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄረተኖች፣ በዶር መራር ጉዲና የሚመራዉን ኦፌኮ ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች እና አንዳንድ የኦሮሞ ሜዲያዎች ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበልና አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች...
View Articleክብርነቶ በተናገሩበት ሳመንት? (ከዳዊት ዳባ)
ከዳዊት ዳባ Sunday, April 27, 2014 ሰኞ መያዚያ 13 2006 ባሌ ውስጥ የሁለት ንፁሀን ዜጎችን መገደል በመስማት ሳምንቱን ጀመርነው። አገዳደላቸው ወንጀላችሁን ከባድ ያደርገዋል። የመጀመርያው ልጅ በቁጥጥራችሁ ስር ነበር። በህግ አግባብ መጠየቅ ስትችሉ ነው በነጻ እርምጃ የገደላችሁት። አፉ ውስጥ...
View Articleየሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት (ያሬድ ኃይለማርያም)
ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ፣ ቤልጂየም ሚያዝያ 23፣ 2006 ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰዷት እንደሆነ አገሪቱ ዛሬ ያለችበት ውጥንቅጥ ሁኔታ በግላጭ ያሳያል። በመግደል አባዜ የተለከፉት የወያኔ ተጋዳላዮች ዛሬም መግደላቸውን ቀጥለዋል። ለይስሙላ በወረቀት ላይ...
View Articleጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል። የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን...
View Articleአንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ይቀላቀሉ!...
ጤና ይስጥልኝ ! ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ። አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ግለሰብና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ...
View Articleየአዲስ-ኦሮምያ ጉዳይ በመቐለ-እንደርታ ዓይን –ከአብርሃ ደስታ
ስለ አዲስ አበባ ማስተር ፕላንና የኦሮምያ አርሶአደሮች መፈናቀል ጉዳይ በፃፍኩት ላይ “የኦሮሞ ተማሪዎች ዓመፅ ከብሄር አንፃር አትየው፤ መታየት ካለበት አርሶአደሮቹ ከቀያቸው ካለመፈናቀል መብት አንፃር ነው” የሚል አስተያየት ደርሶኛል። እኔም ይሄን ጉዳይ በቅርበት ከማውቀው የመቐለ እንደርታ አርሶአደሮች ልምድ አንፃር...
View Articleየነፃነት – ቃና። (ከሥርጉተ ሥላሴ)
ከሥርጉተ ሥላሴ 02.05.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ) የነፃነት ቃና የነገሮች ሳይሆን ይልቁንም ሰው የመሆን ልዩ ቃና ነው። ቃና መሆን እራሱ ሲያንሰው ነው – ለነፃነት። ነፃነት ትርጉም ያለው መኖር ማለት ነው። መኖር ሲተረጎምም ነፃነት ማለት ይሆናል። ነፃነት እንደ ጎረቤት ሳይሆን እንደ እራስ ሆኖ መኖር...
View Articleበሚኒሶታው መድኃኔዓለም ቤ/ክ ስም መነገድ ይቁም!!! [አቡነ ማርቆስ ቤ/ክርስቲያኑንን አሳማ ያርቡበት ያሉበት አነጋጋሪ ቪዲዮ]
በቀጣይ ያስተናገድንላችሁ መልዕክት ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙ የሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን የተላለፈውን ጥሪ ነው። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን። 5/3/2014 የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሰላም ለመናድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በታላቁ ደብራችን በደብረሰላም...
View Article“ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ” “ከእውነት ጋራ የሚጋጭ ነገር እየሰራን ለመኖር አንድፈር” –ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ቀሲስ አስተርዕየ አቡነ ማቲያስ nigatuasteraye@gmail.com ሚያዚያ ፳፻፮ ዓ.ም. ማሳሰቢያ፦ እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም በተከታታይ ያቀረብኳቸው ጽሁፎች፤ አንባቢ በግልጽ ወደሚያያቸው ክስተቶች ቀጥታ ዘልዬ በመግባት አይደለም። ይህም ባለመሆኑ፤ ከነገረ መለኮት ውስጥ ሳልገባ ህዝባውያን የሆኑትን ነገሮች ብቻ...
View Articleወደ ህሊናችን እንመለስ (አንተነህ መርዕድ)
የመሬት ጥያቄ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ቢሆንም አሁን በባሰ ሁኔታ ወያኔ ከሁሉም ዜጋ ነጥቆ በግሉ አድርጎታል። ማንም ኢትዮጵያዊ የሃገሩ፣ የመሬቱ ባለቤት አይደለም። ከዚህ የባሰ ዜጎችን የማዋረድ ተግባር የለም። አባቶቻችን መሬታቸውን ለባዕድ አንሰጥም በማለት ህይወታቸውን ከፍለው አቆይተውናል። ዛሬ እኛ የራሳችን...
View Articleህመሙ የጋራ ሀመም ነው ጩኸቱም የሁላችንም ጩኸት ነው (የአቋም መግለጫ እና ምክር ብጤ!)
ከአቤ ቶክቻው በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ እያሰማ ነው። መንግስትም በበኩሉ የፈሪ ዱላውን እያወረደው ይገኛል። እውነቱን ለመናገር መፍራት ተቃወሞ የሚያመጣ ተግባር ሲፈጽሙ ነበር እንጂ ተቃውሞውን አለነበረም። ኢህአዴግዬ በክላሿ...
View Article(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ሁሉም ለበጎ ነው
በቀለ ገብርኤል (ሲሳይ) – ከሚኒሶታ እስኪ ወደ ኋላ ሄድ ብለን ያለፍንበትን መንገድ በትዝታ እንቃኝ – ጥናታዊ ጹሑፍ በሁለቱም ወገን ይቅረብ ተብሎ ለወራት ከተዘጋጁ በኋላ፣ የቀረበውን ካዳመጥንና ከሰማን በኋላ ስድስት ሰዓት የፈጀው ስብሰባችንን ማንም ሰው ረግጦ ሳይወጣ ድምጽ ቢሰጥበትም ኮረም አልሞላም በሚል ወዝግብ...
View Articleየአራቱ ሃዋርያት በትግራይ ጉብኝት አነጋጋሪ ሆኗል (ከአስገደ ገ/ስላሴ)
ከአስገደ ገ/ስላሴ፣ መቐለ አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ሰሞኑን ባልተለመደ መንገድ ከትግራይ ክልል የሰልጣን መዋቅር እርከን ወጣ ያለ የክልሉን ስልጣን የተጋፋ (የነጠቀ) የስለላ ስራ የሚመስል እንቅስቃሴ ከ23 አመት የህ.ወ.ሃ.ት አገዛዝ በኃላ አራት አዛውንት የለውጥ ሃዋርያት መስለዉ በመላው ትግራይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ...
View Articleየቁጥር ጨዋታ?! – ፂዮን ግርማ
ጠ/ሚ ኃይለማሪያም በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ (በፋክት መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 33 የካቲት 2006 ታትሞ የወጣ) ሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ...
View Articleኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
በዚህ ርእስ ላይ የምጽፈው ሃይማኖትን ለመስበክ ፈልጌ አይደለም፤ ከውስጥ የሚኮረኩረኝን ነገር ለማውጣት ነው፤ በኢትዮጵያ የተስፋ ሕልም አይታየኝም፤ የሚታየኝ የጥፋት ቅዠት ነው፤ ከሃያ ዓመት በላይ በመለስ ዜናዊና በጓደኞቹ በኩራትና በእብሪት የተዘራው ጥላቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ የደም መግል እንዲቋጥር አድርጎታል፤...
View Article